Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Emperor’

Emperor Yohannes IV | ዐፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 28, 2022

💭 “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት።ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት፤ ሁለተኛ ክብርህ ናት፤ ሶስተኛም ሚስትህ ናት፤ አራተኛም ልጅህ ናት፤ አምስተኛም መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፤ የዘውድ ክብር፤ የሚስት ደግነት፤ የልጅ ደስታ፤ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሳ።” አፄ ዮሐንስ ፬ኛ

💭 የአፄ ዮሐንስ እና የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ

________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

France24 | አብዮት አህመድ ሰሜን ኢትዮጵያውያንን እንደ አፄ ኃይለ ሥላሴ በርሃብ ሊቀጣ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 15, 2020

The Last Emperor of Ethiopia: Haile Selassie’s Legacy Remains Divisive

ሰሜን ኢትዮጵያውያንን በረሃብ የመጨረሱ ሤራ ዛሬም ቀጥሏል እያለን ነው ይህ ዛሬ በፈረንሳዩ የቲቪ ጣቢያ የተሰራጨው ቪዲዮ።

እነዚህ አውሬዎች እኮ በመፈንሳውያኑ ሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ ያላቸው ጥላቻ ተወዳዳሪ የለውም፤ ከእረኛው እስከ ተማሪው ፣ ከጋዜጠኛው እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ ያላቸውን ጥላቻ ከጦርና ጋሻ በቀር ሌላ ሊያስወግደው የሚችል ነገር የለም።

ላለፉት 150 ዓመታት ስጋውያኑ ደቡብ ኢትዮያውያን(አፄ ሚኒልክና ኦሮሞ አማካሪዎቻቸው፣ አፄ ኃይለ ሥላሴና ኦሮሞ አማካሪዎቻቸው፣ መንግስቱ ኃይለ ማርያም እና ኦሮሞ መንግስቱ፣ ህዋሀት እና ኦሮሞ አጋሮቹ፣ ዛሬ ደግሞ አብዮት አህመድና የዋቄዮአላህ አህዛብ መንግስቱ መንፈሳውያኑን ሰሜን ኢትዮጵያውያንን (ቤተ አምሓራን እና ትግራይን) በረሃብ ሲጨፈጭፏቸውና ለመጨፍጨፍ በመዘጋጀት ላይ ናቸው። አልመኝላቸውም፤ ነገር ግን ስጋውያኑ ደቡብ ኢትዮጵያውያን ላለፍቱ 150 ዓመታት አንዴም በረሃብ ያልተጠቁበት ምስጢር ይሄ ነው። በዚህ ዘመን እያንዳንዱ መንግስት መንፈሳውያን ኢትዮጵያውያንን በጣም የሚጎዳ ነበር። በዚህ ዘመን እንኳን ከሰሜን መጡ የተባሉት ህዋሃቶች ያው ስልጣኑን ለመንፈሳዊቷ ኢትዮጵያ ጠላቶች አስረክበው ሄደዋል። በዚህ ድርጊታቸው በጣም ተጠያቂዎች ይሆናሉ! ወገን ልብ በል፤ ከታሪክ ተማር!ጠላት መጥፎው የታሪክ ሂደት እንዲደገም ይሻል፤ የተዋሕዶ ክርስቲያኑ በረሃብ ተገርፎ፣ ወኔው፣ ሃሞትና ነፍጡ ሲኮላሽ ማየቱን በጣም ይመኘዋል፤ ጣቢያውም ይህን ማቅረቡ ያለምክኒያት አይደለም ፥ በደንብ ያውቁታል፤ መንፈሳውያን ኢትዮጵያውያንን በጦርነት ሳይሆን በረሃብ ብቻ ማንበርከክ እንደሚቻል አይተውታል።

_______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የአፄ ዮሐንስ እና የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 27, 2011


*ከማሞ ውድነህ*

የእስበሳችን ነገር ያለ ማክረሩ ነው የሚሻለው። ጠንካራ ክንድና ብርቱ ትኩረት የሚገባው ግን እንደ አዞ ከውሀ ውስጥ ብቅ የሚለው ነው (አሉላ አባነጋ)

አፄ ዮሐንስ ከጉራዕ ጦርነት በኋላ ሐማሴን ውስጥ ሰነባብተው ወደ ዐደዋ ከመመለሳቸው በፊት የሰሜን ኢትዮጵያ በር የተከበረና የታፈረም እንዲሆን ሲሉ ደጃዝማች ኃይሉ ተወልደ መድኅንና ራስ ባርያውን በገዥነት ሲሾሙ፡ ስመጥሩውን አዋጊያቸውን ሊጋባ አሉላን በራስነት ማዕረግ አስኮፍውሰና አስጊጠው ከመረብ ማዶ ያለውን አገር በጦር አበጋዝነት እንዲጠብቁ ሾሙዋቸው። ከዚያ በኋላም የአፄ ዮሐንስ ትልቁ የሥራ ምዕራፍ የኢትዮጵያን የውስጥ ጉዳይ ማደላደልና ማለሳለስ አንድነቷን ማጽናትና ሕዝቡ ፍትሕ አግኝቶ አርሶና ነግዶ እንዲተዳደር የማድረጉ ጉዳይ ነበር።

ይህን ዓላማቸውን ሊያደናቅፉባቸው እንደሚችሉ አሥግተዋቸው ከነበሩት ሁኔታዎችም ጋር መፋጠጡን ተያያዙት። በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የውስጡን ተቀናቃኝ ቀርቶ የውጭውንም ወራሪ ጠላት ከአንዴም ሁለቴ ኃያሉ ክንዳቸውን ስለአሳረፉበት ለጊዜው ረጭ ብሎላቸዋል። በምዕራብና በመካከል ኢትዮጵያም በኩል የቤገምድር የወሎና የጐጃም ሁኔታ ጋብ ብሎላቸዋል። የጥርጣሬና የሥጋት ትኩረታቸውን የሳበባቸው ግን ሸዋ ሆነ። የወጣትነት ጓደኛቸውና ምስጢረኛቸው ምኒልክ አፄተብለው ቁጥሩ እስከ ሰባ ሺህ በሚደርስ ሠራዊት ጐልብተው፡ ከሸዋም አልፈው ወሎንና ጐጃምን ለመደረብ ከሚያስፈራሩበት ደረጃ ላይ ወጥተዋል።

አፄ ዮሐንስ ግን፡ የምኒልክን ሁኔታ አንሥተው ከመኳንንቶቻቸውና ከጦር አበጋዞቻቸው ጋር በሚወያዩበት ሰዓት ሁሉ ደጋግመው የሚያነሡት ጉዳይ ነበራቸው።

ዋናው ሥጋቱና ችግሬ የሠራዊቱ ብዛት አይደለም። ለዚህ ለዚህስ እኔም ላቅ ያለ እንጅ ከእርሱ ዝቅ ያለ ሠራዊት የለኝም። ግን እንደዚያ ማሳያ እንደሚሉት የሰይጣን መልእክተኛ የመሰለ ፈረንጅ ከአጠገቡ አስቀምጦ፡ ከነሙንዚንገር ጋርም የሚያደርገው መላላክና መስማማት ነው።

ከዚያ ሌላ ደግሞ እነዚህ ሚሲዮኖችም በዚያ በኩል ገብተዋል፡. ዋናው ዓላማቸውም ምኒልክን አሳስተውና ጦር አስመዝዘው ከኔ ጋር ለማጋጨት መሆኑን አላጣሁትም። ግዴለም የማደርገውን ዐውቃለሁእያሉ ዛቻ አዘልና ትካዜለበስ አነጋገር ያሰሙ ነበር። እርግጥም ነው በዚያ ዘመን ፒዬር አርኖ የተባለ ፈረንሳዊ በዘይላ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ የምኒልክ ባለሟል ሆኖ የእርሳቸውንም መልእክት ይዞ ወደ ግብጽና ፈረንሣይ እየሔደ ዮሐንስን ለመጣል ትልቅ መሣሪያ ይሆናችኋልእያለ ያሽቃብጥ ነበር። ከእርሱም ሌላ ደግሞ በምሕጻረ ቃል አባ ማስያስእየተባለ የሚጠራው ሎሬንዞ ጉልየሞ ማሳያ የሚባለው የሮማ ካቶሊክ ሚሲዮን አባል በሸዋና በከፋ ውስጥ ድርጅቱን አቋቁሞ የምኒልክን ባለሟልነትም አትርፎ ከሚሲዮናዊነቱ ይልቅ በዲፕሎማቲክና በስለላው ሙያ ተሠማርቶ ዮሐንስንና ምኒልክን ለማራራቅና ለማጋጨት በመካከላቸው ገብቶ ነበር።

እነዚሁ ሁለቱ አውሮጳውያን የምኒልክን ጉልበት ከዮሐንስ ጉልበት የጠነከረ ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት ሲከታተሉት የነበሩት ዮሐንስም ክንዳቸውን በቀላሉ የማይታጠፍ ለማድረግና ምኒልክንም ለማስገበር ሲሉ የሠራዊታቸውን ቁጥር እስከ አንድ መቶ ሺህ ከአደረሱት በኋላ፥ ክዚሁ ውስጥ እስከ ዐርባ ሰባት ሺህ

የሚደርሰውን ልዩ ልዩ መሣሪያዎች አስታጠቁት። ከጉንደትና ጉራዕ ጦርነቶች የተገኘው ቀላል መካከለኛና ከባድ መሣሪያም የበላይነታቸውን ያረጋገጡበት ዋናው ትጥቃቸው ነበር።

ከመሣሪያው ጥራትና ብዛትም ሌላ በአጼ ተክለ ጊዮርጊስና በግብጾች ላይ ያገኙት ድል ዝናቸውንና ጥንካሬያቸውን አበሻ መሬት አውጥቶ በአፍሪቃ፡ በእስያና በአውሮጳ ውስጥ አስተጋብቶላቸው ነበር። በአሜሪካም ውስጥ ቢሆን፡ የኛ የጦር መኮንኖች ያዘመቱትን የግብጽን ጦር ድል ያደረገ ብርቱ ንጉሥየሚል ጸጸትለበስ ታዋቂነት አትሮላቸው ነበር።

ታዲያ እንደዚያ ሆኖ ስሙ የገነነ ሠራዊት ሸዋ የገባ እንደሆነ ሊያደርስ የሚችለውን ብርቱ ጉዳት አስቀድመው የተረዱትና የተጠነቀቁበት ከጐልማሳው ምኒልክ ይልቅ አዛውንቱ አጐታቸው ዳርጌ ንበሩ። ጉዳዩን በቀላሉ አትዩት፤ በየልቦናችሁ ምከሩበትና በእርቅ ይለቅሲሉ አዛውንቱ ጦር ጠማኝይሉ የንበሩት የምኒልክ የጦር አበጋዝ ግን፤

ወይ እሳቸው መጥተው፥ ያለዚያ እኛ ዘምተንባቸው ሳንሞካከር እንዴት አስቀድመን እንገብራለንእያሉ ምኒልክን ይወተዉቱ ነበር።

በዮሐንስ ቤተ መንግሥት እንደአባት ይታዩ የንበሩት ራስ አርአያም በበኩላቸው፤

የሁለት ወንድማማች ጠብ ማንን ጐድቶ ማንን ይጠቅም ይመስላችሁ? ኢትዮጵያን እኮ ነው የሚያዳክማት! ኢትዮጵያን እኮነው የሚያሳንሳት! ኢትዮጵያን እኮ ነው የጠላቶቿ መሳቂያ የሚያደርጋት! ታሪክ ይወቅሰናል፤ ትውልድ ያፍርብናል፤ ታቦትና መስቀል አስይዘን ካህናትን ወደ ምኒልክ እንስደድ እንጂ ጦር መምዘዙን አልስማማበትምእያሉ የእህታቸውን ልጅ ከነጦር አበጋዞቻቸው ይቆጡ ነበር።

 

 

Continue reading…AtseYohannesNegusMenilik

 

 

 

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: