Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Kidnapping’

75-Year-Old Protestant Lady Arrested for Plotting to Kidnap German Health Minister

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 14, 2022

💭 የ ፸፭/75 ዓመቷ ፕሮቴስታንት ፓስተር የጀርመን ጤና ጥበቃ ሚኒስትርን ለመጥለፍ አሲረው ተያዙ።

🔥 ሽብር አያት ከድንች ማቅ ጋር 🔥

💭 የነገረ መለኮት ፕሮፌሰር የሀገሪቱን የሃይል አውታር ለማፍረስ የጦር መሳሪያ እና ፈንጂዎችን ገዝተዋል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

በራይንላንድ-ፓላቲኔት ግዛት የሚገኘው የጀርመን ፖሊስ ሐሙስ ዕለት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩን ካርል ላውተርባኽን ለማፈን እና የሀገሪቱን የኃይል አውታር ለማውረድ በማሴር የ ፸፭/75 ዓመቷን ሴት በቁጥጥር ስር አውሏል ።

በጀርመን የዜና ማሰራጫ ቲ-ኦንላይን ዘገባ መሰረት ሴትዮዋ የፕሮቴስታንት ፓስተር በመሆን የሰራችውን የሜይንዝ ዩኒቨርሲቲ የስነ መለኮት ፕሮፌሰር የሆነችው ኤሊሳቤጥ አር. ይባላሉ።

ወስካታው የጤና ሚንስትር ላውተርባኽ አገሪቱ በኮቪድ-19 ላይ ላላት ጭፍን አካሄድ ተጠያቂ በሚያደርገው እና እሱን እንደ ዋና ጠላታቸው በሚያየው የታጣቂ ፀረ-ክትባት እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሟጋች ነበረች። ወይዘሮ ኤሊሳቤጥ አር. በዚህ አውድ ውስጥ ስለ “የአንጎል አወቃቀሮች ሚስጥራዊ ማሻሻያ” የሴራ ፅንሰ-ሀሳቦችን አበረታች እና ስለ “አለም አይሁዳዊነት” ፀረ-ሴማዊ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

ኤሊሳቤጥ አር መሪ የሆኑበት “የተባበሩት አርበኞች” የተሰኘው ቡድን አራት ሌሎች አባላትም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል። ከዓመታት በፊት በወጡ ፀረ-ህገ-መንግስታዊ መግለጫዎች ምክንያት ትኩረትን ከሳቡ በኋላ የጡረታ አበላቸውን ተነጥቀዋል።

ኤሊሳቤጥ አር የጦር መሳሪያዎችን እና ፈንጂዎችን በመግዛት የተሳተፉ ሲሆን እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የተወሰኑ ቀናትን ሀሳብ እንዳቀረቡ ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል ። የቡድኑ አላማ በጀርመን የእርስ በርስ ጦርነትን መቀስቀስ እና በ1871 ላይ የነበረውን የጀርመን ግዛትን መመለስ ነበር ሲሉ ባለስልጣናት ጨምረው ገልፀዋል።

ኤሊሳቤጥ አር. የቬርሳይ ስምምነት በሕጋዊ መንገድ እንዳልመጣ እና አሁንም በፓርላማዊ የንጉሣዊ አገዛዝ እንደሚኖሩ የሚገልጽ ግልጽ ደብዳቤ ፈርመዋል። እንደሚታወቀው ከጥቅምት 28 ቀን 1918 ዓ.ም ጀምሮ ጀርመን ያለ ንጉሠ ነገሥት ቀርታለች።

💭 Ethiopia: Protestant Jihad on Orthodox Christians: US Senators Meet The Black Hitler A. Ahmed

🔥 The Terror Granny With The Potato Sack 🔥

💭 The professor of theology also procured weapons and explosives to bring down the country’s power grid, authorities say.

German police in Rhineland-Palatinate on Thursday arrested a 75-year-old woman for plotting to kidnap Health Minister Karl Lauterbach and bring down the country’s power grid.

According to reports by the German news outlet T-Online the woman is called Elisabeth R., a professor of theology from the University of Mainz who has worked as a protestant pastor.

She was active in the militant anti-vax movement that holds Lauterbach accountable for the country’s hawkish approach toward COVID-19 and sees him as their arch-enemy. Elisabeth R. promoted conspiracy theories about “secretive remodeling of brain structures” in this context and made anti-Semitic remarks about the “world jewry.”

Four other members of a group called “United Patriots,” of which Elisabeth R. is the leader, have also been arrested, according to the authorities. She was already stripped of her pension after attracting attention due to anti-constitutional statements years ago.

Elisabeth R. was involved in procuring weapons and explosives, and had proposed specific dates for the implementation of the plan, authorities said. The group’s goal was to incite a civil war in Germany and to restore the German empire of 1871, authorities added.

Elisabeth R. has signed an open letter stating that the Treaty of Versailles had not come about legally and that she still lives a parliamentary monarchy — without an emperor since October 28, 1918.

______________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሃበሻ እንባ፡ ምነው ተሞኘን? ተጨቃከንን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 19, 2014

ከአራት ዓመታት በፊት፡ በጾመ ነነዌ ዕለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በእርኩስ ኃይሎች ቤይሩት ከተማ ተቃጠለ፣ ከዚህ ድርጊት በኋላ በየዓመቱ በነነዌ የፆም ሰሞን ከአየር ጋር / ከአውሮፕላን ጋር የተያያዙ አደጋዎች በየቦታው ተከስተዋል። ለምሳሌ፦

2011ቱ ነነዌ

አውሮፕላኖች ተከስክሰው ተሳፋሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

2012ቱ ነነዌ

2013ቱ ነነዌ

አሁን በጾመ ነነዌ ሳምንት (መስቀል ኢየሱስ) በአየር መንገዳችን ላይ በጣም ግራ የሚያጋባ ድርጊት ተፈጸመ።

ረዳት ፓይለቱ ጠላፊ መሆኑን ስሰማ ወዲያው የመጣልኝ፡ ምናልባት የሕሊና በሽታ ደርሶበት ይሆናል! እንዲያውም የ “Manchurian Candidate” ሊሆን ይችላልየሚለው ሃሳብ ነበር።

 

ይህ የጠለፋ ተግባር በሱዳን ዓየር፡ በዓባይ ወንዝ ከፍታ ላይ እንደተካሄደ ተገልጿል። ታዲያ በዚህ ወቅት በረዳት ፓይለቱ ላይ ምን አይነት ድርጊት ተፈጽሞበት ይሆን? “Hypnotize” ተደርጎ ይሆን? “Manipulate” ተደርጎ ይሆን? ጣልያናዊው ፓይለትስ ምን ዓይነት ሚና ተጫውቶ ይሆን?

ግለሰቡ ጤናማእንደሆነ፡ ነገር ግን በአጎቱ ሞት ተጨንቆ / ተረብሾ እንደነበር ተገልጧል። ምንም እንኳን አስቀድሞ መፍረድ ተገቢ ባይሆንም፣ ግለሰቡ የፈጸመው ተግባር ግን የወንጀለኛነት፣ የከዳተኝነት ባሕርይ የያዘ ነው። በአገሩ ላይ ይህን መሰሉን ጥራዝነጠቅ የከዳተኝነት ተግባር የሚፈጽም፣ አብዛኛው የአገራችን ሕዝብ ያላገኘውን ዕድልና ገፀበረከት አግኝቶ አሳፋሪ በሆነ መልክ በፈቃዱ ወደገደል የሚጥል ምስጋናቢስ ግለሰብ ነው። ከጀግኖቹ የምድር ባቡሮቻችን / ሯጮጫችን ጎን በአፍሪቃ አየር ለመላው አፍሪቃውያን መኩሪያ የሆነውን አየርመንገዳችንን ባላጋጩ አለም ዘንድ እንድንዋረድበት ማድረጉ እጅግ በጣም፡ በጣም የሚያሳዝን ነው። በተለይ፡ አሁን እንደ ግብጽ የመሳሰሉት ጠላቶቻችን የተንኮል መርዛቸውን ባገራችን ላይ ከያቅጣጫው በመርጨት ላይ በሚገኙበት ወቅት ይህን መሰሉን ተግባር መፈጸሙ ምሕረት የሚያስከለክለው ይሆናል። ይህ ጠለፋ፣ በሕዳሴው ግድብ ላይ ጥቃት ለማድረስ ከሚሻ የግብጽ ቅጥረኛ ጋር ተነጻጻሪ ነው።

በተለያዩ አጋጣሚዎች ከብዙ አገር ሰዎች ጋር አብሬ ለመማር፣ ለመሥራትና ለመኖር፡ አገሮቻቸውንም ለመጎብኘት እድሉ ነበረኝ፤ ታዲያ ከዚህ ሁሉ ለመማር የበቃሁት፤ እንደ አገር ሰው ማንም እንደማይሆነን፣ እንደ አገራችን የትም ሌላ አገር ተድላ፣ ደስታና የመንፈስ ተሃድሶ ልናገኝ እንደማንችል ነው። ሆኖም፤ በአገራችን እንደምንደሰት ሁሉ እንደ አገራችን በይበልጥ የምንከፋበት ሌላ ቦታ የለም። በተለይ መጨረሻ ጊዜ በአንዳንድ ወገኖቻችንን ዘንድ ትህትና፣ መተማመን እና መከባበር እየጠፋ፣ ፍቅር እየቀዘቀዘች መምጣታቸው በጥልቁ ያሳስበኛል።

ባለፈው ዓመት፣ ከአንድ አነስተኛ የፍራፍሬ መደበር ፊት ለፊት በሚገኘው የጫማ መጥረጊያ ቦታ ቁጭ ብዬ በመደብሩ የሚካሄደውን መስተንግዶ እከታተል ነበር። አንድ ወገናችን ቆሞ እንዲያስተናግዱት ወደ 10 ደቂቃ ያህል ቆሟል፣ ከእርሱ በኋላ ሁለት አረቦች/ቱርኮች እንደመጡ የእስላም ቆብ የደፋው የመደብሩ ባለቤት ቶሎ ቀርቧቸው ሲያስተናግዳቸው አየሁ። አላስቻለኝም፣ ከጫማ መጥረጊያው ተነስቼ ፍራፍሬው የተቀመጠበትን መደርደሪያ ወርውሬ በመጣል፣ በባለቤቱ ላይ ያልተለምዶዬ ጩኽቴን ጀመርኩ፤ ለምንድን ነው ወገናችሁን የማታስቀድሙት?” “ቱርኩም አረቡም የራሱን ወገን እንጂ ሌላውን በፍጹም አስቀድሞ አያስተናግድም እኮ፡ ምናለ ወገናችሁን ብታከብሩ?!” አልኩ። የባለመደብሩ ሚስት መሰለችኝ እየተጸጸተሽ፡ አዎ! አዎ!” አለች። ይህን መሰሉ ኩፉኝ በየሱቁ፣ በየምግብ እና ቡና ቤቱ፣ በየሆቴሉ ሁሉ በጣም እንደተስፋፋ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ። ይህ በጣም አሳሳቢና አሳዛኝ ጉዳይ ነው።

የረዳት ፓይለቱም ተግባር በጣም የሚያሳስብ ነው። ከጠለፋው ሌላ የሚያስገርመው ነገር፡ ክሣምንት በፊት በስደተኞች ላይ ጥብቅ ሕግ ለማውጣት ሬፈረንደም ወዳካሄደችበት ወደ ስዊትዘርላንድ ሄዶ የፖለቲካ ጥገኝነት ለማግኘት መሻቱ ነው።

ይህ ጠለፋ የሚያሳያን ሌላው ነገር፣ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደምንሰማው ድኽነትለኢትዮጵያውያን መሰደድ ዋናው ምክኒያት አለመሆኑን እና ከፊሉ ሕዝባችን ለከፍተኛ የመንፈሣዊ ቀውስ መጋለጡን ነው።

ሌላ የሚያሳዝነው፡ ጠላፊው ይህን ቅሌታማ ተግባር ከፈጸመ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ፣ የጠላፊው ማንነት ከመታወቁ በፊት፣ ቀደም ሲል ከዋሃቢ ጠላቶቻችን ጎን ሰልፍ ሲወጡ የነበሩት የ ሰማያዊፓርቲ መሪ የኢትዮጵያውያንን ውድቀት ከሚሹት የውጭ መገናኛ ብዙኃን ወኪሎች ጋር የአንድ ንጹህኢትዮጵያዊ ስነምግባር መንጸባረቂያ ያልሆነ መግለጫ መስጠታቸው ነው። በእውነት ይህ ተግባራቸው ግብዝ! ቅሌታም!” ያሰኛቸዋል።

ስዊዘርላንዶችን በጣም እያጠያየቀ ያለው ነገር በስዊትዘርላንድ የአየር ክልል የኢትዮጵያ አየር መንገድን ያጀቡት የጦር አውሮፕላኖች የስዊትዘርላንድ ሳይሆኑ የጣልያንና የፈረንሳይ መሆናቸው ነው። ለካስ የስዊትዘርላንድ ተዋጊ አውሮፕላን ፓይለቶች ገና እንቅልፍ ላይ ነበሩ፤ ከጠዋቱ 2 ሰዓት በፊት ሥራቸውን አይጀምሩም ነበርና።

በሌላ በኩል ግን፡ ይህን የጠለፋ ክስተት በሚመለከት አንድ የምጠይቀው ጥያቄ አለ፦

  • ድኻዋአገራችን ያሰለጠነቻቸው የአየርመንገዳችን ፓይለቶችና ቴክኒሻኖች ለተሻለ የምሥር ወጥሲሉ አገራቸውን በመክዳት ወደ ሃብታምየአረብ አገራት በብዛት ይጎርፋሉ፣ በተቃራኒው ደግሞ አውሮፓውያን ፓይለቶች የኢትዮጵያን አውሮፕላኖች እንዲያበሩ ይደረጋሉ። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ይህ ጠለፋ በዕጥፍ እንድንዋረድበት ካደረጉን ተግባሮች መካከል፣ ፓይለቱ ጣልያናዊ መሆኑን መላው ዓለም መስማቱ ነው። ኢትዮጵያ አውሮፕላን አላት እንዴ?’ ‘አህ፡ ኢትዮጵያውያን ማብረር ስለማይችሉ ፈረንጅ ቀጥረዋል!” የሚሉትን የጭፍኖች ትችት በየቦታው በማንበብ ላይ ነን። ከ50 ዓመታት በፊት እነ ኔልሰን ማንዴላ የኮሩበት ዓየር መንገዳችን አሁን እንዴት ፈረንጆችን ለመቅጠር በቃ?

በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል” [ማቴዎስ ፳፬᎓፲፥፲፫]

Tears of Eritrea — የሀበሻ እምባ

__

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: