Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2023
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Frog’

ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 20, 2022

❖❖❖[፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፲፫]❖❖❖

፩ በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።

፪ ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

፫ ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

፬ ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤

፭ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤

፮ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤

፯ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።

፰ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም፤ ትንቢት ቢሆን ግን ይሻራል፤ ልሳኖች ቢሆኑ ይቀራሉ፤ እውቀትም ቢሆን ይሻራል።

፱ ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና፥ ከትንቢትም ከፍለን እንናገራለንና፤

፲ ፍጹም የሆነ ሲመጣ ግን ተከፍሎ የነበረው ይሻራል።

፲፩ ልጅ ሳለሁ እንደ ልጅ እናገር ነበር፥ እንደ ልጅም አስብ ነበር፥ እንደ ልጅም እቈጥር ነበር፤ ጎልማሳ ሆኜ ግን የልጅነትን ጠባይ ሽሬአለሁ።

፲፪ ዛሬስ በመስተዋት በድንግዝግዝ እንደምናይ ነን በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ ዛሬስ ከእውቀት ከፍዬ አውቃለሁ በዚያን ጊዜ ግን እኔ ደግሞ እንደ ታወቅሁ አውቃለሁ።

፲፫ እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።

❖❖❖[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬]❖❖❖

፩ ወዳጆች ሆይ፥ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፥ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነው እንደ ሆነ መርምሩ፤ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።

፪ የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥

፫ ኢየሱስ ክርስቶስም በሥጋ እንደ መጣ የማይታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ይህም የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፤ ይህም እንዲመጣ ሰምታችኋል፥ አሁንም እንኳ በዓለም አለ።

፬ ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።

፭ እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል።

፮ እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።

፯ ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።

፰ ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።

፱ በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።

፲ ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።

፲፩ ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።

፲፪ እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።

፲፫ ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እርሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን።

፲፬ እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።

፲፭ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።

፲፮ እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።

፲፯ በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።

፲፰ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።

፲፱ እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።

፳ ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

፳፩ እግዚአብሔርንም የሚወድ ወንድሙን ደግሞ እንዲወድ ይህች ትእዛዝ ከእርሱ አለችን።

🔥ስለ ጽዮን ዝም አንልም፤ አሉን ይሁዳዎቹ!ለሦስት ዓመታት ያህል አማራ እና ተጋሩ ተዋሕዷውያንን + ጌዲዮኖችን ወዘተ በኦሮሚያ ሲዖል ሲጨፈጨፉ የቆዩት የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው የግራኝ ኦሮሞዎች ዛሬ ከእስማኤላውያን እና ኤዶማውያን፣ ከአማራው፣ ከሶማሌው፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አረቦች፣ ቱርኮች እና ኢራኖች ጋር ሆነው ተዋሕዶ ጽዮናውያንን ጨፈጨፏቸው።

የዋቄዮአላህ ጭፍሮች ነገርስ ግልጽ ነው፤ የስጋ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን ክደው ወደ ክርስቶስ እስካልመጡ ድረስ ሁሌ የጽዮናውያን ጠላት መሆን ግድ ስለሚሆንባቸው ፈጠነም ዘገየም በአክሱም ጽዮን ላይ እንደሚዘምቱ ግልጽ ነው። የሚገርመውና የሚያንገበግበው “ተዋሕዶ ክርስቲያን ነኝ! ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያለ ሰንድቁን ያላግባብ የሚያውለበልበው፣ ከእስማኤላውያኑ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ጋር አብሮ ክርስቲያን ወንድሞቹን የጨፈጨፈ እና በረሃብ እየቆላ ያለው ብቸኛው የዓለማችን መንጋ አማራ ብቻ መሆኑ ነው! ዛሬም፤ ሁሉም ነገር ግልጥልጥ ብሎ በሚታይበት ዘመን እንኳን ከፈጸመው በጣም ከባድ ግፍና ወንጀል ምናልባት በንስሐ ተመልሶ እጁን ወደ እግዚአብሔር በመዘርጋት ፈንታ፤ የአጥፍቶ ጠፊን ካባ በማጥለቅ ከአበቃለት የአራጁ ፋሺስት ኦሮሞ አገዛዝ ጋር አብሮ በጭካኔና በፈርዖናዊ ግትርነት/እልህ የንጹሐንን ደም ማፍሰሱን፣ ሕፃናትን በረሃብ መቁላቱን ቀጥሏል። ስሙን በፈቃዱ ከሕይወት ዛፍ እያስሰረዘ መሆኑን የሚመክረው አንድ አባት እንዴት ይጥፋ?!

👉 እስኪ ይታየን፤ አማራው ከሦስት ዓመት በፊት ጀምሮ፣ በተለይ ዓምና ላይ፤

“በአባቶቼና እናቶቼ ላይ፣ በወንድሞቼና እኅቶቼ ላይ አልዘምትም ፥ አባቶቼንና እናቶቼን፣ ወንድሞቼን እና እኅቶቼን ለማስራብ መንገድ አልዘጋም!”

ቢል ኖሮ ምን ያህል እግዚአብሔርን ባስደሰተና አሁን ከገባበት እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ሁኔታ ውስጥ ሳይሰቃይ ለራሱም ሆነ ለመጭውም ትውልዱም ብሎም ለሌሎቹም ስንት በረከት፣ ዘላቂ ሰላም፣ ፀጋና ብልጽግና ባመጣ ነበር። በእውነት በወርቅ ቀለም የተጻፈ ታሪክ ባለቤት መሆን በቻለ ነበር።

የኢትዮጵያና ተዋሕዶ እምነቷ ቍ.፩ ታሪካዊ ጠላት ፳፯ ጥንታውያን የኢትዮጵያን ነገዶችን ከምድረ ገጽ ያጠፋቸው ኦሮሞ ቢሆንም፤ የኦሮሞን ተንኮልና አረመኔነት ዛሬም ያልተረዳው አሻንጉሊት አማራ ግን ቍ.፩ የኢትዮጵያና ተዋሕዶ አፍራሽ ነው! ጠላቱን እንኳ ለይቶ ማወቅ የማይችል ይጠፋል። ቶሎ ካልተመለሱ ያው ዛሬ በኦሮሚያ ሲዖል እንደምናየው የድርቅ፣ የረሃብ፣ የበሽታና የእርስበርስ መበላላት ሰለባ ይሆናሉ፤ አክሱም ጽዮንን ደፍረዋልና ገና ከሰማይ እሳቱም ይወርድባቸዋል! አንድ በአንድ! ቀስበቀስ

🐸 እንቁራሪት በድንገት በፈላ ውሃ ውስጥ ከተከተተች ትዘላለች፤ ነገር ግን እንቁራሪቷ ሞቅ ባለ ውሃ ውስጥ ከተከተተች እና ውሃው ቀስ በቀስ እየፈላ ከመጣባት አደጋውን ስለማትገነዘብ ተቀቅላ ትሞታለች።

😠😠😠 አይይ አለመታደል!😢😢😢

❖❖❖[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፫፥፲፬፡፲፭]❖❖❖

እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል። ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።”

_____________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: