Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Full Moon’

ሆሣዕና ፪ሺ፲፫/ 2013 ዓ.ም | ሁለት ጨረቃዎች? | Two Moons?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2021

በትናንትናው ዕለት ቴዎድሮስ “ርዕዮት” ፀጋዬን እና አቶ ታምራት ላይኔን እያዳማጥኳቸው (ስለ ትግራይ እነደሚጠበቅባቸው ብዙ አልተናገሩም፤ በተለይ የአማራ ፋሺስት ፋኖ ሚሊሺያ በምዕራብ ትግራይ ስለሚፈጽመው ወንጀል: ይሉኝታ/PC?) የምሽት ሰማዩ ላይ የታየኝ ይህ አስደናቂ ክስተት ነበር። አምና ልክ በዚሁ በሆሣዕና ዕለት እመቤታችንን እና ልጇን አማላካችንን ጨረቋዋ ላይ “ታዩኝ” በማለት ቪዲዮ አንስቼ የዲያብሎስ ጭፍሮች ባዘጉብኝ ዩቲውብ ቻኔሌ ላይ ለቅቄው ብዙ አድናቂዎችን አግኝቶ እንደ ነበር አስታውሳለሁ። ዘንድሮ ደግሞ ያው!

በነገራችን ላይ ዘንድሮም ልክ በዚሁ የሑዳዴው ጾም ወቅት እነ ግራኝ + የተባበሩት መንግስታት ወኪሎቹ ይህኛውን ቻነሌንም ለማዘጋት ሞክረው ነበር፤ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

_____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ከወር በፊት ልክ በዛሬው መድኃኔ ዓለም ዕለት ጨረቃዋ ላይ ያየሁት ተዓምር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 7, 2020

👉 መድኃኔ ዓለም ነሐሴ ፳፯ / 27 / ፪ሺ፲፪ ዓ.

እጄ ያለወትሮው እየተንቀጠቀጠ ካሜራውን መያዝ እኪያቅተኝ ድረስ፤ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ክቡር መስቀሉን፣ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስን ቀለማቶቻችንን እና ኢዮጵያን ያየሁ መሰለኝ፤ የተሰማኝም ይህ ነው።

ጨረቃዋ እንደ መስተዋት ሆና ጌታችንን፣ እመቤታችንን፣ ክቡር መስቀሉን፣ ኢትዮጵያችንን፣ ቀለማቶቻችንን፣ የላሊበላን መስቀል (ያለፈውን የፀሐይ ግርዶሽ እናስታውሳለን?) ለመላው እያሳየች እኮ ነው። ኢትዮጵያኛው እና መስቀለኛው “ት” ፊደል እኮ በግልጽ ይታያል፤ በጣም ይገርማል! ይህ ተዓምር ቀላል ነገር አይደለም። በዚሁ ዕለት በአዲስ አበባ ኮተቤ ሚካኤል አካባቢ ከተከሰተው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ጋር ምን ሊያገናኘው እንደሚችል አላውቅም። ግን የሆነ ነገር አለ።

👉 ባለፈው የሆሳዕና ዕለት እመቤታችንን እና ልጇን ጌታችንን ነበር የታዩኝ፤

____________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የቅ/ ሚካኤል ድንቅ ተዓምር | ቀይዋ ጨረቃ ላይ እና የጥምቀት ምንጣፌ ሥር ኢትዮጵያን አየኋት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 21, 2019

ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ መልክ ጨረቃዋ ታይታኝ እንደነበረው፥ አሁን ደግሞ በቃና ዘገሊላ፣ በቅዱስ ሚካኤል ዕለት፣ በጥምቀት ማግስት፣ በጨረቃ ግርዶሽ ወቅት፤ ደም የለበሰችው ጨረቃ የኢትዮጵያን ቅርጽ ቁልጭ አድርጋ ታሳያለች።

ይህ አልበቃ ብሎ፣ በየጊዜው በጸበል ስጠመቅበት የነበረውን የቤቴን ምንጣፍ ሳነሳው ላሚኔቱ ወለል ላይ (እርጥበቱ አወፍሮታል) የኢትዮጵያ ቅርጽ ቁጭ ብላ ታየችኝ፤ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ፤ ምን ይሆን? አልኩ። ድንቅ ነው!

ለማንኛውም ከሰይጣን ጋር ተመሳጥራችሁ በእናት ኢትዮጵያ ላይ ሤራ የምትጠነስሱ የውስጥም የውጭም ጠላቶቿ የስልጣን ጊዚያችሁ እያለቀ ነው። ቅዱስ ሚካኤል በቅርቡ ጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ይከታችኋል!

ጨረቃዋ ዛሬም ደም ለብሳ ትታያለች!

____________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ደም የለበሰችው ጨረቃ | የሆነ ኃይል ከ ቍጥር ፳፩ / 21 ጋር ትልቅ ጕዳይ አለው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 20, 2019

ጃንዋሪ 21ን በጣም የሚፈልጋት ኃይል ባለፉት ቀናት ብዙ የግድያ መስዋዕቶች እንዲፈጸሙ አድርጓል

ኬኒያ፥ ጃንዋሪ 15 /2019

  • ሆቴል ውስጥ 21 ሰዎች ተሰው፥ ከመስከረም ፩ ጥቃት የዳነውን አሜሪካዊ ጨምሮ

ኮሎምቢያ፥  ጃንዋሪ 17 / 2019

  • በቦምብ ፍንዳታ 21 ሰዎች ተገደሉ

ሜክሲኮ፥ ጃንዋሪ 18 / 2019

ኃይለኛ የእሳት ቃጠሎ በመቀስቀሱ፤

  • መጀመሪያ፦ 66 ሰዎች ሞቱ
  • ቀጥሎ፦ 73 ሆኑ 7×3 = 21
  • ቀጥሎ፦ 79 ሆኑ፤ 7+9 = 16
  • 666

የጨረቃ ግርዶሽ፡ ጃንዋሪ 21/2019

ጨረቃዋ በመሬት እና በፀሐይ መካከል ትሆናለች፦ ቀይ ደም የለበሰችው ጨረቃ በተለይ በአሜሪካ ላይ ስትሽከረከር ትታያለች።

አስገራሚ የሆነውን የእሳት ገጽታ እንመልከት፦

ዔሳውያኑ አሜሪካ እና አውሮፓ ኢትዮጵያን መተናኮል ከጀመሩ ቆይተዋል፤ በየጊዜው ምልክትና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶዋቸዋል ግን እንደ እስማኤላውያኑ አጋራቾቻቸው በፈረዖናዊ ትዕቢት ስለተወጠሩ እጆቻቸውን ከአገራችን ላይ ማንሳት ተስኗቸዋል።

በዚህ የፈረንጆች ዓመት ሉሲፈራውያኑ በፕሬዚደንት ትራምፕ ላይ ምናልባት አስከፊ ጥቃት ሊፈጽሙ ይሆናል፤ ሥልጣኑን ሙሉ በሙል ለመቆጠጠር። ስለዚህ የአገራችን ጠላቶች ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ ሚነሶታ ውስጥ የጠነሱስትን ተንኮል ይገፉበት ይሆናል። በዚህም በአሜሪካ ላይ ከመስከረም ፩ ከበድ ያለ ፍርድ ይመጣል!!!

_________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: