Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Israeli Police’

የእሥራኤል ፖሊሶች ኢትዮጵያውያን መነኮሳትን በማንገላታቱ ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ማዛወሯን ለጊዜው ገታች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 13, 2018

በኢየሩሳሌም ከተማ፡ የኢትዮጰያውያን ርስት ወደ ሆነውና፡ የእስራኤል ሬድዮ ጣብያ ተከራይቶ ይሠራበት ወደነበረው ከ110ዓመት በላይ ያስቆጠረ ህንፃ የእስራኤል መከላክያ ሰራዊት በራሱ ፈቃድ ገብቶ አባቶችን በኃይል ማስወጣቱ፣ ማንገላታቱና ማሠሩ አንድ ተንኮል ከበስተጀርባው አለ ያስብላል።

የግብጽ እጅ፡ ወይስ ኢትዮጵያ በኢየሩሳሌም ጉዳይ ከጥቂት ወራት በፊት ባልተባበሩት መንግሥታት ከመሀመዳውያኑ ጋር በመሰለፏ?

ያም ሆነ ይህ፡ በአባይ ወንዝ ሳቢያ፡ እስራኤልም ሆነች አውሮፓ፡ ሁሉም ከግብጽ ጋር ማበሩን ይመርጣሉ።100 ሚሊየን ቁንጥንጥ ግብጻውያን ከሚጠሙና ከሚራቡ 100 ሚሊየን ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን መቸገራቸውን ይመርጣሉ። 100 ሚሊየን የተራቡ ግብጻውያን እስራኤልንም ሆነ አውሮፓን በስደትና በሽብር ያተረማምሷቸዋልና።

ስለዚህ፡ ዓለማዊው የእስራኤል መንግስት ኢትዮጵያን ወደ አረቦቹ በይበልጥ እንድትጠጋ መግፋት፣ ከእስራኤል ጋር ያላትንም ቅርርብ በጣም እንዳታጠብቅና በረከቱንም እንድታጣ ይሻሉ። የአባቶቻችንም መንገላታት የሚነግረን፡ ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም አዙራ፡ በእስራኢል ዘንድ መልካም ግምት እንዳይሰጣት ለማድረግ በማሰብ ሊሆን ይችላል። Problem – Reaction – Solution.

ለማንኛውም፡ እስራኤል ዕብራይስጥ ቋንቋን እንደ አረብኛ ከቀኝ ወደ ግራ መጻፉን ማቆም አለባት፤ ኢትዮጵያም ከአረቦች ጋር ጢብጢብ መጫዋቱን መተው ይኖርባታል።

[ትንቢተ አሞጽ ፱፥፯]

የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር

______

 

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: