Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

Posts Tagged ‘England’

Money Rankings: Soccer Vs. Football

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 17, 2012

እስፖርት ጥሩ ነገር ነው፡ ግን ገንዘብና ዝና ላሰከራቸው ታዋቂ ቡድኖች ወገኖቻችን ቴሊቪዥንና ሪዲዮ ጋር ተጣብቀው ልባቸው እስኪወጣ ሲጋደሉ ሳይ ግርም ይለኛል፤ አዝናለሁ፤ ያውም ለሚያንቋሽሹንና ለማይወዱን እንግሊዞች! የአዲስ አበባ ወጣት የሳምንቱን መጨረሻ የሚያሳልፈው ከነ ማንቸስተር ጋር ሆኗል፤ አንዳንዴ ምናለ ለነ ኃይሌ ገብረስላሤ፤ ለነጥሩነሽ ዲባባ የልባቸው ትርታ ያን ያህል ከፍ ቢል እላለሁ።

Manchester United lost the Premier League title on the last day of the season in heartbreaking fashion, when rival Manchester City scored a last-minute goal to defeat Queens Park Rangers and clinch its first title ever in May. Man City’s win prevented Manchester United from winning a second straight Premier League title–and record 20th overall–disappointing the team’s 659 million fans around the world.

The Red Devils still lay claim to another title, though: The world’s most valuable sports team. Forbes estimates Manchester United is now worth 2.23 , 19% more than No. 2 Real Madrid, which is worth 1.88 .

Soccer clubs hold the top two spots among the world’s most valuable franchises, but it is American football teams that dominate the rest of the top 50.

Continue reading…

_

Rank

Team

Type

Country

Value in Billion $

Manchester United

Soccer

England

2.23

Real Madrid

Soccer

Spain

1.88

New York Yankees

Baseball

USA

1.85

Dallas Cowboys

American Football

USA

1.85

Washington Redskins

American Football

USA

1.56

Los Angeles Dodgers

Baseball

USA

1.4

New England Patriots

American Football

USA

1.4

FC Barcelona

American Football

Spain

1.31

New York Giants

American

Football

USA

1.3

 10.

Arsenal

Soccer

England

1.29

_

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infotainment | Tagged: , , , , , , , , , | 2 Comments »

‘Little’ Great Britain: Christian Worker Loses Her Job After Being Targeted by Islamic Extremists

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 30, 2011


Nohad Halawi, who worked at Heathrow Airport, is suing her former employers for unfair dismissal, claiming that she and other Christian staff at the airport were victims of systematic harassment because of their religion.

She claims that she was told that she would go to Hell for her religion, that Jews were responsible for the September 11th terror attacks, and that a friend was reduced to tears having been bullied for wearing a cross.

Continue reading…

____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Life | Tagged: , , , , , , , | 1 Comment »

ታላቋ ብሪታኒያ ስታንስ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 4, 2011


ኢትዮጵያ አገራችን ጠላቶቿ የበዟባት አገር መሆኗ የሚያጠያይቅ አይደለም። ሆኖም አሁን በምንገኝበት ዘመን በተለይ ከአውሮፓ አገሮች በኩል እየተካሄደ ያለው የጥላቻና የተንኮል ዘመቻ በጣም አሰልች እና ኋላ ቀር መስሎ ይታያል። ብዙ ነገሮችን በግልጽ አይተን መረዳት በምንችልበት ዘመን፡ እነዚህ የአውሮፓ ኃይሎች መልካቸውን እየቀያየሩ ሲመጡብን ስናይ፡ ይህ ለኛ ያላቸው ጥላቻ ምን ያህል ሥር የሰደደ ቢሆን ነው ያሰኛል።

በዚህች ምድር ላይ አገራቱንና ሕዝቦችን እንደ እንግሊዞች ሲያበጣበጥ የቆየ ሕዝብ የለም። ከምስራቅ አፍሪቃ እስከ መካከለኛው ምስራቅ፤ ከደቡብ እስያ እስከ ባልካን አገሮች ድረስ የሚታየው ውጥንቅጥ እንግሊዞች ከቀበሩት መርዝ የተነሳ ነው።

አገራችን ተደላድላና ጠንክራ አንድነቷንም አጽንታ እንዳትኖር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንግሊዝ አሁንም እየሞከረች ነው። ከ10ሺህ ኪሎሜትር በላይ እየተጓዘች ከአርጀንቲና ጋር ሆነ ከኢራቅና አፍጋኒስታን ጋር ጦርነት የምትገጥመዋ እንግሊዝ ለኦጋዴን ነዋሪዎች ተቆርቋሪ መስላ በኢትዮጵያውያን ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት ሁከት ለመፍጠር ትሞክራለች። የኦጋዴን ነፃ አውጭ ድርጅት በሚል መጠሪያ ሥር ለሚታገሉት አክራሪ እስላሞች የሞራልና የገንዘብ እርዳታ ታቀብላለች፡ በለንደን ከተማም ጽህፈት ቤት እንዲከፍቱ ፈቅዳለች። በጣም የሚገርመው፡ 15 ሚሊየን ለሚጠጉ ጭቁን ኩርዶች ከ20 ዓመታት በላይ የሚታገለው የቱርኩ ኩርዳውያን ነፃ አውጭ ድርጅት (PKK) ፡ እንኳን ጽህፈት ቤት ሊኖረው፡ የሽብር ፈጣሪ ድርጅት ነው ተብሎ በምዕራባያውያኑ ዘንድ ለመኮነን በቅቷል። በኢትዮጵያና በእስራኤል ላይ ግን የሌባ ጣታቸውን ቀድመው ይሰዳሉ።

እየተበላሸና ዋጋ ቢስ እየሆነ የመጣው የቀድሞው አንጋፋ የዜና ማሰራጫ ድርጅት፡ ቢቢሲ፡ በኢትዮጵያ እና በእስራኢል ላይ፥ በአፍሪቃ እና በጥቁር ሕዝቦች ላይ፡ በክርስትና እና ክርስቲያናዊ በሆነ ሞራል ላይ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ላይ ይገኛል።

ከጥቂት ሣምንታት በፊት በእንግሊዝ ፖሊሶች አንድ ጥቁር እንግሊዛዊ ተገደለ። ይህን ግድያ በመቃወም ብዛት ያላቸው ጥቁሮች አቤቱታቸውን ሰላማዊ በሆነ መልክ በሰልፍ ለመግለጽ ሞከሩ። ይህም ሰላማዊ ሰልፍ ያስደነገጣቸው ባለሥልጣናት ለዓመታት ያዘጋጇቸውን የከተማ ዱርየዎችና ቦዘኔዎች ቀስቅሰው በመጥራት በየከተሞቹ ብጥብጥ እንዲፈጥሩ አደረጉ። የባለሥልጣኑ ዓላማም የማርቲን ሉተር ኪንግ ዓይነት እንቅስቃሴ በእንግሊዝ ጥቁሮች ዘንድ እንዳያድግ ገና በእንጭጩ ለመቅጨት ነው።

ምንም እንኳን ብጥብጥ ፈጥረው የነበሩት ግለሰቦች አብዛኞቹ ነጮች እና እስያውያን ቢሆኑም፡ እንደ ቢቢሲ የመሳሰሉት የዜና ማሰራጫዎች፡ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ጥቁሮችን ወነጀሉ። ይህን ፕሮግራም ከ ቢቢሲ ዎርልድ ሰርቪስ ያዳምጡ

ቢቢሲን ወይም ሲ ኤን ኤንን ብናይ የዜና አንባቢያንና ቃለ አቀባይ ሆነው የሚያገለግሉት አብዛኞቹ ጋዜጠኞች የፓኪስታን፡ የህንድ ወይም እስላማዊ አመጣጥ ያላቸው ግለሰቦች ናቸው። አንድ ሁለት ጥቁር ጋዜጠኞች በቴሌቪዥን ብቅ ቢሉ፡ ለቴሌቪዥን ፈጽሞ አመቺ ያልሆኑት እየተመረጡ ነው። ችሎታውና ብቃቱ ያላቸው ብሎም ተወዳጅ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ አፍሪቃውያንና ጥቁሮች አሉ፡ የዜና ማሰራጫዎቹ ግን ሊቀጥሯቸው አይፈልጉም፡ ከአጀንዳቸው ጋር አይሄድምና። በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው፣ የቢቢሲ አብዛኛው ተመልካች ሆነ አድማጭ አፍሪቃ የሚገኝ ነዋሪ መሆኑ ነው። እስያው፡ አረቡ ሆነ አውሮፓዊው የየራሱን ቴሌቪዥንና ራድዮ የሚከታተል በመሆኑ ቢቢሲን የሚከፍተው ጥቂቱ ነው።

በለንደኑ ብጥብጥ ወቅት ጠቅላይ ምኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ከጽህፈት ቤታቸው ከዳውንኒን ስትሪት ሆነው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ከጀርባቸው የሕንጻው ጠባቂ ሆኖ የሚታየው ፖሊስ ጥቁር መሆኑን ለማሳየት ካሜራው በሁለቱ ላይ አተኩሮ ነበር። ጥቁር ፖሊስ ከዚህ በፊት በጽሕፈት ቤቱ ታይቶ አይታወቅም። እዚህ ይመልከቱ።

ቢቢሲ ኢትዮጵያን የሚመለከት ነገር ሲያቀርብ ንቀትና ጥላቻ በተሞላበት መልክ ነው። አንዳንዴ ፖሰቲቭ የሆኑ ወሬዎችን ጣል ስለሚያደርግ ሚዛናዊ የሆነ ነገር የሚያቀርብ መስሎ ሊታየን ይችላል፡ ይህ ግን ረቂቅ ማደንዘዣ፡ ከዜና ማሰራጫው እንዳንርቅ የማድረጊያ ስልቱ እንጅ ሃቅ የጠማው ድርጅት ስለሆነ አይደለም። ይህ ኒዮሊበራል የዜናና ፕሮፓጋንዳ አሰራጭ ድርጅት ጸረኢትዮጵያ፣ ጸረአፍሪቃ፣ ጸረእስራኤል እና ጸረክርስትና የሆነ አጀንዳ እንዳለው አጠንቅቀን ማወቅ ይኖርብናል።

ለምሳሌ፡ በሶማሊያ የተከሰተውን ረሃብ በሚመለከት አስቀድሞ እና ደግሞ ደጋግሞ ረሃብ በምስራቅ አፍሪቃ” “ረሃብ በአፍሪቃው ቀንድእያለ መላው ምስራቅ አፍሪቃን በማጠቃለል እንዲሁም የ 1985 .ምህረቱን የኢትዮጵያ ረሃብ ከልሶ ከላልሶ በማንሳት የኢትዮጵያ ስም ሁሌ ከረሃብና በሽታ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ማሳወቁን ይመርጣል። በብዙህ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሶማሊያዎች ጠላቴ ነው የሚሉት፡ በደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለፈቱ 20 ዓመታት ጥገኝነት አግኝቶ በሰላም እንደሚኖር ቢቢሲና አጋሮቹ አንዴም አትተውት አያውቁም። ነገር ግን 1000 የሚሆኑ ሶርያውያን ስደተኞች በጎረቤታማዋ ቱርክ ጥገኝነት ሲያገኙ፡ እነ ቢቢሲ ቱርኮች ምን ያህል እንግዳ ተቀባዮችና አስተናጋጆች መሆናቸውን ለተመለካቹና አድማጩ ለማሳወቅ ሲቸኩሉ ይታያሉ።

ከጥቂት ሣምንታት በፊት ደግሞ ቢቢሲ ኢትዮጵያውያን የባሪያንግድ ያካሂዱ እንደነበር ለማሳወቅ ደቡብ አፍሪቃ ድረስ ሂደው የአንዲት የቀድሞ ኢትዮጵያዊት የሕይወት ታሪክ አቀረቡልን። በዚህም አማካይነት የኢትዮጵያን አኩሪ ታሪክ፡ ጽኑ ሃይማኖት ባጠቃላይ ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያውያን ያሰኛቸውን ማንነት ለመተናኮል ይሞክራሉ። እኛ አውሮፓውያን ብቻ ሳንሆን፡ አኩሪ ታሪክ አለን የሚሉት ኢትዮጵያውያንም ኢሰብዓዊ የሆነ ታሪክ ሲፈጽሙ ነበር፡ ኢትዮጵያውያን በባርነት ሲሰማሩ እኛና በአፓርታይድ ሥርዓት የምትታወቀው የነጮቹ ደቡብ አፍሪቃ፡ ኢትዮጵያዊዋን ባሪያ የአስተማሪ ሙያ እንዲኖራት ረድተናት ነበር፡ ለማለት ነው ነገሩ። የተንኮሉን ጥበብ የተካኑት እንግሊዞች የሰላሳ፡ የሃምሳ የመቶ ዓመታት መርዛማ ዕቅድ ነውና የሚያዘጋጁት፡ ፍላጎታቸው አሳዛኝ በሆነ መልክ የተከፋፈሉት የኢትዮጵያ ጎሣዎች እርስ በርሳቸው እየተኮረኳኮሙ እንዲደክሙ እንዲወድቁ፡ ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው የመንፈስ እና የጥሬ ዕቃ ጥማታቸውን ለማርካት ይመኛሉ።

19ኛው ክፍለ ዘመን በስዊድን አገር ነግሠው የነበሩት ጉስታቭ 3ኛ የኢትዮጵያ ቡና‘ “መርዝ ሳይሆን አይቀርምብለው ጠረጠሩ። ይህንም ለማረጋገጥ ሁለት የወህኒ ቤት እስረኞች ተመርጠው አንደኛው ቡና ሁለተኛው ደግሞ ሻይ እንዲጠጡ ተደረጉ። ይህንንም ጥናት ለዓመታት እንዲከታተሉ የስዊድን ሊቆች ተመረጡ። እስረኞቹ ቡናቸውንና ሻያቸውን ፉት እያሉ ለብዙ ዓመታት ቆዩ፡ በዚህ ወቅት፡ መጀመሪያ ሊቆቹ ሞቱ፡ ከዚያም ንጉሥ ጉስታቭ፡ በመጨረሻም ሻይ እንዲጠጣ የተደረገው እስረኛ አረፉ። ቡና ጠጪው ግን የወህኒ ቤት ጊዜውን ጨርሶ ወጣ።

ከኢትዮጵያ በፊት ታላቋ ብሪታንያ ቀድማ እንደምትከፋፈል፡ ይህንም በህይወታችን ለማየት እንደምንበቃ እርግጠኛ ነኝ። ይህ ታታሪ የብሪታኒያ ሕዝብ በዚህ መልክ አሁን እየወደቀ መምጣቱ ሊያስገርመን አይገባም።

 

_________________________________________________________

 

 

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: