የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፡ ጀረሚ ሀንት በአለፈው ሳምንት አዲስ አበባን በጎበኘበት ወቅት ነበር ይህን ከብሪታኒያ መንግስት ያልተጠበቀ መግለጫ የሰጠው። (ኢትዮጵያን በሚጎበኝበት ወቅት (በተለይ የክርስትና ጠላት የሆነው ቢ ቢ ሲ) ይህን ማሳወቁ በአጋጣሚ አይደለም)
በዓለማችን በሚገኙ ሃምሳ ስምንት ሀገራት ውስጥ ክርስቲያኖች ከፍተኛ ስቃይና በደል እንዲሁም መገለል እንደሚደርስባቸው፤ ከእነዚህም መካከል ሃምሳዎቹ የሙስሊም ሀገራት መሆናቸው ተገልጿል።
በክርስቲያኖች ላይ ይፈጸማሉ የተባሉ በደሎችና ጭቆናዎችም፣ እምነታቸውን ወደ ክርስትና ለውጠዋል በመባል፣ ጋብቻን አስገድዶ መፈጸም፣ የአጠፍታ ጥውፊ ጥቃት፣ ዘረፋ፣ የአምልኮ ስፍራዎችንና መንፈሳዊ ምስሎችን፣ ቅርሶችንና ምልክቶችን ማውደም፣ አፈና፣ የሐሰት ክሶችን ማቅረብ፣ በሐይማኖት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባት፣ በእምነት ተቋማት ላይ ቁጥጥር ማድረግና በሐይማኖት ነጻነት ላይ ገደብ መጣል ይገኙባቸዋል።
ከባድ የሐይማኖት ነጻነት ጥሰቶች ከሚካሄድባቸውና በክርስቲያኖች ላይ የከፋ ስቃይ ከሚያደረሱት ሙስሊም ሀገራት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
ሳውድ አረቢያ፣ ባንግላደሽ፣ ሕንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ኢራቅ፣ ሊቢያ፣ ኒጀር፣ ናይጀሪያ፣ ፓክስታን፣ ፍልስጤም፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ቱርክመኒስታን፣ ኡዝቤክስታን፣ የመን፣ አልጀሪያ፣ አዘርባዣን፣ ብሩኔይ፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ካዛክስታን፣ ኪርጊዚስታን፣ ማልዲቭስ፣ ማውሪታኒያ፣ ኳታር፣ ታጂክስታን፣ ቱርክ።