ከደምቢዶሎ ከጠፉት ህፃናት ተማሪዎች መካከል አንዷ “አሳቤ አየለ አለም “ ናት። አዎ! በአሁኑ ሰዓት በዚህ አለም አሳባችን ሊያይል የሚገባው በእነዚህ ምስኪን ልጆች ጉዳይ ላይ መሆን ነበረበት፤ ሆኖም የኛዎቹ ወንጀለኞች የመጠረጊያ ሰዓታቸው እስኪደርስ ድረስ ዝምታውን መርጠዋል፣ አለምም ጆሮ ዳባ ብላለች። እግዚአብሔር ግን ዝም አይልም!
በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት በመላው ዓለም ከአምስት መቶ ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ወደ ትህምርት ቤት መሄድ አልቻሉም። አሜሪካ፣ ብሪታኒያ እና አረቢያ ትምህርት ቤቶችን በመዝጋት ላይ ናቸው።
ለመሆኑ በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ከተሰወሩት እህቶቻችን ጋር አብረው ሲማሩ የነበሩት ኦሮሞ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በሰላም ቀጥለዋልን? ጉዳዩን በማስመልከት ወደ ዩኒቨርሲቲው ሄዶ ሊመረምር፣ ሊያጣራና ሊጠይቅ የሚችል አንድም ተቆርቆሬ ሜዲያ ወይም ግለሰብ የለም? ዋ!