Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2024
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    2930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Feast of Pentecost’

በዓለ ጰራቅሊጦስ | የእግዚአብሔር መንፈስ በሰው ላይ ሲያድር ጥበብን ይገልጣል በአእምሮ ያጐለምሳል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 3, 2017

በዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው: ግንቦት ፳፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.

ጰራቅሊጦስ የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ

  • ናዛዚ (የሚናዝዝ)
  • መጽንዒ (የሚያጸና)
  • መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደበት ዕለት በቤተ ክርስቲያን የሚከበረው ይህ በዓል ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ወይም ‹በዓለ ጰንጠቆስጤ› በመባል ይታወቃል፡፡ ‹ጰንጠቆስጤ› በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮፱፻፯)፡፡

ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት፣ አምስት መቶው ባልንጀሮች እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤›› ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)፡፡ ዅሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በዅሉም ላይ አረፉባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ዅላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ዅሉ ተናገሩ (ሐዋ.፪፥፩)፡፡

ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል፡፡ የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ኾነው ዅሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚኾነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር፡፡

ከግብጽ እስከ ከነዓን ምድር የደረሰው የእንስሳት መሥዋዕት ሲጠናቀቅ በኀምሳኛው ቀን ይሰባሰብ የነበረው የአይሁድ ጉባኤም መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ዕለት ጀምሮ ተበትኗል፡፡ መሥዋዕተ ኦሪቱ በአማናዊው መሥዋዕት በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም እንደ ተለወጠ ዅሉ ጉባኤ አይሁድም በኢየሩሳሌም ከተማ በተሰበሰቡ በቅዱሳን ሐዋርያት ጉባኤ ተለውጧል (ተቀይሯል)፡፡ ይህችውም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ከጉባኤያት ዅሉ ከፍ ከፍ ያለች የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናትና፡፡ ‹‹ከዅሉ በላይ በምትኾን፣ ሐዋርያት በሰበሰቧት፣በአንዲት፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፤›› እንዳሉ ሠለስቱ ምእት በጸሎተ ሃይማኖት፡፡

ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋልጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ ቋንቋዎች ተገልጠውላቸው ምሥጢራትን በልዩ ልዩ ቋንቋ መተርጐም ጀምረዋል፡፡ ሐዋርያት በየገአሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ በዚያ የነበሩ ሰዎችም በሐዋርያት ተገረሙ፡፡ አንዳንድ የአይሁድ ወገኖች ግን በሐዋርያት ላይ ያዩት ክሥተት አዲስ ነገር ስለኾነባቸው ‹‹ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የኾነ ያልኾነውን ይቀባጥራሉ›› እያሉ ሐዋርያትን ያሟቸው ነበር፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ዐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ‹‹ሰክረዋል የምትሉ

እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ዳሩ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይኾናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ዅሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ› (ኢዩ.፪፥፳፰) ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ፣ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤›› በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥቷቸዋል፡፡

በትምህርቱም ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ ምሳሌ የመሰሉለት አምላክ ወልደ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መኾኑን ሐዋርያት እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡ በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ‹‹ምን እናድርግ?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ ንስሐ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገሯቸዋል፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል (ሐዋ.፪፥፩፵፩)፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት፡– ‹‹በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን፤›› በማለት በዕለቱ ያዩትንና የተደረገላቸውን፣ እንደዚሁም የበዓሉን ታላቅነት ከመሰከሩ በኋላ ይህንን በዓል ማክበር እንደሚገባ አዝዘዋል፤ በዚህ ወቅት መጾምና ማዘን ተገቢ አለመኾኑንም ተናግረዋል (ዲድስቅልያ ፴፥፴፰፴፱፤ ፴፩፥፷፱)፡፡

ከዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባን ቁም ነገር ‹መንፈስ ቅዱስ ወረደ› ሲባል፣ በሰዉኛ ቋንቋ መንፈስ ቅዱስ ከከፍታ ወደ ዝቅታ፣ ከሩቅ ወደ ቅርብ መምጣቱን ወይም መምጣቱን ለመናገር አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በሐዋርያት ላይ አድሮ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትን፣ ጥበብንና ልዩ ልዩ ጸጋን ማደሉን ለማስረዳት ነው እንጂ፡፡ ይኸውም ሥራዉን በሰው ላይ መግለጡን፣ ጸጋዉንም ማብዛቱን ለማመልከት የሚያገለግል ቋንቋ ነው፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ ወረደ የሚለው ትምህርት መንፈስ ቅዱስን በቦታ፣ በጊዜና በወሰን መገደቡን አያመለክትም፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ በዓለሙ ዅሉ የሞላ ነውና፡፡ በሰው ላይ አድሮ ጥበብን ሲገልጥ ግን ‹ሞላ፤ አደረ፤ ወረደ› ተብሎ ይነገራል፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ለጊዜው ለሐዋርያት ቢሰጥም፣ በእነርሱ ላይ ብቻ ሳይገደብ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በምእመናን ላይም አድሮ ይኖራልና፡፡

በዓለ ትንሣኤውን በደስታ እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ኾነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይኹን፡፡

የዘመነ ጰራቅሊጦስ ምንባባት

በዓለ ጰራቅሊጦስ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የተሰጠበት፤ ብዙ ሺሕ ምእመናን የሥላሴን ልጅነት ያኙበት ዕለት በመኾኑ ‹የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን› ተብሎ ይጠራል፡፡ በዓሉ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲኾን፣ በያዝነው ዓመትም ግንቦት ፳፯ ቀን ይዘከራል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ሰንበት (ከኀምሳኛው ቀን) ጀምሮ እስከሚቀጥለው ሰንበት ያለው ጊዜም (ስምንቱ ቀናት) ‹ዘመነ ጰራቅሊጦስ› ወይም ‹ሰሙነ ጰራቅሊጦስ› ይባላል፡፡ ይህም መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ ስለ መውረዱና በምእመናን ላይ ስለ ማደሩ የሚነገርበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ሰሙን በቤተ ክርስቲያን የሚነገረው ቃለ እግዚአብሔር፣ የሚሰጠውም ትምህርት የመንፈስ ቅዱስን በሐዋርያት ላይ መውረድ የሚመለከት ነው፡፡

በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዕለት ‹ይትፌሣሕ› የሚለው የትንሣኤ መዝሙር በቤተ ክርስቲያን ይዘመራል፡፡ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎችም በትንሣኤ ዕለት የተነበቡት ናቸው፡፡ ምንባባቱ ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ፣ በማረጉና መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት በመላኩ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ቈርሶ፣ ደሙን አፍስሶ የሰውን ልጅ ከዘለዓለም ሞት በማዳኑ የሰው ዘር ብቻ ሳይኾን የሰማይ መላእክት፣ የምድር ፍጥረታት ሳይቀሩ ሐሤት እንደሚያደርጉ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም በመንጻቷ የጌታችንን ትንሣኤ በደስታ እንደምታከብር የሚያስረዳ መልእክት አላቸው፡፡

ከበዓለ ጰራቅሊጦስ በኋላ ባሉት ሰንበታት (እሑዶች) የሚዘመሩ መዝሙራትም ትንሣኤን፣ ዕርገትን፣ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ የሚያስረዱ ሲኾኑ፣ ምሥጢራቸውም ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው፣ አዳምና ልጆቹን ከዲያብሎስ ተገዢነት እና ከሲኦል ባርነት ላወጣቸው ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ እንደሚገባ ያስተምራል፡፡ ከኀምሳኛው ቀን (ከበዓለ ጰራቅሊጦስ) ቀጥሎ በሚመጣው እሑድ (በስምንተኛው ቀን) የሚዘመረው መዝሙር፡– ‹‹ወረደ መንፈስ ቅዱስ ላዕለ ሐዋርያት ከመ ዘእሳት ወተናገሩ በነገረ ኵሉ በሐውርት …›› የሚል ሲኾን፣ ትርጕሙም መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል በሐዋርያት ላይ መውረዱንና በእርሱ ኃይል በዓለሙ ዅሉ ቋንቋዎች መናገራቸዉን የሚያስረዳ ነው፡፡

በዚህ ዕለት በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፡ኤፌ.፬፥፩፲፯፤ ፩ኛዮሐ.፪፥፩፲፰፤ ሐዋ.፪፥፩፲፰፤ መዝ.፷፯፥፲፰ (ምስባክ)፤ ዮሐ.፲፬፥፩፳፪ ሲኾኑ፣ የምንባባቱ ፍሬ ሐሳብም የሚከተለው ነው፤

የጳውሎስ መልእክት፡እያንዳንዳችን መንፈስ ቅዱስ በገለጸልን መጠን የየራሳችን ልዩ ልዩ ጸጋ እንዳለን፤ የዮሐንስ መልእክት፡የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ለዘለዓለም ሕያው እንደ ኾነ፤ የሐዋርያት ሥራ፡መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ እንደ ወረደና በዓለሙ ዅሉ ቋንቋዎች መናገር እንደቻሉ፤ መዝሙረ ዳዊት (ምስባኩ)እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ልዩ ልዩ ጸጋን እንደሚሰጥ፤ የዮሐንስ ወንጌል፡እግዚአብሔር እኛን ልጆቹን እንደ ወላጅ አልባ እንደማይተወን ያስረዳሉ፡፡ ቅዳሴው ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ሲኾን፣ ይህም ምሥጢረ ሥላሴን፣ የጌታችንን ሰው መኾን፣ ሕማሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤዉን፣ ዕርገቱንና መንፈስ ቅዱስን መላኩን ይናገራል፡፡

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ምንጭ

በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ‹‹ምን እናድርግ?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ ንስሐ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገሯቸዋል፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል (ሐዋ.፪፥፩፵፩)፡፡

አዳምና ልጆቹን ከዲያብሎስ ተገዢነት እና ከሲኦል ባርነት ያወጣው ቸሩ መድኃኔ ዓለም የወደቁትን ወገኖቻችን ያንሳቸው፣ ጰራቅሊጦስንም ያውርድላቸው

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

በ ዓ ለ ጰ ራ ቅ ሊ ጦ ስ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 19, 2016

Peraclitos2

*ጰራቅሊጦስ* የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ ለኾነው ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስሙ ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ ናዛዚ (የሚናዝዝ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው፡፡ በዓለ ጰራቅሊጦስ በሌላ ቃል በዓለ ጰንጠቆስጤ በመባልም ይታወቃል፡፡ ይኸውም በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮ እና ፱፻፯/፡፡

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ፲፪ቱ ደቀ መዛሙርት፣ ፸፪ቱ አርድእት፣ ፭፻ው ባልንጀሮችና ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት በኢሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው ለጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ በሚያርግበት ጊዜም *እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤* /ሉቃ. ፳፬፥፵፱/ ሲል ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ባረገ በ፲ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡

በሐዋርያት ሥራ እንደ ተጻፈው በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ ኹሉም በአንድ ቦታ ተሰብስበው ሳሉ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጣና የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በኹሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ኹላቸውም መንፈስ ቅዱስን ከተሞሉ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ኹሉ መናገር ጀመሩ /ሐዋ.፪፥፩/፡፡ ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ጰራቅሊጦስ ይባላል፡፡

ጌታችን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ ከ፶ኛው፤ ከዐረገ ከ፲ኛው ቀን ጀምሮ እስከሚቀጥለው እሑድ ድረስ ያለው ወቅትም ዘመነ ጰራቅሊጦስ ተብሎ የሚጠራ ሲኾን፣ ይህ በዓል ካህናተ ኦሪት ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ይቀበሉበት ነበርና በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ይባል ነበር፡፡ በበዓለ ጰራቅሊጦስም ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለውበታልና በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል፡፡

የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብፅ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ኾነው ኹሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው፡፡ የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በ፶ኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚኾነውን በዓለ ሠዊት ያከብሩ ነበር፡፡

ከግብፅ እስከ ከነዓን ምድር የደረሰው የእንስሳት መሥዋዕት ሲጠናቀቅ በ፶ኛው ቀን ይሰባሰብ የነበረው የአይሁድ ጉባኤም መንፈስ ቅዱስ ከወረደበት ዕለት ጀምሮ ተበትኗል፡፡ መሥዋዕተ ኦሪቱ በአማናዊው መሥዋዕት በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም እንደ ተለወጠ ኹሉ ጉባኤ አይሁድም በኢየሩሳሌም ከተማ በተሰበሱ በቅዱሳን ሐዋርያት ጉባኤ ተለውጧል (ተቀይሯል)፡፡ ይህችውም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ *ከኹሉ በላይ በምትኾን፣ ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፤* እንዳሉ ሠለስቱ ምእት /ጸሎተ ሃይማኖት/፡፡

ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋልና ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ከዕብራይስጥ ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ ቋንቋዎች ተገልጸውላቸው ምሥጢራትን መተርጐም ጀምረዋል፡፡ ሐዋርያት በየገአሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ ከአይሁድ ወገን አንዳንዶቹም ሐዋርያት ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የኾነ ያልኾነውን ይቀባጥራሉ ይሏቸው ነበር፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ዐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ *ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ዳሩ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ /ኢዩ.፪፥፳፰/ ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤* በማለት ሐዋርያት ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት፣ ምሳሌ የመሰሉለት አምላክ ወልደ አምላክ መኾኑን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም በክብር በምስጋና መጥቶ በሕያዋንና በሙታን ላይ የሚፈረድ መኾኑን እንደሚመሰክሩ በአይሁድ ፊት አሰምቶ ተናገረ፡፡

በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት የተማረኩ አሕዛብም ምን እናድርግ ብለው በጠየቁት ጊዜ ከክፋታቸው ተመልሰው፣ ንስሐ ገብተው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ ነገራቸው፡፡ በዚያችም ሰዓት ሦስት ሺህ ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል /ሐዋ.፪፥፩፵፩/፡፡ ይህም ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ያደረባቸው የማሳመን ጸጋና ተአምራትን የማድረግ ኃይላቸው እንደ በዛላቸው ያመላክታል፡፡

ይህ ዕለት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠበት፤ ብዙ ሺሕ ምእመናን የተገኙበት ዕለት በመኾኑ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲን የልደት ቀን በማለት ይጠሩታል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላ ሐዋርያት በአእምሮ ጎለመሱ፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾኑ፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታደሉ፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት *በዚህች ቀን በሦስት ሰዓት ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና በላያችን ኃይልን ሞላ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን እንዳለው በአዲስ ቋንቋ ተናገርን፤* በማለት በዕለቱ ያዩትንና የተደረገላቸውን፣ እንደዚሁም ስለ በዓሉ ታላቅነት መስክረው ይህንን በዓል ማክበር እንደሚገባ ወስነዋል፡፡ እንደዚሁም በዚህ ወቅት (በበዓለ ኀምሳ) መጾምና ማዘን እንደማይገባ አዝዘዋል /ዲድስቅልያ ፴፥፴፰፴፱፤ ፴፩፥፷፱/፡፡

የጰራቅሊጦስ መዝሙርና ምንባባት

በዓለ ጰራቅሊጦስ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላት አንዱ ሲኾን በዕለቱ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሚዘመረው የቅዱስ ያሬድ መዝሙርም ይትፌሣሕ የሚለው የትንሣኤ መዝሙር ነው፡፡ እንደ መዝሙሩ ኹሉ በጰራቅሊጦስ በዓል በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎችም በትንሣኤ ዕለት የተነበቡ ምንባባት ናቸው፡፡

እነዚህም ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በመነሣቱ፣ በማረጉና መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት በመላኩ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ቈርሶ፣ ደሙን አፍስሶ የሰውን ልጅ ከዘለዓለም ሞት በማዳኑ የሰው ዘር ብቻ ሳይኾን የሰማይ መላእክት፣ የምድር ፍጥረታት ሳይቀሩ ሐሤት እንደሚያደርጉ፤ ምድርም በክርስቶስ ደም በመንጻቷ የጌታችንን ትንሣኤ በደስታ እንደምታከብር ያስረዳሉ፡፡

ከበዓለ ጰራቅሊጦስ በኋላ ባሉት ሰንበታት (እሑዶች) የሚዘመሩ መዝሙራት ትንሣኤን፣ ዕርገትን፣ የመንፈስ ቅዱስን መውረድ የሚያስረዱ ሲኾኑ፣ ዓላማቸውም ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው፣ አዳምና ልጆቹን ከዲያብሎስ ባርነትና ከሲኦል ላወጣቸው ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ ነው፡፡

ከዚሁ ኹሉ ጋር ለማሳሰብ የምንፈልገው ቁም ነገር በዓለ ጰራቅሊጦስን ተከትለው ሁለት ዐበይት አጽዋማት እንደሚጀመሩ ማስታዎስ ነው፡፡ እነዚህም ጾመ ሐዋርያት እና ጾመ ድኅነት (ረቡዕና ዓርብ) ናቸው፡፡ ቍጥራቸውም ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ነው፡፡ ስለኾነም ኹላችንም ልንጾማቸው እንደሚገባ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ታዝዟል፡፡ ይህም ከቀደሙ አባቶቻችን ጀምሮ የመጣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓት እንጂ እንግዳ ሕግ አይደለም፡፡

ምንጭ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , | Leave a Comment »

Holy Spirit: The Most Precious Gift

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 3, 2012


This Sunday marks the high point in the Church’s post-Paschal celebrations. After proclaiming the Resurrection of Christ for the past several weeks, the Church has called our attention to several post-Resurrection appearances to underscore the reality of the risen Lord for the life of the Church.

Today marks the highpoint of those celebrations. Today we celebrate the coming of the Holy Spirit on the twelve disciples in the upper room on the Day of Pentecost. Why is this so important? Historically, Pentecost was the Jewish feast which celebrated the first fruits of the harvest. Every Jewish home celebrated God’s good gifts to them by giving the Lord a portion of their grain harvest, in anticipation of the full crop to come. It is simply a thank-you gift.

On this day the Church celebrates God’s gift of the Holy Spirit to the Church. Much of the service is devoted to two things: the Trinity and the coming of the Holy Spirit in the life of the believer. There is so much to say on a day like today, but there is one truth that especially stands out that I would like to emphasize. It comes from a phrase we find repeated several times in the special hymns for today, which reads, “Verily, the fire of the Comforter has come and lit the world.”

Verily, the fire of the Comforter has come and lit the world. Let’s look at this a little closer. The comforter is the Holy Spirit, described by Jesus in John 14 when he said, “I will pray to the Father and he will give you another Helper, or Comforter, that he may abide with you forever: the Spirit of truth.”

That’s what the Holy Spirit does for us. He is sent by the Father, through the Son, and abides in us through his Holy Spirit. That’s where the Church gets its emphasis on the Trinity today. But the other lesson focuses on the presence and power of the Holy Spirit in the lives of the disciples.

In Acts 1:8 Jesus said:

But you shall receive power when the Holy Spirit comes upon you, and you shall be my witnesses in Jerusalem, and in all Judea and Samaria, and to the uttermost part of the earth.

Why did Jesus focus on the power of the Spirit’s presence in the life of the disciples? Simply because they needed it. Up to now they were shaky and timid people, for the most part. They were following Jesus, but the Jesus they followed died and rose from the dead, and now they did not know what to do except to wait for the Spirit, as Jesus told them to do.

And then, it happened. We are told in Acts 2:

When the day of Pentecost had fully come, they were all with one accord in one place, and suddenly there came a sound from heaven as of a rushing, mighty wind, and it filled the whole house where they were sitting. Then there appeared to them divided tongues, as of fire, and one sat on each of them, and they were all filled with the Holy Spirit and began to speak with tongues, as the Holy Spirit gave them utterance.

And then, shortly after that:

Peter, standing up with the eleven, raised his voice and said to them, “Men of Judea, let this be known to you. This is what was spoken by the Prophet Joel.”

Power, power, power. That’s one of the most important truths we learn from Pentecost. Christ gave his Holy Spirit to his followers to take his place on earth, and to empower them for Christian service. That’s what Peter was doing when he preached. Why is the power of the Holy Spirit so important to have?

The power of the Holy Spirit is important because he enables us to fulfill Christ’s demands. It is as simple as that. We simply cannot fulfill the Lord’s commands apart from the inner strength to obey them.

Every once in a while I meet people who tell me, “I have tried and tried to live the Christian life, but just cannot do it. I have this hang-up, and I just cannot get over it. I have tried hard, and, well, I just cannot do it. I cannot live, and I cannot obey, Jesus’ teachings, even though I have tried with all my heart.”

Have you ever felt like that? Have you tried living the Christian life and felt like giving up because you do not have the power to live it? If so, I have good news for you today. You are absolutely right. You have just discovered one of the most important truths you could ever learn about the Christian life. That truth is the truth that will set you free from all self-help and all the self-reliance that has made you so discouraged.

And what is that truth? It is the truth that only the Holy Spirit can give you the power to live as Jesus wants you to live. You cannot live by the power of your own sweat. On the contrary, the inner power for living the Christian life is summed up on this Day of Pentecost, and it is given in the words of Jesus, who declared, “Without me you can do nothing.”

And that is the good news of the Gospel.

Source: AncientFaithRadio

________________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | 1 Comment »