ኢትዮጵያ ተከባለች
አውሬው ተለቅቋል፡ አውሬው ከግራ ከቅኝ፡ ከላይ ከታች፡ ከውጭ ከውስጥ እያለ ይፈታተነናል። አውሬው በተከታዮቹ አማካይነት ምድረ ሞርያን እና ምድረ ኢትዮጵያን ለመዉረር ዳር ዳር ይላል። የኢትዮጵያ አምላክ ግን እንደተለመደው በኢትዮጵያ ተራሮች ላይ በሠፈረው መንፈሳዊ ሠራዊቱ አማካይነት በዝምታ ይከታተላቸዋል።
ከየመን እስከ ሶማሊያ ከባህረ ገሊላ እስከ ቪክቶሪያ ሃይቅ ድረስ የአውሬው ሠራዊት እየቀበረ ያለውን ወጥመድ የኢትዮጵያ አምላክ ፎቶ በማንሳት ላይ ይገኛል።
የአውሬው አገልጋዮች፡ ሸህ ቢን ላድንን ወደ ሶማሊያ ሃጂ አልሳርካዊንን ደግሞ ወደ ጋዛ ለማሸጋገር ዝግጁ ይመስላሉ፡ እስካሁን ካልተሸጋገሩ።
ሊያውቁትና ሊቀበሉት ያልፈለጉት የእስራኤል አምላክ ቅዱስ መንፈስ በምድረ ኢትዮጵያ እንደሚገኝ ደርሰውበታል። ኢትዮጵያን ሊደፍሩ ይፈልጋሉ፡ ግን እስካሁን አልተቻላቸውም፡ ስለዚህ፡ በአውሬው ዓይን ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ ነገሮች ተመሳሳይነትን በምታሳየው፡ ነገር ግን የቅዱሱ መንፈስ ተቃራኒ መንፈስ በተንሰራፋባትና የኢትዮጵያ ጆግራፊያዊ የመስተዋት ግልባጭ በሆነችው በአፍጋኒስታን አስፈላጊ ያልሆነ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ መስዋእትን በመክፈል ላይ ይገኛሉ።
በአሜሪካ ግዛቶች ብዙ ጥፋት የሚያስከትሉት አውሎ ንፋሶች መነሻ የኢትዮጵያ ተራሮች መሆናቸውን መመልከት የቻለው የጠፈር መርማሪው አሜሪካዊ ድርጅት፡ “NASA” ለኢትዮጵያ መንግስት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚከፍል ይታወቃል። የሚገርመውና ብዙዎቻችንን ምናልባት ሊይስደነግጥ የሚችለው ነገር፡ በመስከረም ፩፩ ፪ ሺ ፩ ዓ.ም. ሽብርተኞች በኒውዮርክ ከተማ ላይ ጥቃት ባደረጉበት በአዲሱ አመታችን መግቢያ እለት፡ “ISS” በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፋዊው የህዋ መመርመሪያ ጣቢያ፡ የኦርቢታዊ ቦታ አቅጣጫው፡ (Orbital Position) ልክ አፍሪቃ ቀንድ ላይ ማረፍ እንደነበረበት፡ ነገር ግን ፕላኑ በጊዜው በስራ ላይ እንዳልዋለ ጭምጭምታዎች መሰማታቸው ነው። ምስጢሩ ምን ይሆን?
ከክትባት እንቆጠብ
እ.አ.አ በ August 1, 1989ዓ.ም. “The Sun” ተብሎ የሚታወቀው ታዋቂ የእንግሊዝ አገር የመንገድ ወሬ አሳዳጅ ጋዜጣ፡ “Big Brother’s Coming!” በሚል ርዕስ፡ በላብራቶሪ ውስጥ የተፈጠረ የአሳማ ጉንፋን ኤፒደሚ ገብቷል ይባልና የክትባት ዘመቻ ይካሄዳል ፣ ክትባቱ የሚያስፈልግበትም ምክኒያት በዚህ ሰበብ ህዝቡን ሁሉ በጸረ–ክርስቶሱ የአውሬው መርዝ ለመንደፍ በማሰብ ነው የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር።
ጋዜጣው ገና ከ 20 ዓመታት በፊት እንዲህ የሚል ነገር በገጾቹ ላይ አስፍሮ ነበር፡
“Coded microchips implanted in every person in the country would tie all of us into a master computer that could track anyone down at any moment, and plans for such a system are already under way whether you like it or not!”
ይቀጥልና…
“The tiny transmitters can be injected painlessly from a tiny gun in humans without them even knowing it through a nationwide vaccination program.”
በመጨረሻም፡
“All the government would have to do is make up something like the swine flu vaccine.”
በማለት ጽፎ ነበር።
እነዚህ የዲያብሎስ አገልጋዮች፡ እንዲህ የመሳሰሉትን ሴራዎች ገና ጥንት ነው ሲጠነስሱ የቆዩት። እግዚአብሔር ይይላቸው፡ እግዚአብሔር ከተንኮላቸው ሁሉ ይጠብቀን።
ባካችሁ እኛ አንተነኳኮል፡ አንድከም፡ በመጨቃጨቅ በመሰዳደብ አውሬውን አንመግብ። እንቀራረብ፡ እንሰባሰብ፡ እንተሳሰብ፡ እንተባበር፡ እንፈቃቀር፡። በኋላ አቅሙም ጊዜውም ስለማይኖረን እንዳይዘገይብን።
http://www.mediafire.com/?mnhltmmyzqn
______________________________________