ገንዘቤ፤ ማሬ፤ አልማዝና ሌሎች
የኢትዮጵያን ክብር አስጠባቂዎች
እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን!
የወንዶቹ ነገር አሳፋሪ ነው
ነገሩ ምንድን ነው? ለመሆኑስ ማን ነው
ጡረተኛውን መርጋ ከክትፎ ቤት ያመጣው?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 30, 2015
ገንዘቤ፤ ማሬ፤ አልማዝና ሌሎች
የኢትዮጵያን ክብር አስጠባቂዎች
እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያለን!
የወንዶቹ ነገር አሳፋሪ ነው
ነገሩ ምንድን ነው? ለመሆኑስ ማን ነው
ጡረተኛውን መርጋ ከክትፎ ቤት ያመጣው?
Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: Ethiopian Athletes, IAAF, Long Distance Running, Track & Field, World Athletics Championship | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 6, 2009
ኢትዮጵያ አገራችን እንደ ቀነኒሳ የመሳሰሉትን ድንቅ ሯጭ ስፖርተኞች በማፍለቋ ምን ያህል የታደልን ነን!
ባለፈው ወር በተገባደደው የዓለም አትሌቲክስ አሸናፊነት ላይ በስፖርት ዓይነቱ ታሪክ አንድ አትሌት የ 5 እና 10 ኪሎሜትሮች ርቀትን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማሸነፍ በቅቷል። ባለፈው ዓርብ እለት ደግሞ፡ “ጎልደን ሊግ” የሚል መጠሪ የያዘውን ዓመታዊ ውድድር በ6 የዓለም ከተሞች እየተዘዋወረ ለ6ኛ ጊዜ ድሉን ተቀዳጅቷል።
ቀነኒሳ እነዚህን አስቸጋሪ የርቀት ውድድሮች በሚያስደንቅ መልክ ለማሸነፍ ሲበቃ ያልተደሰተ፡ ያላደነቀ የስፖርት አፍቃሪ አልነበረም። ከጀርመን፡ እስከ ጃፓን፡ ከሰዋዚላንድ እስከ ስዊትዘርላንድ፡ ከኮሎምቢያ እስከ ካምፖዲያ፡ ቀነኒሳን እያሞገሰ ያልጻፈ ጋዜጣ የለም።
ምንም እንኳን የምዕራቡ የዜና ማሰራጫዎች ተቀዳሚ ትኩረት ለምእራባዊው ድንቅ ሯጭ ለ ጃማያካዊው ኡሴን ቦልት ቢሰጡም፡ በይበልጥ ሊደነቅ የሚገባው የአትሌቲክስ ስፖርት ጀግና ግን ቀነኒሳ እንደሆነ ባለሙያዎች ሁሉ ይናገራሉ።
ታላቁ ቀነኒሳ በቀለ፡ የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ጸጋ፡ ምን ያህል ብርቱ፡ ጽኑና ተወዳዳሪ የማይገኝለት ልዩ ጸጋ እንደሆነ ሊያረጋግጥልን ችሏል። አንዳንድ ሰዎች የቀኒንሳን ሆነ የኡሴን ቦልትን ተፈጥሮአዊ ጸጋ ከ ዶፒንግ ጋር በማያያዝ፡ ችሎታቸውን ለማጣጣል ይሞክራሉ። እነዚህ ወገኖች ግን በቅናት የተወጠሩ ደካሞች፡ ልፍስፍሶች መሆናቸውን ነው እንጂ የሚያሳዩት የሯጮቻችንን ሞራል ሊነኩ እንደማይችሉ ይታወቃል።
በተለይ በህክምና ሳይንስ ጥበባቸው የሚመኩት ተመራማሪዎች ተፈጥሮን ለማሸነፍ በሚያካሂዱት ትግል ላይ እንቅፋት ሲገጥማቸው፡ ብዙ ያልሆነ ተልካሻ ነገር ለመቀባጥር ይቸኩላሉ።
ድኃ ከሆኑት ኢትዮጵያን፡ ኬኒያን፡ ደቡብ አፍሪቃን ወይም ጃማይካን ከመሳሰሉት አገሮች የሚመጡት ድንግል የተፈጥሮ ጸጋዎቾ፡ በሰው ሰራሽ ጥበብ የተካኑትን የስፖርት ሮቦቶች ሲቀጡ ለማየት አሻፈረኝ የሚሉ ሰዎች በተለይ ባሁኑ ጊዜ በጣም እየበዙ መጥተዋል። እነ ቀነኒሳ፡ እነ ጥሩነሽ፡ ኃብታም በሆኑ አገሮች የሚገኙትን የስፖርት ተቋሞችና የስፖርቱ አፍቃሪዎች ዓይን መከንከን ከጀመሩ ውለው አድረዋል።
ብልጥ የሆኑት የአውሮፓ ሯጮች እስከ ኢትዮጵያና ኬኒያ ተራራዎች ድረስ በመጓዝና ልክ እንደ አፍሪቃውያኑ ሆነው ልምምዳቸውን በማካሄድ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ሲሞክሩ ቆይተዋል። ይህ መንገድ ሳይሳካላቸው ሲቀር ደግሞ ባቋራጭ ወደ ላብራቶሪ ተመራማሪዎቹ ቤት በመሄድና በተራቀቁ የኬሚካል ጭማቂዎች እራሳቸውን በሞሙላት ሯጮቻችንን ለመቅጣት ሲወራጩ ታይተዋል።
ይህ በእንዲህ ሆኖ፡ በርግጥ፡ የአፍሪቃውያንን ተፈጥሮአዊ ጸጋ እንደ መላው የሰው ልጆች ጸጋ፡ እንደራሳቸው ድል አድርገው በመውሰድ ከእኛ ጋር አብረው የሚደስቱ አውሮፓውያን፡ እስያውያንና አሜሪካውያን ብዙ ናቸው።
ሆኖም ግን፡ በእስፖርት ዓለም ለረጅም ጊዜ የበላይነቱን ይዛ የቆየችውና፡ የስፖርት ንግሥት በመባል የምትታወቀው ‘አትሌቲክስ‘ ባለፉት 20 ዓመታት ጥቁር የቆዳ ቀለም ባላቸው ስፖርተኞች ግዛት ሥር ለመውደቅ በቅታለች። ታዲያ፤ ይህ ሁኔታ ሌሎች ሕዝቦችን፡ በተለይ አትሌቲክስ አፍቃሪ የሆኑትን አውሮፓውያንን ቀስ በቀስ የበታቸኝነት ስሜት ውስጥ እንዲገቡ ስላደረጋቸው፡ የአትሌቲክስ ስፖርት በተመልካቾች ዘንድ የነበረው ተወዳጅነት በጣም እየቀነሰ መጥቷል። ይህን አሉታዊ ዝንባሌ የታዘቡት የስፖርት ባለሙያዎችና የዜና ማስራጫዎች የአትሌቲክስን ንግሥታዊ ዙፋን በይበልጥ ዝቅ ለማድረግ የሚከተሉትን ስልቶች ለመጠቀም እየሞከሩ ነው፦
የአትሌቲክስ ስፖርት ዋና ዋና በሆኑት የዜና ማሰራጫዎች ቅድሚያ የሆነ ቦታ እንዳይሰጠው ማድረግ። ለምሳሌ እንደ “ጎልደን ሊግ” የመሳሰሉትን የአትሌቲክስ ውድድሮች ለተመልካች በቴሌቪዥን የማቅረብ መብቱን የሚወስዱት የኬብል ቴሌቪዥን ባለቤቶች ስለሆኑ፡ ለሰፊው ተመልካች ውድድሮቹን በቀላሉ አቅርቦ ለማሳየት አይቻልም።
እነዚህን የመሳሰሉት ድርጊቶች በ21 ክፍለ ዘመን ዓይን ባወጣ መልክ ሲፈጸሙ መታየታቸው፡ የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነው። ኢትዮጵያውያን አፍሪቃዊው ሆነ፡ አውሮፓዊው፡ እስያዊው ሆነ አሜሪካዊው፡ በፈለገው የስፖርት ዓይነት፡ ልዩ የሆኑ ስፖርታዊ ውጤቶችን ሲያመጡ ልክ እንደራሱ ስፖርተኛ አድርጎ አብሮ ይደሰታል። እንደ ቀነኒሳ ያሉ ኢትዮጵያውያን ግን የአሸናፊዎችን ደረጃ ለመያዝ ሲበቁ፡ የተቀረው ዓለም፡ ሳይወድ በግድ አድናቆትን ያተርፋል እንጂ፡ በአትሌቶቻችን ድል ከ እኛ ጋር አብሮ አይደሰትም። እንኳን አውሮፓዊውና አሜሪካዊው፡ ሌላው አፍሪቃዊም ቢሆን በኢትዮጵያውያኖች ድል እስካሁን የሚደሰት “የስፖርት አፍቃሪ” አላጋጠመኝም።
ይህ በቅናት ላይ የተመረኮዘው ኢ–እስፖርታዊ ባሕርይ መወገድ ይኖርበታል። የሚመለከታቸው ወገኖችም ይህን አድሏዊ መንፈሥ ቢዋጉ በይበልጥ እራሳቸውን ነው ሊጠቅሙ የሚችሉት።
_________________________
Posted in Ethiopia | Tagged: Ethiopia, Ethiopian Athletes, IAAF, World Athletics | 1 Comment »