😇 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
😈 ዓለምን ሲያውኩት ያጋንንት ሥራቸው እንዳይተርፈን ለእኛ የእነርሱ ግብራቸው ገብርኤል በሰይፉ ቀጥቅጦ ጣላቸው፤ እናመልክት ለሱ እናስታውስ ጠዋት ማታ እንዲያስተራርቀን ለምኖ ከጌታ።
❖ ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው ❖
😇 “ሰለጠነ” የተባለውን ዓለም ጨምሮ ምስጢራዊውን ዓለም ሁሉ እያስደነቀ ያለው ድንቁ መጽሐፈ ሔኖክ የተጻፈበት የግእዝ ቋንቋ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ዛሬ እነ “አቡነ” ናትናኤል፤ “ኦሮሞ” ነን ብለውና ክቡር ስጦታ፤ ትልቅ ስጦታ የሆነውን የግ እዝ ቋንቋን የሰሜናውያን ቋንቋ ነው አንፈልግውም፤ በሚል ድፍረትና ምስጋና-ቢስነት ቅዳሴውን አጋንንታዊ በሆነው የኦሮምኛ ቋንቋ ለማድረግ ደፍረዋል። በምኒልክ የብሔር-ብሔረሰብ ርዕዮተ ዓለም የሰከሩት የሕወሓት ቀሳውስትስ፤ በትግርኛ ካልቀደስን ይሉን ይሆን? በትግራይ ጽዮናውያን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነቱ ልክ ሊጀምር ሦስት ወር ሲቀረውና “ምርጫ” የተባለውን የሙቀት መለኪያ ለማካሄድ በሚዘጋጁበት ዋዜማ እነ ዶ/ር ደብረ ጽዮን፤ “ካሁን ጀምሮ የግዕዝ ቋንቋ በመላዋ ትግራይ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደ መደበኛ ትምህርት ይሰጥ!” የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈው ነበር። ዛሬስ እንዲህ ያለ ትዕዛዝ ለማስተላለፍ ይሹ ይሆንን? አይመስለኝም። ያኔም ትክክለኛዎቹን አጋዚያን-ተጋሩ-ጽዮናውያንን ለመደለል የተደረገ እርምጃ መሆኑን ዛሬ በግልጽ እያየነው ነው። ሕወሓቶችን ጨምሮ ሁሉም ምንሊካውያን ጦርነቱን በጋራ ጀምረውታልና።
👉 ጦርነቱ ልክ እንደጀመረ፤ “ለመሆኑ ይህ ጦርነት ማንን ነው “የሚጠቅመው”?” በሚል ጥያቄ ሥር
“የጦርነቱ ዓላማ ፤ ኢ–አማንያኑ የሻእቢያ እና ህዋሀት ቡድኖች ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ቅዱስ ያሬድን፣ አቡነ አረጋዊን፣ አባ ዓቢየ እግዚእን፣ ነገሥታቱን ኢዛናን፣ ዮሐንስን፣ ሰንደቁን፣ ግዕዝን፣ አክሱምን አጥፍተው በሃምሳ ዓመታት ውስጥ በተገኘ ጣዖታዊ ማንነት “ኢ–አማኒ የትግራይ ሶሻሊምዝ–ብልጽግና” ርዕዮተ ዓለምን በመከተልና የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን የቻይና ባንዲራም በማውለብለብ ከኤርትራ ጋር ለብቻቸው መኖር ይሻሉና ነው። በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የግራኝ አብዮት አህመድ እና የስብሃት ነጋ ጦርነት ነው።” በማለት ጽፌ ነበር።”
😈 ጠላታችን ዲያብሎስ ለመንፈሳዊ ሕይወት ብዙም የማይረዱንን ወይንም መንፈሳዊ ድክመት ያላቸውን(አማርኛ፣ ትግርኛ)እንዲሁም አጋንንታዊ የሆኑትን ቋንቋዎችን (ኦሮምኛ፣ አረብኛ፣ ሶማልኛ) ተጠቅሞ እርስበርሳችን እንድንጨፋጨፍ፣ ሰአራዊቱን እየላከ ያልተደቀለውን የትግራይን ሕዝብ ደቅሎ በማዳከም የኤዶማውያኑን እና የእስማኤላውያኑን የእንግሊዝኛን እና የአረብኛን ቁንቋ ከእነ ሉሲፈራዊ አምልኮታቸው ለማንገስ ሲል ነው በትግራይ ጽዮናውያን ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን በምዕራቡም በምስራቁም እርዳታ የጀመረው። የገዳማትና ዓብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም የቅርስ ማውደም ጂሃዱን የከፈተባቸውም የመንፈስ ማንነታቸንና ምንነታቸውን አጥፍቶ እንደ ኦሮሞው የስጋን ማንነትና ምንነትን ለማንገስ ነው እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ሁሉንም ነገር ሸፋፍኖ ምንም ነገር እንዳይታወቅበት በስልት መረጃዎችን በማጥፋት/በመሰወር ላይ የሚገኘው።
ይህ ጥቃት/ጂሃድ የጀመረው የእግዚአብሔር የሆነውንና ለመንፈሳዊ ሕይወት በዓለማችን ተወዳዳሪ የሌለውን የግእዝ ቋንቋችንን በኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ሤራ ጠንሳሽነት የስጋ ማንነትና ምንነት ባላቸው ጋላ/ ኦሮሞ ወራሪዎች በኩል ለማጥፋት ከተነሳበት ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት አንስቶ ነው። ጂሃዱን ጦርነቱን በስጋችን ላይ ብቻ አይደለም የከፈቱብትን፤ በነፍሳችን፣ በመንፈሳዊ ሕይወታችን፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን፣ በቋንቋችን፣ በጽዮናዊው ሰንደቃችን፣ በታሪካችንና በባሕል/ትውፊታችን ላይም ጭምር ነው። ይህ ውጊያ በየደረጃው/በየዘመኑ ከመቶ ሰላሳ ዓመታት፣ ከአምስት መቶ ዓመታት፣ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊትና ከስድስት ሺህ ዓመታት አንስቶ ዲያብሎስ እና ጭፍሮቹ ዝግጅት አድርገው ሲያካሂዱት/እያካሄዱት ያለው ውጊያ ነው። በአክሱም ጽዮን ላይ ያተኮሩበት ምስጢርም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላዋ መንፈሳዊቷ ዓለማችን ቁልፍ መሠረት በጥልቁ ተደብቆ የሚገኝባት ምድር ስለሆነች ነው። ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ይህን በደንብ ያውቁታል/ደርስውበታል።
ለዚህም ነው፤ በጽዮናውያን ላይ የዘር፣ የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የትውፊት፣ የቅርስ፣ የቋንቋ ማጥፋት ጂሃዳዊ ዘመቻ የከፈቱት ኤዶማውያንና እስማኤላውያን ( መሀመዳውያን + ፕሮቴስታንቶች + ኢ-አማንያን + ኦሮሞዎች + ሶማሌዎች + ከሃዲ አማራዎች + ከሃዲ ተጋሩዎች)ሁሉ የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ተከፍቶ እየተንከተከተ ይጠብቃቸዋል የምንለው። ፻/100%
በተለይየዛሬይቷ ኢትዮጵያ ብሎም መላዋ አፍሪካ እና ዓለም መዳን የሚችሉት ሕዝቦቻቸው የእግዚአብሔር የሆነውንና በመንፈሳዊ ጠቀሜታው ከዓለማችን ቋንቋዎች ሁሉ በጣም ግዙፍ የሆነውን የግእዝ ቋንቋን በብሔራዊ ቋንቋ መልክ መናገር ሲጀምሩ ብቻ ነው። ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያን ይህን ደርሰውበታል!
😇 ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል
❖ ትውፊታዊ ታሪኩ
ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ፍጥረታት በሐሌዎ‘ በነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ። ግእዝ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ስንል አዳም ማለት ያማረ የተዋበ ማለት ሲሆን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው፤ አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው ቋንቋ በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል።
😇 ግእዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ ለማረጋገጥ ከሚያቀርቧቸው ፲ ምክኒያቶች መካከል፦
፩ኛ. የ ”ግእዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ
፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ
፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ
፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምሥጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ
፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ትግርኛ በትግሬዎች፣ ኦሮምኛ በኦሮሞዎች፣ ሶማልኛ በሶማሌዎች፣ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች፣ እንግሊዝኛ በእንግሊዞች፣ ቻይንኛ በቻይኖች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ
፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግእዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ
፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።
፰ኛ. «ግእዝ» የሚለው ቃል እራሱ አንደኛ፣ የመጀመሪያ ማለት ነው። የሰው ልጅ የመጀመሪያ የሆነው ቋንቋ “አንደኛ” ቢባል ይስማማዋል።
፱ኛ. የዚህ ቋንቋ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሰው አዳም ነው። የዚህ ሰው ስም በቋንቋው ትርጉም ሊኖረው ይገባል። በግእዝ «አዳም» ማለት ያማረ ማለት ነው።
፲ኛ. ሌላው ነገር የግእዝ ፊደላት ከአምላክ የተገኙ ናቸው ለዚህም የአዳም ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖስ በሰማይ ገበታ እንዳያቸው አባቶች ይናገራሉ።
አማርኛ ቋንቋ ከግእዝ ያገኛቸውን በሙሉ ይዞ ሌሎች ፯ ፊደላትን በመጨመር ግእዝ ፳፮ ሲሆን አማርኛ ደግሞ ፴፫ ነው “ቨ”ን ሳይጨምር ማለት ነው።
😇 የግእዝን ፊደሎች ትርጉም ስንመለከት፦
ሀ፦ ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ፥ የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው
ለ ፦ ብሂል ለብሰ ሥጋ እምድንግል ፥ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን ለበሰ
ሐ ፦ ብሂል ሐመ ወሞተ ፥ ስለኛ ታመመና ሞተ
መ፦ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ፥ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው
ሠ ፦ ብሂል ሠረቀ በሥጋ ፥ በሥጋ ተገለጠ
ረ ፦ ብሂል ረግዓት ምድር በቃሉ ፥ ምድር በቃሉ ረጋች
ሰ ፦ ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ
ቀ ፦ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ፥ ቃል መጀመሪያ ነበር
በ ፦ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ፥ ጌታችን በትሕትናው ወደኛ ወረደ
ተ ፦ ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ
ኀ ፦ ብሂል ኀያል እግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔር ኀያል ነው
ነ ፦ ብሂል ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ፥ መከራችንን ያዘልን ሕመማችንን ተሸከመልን
አ ፦ ብሂል አእኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔርን ፈፅሜ አመሰግነዋለሁ
ከ ፦ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር ፥ ጌታችን ቻይ ነው
ወ ፦ ብሂል ወረደ እምሰማይ ፥ ጌታ ከሰማይ ወረደ
ዐ ፦ ብሂል ዐርገ ሰማያተ ፥ ወደ ሰማይ ዐረገ
ዘ ፦ ብሂል ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ፥ ጌታ ሁሉን የሚይዝ
የ ፦ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይልን ታደርጋለች
ገ ፦ ብሂል ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ፥ ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሠራ
ጠ ፦ ብሂል ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ፥ ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱና ዕወቁ
ጰ ፦ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፥ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው
ጸ ፦ ብሂል ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ ፥ ጸጋ እና በረከት ተሰጠን
ፀ ፦ ብሂል ፀሐይ ጸልመት በጊዜ ስቅለቱ ለእግዚእነ ፥ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመች
ፈ ፦ ብሂል ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ፥ ጌታ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ
ፐ ፦ ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ፥ ፓፓኤል የአምላክ ህቡዕ ስም
ትርጉማቸዉ ይሄን ይመስላል።
😇 ስለዚህ ግእዝ የአዳም ቋንቋ ነው የሚለው መላምት የበለጠ ጥንካሬ አለው።
አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ፍቺውን ስንመለከት ደግሞ ግእዝ (የዜማ ስም፥ ግእዝ፣ እዝል እና አራራይ። የፊደል ስም ሀ ፦ ግእዝ ሁ ፥ ካዕብ ሂ ፥ ሳልስ …… ) በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ ፲፩ ፥ ፮ ላይ እግዚአብሔርም አለ ” እነሆ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው” ይላል።
_______________