የድንግል ማርያም ልዩ ልዩ ድንቅ ሥራዎች እና ገቢረ ተአምራት
በእንጦጦ ደብረ–ፀሐይ ጠበል
በሀገራችን ኢትዮጵያ የቀደሙ አባቶች በፋቀደ እግዚአብሔር እየተመሩ ብዚ ገዳማትንና አብያተ ክርስቲያናትን ሲያሠሩ መኖራቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።
በእግዚአብሔር ፈቃድ ከተሠሩት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት የታነፀችው ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የእንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ናት።
አፄ ዳዊት በ፩ ሺህ ፫፻፺፭ (1395) ዓ.ም. ነግሠው በዘመነ መንግሥታቸው ግማደ መስቀሉን ወደ ሀገራችን እንዲመጣ ጥረት አድርገዋል። የእመቤታችን ድንግል ማርያም ፅላት ከቡልጋ በማምጣት የእንጦጦን ከተማ መሥርተው በመጀመሪያ ጊዜ በእመቤታችን ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን እንዲተከል አድርገዋል።
ከአፄ ዳዊት በኋላ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ገደማ መስቀሉን ካሳረፉበት ቦታዎች አንዱ በእንጦጦ ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ታሪክ ጸሐፊዎች ዘግበዋል በዚሁ ቦታ ለ፫ ወራት ያህል ገደማ መስቀሉ ከተቀመጠ በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃድ ባለመሆኑ ወደ መናገሻ ከመናገሻ ወደ ግሸን እንደተወሰደ ይነገራል።
በ፩ ሺህ ፭፻፳፩ (1521)ዓ.ም. በተነሣው ክርስቲያንንና አብያተ ክርስቲያናትን የማጥፋት የግራኝ መሐመድ ወረራ በሀገራችን ካጠፏቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት አንዷ አፄ ዳዊት ያሠሯት የእንጦጦ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ናት።
አፄ ምኒልክ ለመጀመሪያ ጊዜ የመናገሻ ከተማቸውን የቆረቆሩት በእንጦጦ ስለነበር ግራኝ ሌላ ስም ሰጥቷት የነበረውን የአባቶቻቸውን ከተማ የቀድሞውን ስሟን መልሰው እንጦጦ ብለው ጠሯት፡ በስደት የነበረችውን የእመቤታችን ፅላት ወደ መናገሻ ከተማቸው እንጦጦ ሰኔ ፲፱ ቀን ፩ ሺህ ፰፻፯፫ (1873)ዓ.ም. ይዘዋት ገቡ ለእመቤታችን ቅድስት ማርያም ዕለት ወዲያውኑ መቃኛ ቤት ሠሩ በዚያ ዘመን ያሠሯት መቃኛ በአሁኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ በሸክላ ጉልላት አጌጣ ትገኛለች።
የአዲሱ ቤተ ክርስቲያን ሥራ ሲጀመር በዘመናቸው የነበሩት ግብፃዊው ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በሥርዓተ ክህነት ሆነው እያጠኑ ንጉሠ ነገሥቱ አፄ ምኒልክ እና ንግሥተ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በሥርዓተ መንግሥት ቆመው በጳጳሱ መሪነት ካህናቱ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ወንጌል እየደገሙ በየማዘኑ አራት መቶ እግዚአታ አድርሰው ጳጳሱ አራት ድንጊያዎችን ባርከው በአራት ማዕዘን መሠረት ጣሉ ንጉሥ ምኒልክም ዘጠኝ አናፂዎች ከጎንደር አስመጥተው ሥራውን ዘወትር እየተከታተሉ አሠሩ።
ይህ በንጉሡና በንግሥቷ ከፍተኛ ክትትል የተሠራው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ እንዳለቀ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብዙ ተአምራት እንደተደረገ በየጊዜው ይገለፃል።
ባህታዊ ገ/መድህን እንደሚሉት እሳቸው በተለያዩ ገዳማትና በበረሃ ሲኖሩ ለሁለት ጊዜ ያህል አዲስ አበባ መጥተው ተመለሱ ከነበሩበት በረሃ ቦታ በ፲፮ መዓዘን እመቤታችን ድንግል ማርያም አሳየቻቸው የእመቤታችንን ሥራ እያደንቁ ሲጠባበቁ ወደ እንጦጦ መንበረ ፀሐይ እንዲሔዱ ፈቃዷ ስለሆነ ድኩላ እየመራቸው ከፀበሉ ቦታ ደረሱ፡ ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ ከጽ/ቤቱ ጋር ተነጋግረው ሥራ ጀመሩ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቸርነት ስለአልተለያቸው አሁን እንደሚትየው ብዙ ሕመምተኞች በእግዚአብሔር ፈቃድ በድንግል ማርያም አማላጅነትና ልመና ጤንነታቸውን እያገኙ ነው።
ከመስከረም ፩ ሺህ ፱፻፺፪ (1992)ዓ.ም ወዲህ ከተለያዩ በሽታዎች የዳኑት የሚከተሉት ናቸው፦
የበሽታው ዓይነት የተፈወሱት ሰዎች
|
||
1 |
ከኤድስ በሽታ የዳኑ |
2022 |
2 |
ከሽባነት |
750 |
3 |
ከዐይነ ሥውርነት |
350 |
4 |
ከአስም በሽታ |
5003 |
5 |
ከስኳር በሽታ |
3642 |
6 |
ከደም ብዛት |
6874 |
7 |
ከነቀርሳ / ካንሰር |
2561 |
8 |
ከሚጥል በሽታ |
5734 |
9 |
ከታይፎይድና ከታይፈስ |
2397 |
10 |
ከአጋንንት ቁራኝነትና ከስኳር – ከዓይነ ጥላ |
25000 |
11 |
ከአልማዝ ባለጭራ |
889 |
12 |
ከኩላሊት |
450 |
13 |
የሐሞት ጠጠር የወጣላቸው |
26 |
14 |
አውሬ/አይጥ/ከሆዳቸው የወጣ/ከወባ |
15 |
|
|
|
ከውጭ አገር መጥተው በጠበሏ የተፈወሱ |
||
1 |
ከአረብ አገር |
180 |
2 |
ከካናዳ |
110 |
3 |
ከእንግሊዝ |
68 |
4 |
ከኢጣሊያ |
15 |
5 |
ከጀርመን |
32 |
6 |
ከጃማይካ መጥተው ክርስትና የተነሱ |
152 |
7 |
ከእስልምና ወደ ክርስትና እምነት የተመለሱ |
710 |
የበሽታው ዓይነት የተፈወሱት ሰዎች
|
||
1 |
ከልምሻነት |
380 |
2 |
ከሚጥል በሽታ |
76 |
3 |
ከደም ብዛት |
232 |
4 |
ከአስም |
64 |
5 |
ከጨጓራ |
55 |
6 |
ከደም ብዛት |
233 |
7 |
ከአእምሮ ጭንቀት |
182 |
8 |
ከትምባሆ ማጨስ |
2543 |
|
|
|
ምንጭ፡ እንጦጦ ማርያም ቤ/ክርስቲያን 2004 ዓ.ም
________________________________