Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Kolfe Michael’

ቅ/ሚካኤል የአሥር ዓመት ዓይነ-ሥውር አበራ — Miracles of Archangel Michael

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 20, 2011

የአገራችንን ዓብያተ ክርስቲያናት ልዩና ቅዱሳዊ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል የቤተክርስቲያኖቹ ሕንፃዎች ዛፎችንና አእፅዋታትን ከተፈጥሮ ጋር በተስማማ መልክ አብቀለው ለምዕመናኑ አመች የሆነ ሁኔታ መፍጠር መቻላቸው ነው።

እላይ ቪዲዮው ላይ በከፊል እንደሚታየው ምዕመናኑ የቤተክርስቲያኖቹ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙት ውብ የተፈጥሮ ሣሮች፡ አበቦች ወይም ዛፎች አጠገብ በመሆን እንዲሁም ቀዝቀዝ ያለውንና ነፋሻማውን ንጹህ አየር እየተቀበለ ለፈጣሪው ጸሎቱን ያደርሳል።

ብዙ ዓብያተ ክርስቲያናትን በመላው ዓለም ተዘዋውሬ ለማየት በቅቻለሁ፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በቀላሉ ሊያገናኙ የሚችሉትና ለመንፈሳዊ ሕይወት በጣም አመቺ የሆኑ ዓብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ እንደሚገኙ አሁን ለመገንዘብ በቅቻለሁ። ይህን ለመሰለው ጸጋ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል። ምናልባት ይህ እድል አሁን በእጃችን ስላለ ላንገነዘበው እንችል ይሆናል፡ ሆኖም ግን በመልክአምድር እንደ አዲስ አበባ ከፍ ብለው በሚገኙ ቦታዎች ላይ የቤተክርስቲያኖች ቁጥር በዓለም በብዛት የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው። ይህ እራሱ እንደ አንድ ትልቅ ምልክት ሊሆነን ይገባል፡ ቤተክርስቲያን ልጆቿን ለመጭው ጊዜ እያዘጋጀች ነውና!

በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።” {ኢሳያስ 22}

/ሚካኤል የአሥር ዓመት ዓይነሥውር አበራ

የደወሌ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከድሬዳዋ ማሥራቃዊ ክፍል በኢትዮጵያና በጅቡቲ ወሰን አቅራቢያ በረሃማ በሆነችው ከተማ ነው።

በደወሌ በረሃማ ሥፍራ ላይ በተመሠረተው የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ተአምራት ታይቷል።

ከነዚህም አንድ ዓይነሥውር ከማየቱም በላይ ሁለተኛው ሊቀ መላእክት ቅ/ሚካኤል የተወሰደበትን ቆርቆሮ በተአምር ወደ ቤተ መቅደሱ መመለሱ ነው።

ዓያናቸው የበራው ግለሰብ አቶ ጥላሁን ታደሰ የሚባሉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ለዓይናቸው መታወር መነሻው በውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የቦኖ ውሃ አስቀጂ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ቢርካውን ሲከፍቱ እንደ ደም ያለ ነገር ይታያቸዋል ከዚህም ጋር የጋዜጣ ንባብ ሱስ ስለነበራቸው አዘውትረው ጋዜጣ ያነቡ ነበር። በእነዚህ ሁለቱ ምክንያቶች በየትኛው ዓይናቸው እንደጠፉ በትክክል ባይታወቅም ዓይናቸው ደም ካየበት ጀምሮ እየደከመ መምጣቱን በዝርዝር ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን እንዳስገነዘቡት ከልጅነቴ ጀምሮ ቅ/ሚካኤልን እወደዋለሁ አከብረዋለሁ እዘክረዋለሁ ግን ዓይኔ በመታወሩ ምክንያት ከሥራ ተወገድኩ ለመኖር ስል አንድ መሪ ልጅ ይዤ ከድሬዳዋ ደወሌ በመመላለስ የጫት ንግድ ጀመርኩ በዚህም ምክንያት በሄድኩ ቁጥር በረኸኛው ቅ/ሚካኤል በድርሳንህ እንደሚነገረው ብዙ ተዓምር ሠርተሃል በእኔም ላይ ተአምርህን አሳይ እለው ነበር። በንግዱ የዕለት ጉርሴን የዓመት ልብሴን በሚገባ እያገኘሁ የደወሌን ቅ/ሚካኤል አጥብቄ እማፀነው ነበር። ዕለቱ ማክሰኞ ሐምሌ 12 በዚሁ ዕለት የደወሌው ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተባርኮ እንደሚገባ ባለቤቴ ነገረችኝ እኔ ግን እጄም እግሬም በመተሣሠሩ ምክንያት አንቺ ሄደሽ አክባሪ አልኳት ሄዳ አክብራ ተመለሰች።

በዚሁ የቅ/ሚካኤል ዕለት ልጄን ይዤ ዳቦዬን አቅርቤ ከዘከርኩ በኋላ ከጐረቤቶቼ ጋር ጠበሉን ጸዲቁን ቀምሰን ቅ/ሚካኤልን አመስግነን ጐረቤቶቼ ሲወጡ ጋደም አልኩ እንቅልፍ ያዘኝ በእንቅልፍ ላይ እንዳለሁ አንተ አንተ የሚል የጥሪ ድምፅ ሰማሁ ድምፁም ተደጋግሞ መጣ ብድግ አልኩ ልጁን ብጠራው የለም ነገሩ ግራ አጋባኝ በቤቴ ወለል ላይ በመተከዝ እንዳለሁ አንተ አንተ አታየኝም እንዴ? አለኝ እኔም መልሼ እኔ እኮ ዓይን የሌለኝ በመሆኔ ላይህ አልችልም አልኩ፤ መልሶም እኔ የደወሌው የመቶ አለቃ ኃይለ ሚካኤል ነኝ እንዴት አታውቀኝም አለኝ እኔም በደወሌ የማውቀው መቶ አለቃ ገበየሁን ነው አልኩት ዕለቱ ቅ/ሚካኤል በመሆኑ ከልጅነት የምማፀነው ቅ/ሚካኤል ይሆናል በዬ አስብ ነበር።

ሆኖም የደወሌው መቶ አለቃ ኃይለ ሚካኤል ነኝ ሲለኝ ልቤ በደስታ እየመላ መጣ እሱም በመቀጠል የለበስኩት ምንድር ነው? የእኔስ መልክ ምን ይመስላል? ሲል ጠየቀኝ፤ እኔም የለበሰው ልብስ በኮከብ የተጥለቀለቀ መሆኑንና መልኩም ቀይ እንደሆነ ነገርኩት ከዚህ በኋላ ለ10 ዓመታት ብርሃን አጥቶ የኖረው ዓይኔ ለማየት በመታደሉ በደስታ ተመላሁ ከዚሁም ቀጥሎ መሉ እንደ ብርሃን የሚያበራው ይኽ ሰው በቀጥታ እያየሁት የወርቅ ኃብል በአንገቴ ላይ አጠለቀልኝ የዓይኔን ብርሃን አረጋግጦ የድሮውን የወታደሮች ካኪ ልብስ አለበሰኝ ወርቁንም ሆነ ልብሱን ለማንም እንዳትሰጥ በማለት አስጠነቀቀኝ ከእኔ ተሠወረ።

ከተሠወረ በኋላ ለእኔም ሆነ ለጐረቤቶቼ ነገሩ እውነት አልመሰለም ባለ 50 ባለ 25 ባለ 10 ሳንቲም ገንዘብ በእግሬ ሥር እየጣሉ ይኽ ምንድር ነው? እያሉ ፈተኑኝ ሁሉንም ነገርኳቸው ይህን ሲያረጋግጡ ደስታው ልዩ ሆነ።

እግዚአብሔር ይመስገን የቅ/ሚካኤል ተረዳኢነት አማላጅነት በሁሉም ሰዎች ዘንድ ለዘለዓለም ይኑር” ማለታቸውን የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በወቅቱ ገልጿል።

ከዚህም ሌላ ከባድ ነፋስ የተቀላቀለ ኃይለኛ ዝናብ ጥሎ በከተማ ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ሕንፃዎች ተሰነጣጠቁ፥ በላያቸው የነበረው የጣራ ቆርቆሮ የነፋሱ ኃይል ተገነጣጠሎ ሲወስድ ቀደም ሲል ከቤተ መቅደሱ ላይ ተወስዶ የነበረውና ግለሰቦች በራስ ወዳድነት ይጠቀሙበት የነበረው ቆርቆሮ በዚሁ ከባድ ነፋስ ተጭኖ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በመምጣት በቅጽረ ግቢው ውስጥ ተቀመጠ፤ የተወሰደው ቆርቆሮ ተመልሶ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በመገኘቱ ቅ/ሚካኤል የሠራውን ገቢረ ተአምር ሕዝበ ክርስቲያኑ በአድናቆት ተመልክቶታል።

___________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: