“ፈረንጁ ወይም ነጩ ኢትዮጵያዊ” በሚል ስም ብዙ ተመልካቾች የነበሩትን ይህን ፊልም የመጀመሪያው የጀርመን ቴሊቪዥን ጣቢያ ባለፈው የፈርንጅ ገና በዓል ሳምንት አሳይቶት ነበር።
በተቻለ መጠን በጎ በጎው ነገር ላይ ያተኮረ ፊልም ቢሆንም፤ ያው እንደተለመደው ከአንዳንድ ግትርነት ነፃ አይደለም። ሳያት ደምሴ (ዓያንቱ) — ምንም እንኳን እናቷ መስቀል የአደረገች ኢትዮጵያዊት መሆኗ ቢታይም – እርሷ ግን የአረብ ሙስሊሞች ልብስ እንድትለብስ መደረጓ ስህተት እና ቅር የሚያሰኝና “ተይ ማነሽ!” የሚያስብል ነው። ይታየን፡ ቆንጆዋ “ሚስ ኢትዮጵያ” የአረብን ባህል እንድታስተዋውቅ ስትደረግ! ይህ በጣም አሳፋሪና ትልቅ ቅሌትም ነው!
ቀነስ አድርጌ ያቀርብኩት ይህ ፊልም በብዛት ጀርመንኛ ቋንቋ የሚነገርበት ቢሆንም፡ አንዳንዶቹ ውይይቶች ላይ አማርኛ አለፍ አለፍ ብሎ ስለገባበት ዋናውን መልዕክት በቀላሉ መረዳት ይቻላል።
‘ፈረንጁ ኢትዮጵያዊ‘ በ ‘ሳያት ደምሴ‘ እና በኢትዮጵያ ፍቅር ሲጠመድ
ከባድ ልጅነት የነበረውና ሚኻልከ የተባለው ጀርመናዊ አንድ ቀን ባንክ ይዘርፍና ወደ አዲስ አበባ ይጠፋል። እዚያም ሲደርስ ቶሎ ብሎ ወደ አንድ ገጠራማ የኢትዮጵያ ክፍል ያመራና ባንዲት ትንሽ መንደር ይሰፍራል። እዚያም ከዚህ በፊት ገጥሞት የማያውቀው አይነት ሞቅታ የተሞላበትን ኢትዮጲያዊ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ይታዘባል። በዚህም ጊዜ ከቆንጆዋ “ዓያንቱ” (ሳያት ደምሴ) ጋር ይተዋወቅና በፍቅር ተጠምዶ መጨረሻ ላይ “አገሩን” ያገኛል፤ አማርኛም መማር ይጀምራል። ቀጥሎም የቡና ልማት ተግባር ላይ ይሠማራል። እነዚህ ሁኔታዎች ቀስ በቀስ ከ ዓያንቱ ጋር ሠርግ ለመደገስ እና ልጅ ለመውለድም መንገዱን ይከፍትለታል።
የሚኻልከ የኢትዮጵያ ህይወት የተተረከው ወደ ኋላ በመመለስና ግለሰቡም ወደ ፍርድ ቤት ችሎት በቀረበበት ወቅት ነበር። ይህም፡ ሚኻልከ በጀርመን ባንክ የዘረፈ ወንጀለኛ በመሆኑ ኢትዮጵያ ተፈልጎ ከተያዘ በኋላ ወደ ትውልድ አገሩ ተመልሶ እስር ቤት ከገባ በኋላ መሆኑ ነው፦
በእስር ቤት እንዳለ ራሱን ለመግደል ይሞክራል፤ በዚህ ጊዜ አንዲት ትጉ የሆነች የፍርድ ተሟጋች ትመጣለታለች። በዚህም ወቅት መናገር አሻፈረኝ ሲል የነበረው ሚኻልከ መተንፈስ ጀመሮ፡ በጀርመን ስለነበረው መራራ የልጅነት ሕይወት እና ካደገ በኋላም በኢትዮጵያ ስለገጠመው ደስተኛ የሆነ ኑሮ በዝርዝር ለእርሷ ያጫውታታል። ይህንም አዲስ መረጃ በፍርድ ቤት ውስጥ በማቅረብ ለስለስ ያለ ፍርድ ያስገኝለታል።
ዋናው የጀርመን ቴሊቪዥን ጣቢያ ይህን ፊልም ያቀረበበት ቀዳሚ ምክኒያት በተለይ በአሁኑ ሰዓት ጀርመን በሙስሊም ስደተኞች በውጥረት ላይ የምትገኝ በመሆኑና ህዝቡም በስደተኛው ላይ እያጉረመረም ስለሆነ፡ የሌላውን ዓለም ትሕትና በኢትዮጵያውያን በኩል ለማሳየት በመሻትና
ሕዝቡንም ለማቀዝቀዝ በማሰብ ይመስላል። በተለይ በ ገና በዓል ሰሞን መታየቱ ያለ ምክኒያት አልነበረም። አረብ አገር ሄደው ይህን መሰል እንግዳ ተቀባይነት እና ሞቅ ያለ ፈገግታ ማግኘት ፈጽሞ አይቻልም። ለዚህም ይመስላል ቆንጆዋን “ሚስ ኢትዮጵያን” ሃያት ደምሴን የአረብ ልብስ እንድትለብስ ያደረጓት። የእኛ አጥባቂ ክርስቲያናዊነት በጣም ያስቀናቸዋል፣ ያንገበግባቸዋል!
ባህላዊና ሃይማኖታዊ አለባበሶች፡ ልክ እንደ ምስል፡ በተመልካቹ ህሊና ውስጥ ቶሎ የመቀረጽ ብቃት ያላቸውና ለረጅም ጊዜም የሚቆይ ትውስታን የሚያመጡ ናቸው። ለዚህም ነው በተለይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢትዮጵያኛውን ባህላዊ አለባበስ፡ ይህን ሁሉ ዘመን ከኛ ጋር እየኖሩ፡ ለመቀበል አሻፈረኝ የሚሉት። “ቀበቶህን አጥብቅ!“ የምትለው ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ቆንጆ የአለባበስ ባህል ያላት አገር ሆና በውስጧ የሚኖሩት “ኢትዮጵያውያን” ግን የኢትዮጵያን የባህል ልብስ አንለብስም እያሉ የአረቡን ልቅ እና ሰነፈኛ አለባበስ ይመርጣሉ። ዊስል ስሚዝና ባለቤቱ ኢትዮጵያ መጥተው የባህል ልብሳችንን ይለብሳሉ፤ ታዋቂቷ ኢትዮጵያዊት ግን የአረቡን ልብስ ለዓለም ታስተዋውቃለች። አይገርምም?
እባብ ቀስበቀስ በእግሩ ይሄዳል!
አዎ! ይህ በጣም ይገርማል! ከበስተጀርባውም እባባዊ ተንኮል ስላለበት ደም ያፈላል። በእስልምና ዘንድ ምስሎች የተከለከሉ ናቸው፤ ሆኖም እንደ ምስል ከሚጠቀሙባቸው መንገዶች መካከል አንዱ አለባበሳቸው ነው፤ ይህም ቁልፍ የሆነ ሚና ይጫወታል። ክርስቲያኖች በራሳቸው ህይወት ብቻ ላይ በማተኮር እራሳቸውን ችለው መኖር ይችላሉ፡ የእስልምና ተከታዮች ግን ልክ እንደ ነቀርሳ ጥገኞች ናቸው፤ ጤናማውን ህብረተሰብ መጠጋት ግዴታቸው ነው፡ በውስጣቸው የታመቀውን ሺህ ጋኔን በተለይ በክርስቲያኖች ላይ እያራገፉ ማስገባት የመጀመሪያው ተልዕኳቸው ነው። ለዚህ በግብጽ አገር በኮፕት ወገኖቻችን ላይ ለሺህ ዓመት የተካሄድው ጸረ–ክርስቲያን ዘመቻ ትልቅ ማስረጃ ነው። ኮፕቶች የራሳቸውን ባህል፣ ቋንቋና አለባበስ ለማጣት የበቁት በሰይፍ ብቻ ሳይሆን፡ ለሙስሊሞች ጋር ተደበላልቀው በጉርብትና ለመኖር በመብቃታቸው ነው። እንደ አምደጺዮን እና ዮሐንስ የመሳሰሉት ድንቅ ኢትዮጵያውያን ንጉሦች፡ ህዝብ ክርስቲያኑ እና ሙስሊሙ በአንድ ላይ በአንድ አካባቢ መኖር እንደሌለባቸው አስቀድመው ያስጠነቅቁን ነበር። ይህን አሁን ግልጥ ብሎ የምናየው ነው፤ ህዝበ ክርስቲያኑ በጣም ሊያስብበት የሚገባው ጉዳይ ነው።
ሙስሊሞች የሚፈልጓቸውን ግለሰቦችና ህዝቦች እንደ እባብ ነው ለስለስ ባለ መልክ የሚቀርቧቸው። ለምሳሌ፡ እጅ ለእጅ መሳሳምን፣ እስላማዊ የአረበኛ ቃላቶችን ደጋግመው መለፍለፍን፡ ሳቅ–አልባ ቁጡነታቸውን እንዲሁም አረባዊ ስነምግባሮቻቸውን እና አለባበሳቸውን ያለምንም ግድጃ ቀስበቀስ ነው የሚያለማምዱት። “ከ አህያ ጋር የዋለ…“ ይባል የለ! ከዚያም አንድ አካባቢ ላይ ሙጥኝ ብለው በመኖር ቡና አፍልተው፡ ቄጤማ ጎዝጉዘው፡ “ጀባ ጀባ ውጭ ያለህ ግባ!„ እያሉ ወደ ውስጣቸው ማስገባት ይጀምራሉ። ህፃናት ሴቶችን መግረዝ እና ወዘተ የመሳሰሉትን አጸያፊ ባሕሎችን አጠገባቸው ለሚኖሩ እስላም ላልሆኑ ማህበረሰቦች የሚያካፍሉት በዚህ መልክ ነው። በኋላም – ይህ ዋናው ዒላማቸው ነው — የክርስቲያኑን መንፈስ በማድከም ስጋውን ወደ መግደል ያመራሉ፤ ማንነቱንና ነፍሱን ነጥቀው ለዲያብሎስ አባታቸው ለማስረከብ ይሞክራሉ።
ግን በመንፈስ በጣም ጠንካራ የሆኑትን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያን የእግዚአብሔር ልጆች በፍጹም አልቻሏቸውም፣ ወደፊትም አይችሏቸውም።
የመጀመሪያው ቪዲዮ ወደ መጨረሻ ላይ እነደሚታየው ይህ እስላማዊ የአጋንንት መንፈስ የያዛቸው ክርስቲያን ወገኖቻችን በዚህ መልክ የዲያብሎስ ጥቃት እንደደረሰባቸው በግልጽ መስካሪ ነው።
ለእኛ በሩ ዝግ በሆነው ዓለም አቀፋዊ የፊልም እና ሜዲያ መድረክ ላይ፡ ሳያት ደምሴ የኢትዮጵያን ሳይሆን ይህን የሰነፍ አረቦች አለባበስ (ሰነፍና ዝልግልግ ነው ይህን የሚለብስ) እንድታስተዋውቅ መደረጓ በጣም የሚያሳዝን ነው። የማን ምርጫ ይሆን? የአረቡ ጨርቅ ቆንጆ ፊቷን ሸፍኗት ሳያት በጣም ነበር ያቅለሸለሸኝ። ቆርጬ ባስገባሁት ፊልሙ ውስጥ በጋኔን የተያዘችው እናት ይህን ጋኔናዊ የአረብ አለባበስ በጣም በሚያስገርም መልክ ነው ያቀረበችልን፤ መስጊድ ሳይቀር አላቸው። ሁሉም መገጣጠሙ በጣም የሚገርም ነው! እናት ቤተክርስቲያናችን አለባበስን በሚመለከት መመሪያዎችን መስጠቷ ያለምክኒያት አልነበረም። ክርስቲያን የሆኑ ሴቶች ይህን ዓይነት ልብስ ካላቸው አሁኑኑ ቶሎ ብለው እንዲያቃጥሉት ይመከራሉ!
ዩቲውብ ፊልሙን ስለሚከለክል ሦስቱንም ክፍሎች እዚህ መመልከት ይቻላል፦
P.S: የ “አረመኑ እልቂት” ፊልም ዋናው ተዋናይ “ምካኤል” የሳያት ደምሴም ፍቅረኛ “ሚኻልክ ወይም ሚካኤል ያባላል።