Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Holland’

የኔዘርላንዶች ንግሥት ኢትዮጵያ ናት | ቢራ ጠጡ! ገብሱን አምጡ! ለማለት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 14, 2019

የእኛን ነገሥታት አንድ ባንድ ገድለው አሁን የእነርሱ ነገሥታት በኢትዮጵያ ላይ አንድ ባንድ ይፈነጫሉ

ንግሥት ማክሲማ በትናንትናው ዕለት ወደ አዲስ አበባ በርራለች። “የተባበሩት መንግሥታት ልዩ አምባሳደር” ከሚል ተልዕኮ ጋር “እግረ መንገዷን” የቢራ ፋብሪካዎችን ትጎበኛለች። “ሄነከን” እና “ሀበሻ” የተባሉት ቢራዎች ውስጥ የኔዘርላንዶች እጆች አሉባቸው። ንግሥት ማክሲማ መጋቢት ወር ላይ ወደ ጀርመን ጎራ ብላ ባቫሪያ የሚገኘውን አንድ የቢራ ፋብሪካ ጎብኝታ ነበር።

ቢራ፣ ቢራ ለኢትዮጵያውያኖች የተገኘ ተንኮለኛ ሥራ

ደጋግሜ የምለው ነው፤ እንጀራና በርበሬ ተመጋቢ ለሆኑት ኢትዮጵያውያን ቢራ እንደ መርዝ ነው፤ እንጀራ እርሾ፣ ቢራም እርሾ፤ ቢራ ለኢትዮጵያውያን ሆድ የማይመች መጠጥ ነው። ጣፋጩ እንጀራና ወጣችን እንደ ጠላ፣ ጠጅ ወይንም ቀይ ወይን ጠጅ ጣፋጭ ከሆኑ መጠጦች ጋር ነው የሚሄደው። ቢራ ግን ከቦርጭና ጨጓራ በሽታ በቀር ሌላ የሚሰጠን ነገር የለም። ሁልጊዜ የማስታውሰው ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት ብሔራዊ ቴያትር አካባቢ በሚገኝ አንድ ምግብና መጠጥ ቤት ውስጥ ጣፋጭ የሆነ ምግብ ከበላሁ በኋላ ያማራኝ ጠላ ስለነበር፤ “ባክዎ ጠላ ያምጡልኝ” አልኳት ለአንዲት አስተናጋጅ፤ እርሷም “ይቅርታ ጠላ አንሸጥም፤ ምግብ ቤታችን ደረጃው ከፍ ያለ ስለሆነ ቢራ ብቻ ነው የምንሸጠው” አለችም። አያሳዝንም?!

ለማንኛውም፤ እያንዳንዱ የሳጥናኤል አገር በኢትዮጵያ ላይ ላለው ጽንፈኛ ተልዕኮ የየራሱ ድርሻና የሥራ ክፍል አለው። ባለፉት ወራት የዴንማርኳ ልዕልት “የኢትዮጵያን ሴቶች ለማጎልበት” በሚል ሽፋን የኢትዮጵያ ቤተሰቦች መዋቅርን ለማናጋት ከሰዶማዊ ተልዕኮ ጋር ብቅ ስትል፤ ቀጥላ ደግሞ ይፋ ያልሆነችው የአሜሪካ ልዕልት፡ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጅ፡ ኢቫንካ ትራምፕ (የባሏን ስም ለምን አልያዘችም? ኢቫንካ ኩሽነር መባል ነበረባት) እንደዚሁ “የኢትዮጵያን ሴቶች ለማጎልበት” በማለት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዛ በዓለም አቀፋዊው ፀረኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ላይ ተደመረች። ወደ ኢትዮጵያ የሄደችበት ዋና አላማ ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተከሰከሰበት አውሮፕላን ምክኒያት ቦይንግን እንዳይከስ ለማድረግ ነው። የቦይንግ ቅሌት ፕሬዚደንት ትራምፕን በጣም አስደንግጧቸዋልና።

ጤፉን መንጠቅ አልተቻላቸውም ፥ ስለዚህ አሁን በቢራ በኩል የገብስ ባለቤትነት ይገባናል ይሉ ይሆናል

ወደ ኔዘርላንዶች ስንመለስ፤ የሙከራዎች ወዳጆች የሆኑት ሆላንዳውያን በአገራቸው መሬት ጤፋችንን በመዝራት አመርቂ የሆነ ውጤት በማምጣታቸውና ወደፊት የሰው ልጅን ከገባበት የአመጋገብ ቀውስ ሊያድን የሚችል ልዩ እህል መሆኑን ስለደረሱበት የጤፍን ባለቤትነት በእጃቸው ለማስገባት ሞክረው ነበር፤ ግን አልተሳካም። ታዲያ አሁን ዓይናቸውን በገብስ ላይ ጥለዋል። የገብስም መገኛ እናት አገር ኢትዮጵያ ናት።

በአሜሪካ “ቀይ ህንዶች” የሚባሉት የአሜሪካ ባለንብረቶች ቀስበቀስ እየደከሙ ሊጠፉ የቻሉት፤ ዊስኪና ጥንባሆ በአውሮፓውያን ከተሰጣቸው ጊዜ አንስቶ ነበር። ልክ ለጥቁር አሜሪካውያኑ አድነዛዥ እጾችንና ልጅ ማስወረጃ ኪኒኖችን እየሰጡ ቁጥራቸውን እንደቀነሱባቸው።

በአገራችንም እንደ አሸን የበዛው የቢራ ፋብሪካ ፣ ከቆሻሻው ጋኔን መሳቢያ ሺሻ ጋር ከፊሉ ሕዝባችንን እያለሰለሰ፣ እያደነዘዘ፣ ወኔ ቢስ እያደረገ፣ እያደከመና እያጠፋ ነውና በዚህ ከቀጠለ አንድ ቀን ሆላንዶች ገብስን የመንጠቅ እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው።

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: