Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘James Caviezel’

በ ካህን፣ በ ቄስ እና በ ፖለቲከኛ መካከል ያለውን ልዩነት መለየት አልተቻለንም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 23, 2020

የፊልሙ ክርስቶስ” ድንቁ ጂም ካቪዜል ስለ አዲሱ ፊልሙ “„Infidelወይንም ኩፋር” በሰጠው ቃለ ምልልስ ወቅትሰርዝ ባህልን!’ የሚል ንቅናቄ በዓለማችን ላይ ይታያል፣ ይህ አመጸኛ ንቅናቄ በክርስትናም ላይ ነው ያነጣጠረው፣ ዓብያተ ክርስቲያናትንና መታሰቢያዎችን ያቃጥላል ክርስቲያኖችን ይገድላል፤ ሆኖም የፓስተሮቹና ካህናቱ ዝምታቸው፤ የአመጸኞቹ ረዳቶች ያደርጋቸዋል። “ሰርዝ ባህልን” ፊት ለፊት መጋፈጥ ያቃታቸው ካህናት እና ጳጳሳት “ከሃዲ ይሁዳዎች፣ ፖንትስ ጲላጦስ ወይም ፈሪሳውያን ናቸው” ይላቸዋል ፡፡ በአሁን ወቅት በ ካህን፣ በ ቄስ እና በ ፖለቲከኛ መካከል ያለውን ልዩነት መለየት ካልቻሉ በእውነቱ ይህ በጣም ያሳዝናል ፡፡ ይህ ለብነት ተብሎ ይጠራል፡፡ እናም ክርስቶስ ለእነሱ ልዩ ቦታ እንዳለው በደንብ ያውቁታል፡፡

ዋው! ድንቅና ወቅታዊ የሆነ አስተያየት ነው! በሃገራችንም በብዙ ቀሳውስት፣ ካህናትና ጳጳሳት ዘንድ እየታየ ያለው ይህ በጣም አሳዛኝ የሆነ ክስተት ነው።

ፊልም ካየሁ በጣም ብዙ ዓመታትን አስቆጥሪያለሁ፡ ይህን „Infidel/ኩፋር” የተሰኘውን ፊልም ግን ለማየት ጓጉቻለሁ። “የጌታችን ህማማተ መስቀል / The Passion of the Christ“ በሚለው ፊልም ክርስቶስን የወከለው ጂም ካቪዜል ነው። ይህን እጅግ በጣም የሚመስጥ ስራ ከዘማሪ አቤል ተስፋየ “የመድኃኔ ዓለም ሕማም” የበገና ዜማ ጋር እናዳምጥው እንባ በእንባ ነው የሚያደርግን። ዩቲዩብ ፊልሙን ስለማያስለፈው በሌላ ፕላትፎርም አቀርበዋለሁ። የሚገርመው የተዋናይ James Caviezel (JC) ስሞች ፊደላት = (JC) Jesus Christ.

የሃገራችንም ክርስቲያን የፊልም ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ እያየን ያለውን ሰቆቃ በፊልም እና ድራማ መልክ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል!

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: