Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Ethiopian Churches’

አዲስ አበባ / Addis – ሳሪስ አቦ / Saris Abo

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 13, 2013

ሳሪስ አቦ – የምዕራፈ ቅዱሳን ፈለገ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክርስቲያን

ቀኑ መጋቢት 5 ዕለቱ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ሰዓቱ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ሆኗል፤ አሁንም ህማሙን እየታገለ እያላበው በድካም ለፍጥረቱ ሁሉ ይለምናል፤ “አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህን ኢትዮጰያንም ባርክ” ይላል። ህመም የጀመረው መጋቢት 3 ዓርብ ቀን ነው፤መታመሙን የሰሙ እንደርሱ ቅዱሳን የሆኑት ዘርአ ቡሩክ፤ ፍሬ ቅዱስ፤ያዕቆብ፤ብንያምና ዮሴፍ እንዲሁም በወቅቱ የኢትዮጰያ ንጉስ የነበረው እንድርያስ ሊጠይቁት ተሰብስበዋል ወደ አጠገቡ መድረስ ግን አልተቻላቸውም አባታችን ገብረመንፈስ ቅዱስ የሚጋርደው እንጨት ዛፍ በሌለበት በርሃ እንደ አንበሳ ተኝቶ አዩት በላዩ ያረፈው የእግዚአብሔር ጸጋ ከፊቱ የሚወጣው ብርሃን ቀይ መልኩ ረዥም የራስ ጠጉሩ እንደ ነጭ ሐር የሚሆን ጽሕሙ አስደነቃቸው።

ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሲሆን ከሰማይ ታላቅ ነጎድጓድ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መላአክትን አስከትሎ ወደ አባታችን ወረደ፤ ከሰማይ ወደ ምድር ህብሩ አምሳያው ልዩ ልዩ የሆነ እንደ ጸሐይና እንደ ጨረቃ የሚያበራ እንደ ወንጪፍ ድንጋይ ይወረወር ነበር ከዚያ የነበሩ ሁሉ ፈሩ ወደ ኃላም ሸሹ ምድር ራደች ተራሮች ኮረብቶች ተናወጡ ብርቱ ጩኸት ንውጽውጽታ ሆነ።

ወዳጄ ገብረመንፈስ ቅዱስ ሰላም ላንተ ይሁን” እነሆ የማይታበል ቃል ኪዳን እገባልኃለው ስምህን የጠራ መታሰቢያህን ያደረገውን፤ እጣን ቋጥሮ ግብር ሰፍሮ መባ ይዞ ቤትህ የመጣውን እምርልኃለው አንተ ከገባህበት ገነት መንግስተ ሰማያት አገባዋለሁ አለው፤ አባታችንም “አቤቱ ጌታ ሆይ የኢትዮጰያን ህዝብ ማርልኝ” አለው፤ እነሆ ምሬልኃለው አስራት በኩራት አድርጌም ሰጥቼሃለው፤ ከመጋቢት አምስት ቀን ጀምሮ ዝክርህን ያድርጉ በአማላጅነትህም ይማጸኑ አለው።

ከዚህ በኃላ ሰባቱ ሊቃነ መላክት የአባታችንን ነፍስ ሊቀበሉ ወረዱ በታላቅ ምስጋናም ወደ ሰማይ አሳረጉት ስጋውንም ይዘውት ሄዱ የት እንደተቀበረ ግን እስካሁን አይታወቅም አንዳንዱ በእየሩሳሌም ነው ይላሉ፤ ሌላው በምድረ ከብድ ነው ይላል ግን እስካሁን ልክ እንደ ሊቀ ነብያት ሙሴ ስጋ የት እንደተቀበረ አይታወቅም።

ገድሉ ትሩፋቱ ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ ይበዛል ኢትዮጰያን አብዝቶ ይወዳታል፤ ምድራዊ ምግብ አልተመገበም የእናቱን ጡት እንኳን አልጠባም፤ ልብስ፤ መጠለያ አልፈለገም፤ የክረምት ቁር የበጋ ሐሩር እየተፈራረቀበት በተጋድሎ 562 ዓመት ኖረ፤ በዛሬዋ ቀን ሩጫውን ጨረሰ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ከአባታችን በረከት ያሳትፈን።

ቢዲዮው ላይ በሚታየው የአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ ቤተክርስቲያን ከዕለታት በአንዱ ቀን ጻደቁ አባታችን አቡነ መንፈስ ቅዱስ ወደ ዝቋላ ሲጓዙ ለጥቂት ቀናት ቦታው ላይ አርፈውበት እንደነበር ይነገራል። ከቤተክርስቲያኗ ወረድ ብሎ ሸለቋማ ቦታ ላይ በጣም የምትማርክ አነስተኛ ቤተክርስቲያን በ አቡነ አረጋዊ ስም እየተጠራች መንፍሳዊ ግልጋሎትን ትሰጣለች።

_

Posted in Ethiopia, Ethnicity, Genetics & Anthropology | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ያለ ምላስ ከተፈጠረው ልጅ ሆድ 24 እባቦች ወጡ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2012


አካለ ስንኩል (ሽባ) ሆኖና፡ እጅ እና እግሩ በአካሉ ተሣሥረውበት የነበረው የቄሱ ልጅ በሥላሴ ጠበል ከሽባነት እየተላቀቀና እየተፈወሰ ነው። ምላስ እንኳ አፉ ላይ ሳይወጣለት የተፈጠረው ይህ ልጅ በውስጡ አስረውት የነበሩት 24 እባቦች በጠበል ተነቅለው ከሆዱ ከወጡለት በኋላ፡ እጆቹና እግሮቹ ተዘረጉለት፡ ምላሱ ወጣለት፡ የባሕር አንበሳ እንደሚያሰማው ዓይነት ድምጽ ቢተነፍስም አሁን ቀስበቀስ መናገርም ጀምሯል።


___________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

ቅ/ሚካኤል የአሥር ዓመት ዓይነ-ሥውር አበራ — Miracles of Archangel Michael

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 20, 2011

የአገራችንን ዓብያተ ክርስቲያናት ልዩና ቅዱሳዊ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል የቤተክርስቲያኖቹ ሕንፃዎች ዛፎችንና አእፅዋታትን ከተፈጥሮ ጋር በተስማማ መልክ አብቀለው ለምዕመናኑ አመች የሆነ ሁኔታ መፍጠር መቻላቸው ነው።

እላይ ቪዲዮው ላይ በከፊል እንደሚታየው ምዕመናኑ የቤተክርስቲያኖቹ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙት ውብ የተፈጥሮ ሣሮች፡ አበቦች ወይም ዛፎች አጠገብ በመሆን እንዲሁም ቀዝቀዝ ያለውንና ነፋሻማውን ንጹህ አየር እየተቀበለ ለፈጣሪው ጸሎቱን ያደርሳል።

ብዙ ዓብያተ ክርስቲያናትን በመላው ዓለም ተዘዋውሬ ለማየት በቅቻለሁ፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በቀላሉ ሊያገናኙ የሚችሉትና ለመንፈሳዊ ሕይወት በጣም አመቺ የሆኑ ዓብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ እንደሚገኙ አሁን ለመገንዘብ በቅቻለሁ። ይህን ለመሰለው ጸጋ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል። ምናልባት ይህ እድል አሁን በእጃችን ስላለ ላንገነዘበው እንችል ይሆናል፡ ሆኖም ግን በመልክአምድር እንደ አዲስ አበባ ከፍ ብለው በሚገኙ ቦታዎች ላይ የቤተክርስቲያኖች ቁጥር በዓለም በብዛት የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው። ይህ እራሱ እንደ አንድ ትልቅ ምልክት ሊሆነን ይገባል፡ ቤተክርስቲያን ልጆቿን ለመጭው ጊዜ እያዘጋጀች ነውና!

በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።” {ኢሳያስ 22}

/ሚካኤል የአሥር ዓመት ዓይነሥውር አበራ

የደወሌ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከድሬዳዋ ማሥራቃዊ ክፍል በኢትዮጵያና በጅቡቲ ወሰን አቅራቢያ በረሃማ በሆነችው ከተማ ነው።

በደወሌ በረሃማ ሥፍራ ላይ በተመሠረተው የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ተአምራት ታይቷል።

ከነዚህም አንድ ዓይነሥውር ከማየቱም በላይ ሁለተኛው ሊቀ መላእክት ቅ/ሚካኤል የተወሰደበትን ቆርቆሮ በተአምር ወደ ቤተ መቅደሱ መመለሱ ነው።

ዓያናቸው የበራው ግለሰብ አቶ ጥላሁን ታደሰ የሚባሉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ለዓይናቸው መታወር መነሻው በውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የቦኖ ውሃ አስቀጂ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ቢርካውን ሲከፍቱ እንደ ደም ያለ ነገር ይታያቸዋል ከዚህም ጋር የጋዜጣ ንባብ ሱስ ስለነበራቸው አዘውትረው ጋዜጣ ያነቡ ነበር። በእነዚህ ሁለቱ ምክንያቶች በየትኛው ዓይናቸው እንደጠፉ በትክክል ባይታወቅም ዓይናቸው ደም ካየበት ጀምሮ እየደከመ መምጣቱን በዝርዝር ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን እንዳስገነዘቡት ከልጅነቴ ጀምሮ ቅ/ሚካኤልን እወደዋለሁ አከብረዋለሁ እዘክረዋለሁ ግን ዓይኔ በመታወሩ ምክንያት ከሥራ ተወገድኩ ለመኖር ስል አንድ መሪ ልጅ ይዤ ከድሬዳዋ ደወሌ በመመላለስ የጫት ንግድ ጀመርኩ በዚህም ምክንያት በሄድኩ ቁጥር በረኸኛው ቅ/ሚካኤል በድርሳንህ እንደሚነገረው ብዙ ተዓምር ሠርተሃል በእኔም ላይ ተአምርህን አሳይ እለው ነበር። በንግዱ የዕለት ጉርሴን የዓመት ልብሴን በሚገባ እያገኘሁ የደወሌን ቅ/ሚካኤል አጥብቄ እማፀነው ነበር። ዕለቱ ማክሰኞ ሐምሌ 12 በዚሁ ዕለት የደወሌው ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተባርኮ እንደሚገባ ባለቤቴ ነገረችኝ እኔ ግን እጄም እግሬም በመተሣሠሩ ምክንያት አንቺ ሄደሽ አክባሪ አልኳት ሄዳ አክብራ ተመለሰች።

በዚሁ የቅ/ሚካኤል ዕለት ልጄን ይዤ ዳቦዬን አቅርቤ ከዘከርኩ በኋላ ከጐረቤቶቼ ጋር ጠበሉን ጸዲቁን ቀምሰን ቅ/ሚካኤልን አመስግነን ጐረቤቶቼ ሲወጡ ጋደም አልኩ እንቅልፍ ያዘኝ በእንቅልፍ ላይ እንዳለሁ አንተ አንተ የሚል የጥሪ ድምፅ ሰማሁ ድምፁም ተደጋግሞ መጣ ብድግ አልኩ ልጁን ብጠራው የለም ነገሩ ግራ አጋባኝ በቤቴ ወለል ላይ በመተከዝ እንዳለሁ አንተ አንተ አታየኝም እንዴ? አለኝ እኔም መልሼ እኔ እኮ ዓይን የሌለኝ በመሆኔ ላይህ አልችልም አልኩ፤ መልሶም እኔ የደወሌው የመቶ አለቃ ኃይለ ሚካኤል ነኝ እንዴት አታውቀኝም አለኝ እኔም በደወሌ የማውቀው መቶ አለቃ ገበየሁን ነው አልኩት ዕለቱ ቅ/ሚካኤል በመሆኑ ከልጅነት የምማፀነው ቅ/ሚካኤል ይሆናል በዬ አስብ ነበር።

ሆኖም የደወሌው መቶ አለቃ ኃይለ ሚካኤል ነኝ ሲለኝ ልቤ በደስታ እየመላ መጣ እሱም በመቀጠል የለበስኩት ምንድር ነው? የእኔስ መልክ ምን ይመስላል? ሲል ጠየቀኝ፤ እኔም የለበሰው ልብስ በኮከብ የተጥለቀለቀ መሆኑንና መልኩም ቀይ እንደሆነ ነገርኩት ከዚህ በኋላ ለ10 ዓመታት ብርሃን አጥቶ የኖረው ዓይኔ ለማየት በመታደሉ በደስታ ተመላሁ ከዚሁም ቀጥሎ መሉ እንደ ብርሃን የሚያበራው ይኽ ሰው በቀጥታ እያየሁት የወርቅ ኃብል በአንገቴ ላይ አጠለቀልኝ የዓይኔን ብርሃን አረጋግጦ የድሮውን የወታደሮች ካኪ ልብስ አለበሰኝ ወርቁንም ሆነ ልብሱን ለማንም እንዳትሰጥ በማለት አስጠነቀቀኝ ከእኔ ተሠወረ።

ከተሠወረ በኋላ ለእኔም ሆነ ለጐረቤቶቼ ነገሩ እውነት አልመሰለም ባለ 50 ባለ 25 ባለ 10 ሳንቲም ገንዘብ በእግሬ ሥር እየጣሉ ይኽ ምንድር ነው? እያሉ ፈተኑኝ ሁሉንም ነገርኳቸው ይህን ሲያረጋግጡ ደስታው ልዩ ሆነ።

እግዚአብሔር ይመስገን የቅ/ሚካኤል ተረዳኢነት አማላጅነት በሁሉም ሰዎች ዘንድ ለዘለዓለም ይኑር” ማለታቸውን የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በወቅቱ ገልጿል።

ከዚህም ሌላ ከባድ ነፋስ የተቀላቀለ ኃይለኛ ዝናብ ጥሎ በከተማ ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ሕንፃዎች ተሰነጣጠቁ፥ በላያቸው የነበረው የጣራ ቆርቆሮ የነፋሱ ኃይል ተገነጣጠሎ ሲወስድ ቀደም ሲል ከቤተ መቅደሱ ላይ ተወስዶ የነበረውና ግለሰቦች በራስ ወዳድነት ይጠቀሙበት የነበረው ቆርቆሮ በዚሁ ከባድ ነፋስ ተጭኖ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በመምጣት በቅጽረ ግቢው ውስጥ ተቀመጠ፤ የተወሰደው ቆርቆሮ ተመልሶ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በመገኘቱ ቅ/ሚካኤል የሠራውን ገቢረ ተአምር ሕዝበ ክርስቲያኑ በአድናቆት ተመልክቶታል።

___________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: