Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Hodegetria’

ተዓምረኛዋ የሩሲያ አይከን | ወንጌላዊው ሉቃስ የሣላት የቅ/ ማርያምና ልጇ ሥዕል የኢትዮጵያውያንን ገጽታ ታንጸባርቃለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 26, 2018

..አ በ1383 .ም የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዋና ከተማ የነበረቸው ኮኒስታንቲኖፕል (የዛሬዋ ኢስታንቡል) ፀረክርስቶስ በሆኑት ሴልጁክ ቱርኮች እጅ ከመውደቋ ከ70 ዓመት በፊት ወላዲተ አምላክ ሥዕሏን ወደ ሩሲያ አሸሸቻት። ዛሬ በ ቲኽቪን ግዛትየፍልሰታ ገዳም” ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ትገኛለች። ሩሲያ ከቱርክ ጋር በቅርብ ለምታካሂደው “የመጨረሻ ጦርነት” ይህች ተዓምረኛ ሥዕል ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች። ክርስቲያን ወገኖች ከቱርክ እና ቱርኮች ራቁ፤ መጥፊያቸው ተቃርቧል!

ከዚህች ውብ ሥዕል ጀርባ የሚሰማውን ዜማ ያቀረበው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የወንዶች ዘማሪ ቡድን ነው። በእንጨት ላይ የተሳለችውን ይህችን ተዓምራዊ ቅድስት ሥዕል የሚያወድስ ድንቅ ዜማ ነው። ከፍ እና ዝቅ እያሉ የሚሰሙት የተለያዩት ድምጾች ፍጹምነትየተሞላበት-ተስማሚነት በጣም የሚመስጥ ነው። ስለዚህ ምስል የሚያሳየውን ቀጣዩን ቆንጆ የካርቱን ፊልም፡ ቋንቋው ባይገባንም፡ እስከመጨረሻው እንከታተለው፤ ልብ የሚነካ ነው።

ስለዚህ ምስል የሚያሳየውን ቀጣዩን ቆንጆ የካርቱን ፊልም፡ ቋንቋው ባይገባንም፡ እስከመጨረሻው እንከታተለው፤ ልብ የሚነካ ነው።

ከኦርቶዶክስ ሰዎች መካከል በመለኮታዊው ዓለም ተዓምራዊ ፈውስ ያላቸው ሥዕላት በጣም የተከበሩ ናቸው እነዚህ ሥዕላት ባለፉት ብዙ መቶ ዘመናት በሩሲያ የኦርቶዶክስ ታሪክ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የጋብቻ ግንኙነትን በመፍጠር ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፣ ብዙ ሩሲያውያን ቅዱሳት ሥዕላት ፍሰቶች የተገኘ ጸጋን አግኝተዋል ኦርቶዶክሳዊ አሳሳል ያላቸው እነዚህ ቅዱሳት ሥዕላት የመንፈሳዊ፣ አዕምሮና የአካል ህመም ያላቸውን ብዙ በሽተኞች ፈውሰዋል። ይህም ለየት ያለ አስደናቂ ነገር ለብዙ መቶ ዘመናት በክርስትያኖች ዘንድ ታላቅ አክብሮትና ጥልቅ ፍቅር እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።

የራሳችን የሆነውን ነገር ሁሉ እየናቅን የፈረንጆቹን ቅዱሳት ሥዕላት የምንወስድ ከሆነ የጣሊያኑን ትተን የሩሲያን ብንመርጥ ጥሩ ነው

የዛሬዎቹ የሩሲያ ኦርቶዶክስ የስነጥበብ ማዕከላት ለእነዚህ ድንቅ ሥዕላት ከፍተኛ እንክብካቤ ያደርጉላቸዋል፣ በየጊዜው ጥልቀት ያላቸውን አውደጥናቶችን ያካሂዳሉ።

ከተአምራዊ ፈውስ ሥዕላቱ መካከል ልዩ የሆነችውና በመላው ዓለም ታዋቂነትን ያተረፈችው ወንጌላዊው ሉቃስ የሳላት የማርያም ሰዕል 8 መረጃዎች

  • 1. የቲክቪን የወላዲተ አምላክ ሥዕል በጣም ታዋቂ ከሆኑት የኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ሥዕላት መካከል አንዷ ናት።
  • 2. እንደሚታወቀው፡ በ 5 ኛው ክፍለ ዘመን፣ ሥዕሏ ከኢየሩሳሌም ወደ ኮንስታንቲኖፕል ተዘዋውራ ነበር፣ በዚያም ለርሷ ሲባል ቤተ ክርስትያን ተሠርቶላታል።
  • 3. ሥዕሏ የሕይወት መንገድን የምታሳይወይም (በግሪኩ ድንግል Hodegetria) በመባል የሚታወቀውን የአሳሳል ዘይቤ ተከትሎ የተሳለ ነው። በዚህም ወላዲተ አምላክ (በግሪኩ፡ Theotokos) ልጅዋን ኢየሱስን ከጎኗ አቅፋ፡ የሰው ዘር መዳን ምንጭ ኢየሱስ እንደሆነ በቀኝ እጇ ወደ እርሱ ታመለክታለች።
  • 4. ይህች ሥዕል እ..አ በ 1383 . በሩሲያው ቲኽቪን በሚገኝ ሐይቅ ላይ ተንሳፍፋ ታየች።
  • 5. 14 ኛው ክፍለ ዘመን አንስቶ ቅድስት ሥዕሏ በቲኽቪን ግዛት በተሠራላት የፍልሰታ ገዳም ትገኛለች።
  • 6. ... 1941 .ም የናዚ ጀርመን ወታደሮች ቅድስት ሥዕሏን ከቲኽቪን ወደ ፕስኮቭ፡ ከዚያም በ 1944 .ም ወደ ላትቪያዋ ዋና ከተማ ወደ ሪጋ ወሰዷት።
  • 7. ከጊዜ በኋላም፡ ሥዕሏ ለደህንነት ሲባል በሪጋ ከተማ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ጳጳስ አማካኝነት ወደ አሜሪካዋ ቺካጎ ከተማ በ1949 .ም ተወሰደች። ፉሲያና ላትቪያ በዚያን ጊዜ በፀረክርስቲያኖቹ ሶቪዬት ኮሙኒስቶች ቁጥጥር ሥር ነበሩና። አንዳንዶች እንደሚሉት ከሆነ፤ ቅድስት ሥዕሏ እ..አ በ1917 .ም ከብላዲሚር ሌኒን ፀረክርስቶሳዊ ዘመቻ ትደበቅ ዘንድ ከ ቲኽቪን ገዳም ወጥታ ነበር።
  • 8. በፀረክርስቶሷ ቱርክ እና በሌሉች የሩሲያ ጠላቶች ላይ ሩሲያውያኑ ድል እንዲቀዳጁ ትልቅ አስተዋጽዖ ያደረገችው ይችህ ቅድስት ሥዕል፡ ከ 14 ዓመታት በፊት፡ በቭላዲሚር ፑቲን ዘመን እ..አ በ2004 .ም ከአመርካዋ ቺካጎ ወደ ሩሲያ ተመልሳለች።
  • በዚሁ ዓመት አሜሪካን ለማጥፋት የታጨው ባራክ ሁሴን ኦባማ በቺካጎ ከተማ ብቅ ብቅ አለ። በ 2008 .ም በፐርጋሞን የሰይጣን ኃውልት የተቀባው ኦባማ የፕሬዚደንት ወንበሩ ላይ ከመቀመጡ በፊት፡ ከ2005 እስከ 2008 ድረስ የቺካጎዋ ኢለኖይ ግዛት ሴነተር ነበር።

______

Posted in Ethiopia, Faith, Music | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: