Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Ethiopianism’

መጀመሪያ የማርያም መቀነትን፣ ከዚያ ክቡር መስቀሉን፣ ከዚያም ኢትዮጵያን እየተነጠቅን ነው | ዋ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 27, 2020

በግብረሰዶማውያን ተመርጦ ስልጣን ላይ የወጣው የአብዮት አህመድ አሊ ተልዕኮ ጸረኢትዮጵያ፣ ጸረተዋሕዶና ጸረክርስቶስ መሆኑ ግልጽ ነውና ዛሬ ሰሜን ኢትዮጵያውያንን ለመጨፍጨፍ ብሎም ታሪካቸውንና ቅርሳቸውን አንድ በአንድ ለማጥፋት የተላከውን “ሰራዊት” የሚደግፍ ሁሉ ፀረኢትዮጵያ፣ ፀረክርስቶስ፣ ፀረጽዮን ማርያም ብሎም የግብረሰዶማውያንን አጀንዳ አራማጅ ነው። ይህ ሰራዊት ስለ ጽዮን ዝም የማይሉትን የተዋሕዶ ልጆችን እንጅ ጠላት ሶማሊያን፣ ጠላት ሱዳንን፣ ጠላት ኦሮሚያን፣ ጠላት አረብን፣ ጠላት ግብጽን፣ ጠላት ቱርክን፣ ባጠቃላይ ጠላት ኤዶማውያንን እና እስማኤላውያንን ያጠቃ ዘንድ የተላከ ሰራዊት አይደለም። ወዮላችሁ!

የቪዲዮው መግቢያ ላይ የሚታየው ዛሬ በአውስትራሊያ የታየ ድንቅ የማርያም መቀነት ነው። ልክ በዚሁ ዕለት በአውስትራሊያው የቪክቶሪያ ግዛት ኮሮና ጠፋች ለሰላሳ ቀናት በወረርሽኙ የተያዘ ሰው የለም ተባለ። ድንቅ ነው! እዚህ ይግቡ

+++ ባለፈው የጌታችን ስቅለት ዕለት(ይገርማል፤ በማግስቱ ነበር ምቀኛው አውሬ ያኛውን ቻነሌን ያዘጋብኝ፤ ወገን እንዳያውቅና እንዳይድን) በሃገራችን ታይታ የነበረችውን የማርያም መቀነት እናስታውሳለን? አዎ! በጊዜው የሚከተለውን ጽፌ ነበር

👉 “አውሬው ቤተክርስቲያንን ለጌታ ቍርባን ዘግቶ በ666የተከተቡትን ዶሮዎች እንድትገዙ ገበያዎችን ፈቀደ”

👉 እርግብ እና በግ ታሥረዋል

የቤተ ክርስቲያናችንን እንቅስቃሴ በደንብ ነው የሚከታተሉት፤ በዕለተ ስቅለት የተነሳው ቪዲዮ ላይ የሚታየውን ዓይነት ብርቱ የሆነ የእምነት ፍቅርና ጽናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ ብቻ እንደሚታይ የአውሬው ዓለም እያየው ነው። እናት፣ አባት፣ ህፃናት ከጥዋት እስከ ማታ ለጌታቸው ሲሰግዱ፣ ካህናትና ቀሳውስትም ሌሊቱን ሙሉ ቆመው የሚቀጥለውንም ቀን ያለማቋረጥ በሥርዓተ ጸሎትና ቅዳሴ ሲያሳልፉ የሚታዩባት ብቸኛ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብቻ ናት። ለመሆኑ በፕሮቴስታንቶች በተለይም በእስላሞች ዘንድ ሕፃናት ወደ አምልኮ ቦታዎች ሲሄዱ አይታችሁ ታውቃላችሁን? እኔ አልገጠመኝም።

አውሬው በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በጣም ይቀናል! ለዚህም ነው ልክ ፪ሺ፲፪/ 2012 ዓመተ ምሕረትን ጠብቆ፣ ልክ የሑዳዴ ጾም ሲገባ የኮሮና ቫይረስን ዓየር ላይ የለቀቀው። የአውሬው አምላኪዎች የሆኑት መሀመድውያንም ልክ ፋሲካ ሲገባደድ ረመዳናቸውን መጀመራችውም አውሬው ይህችን ዓመተ ምሕረት በጉጉት ሲጠብቅት እንደነበር ይጠቁመናል።

የአውሬው ተቀዳሚ ዓላማው ሕዝበ ክርስቲያኑን ከክርስቶስ ደም እና ስጋ እንዲሁም ከጥምቀት ማራቅ ነው። ይህንም በግልጽ እያየነው ነው። የተዋሕዶ ልጆች ስጋና ደሙን “በነጻ” እንዳይቀበሉ ቤተ ክርስቲያንን በሠራዊቱ አሳጠረ ፤ ፋሲካ ሲቃረብ ገበያዎቹን ከፍቶና የ”አበሻ” ዶሮዎችንና እንቁላሎችን አጥፍቶ በአውሬው መንፈስ የተበከሉትን የአላሙዲን ኤልፎራ ዶሮዎች ክርስቲያኑ ሺህ ብር እየከፈለ እንዲገዛና ለአውሬው የደም መስዋዕት እንዲያደርግለት ፣ እግረ መንገዱንም የዶሮውን ስጋና እንቁላል ተመግቦ በአጋንንት እንዲታሠር ያደርጋል። ይህ ግልጽ የሆነ የዲያብሎስ አካሄድ አይደለምን? በደንብ እንጅ!

የሚከትሉትን ቀናት በጥሞና እንከታተል፤ ፋሲካ ካለፈ በኋላ የአውሬው መንግስት መስጊዶችን ለስግደት ቢፈቅድ አይግረመን!

አሁን ግን አገር ቤት ያላችሁ የተዋሕዶ ልጆች ትናንትና የማርያም መቀነትን አይታችሁታልና ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰባስባችሁ አምሩ። የማርይም መቀነቱ “ወደኔ ኑ! ምንም አትሆኑም!” የሚለውኝ ምልክት ነው ያሳያችሁ! በዚህ በትንሣኤ ወቅት ኮሮኖ የተባለው ቫይረስ ቤተ ክርስቲያን ድርሽ አይልም! እግዚአብሔርን እንጅ ሌላ ማንንም/ምንንንም አትፍሩ! አባታችንን አብርሃምንና ይስሐቅን አስታውሱ! አሁን ትንሽ ሰዓት ነው የቀረውና ባካችሁ የማንንም ፈቃድ ሳትጠይቁ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሂዱ! መላው ዓለም “ኢትዮጵያውያኖች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዱን?” ብሎ በመጠየቅ ላይ ነው። ባለፈው ሳምንትም ተናግሬው ነበር፤ ይህ ሌላ ጊዜ ተመልሶ የማይመጣ ልዩ አጋጣሚ ነው! በዚህ ጊዜ ከተሰቀለላችሁ አምላካችሁ ጋር ካልሆናቻሁ መቼ?! ለብርሃነ ትንሣኤ ቤተ ክርስቲያንን አጥለቅልቋት!”

__________________________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በእውነተኛና ሃይማኖት ባለው፡ በቆራጥ ሕዝብ ዘንድ፡ መልካሙ ኹሉ ይቻላል!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 15, 2012

 

ኢትዮጵያ ሆይ፥ ሀገራችን! ረስቼስ እንደኾነ፡ ቀኜ ትርሳኝ፣

ያላሰብሁሽ እንደኾን፡ መላሴ ትናጋዬን ሰልቶ ይውጋኝ።

አቤቱ ፈጣሪያችን፡ በኢትዮጵያ ቀን፡ ጠላቶቿን ኹሉ አስብ፤

አፍርሷት፡ ኢትዮጵያን፡ እስከመሰረቷ ድረስ፡ የሚሉትንም ሕዝብ።

እናንት ትምክህተኞች፡ የኢትዮጵያ ጸሮች፥ የተነኰላችሁን ብድራት፤

የሚመልስ ነው አምላካችን፡ በፍትሕ በተአምራት፤

በሚጠሉሽ ላይ፡ በእውነት፥

በቅን ለሚፈርደው ንጉሥ፡ ምስጋናችን ይብዛለት።

ኢትዮጵያ ሆይ፥ ሀገራችን! ረስቸሽ እንደኾነ ቀኜ ትርሳኝ።

 

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት“(የተደበቁ የኢትዮጵያ ምስጢሮች)ከሚለው የንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ ሦስተኛ መጽሐፍ የተወሰደ።

ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር።

ዛሬ ባሉትም ሰዎች ዘንድ፡ እንደጥንቱ እየተፈጸመ ከመቀጠል በቀር፡ ሌላ ዕድል ሊኖረው አይችልም! ምክኒያቱም እውነታ፡ እርግጥ በበለጠ እየጨመረና እየተጠናከረ የኼደ መኾኑን፡ ይኸው፡ እየረሳችን ምስክር በመኾን፡ በገሃድና በግዘፍ እናየዋለን፡ ይኹን እንጂ፡ እየራሳችን ምስክር በመኾን፡ በገሃድና በግዘፍ እናየዋለን፡ ይኹን እንጂ፡ ከሰነፎችና በሰነፎች የሚቀርበው፡ እንዲህ ያለው ምክንያት፡ እዚያው፡ ለሰነፎች የሚያገለግል፡ የሰነፎች፡ ከንቱና ፍሬቢስ አሳብ ሰለሆነ፡ በእኛ፡ በቀዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያን ዘንድ፡ ፈጽሞ ቦታ የለውም።

በሓሰተኞችና በእምነተቢሶች ዘንድ፡ ክፉው ኹሉ እንደሚቻል፡ እንዲሁ፡ በእውነተኛና ሃይማኖት ባለው፡ በቆራጥ ሕዝብ ዘንድ፡ መልካሙ ኹሉ ይቻላል! አንድ ቆራጥ ሕዝብ ከፈለገ ኹሉን ማድረግ የሚቻለው መኾኑን ለማመልከት ባመኑበት እምነታቸውና በፈለጉት ሥርዓታቸው ማንነታቸውን አኩርተው፥ መሪዎቻቸውንም አቅፈው፡ የኃያላን ተቃዋሚዎቻቸውን ጥቃት ተቋቁመው፥ በውጭ ተፅዕኖም ሳይበገሩ፡ ይህን እውነታ፡ በግብር ያረጋገጡ ሕዝቦችን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል።

ከእነዚህም መካከል የዛሬውን ትውልዷን አያድርግባትና ከቀደሙት ታማኞቹ ኢትዮጵያውያን ልጆቿ፡ ምግባርና ገድል የተነሣ፡ ቀንደኛ ኾና በመልካም ምሳሌነት የምትጠቀሰው፡ ኢትዮጵያ መኾኗ፡ በባለጋራዎቿ ዘንድ ሳይቀር የተመሰከረ እውነታ ነው። ለዚህ ቆራጥነት ስለሚያበቃው፡ ሃይማኖታዊ ሥነ ምግባር፡ በዓለም ላይ የሚኖሩት ሕዝቦች፡ የተለያየ ግምት፡ እንዳላቸው፡ ከዚህ የሚከተለው፡ የጊዜያችን ኹነት በቀላሉ ሊያስረዳ ይችላል፦

ከጥቂት ዓመታት በፊት፡ በመካከለኛው ምሥራቅ፡ ኢራቅ ኩዌይትን በወረረች ጊዜ፡ አሜሪካውያንና ምዕራባውያን አገሮች፡ በነዳጅ በኩል ያላቸውን ጥቅም ለመጠበቅ ሲሉ የቃል ኪዳን ጦር አደራጅተው ኩዌይትን በመርዳት ጎረቤቲቱን ሳዑዲ ዓረቢያን ጭምር፡ ከወረራው ማትረፋቸው ይታወሳል። ይህን በመሰለው እርዳታቸው፡ ሊዋጉላቸው፡ ወደእነዚሁ የእስልምና አገሮች የኼዱትን፡ አሜሪካንና የጦር ጓደኞቿን፡ ሳዑዲ ዓረቢያ፡ በቅድሚያ ካስገባቻቸው ግዴታዎች መካከል አንደኛውን ልጥቀስላችሁ! እርሱም ለእርዳታ የደረሱላት ክርስቲያኖቹ ምዕራባውያን የጦር ጓደኞቿ፡ በሳዑዲ ዓረቢያ ምድር ላይ፡ ሃይማኖታውያን የኾኑ፡ የጸሎትም ኾነ የሰንደቅ ዓላማ፥ ወይም የበዓል ሥርዓቶቻቸውን፡ በምንም መንገድ እንዳይፈጽሙ የሚከለክለው ነበር።

ይህም ማለት፡ እናንተ ክርስቲያኖች፡ የክርስትና ሥርዓታችሁን፡ በእስልምና ምድራችን ላይ ከምትፈጽሙ ይልቅ፡ እስላሙ ጠላታችን ኢራቅ ወርራን፡ አገራችንን ብትይዝ ይሻለናል!” በማለት፡ ቅድሚያውን ለሃይማኖቻቸው መስጠታቸው ነው። በተቃራኒው ደግሞ አሜሪካና ምዕራባውያን ተባባሪዎቿ፡ እናንተን ሳንረዳ፡ ሃይማኖታችንን ከምናስከብር ይልቅ፡ ለገንዘብ ጥቅማችን ስንል ሃይማኖታችን ቀርቶ እናንተን ብንረዳ ይሻለናል!”ማለታቸው ነው።

ምሥራቃውያንና ምዕራባውያን፡ ስለሃይማኖት ያላቸው አስተሳሰብና ግምት እንግዴህ በዚህ ተለይቶ ይታወቃል። ኢትዮጵያ፡ ከእግዚአብሔር ያገኘችው፥ ጥንታዊ፥ ቀዳሚና የራስዋ የኾነ ሕዝባዊ የአስተዳደር አቋም የሌላት ይመስል፥ እነርሱም ዛሬ እየሠሩበት ያለው ከዚሁ ከእርሷ የወረሱት መኾኑን ለማዘናጋት በመሞከር በአሜሪካና በቀሩት ምዕራባውያን አገሮች ግፊት፡ በኢትዮጵያ የሕዝባዊ አገዛዝ ሥርዓት (democracy/ዲሞክራሲ) መስፈን አለበት!” ተብሎ ለዚህ ትውልድ ይህን ያህል ነጋሪት የሚደለቅለት ለምን እንደኾነ በቀላሉ መመልከት ነው።

የሳዑዲ ዓረቢያ ሕዝብ፡ ከአሜሪካውያንና በጠቅላላ ከምዕራባውያን ጋር ያለው ግንኙነት ያው በገንዘብ ላይ የተመሠረተ ኾኖ፡ የቱን ያህል የጸናና የተንሰራፋ እንደኾነ በይፋ ይታወቃል። ይኹን እንጂ ግንኙነቱ እንዲህ እጅግ የተቀራረበና የተጠናከረ እንደመኾኑ፥ አገሩም በፈረንጆቹ የሥልጣኔ ምርት እንደመጥለቅለቁ መጠን ሕዝቡ በሃይማኖቱ ላይ የተመሠረተውን ሥነ ምግባሩን ቋንቋውንና ፊደሉን፥ አለባበሱንና ሌላውን ባህሉን በይበልጥ አጠናከረ እንጂ በምንም መንገድ አልለወጠም።

እንዲያውም ዐረቦች፡ የዘመኑን ትውልዳቸውን በእስላማዊው ሃይማኖታቸው ሥርዓተ ትምህርት እያነፁ በማሳደግ እያዘጋጁት ያሉት በክርስቲያኖቹ ምዕራባውያን ላይ በጠላትነት እንዲነሣ መኾኑ በይፋ የሚታወቅ ከመኾኑ ጋር፡ በአሁኑ ጊዜ፡ ከምዕራቡ የክርስቲያን አህጉር ላይ በእስልምና አክራሪዎች ታውጆ እየተካኼደ ያለው ዓለም አቀፍ የ”ሽብር” ጦርነት በቂ ማስረጃ ነው።

ኢትዮጵያም እኮ እስከዚህ እስከዛሬው ትውልድ ድረስ እንደዚህ ነበረች። ያውም በ፯ሺሆች ዓመታት ለሚቆጠር ዘመን። ዛሬ ግን ይህ ትውልድ ከላይ የተጠቀሱትን የአባቶቹንና የእናቶቹን ምሳሌያዊ ምክር ባለማጤንና ባለማስተዋል ወይም ቸል በማለት ወይም በመናቅ እንኳንስ ዓበይት የኾኑትን የተከበሩ ውርሶቹን ሊንከባክብ ይቅርና፡ ጥቃቅንና ተራ የኾኑትን እንኳ መጠበቅ አቅቶት ይኸው፡ ጨርሶ ለመውደቅ፡ ሲፍገመገም ይታያል።

የኢትዮጵያውያን አንዱ የጨዋነታቸው መገለጫ የኾነው የመከባበር ባህላችን በዚህ ትውልድ እየተዳከመ በመኼድ ላይ ይገኛል፤ ለምሳሌ አንድ ኢትዮጵያዊ ቀደም አድርጎ የማያውቀውንና በዕድሜው ከእርሱ ላቅ ያለ መስሎ የሚታየውን ማንንም ሰው፥ ወንድ ኾነ ሴት፡ “እርስዎ” በማለት ወደ “አንቱታ” ደረጃ ከፍ ያደርገዋል፥ ወይም ያደርጋታል እንጂ፡ እንዲያው ተነሥቶ ወንዱን “አንተ!” ወይም ሴቷን፡ “አንቺ!” አይልም ነበር። ዛሬስ፡ ይህ ባህል፡ በምን ኹኔታ ላይ ይገኛል ይህስ የመከባበሩ ባህላችን እየቀረ መኼዱን አያመለክትምን?

የሥጋ ወላጆችን፥ ወንድሞችንና እኀቶችን ብቻ ሳይኾን፡ አዛውንቶችን ወንዶች፡ “አባባ” ወይም ታላላቆችን፡ “ጋሼ” ፥ አዛውንቶችን ሴቶች ደግሞ “እማማ” ወይም ታላላቆችን “እትዬ” ብሎ የመጥራቱ መልካም ባህላችን ደብዘው ሳይቀር፡ እየጠፋ መኼዱን ይኸው እየተመለከትን ነው። እንዲያውም በዚህ ፋንታ በባዕዳን ቋንቋ፡ Father! Mother! Brother! Sister! እያሉ መጥራት በኅብረተሰቡ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነትን አግኝቶ ተጠሪዎቹም፡ በደስታ፡ ወንዶቹ “ወይ!” ወይም “አቤት!”፥ ሴቶቹ፡ “ወይ!” ወይም “እመት!” እያሉ ፈጥነው መልስ በመስጠት ተባባሪነታቸውን ሲያረጋግጡ ይታያል። በነገራችን ላይ “አቤት!” የሚለው ምላሽ የሚሰጠው፡ ጠሪው ወንድ ሲኾን ብቻ እንጂ ለሴት ጠሪ ፈጽሞ “አቤት!” አይባልም፤ ነውር ነው። ለሴት ጠሪ፡ ተጠሪው ምላሹን መስጠት ያለበት “እመት!”ብሎ ነው።

ለዚህም፡ ለኹለተኛው ቁም ነገር፥ በቂ ምክንያት አለ፤ ይኸውም “አቤት!” “አብ የት?” ማለት ሲኾን፡ በግእዝ፡ “አቡየ” አባቴ፥ “አይቴ” የት ማለት ስለኾነ፡ “አባቴ! የጠራኸኝ፡ ወደየት (ወዴት)ልትልከኝ ነው?” ፥ እንደዚሁ ኽሉ “እመት!” “እም የት? ማለት ሲኾን በግእዝ “እምየ” እናቴ፥ “አይቴ”፡ የት ማለት ስለኾነ “እናቴ! የጠራሽኝ፡ ወደየት (ወዴት)ልትልኪኝ ነው?” ማለት ነው ተብሎ ይተረጎማል።

የአለባበሳችን ባህል ስለሚገኝበት ሁኔታ ስንነጋገር በጣም የሚያሳዝነን ነገር ይኖራል። ይኸውም ይህ የዛሬው የኢትዮጵያ ትውልድ በአለባበሱ ረገድ የራሱን ባህል ጨርሶ ትቶ፡ ፈጽሞ አውሮጳዊ፥ ወይም ምዕራባዊ ወይም ፈረንጅ በመኾኑ ነው።

ዘመናዊውን ትምህርት ከተማረው፥ ከጥራዝ ነጠቁና ከከተሜው መካከል በአኹኑ ጊዜ የአገራችንን ልብስ ለዓውደ ዓመት እንኳ የሚለብሰው ስንቱ ነው? እጅግ ጥቂቶች ናቸ፤ ምናልባት የመልበስ ፍላጎት ኖሮአቸው የሚለብሱ ቢኖሩ እንኳ እነርሱ አለባበሱን ስለማያውቁበት አንድ ባዕድ የኾነ ሰው፡ “እንዲህ አድርገህ ልበሰው!” እየተባለ እንደሚናገረው ተዋናይ መስለው እንደሚለብሱት የሚታወቅ ነው።

በአሁኑ ጊዜ ከጥንታውያኑ የዓለም አህጉር መካከል በዘመኑ ትውልዷ ምክንያት በአጠቃላይ ኹለንተናዋ “ባለቤቱ፡ በቤቱ ባይተዋር፡ ባይተዋሩ በሰው ቤት ባለቤት” የኾነባት አገር ቢኖር ኢትዮጵያ ኾና ትገኛለች። ይህ ዝቅጠት አያሳዝንምን? አያሳፍርምንስ?

የዘመኑን ዓለማዊ ሥልጣኔ እንደሃይማኖት በተከተለው ወገን ዘንድ ከአገር ልብሱ ብቻ ሳይኾን ከለባሹም ሰው ይልቅ የክብሩን ቦታ የያዘው የባዕዳኑ ልብስ ስለኾነ የኢትዮጵያዊነት አንዱ ምልክት የኾነውን “ነጠላ” ወይም “ኩታ” ደርቦ መታየት ለዚያ ሰው በዘመናዊ ትውልድ ዘንድ የመጨረሻውን የውርደትና የንቀት ምልክት ተጎናጽፎ እንደመታየት የሚያስቆጥር ከመኾን ደረጃ ተደርሷል። ይህን እውነታም፡ “ባለኩታ”፥ ወይም “ኩታ ለባሽ” የኾነው ኢትዮጵያዊ የዚህ መጽሓፍ አዘጋጅ በራሱ አገር፥ በራሱ ወገኖች ሳይቀር ሲናቅና ሲዋረድ አይቷል። አዎ! በነገራችን ላይ “በራሱ አገር በራሱ ወገኖች”አያስብልም ምክኒያቱም በባዕዳኑ ዘንድማ እየተደነቀና እየተከበረ ነው ያለው። የተናቀውና የተዋረደው እኮ በራሱ አገር፥ በራሱ ወገኖች ዘንድ ብቻ ነው።

ይህ ኹኔታ የደረሰው በኩታውና በባለኩታው አገር በኢትዮጵያ ከዚያም ይባስ፡ በአገሩ በኢትዮጵያ ስም በሚጠራው አየር መንገድ ነው። ባለኩታው ኢትዮጵያዊ ወደባሕር ማዶ የሚበርበትን የጉዞ ወረቀቱን (Ticket)ለማስቆረጥ፡ በመናገሻዪቱ ከተማ ውስጥ ካሉት የአየር መንገድ ጽሕፈት ቤቶች መካከል በአንዱ እንደተገኘ በተራው የተቀበለችው ጸሓፊ ባለጉዳዩ ባልጠበቀው መልክ አነጋግራና የጉዞ ወረቀቱን አዘጋጅታ እስከሰጠችው ጊዜ ድረስ ለአንድም አፍታ ቀና ብላ ዓይን ለዓይን ሳታየው ከእርሱ ለቀረበላት የምስጋና ሰላምታም እንኳ አጸፋውን በአግባቡ ሳትመልስለት አሰናበተችው።

 

Continue reading in PDF>EthioBahel

 

_______________________________________

 

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: