Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Debre Tabor’

የተአምራትና የይቅርታ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል | አንቀጸ ምሕረት ቅ/ሚካኤል ደብረ ታቦር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 18, 2022

✞ በአክሱም ጽዮን ሳይቀቡ እራሳቸውን አላግባብ “አፄ ምንሊክ ፪ኛ”ብለው የሰየሙት ጋላማራ/ ኦሮማራ ዲቃላ ንጉስ፤ እግዚአብሔር አምላክ ያደረገላቸውን ውለታ ሁሉ በመርሳትና እግዚአብሔር የሚጠላቸውን ተግባራት ሁሉ በመፈጸማቸው ዛሬ የምናየውን እርጉም ትውልድ ለማፍራት በቅተዋል።

  • ☆ አፄ ምኒልክ መጀመሪያ ታላቁን ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስን በተንኮል አስገደሏቸው
  • ☆ አፄ ምኒልክ ጽዮናዊውን ወንድማማች ሕዝብን በመከፋፈልና ለባዕድ አሳልፈው በመስጠት “ትግራይ” እና “ኤርትራ የተሰኙትን ግዛቶች እንዲመሠረቱ አደረጉ።
  • ☆ ከዚህም እኵይ ተግባራቸው የተነሳ የትግራይና ኤርትራ ጽዮናውያን ካለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት እስከ ዛሬ ድረስ እየተጨፈጨፉ፣ በረሃብ እየተቆሉና ለጠላት ተላልፈው በመሸጥ ላይ ናቸው።
  • ☆ ዛሬ የምናያትንና ስጋ-አልባ የዶሮ ቅልጥም የምትመስለዋን “ትግራይ” የተባለችውን ግዛት ካርታ የፈጠሯት ጋላማራው ዲቃላ አፄ ምንሊክ መሆናቸውን ጽዮናውያን መገንዘብ ይኖርብናል።
  • ☆ ሻዕቢያና ሕወሓት የሚያውለበልቧቸው የኤርትራና ትግራይ ካርታዎች ጋላማራው አፄ ምንሊክ የሰጧቸውን ካርታዎች ነው።
  • ☆ ጋላ-ኦሮሞዎች፤ “ኢትዮጵያ የመቶ ሃምሳ/ሰላሳ ዓመት ታሪክ ነው ያላት” ሲሉን፤ “እኛ ጋላዎች ኢትዮጵያን ካፈረስናትና ጽዮናውያንን መጨፍጨፍና ማዋረድ ከጀመርን መቶ ሃምሳ/ሰላሳ ዓመታት ሆነውናል” ማለታቸው ነው። የአህዛብን ነገር ገልብጦ በተቃራኒው ማየት ተገቢ ነው። ሕወሓቶችም ይህን ማስተጋባታቸው የምንሊክ “ብሔር-ብሔረሰብ ተረት ተረት” ትውልድ አካላት መሆናቸውንም ያረጋግጥልናል።
  • ☆ እባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ፤ “የምንሊክ ልጆች” ሲል “አማራን” ማለቱ ሳይሆን “ዲቃላ ኦሮማራዎችን” ማለቱ ነው። አማራው በእልህ ከምንሊክ ጋር ሙጭጭ እንዲል። በምንሊክ ቦታ የራሱን ፎቶ የሰቀለውም ለዚህ ነው።

😈 እንግዲህ የጥፋትና የሞት ሥርዓተ አምልኮ ወደ ኢትዮጵያ የገባውና የዲያብሎስ ዙፋን በምድሪቱ ላይ የተተከለው ንጉሥ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዮሐንስን ገድለው ቤተ ክርስቲያንን እና ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ከበቁ በኋላ ነው ማለት ነው። አፄ ምኒልክ በአክሱም ጽዮን ያልተቀቡ ንጉሥ መሆናቸውን በድጋሚ ልብ እንበል።

👉 ከዚህም በመነሳት ከዋቄዮ-አላህ-አቴቴ የአህዛብ ባዕድ አምልኮ ጋር በቀጥታ የተያያዙትና ለዚህም ተጠያቂ የሆኑት አራቱ ትውልዶች እነዚህ ናቸው፦

  • ☆፩ኛ. የሻዕቢያ/ህወሓት/የኢሕአዴግ/ኦነግ/ቄሮ/ብልጽግና/ኢዜማ/አብን/ፋኖ ትውልድ
  • ☆፪ኛ. የደርግ መንግስቱ ኃይለ ማርያም ትውልድ
  • ☆፫ኛ. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትውልድ
  • ☆፬ኛ. የአፄ ምኒልክ/አቴቴ ጣይቱ ትውልድ

✞ ፪ኛይቱ የሙሴ ጸሎት [ዘዳግም ፴፪]

“እነርሱ ረከሱ፤ ልጆቹም አይደሉም፤ ነውርም አለባቸው፤ ጠማማና ገልበጥባጣ ትውልድ ናቸው። ደንቆሮ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው። የዱሮውን ዘመን አስብ፥ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ የአዳምን ልጆች በለየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቍጥር የአሕዛብን ድንበር አቆመ። የእግዚአብሔር እድል ፈንታ ሕዝቡ ነው፤ ያዕቆብም የርስቱ ገምድ ነው። በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።

ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ በክንፎቹም አዘላቸው። እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም። በምድር ከፍታ ላይ አወጣው፤ የእርሻውን ፍሬ በላ፤ ከዓለትም ድንጋይ በሚገኝ ማር፥ ከጭንጫውም ድንጋይ በሚገኝ ዘይት አጠባው፤ የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውም ወተት፥ ከጠቦት ስብ ጋር፥ የባሳንንም አውራ በግ፥ ፍየሉንም፥ ከስንዴ እሸት ጋር በላህ፤ ከወይኑም ደም ያለውን ጠጅ ጠጣህ። ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ የፈጠረውንም እግዚአብሔርን ተወ፤ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ። በሌሎች አማልክት አስቀኑት፥ በርኵሰታቸውም አስቈጡት። እግዚአብሔር ላልሆኑ አጋንንት፥ ለማያውቋቸውም አማልክት፥ በቅርብ ጊዜ ለተነሡ ለአዲሶች አባቶቻቸውም ላልፈሩአቸው አማልክት ሠዉ። የወለደህን አምላክ ተውህ፥ ያሳደገህን እግዚአብሔርን ረሳህ። ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ስላስቈጡት እግዚአብሔር አይቶ ጣላቸው። እርሱም አለ። ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፤ ፍጻሜያቸው ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፥ ያልታመኑም ልጆች ናቸው። አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ ፫ ቍ.፲፭፤ በዕብራይስጥ ይሹሩን የሚለውን ግዕዙ ያዕቆብ ይለዋል። በምናምንቴዎቻቸውም አስቈጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ። እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፥ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፥ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች። መከራን እጨምርባቸዋለሁ፤ በፍላጾቼም እወጋቸዋለሁ።”

ይህ ከብዙ ዘመናት በፊት የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የተለዩና የተቀደሱ ተብለው የእርሱን ስምና ክብር የወረሱበት የህይወት ህግና ሥርዓት አሁን ላለን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የሚያስተላልፍልን መለኮታዊ ሀሳብ፤ እግዚአብሔር አምላክ እንደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ኢትዮጵያውያንንም የ”እኔ” ብሎ “ልጆቼ” ያላቸው በምድር አፈር በኩል በተግለጠው ህግና ሥርዓት በኩል ነበር።

ኢትዮጵያውያን ልክ እንደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ይህን “እግዚአብሔር” ብለው የወረሱትን የተፈጥሮ ህግ ካፈረሱና ከጣሱ እንዲሁም ለእነርሱ ያልሆኑት የአህዛብን አማልክት በምድሪቱ ውስጥ ሲያጥኑና ሲያመልኩ ከተገኙ እነርሱም ለእስራኤል ልጆች እንደተነገራቸው ቃል ሁሉ በሞትና በባርነት ፍርድ ከተቀደሰችው ምድር ይነቀላሉ። እግዚአብሔር አምላክ የእስራኤልን ልጆች በተናገረበት ቃል ሁሉ ደግሞ ኢትዮጵያውያንን ተናግሯልና።

በዚህም መለኮታዊ ቃል መጠን የተገለጠውና ለተቀደሰችው ምድር ለኢትዮጵያ ጥፋትና ሞት የሆነው ትውልድ ደግሞ የአፄ ምኒልክ ትውልድ ይሆናል ማለት ነው። ለዚህ ታላቅ የሕይወትና የነጻነት የበረከትና የገዥነት ኪዳን መፍረስ ዋናው ተጠያቂው ይህ ደካማ ትውልድ ነው። ያን ታላቅና ሊነገር የማይችል ፅኑ ፍቅር በብዙ ተዓምራቶችና በብዙ ድንቆች ያየና የተመለከተ ህዝብ ነው ያን የሕይወት ኪዳን ሽሮ የሊሎችን/የአህዛብን አማልክት ለመተልና ለማምለክ ወደ ኋላው የተመለሰው። የአድዋ የነፃነት ተጋድሎ ብቻ ስለዚህ የህወትና የነጻነት የገዥነትና የበረከት ኪዳን ኃይልና ስልጣን እጅግ ብዙ ነገር ነበረው። አሸናፊ፣ አዳኝ፣ ገዥ እንዳልሆነ በዚያም የጥፋ ህግ ምንም ዓይነት በረከትም ይሁን የነጻነትና ህይወት እንደሌለ እግዚአብሔር አምላክ ሊዋሽ በማይችል ምስክር በዓለም ሁሉ ፊት በምድርና በሰማይ በዚህ ህዝብ ላይ አስመስሮበታል። ይሁን እንጅ ለመመለስ የተጸጸተ ትውልድ አልነበረም።

በኢትዮጵያ ታሪክ ባልታየውና እጅት ታላቅ በተባለለት በዛ ጽኑ የረሀብ ዘመን ኢትዮጵያውያን የሚላስና የሚቀመስ አጥተው ሲቅበዘበዙ ምግብና መጠጥ ሆኖ ያዳናቸውን፣ በምድረ በዳም ተዘግተው በቅኝ ግዛት ሊገዛቸው በፊታቸው ከተገለጠው እጅግ አስፈሪ የሞትና የጥፋት መንግስት የተነሳ የሚታደጋቸው አንድ ሰው አጥተው በሞት ፍርሀት ታስረው ሲታወኩና ሲጨነቁ ሳሉ በሚደነቅ ምህረት በብዙ ፍቅር በመካከላቸው ተገኝቶ ያጽናናቸውን፣ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ በእጅጉ የተደራጀውን በወታደራዊ ዕውቀትና ጥበብም የተካነውንና ሊሸነፍ አይችልም የተባለውን ግዙፉን የኢጣልያንን ጦር በተዘረጋች ክንድ በበረታችም እጅግ ፅኑ እጅ ስብርብሩን አውጥቶ በፊታቸው ያባረረላቸውን፣ ገዳዩን ገድሎ፣ አሳሪውን አስሮ ፣ አጥፊውን አጥፍቶ ፣ በዓለም ሁሉ ላይ እጅግ የገነነውን ሁሉን ገዥ ስምና ክብር የሰጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ የሰራዊት ሁሉ ጌታ እግዚአብሔርን ያ ትውልድ በአይኑ አይቷል፤ ተመልክቷልም። ኢትዮጵያውያንም ብቻ ሳይሆኑ ዓለም ሁሉ አይቶታል ተመልክቶታል። ያ የእግዚአብሔር ድንቅ ፍቅር የቀመሰ ትውልድ ነው እንግዲህ የእግዚአብሔርን ኪዳን አፍርሶ ለእርሱ ላልሆኑ ለአህዛብ አማልክት ሊያጥንና ሊሰግድ ራሱን ለሞትና ለባርነት አሳልፎ የሰጠው። ምንም እንኳ በተደጋጋሚ ቢናገራቸውም መልሰው ለኃጢአት ባሪያ እንደሚሆኑት እንደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ኢትዮጵያውያንም የእግዚአብሔርን እጅግ ታላቅ ውለታና ፍቅር ረስተውና አቅልለው በፊቱ ታላቅ ርኩሰትን አደረጉ።

የእግዚአብሔር ቃል ለዚህ ታላቅ ቅሌትና አመጻ ተጠያቂ ያደረገው ደግሞ በዋናነት “ይሹሩን” በማለት የገለጸውን በዚያ ህዝብና መንግስት ላይ ኃይልና ስልጣን ያላውን አለቃ ወይም መሪ ነው። ይሹሩን በማለት ሙሴ የገለጸው በእርግጥ ለአስራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል አባትና አለቃ የሆነውን ያዕቆብን ነው። አስራ ሁለቱ ነገዶች እንደመንግስታን እንደ ሀገር የተመሰረቱት በአባታቸው በያዕቆብ እስራኤል በሚለው ስምና ክብር ነበርና። ይሹሩን የያዕቆብ ሌላው ስም ነው። እንደ ሙሴ አገላለጽም ይሁን እንደ ህጉ አንድ ለእግዚአብሔር ስምና ክብር የተመረጠ ህዝብ ለጥፋት በሚሆን የሞትና የባርነት ህግ የሚያዘው በዚያ ህዝብ ላይ ኃይልና ስልጣን ባለው አንድ ሰው አለመታዘዝ ምክኒያት ነው። የዛ ህዝብ ማንነትና ምንነት በመሪው ማንነትና ምንነት የሚገለጽ ስለሆነ የመሪው ጥፋት ማለት በሌላ አባባል የዚያ ትውልድ/ህዝብ ጥፋት ማለት ይሆናል። ልክ ዛሬ እንደምናየው!

ለተቀደሰችው ምድር ርኩሰት፣ ለታላቋና ለገናናዋ ሀገር ለኢትዮጵያ ጥፋትና ውድቀት በዋናነት ተጠያቂ የሚሆኑት በእግዚአብሔር ስምና ክብር ተመርጠው “ሞዓ አንበሳ እም ዘነገደ ይሁዳ ምኒልክ ስዩመ እግዚአብሔር ንጉሰ ነገስት ዘ-ኢትዮጵያ” ተብለው የነገሱት አፄ ምኒልክ ናቸው። (ልብ እንበል! አፄ ምኒልክ በአክሱም ጽዮን ተቀብተው ያልነገሱ ብቸኛው የኢትዮጵያ ንጉሥ ናቸው)። አፄ ምኒልክ ከአደዋው ድል በኋላ ለድሉ ያበቃቸውን አምላካቸውንና ጽዮን ማርያምን በመካድ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸውን የህይወት ኪዳን አፍርሰው የጥፋትና የሞት የባርነት አማልክት ማንነትና ምንነት በመትከላቸው ለኢትዮጵያ ጥፋትንና ውድቀትን አስከትለዋል። ውጤቱን ዛሬ እያየነው እኮ ነው!

ጥልቅ በሆነ የጸሎት ጊዜ ውስጥ የሚገኝ ወገን ሁሉ ጋላ-ኦሮሞዎች ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት በጽዮናዊው ሕዝባችን ላይ የሠሩትን ግፍና በደል ጭንቅላቱ ውስጥ በተነቀሳቃሽ ምስል መልክ ማየት ይችላል። እንኳን የዛሬውን ቀርቶ የቀደሙት አባቶቻችንና እናቶቻችንን ስቃይ፣ ሰቆቃና ጩኸት እንደ ደወል መስማት ይችላል። ወገኔ ሆይ፤ ዲቃላ የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው ዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስን አምላኪዎቹ ጋላ-ኦሮሞዎችና ጋላማራዎች በሕዝቤ ላይ ከምንገምተው በላይ አስከፊ የሆነ ግፍና ወንጀል ነው የፈጸሙበት በመፈጸም ላይ ያሉት።

😇 ፈጣኑ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ አስቀድሞ የተጣላህን በቀል ባለመርሳት ጋሻህን በቶሎ አንሣ። ፈጣኑ መልአክ ሆይ ነበልባላዊ ሰይፍህን በጠላታችን በዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ ላይ መዘህ ተነሣሣበት።

😇 ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ ከሰማያት በግርማ ወርደህ አሸባሪውን ዲቃላ አብዮት አህመድ አሊን እና ጭፍሮቹን ባፋጣኝና በአንዲት ሌሊት በእሳት ሰይፉ ፈጅተኻቸው እደር።

😇 ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ ጋላ-ኦሮሞ-አማሌቅ ጠላቶቻችንና ዋቄዮ-አላህ-ሰይጣን አምላካቸውን በሰይፉ ቆራርጦ ከእግራችን ስር ይጣልልን!

😇 የገናናው መልአክ የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃው አይለየን፣ በጸሎቱ ይማረን።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጅራፍ፣ ችቦ & ሙልሙል | እንኳን ለ በዓለ ደብረ ታቦር(ቡሄ)በሰላም አደረሰን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 18, 2018

የደብረ ታቦር ምሳሌነት

የወንጌል ምሳሌ ነው፡፡ ተራራ ሲወጡ በጣም ያስቸግራል፤ ከብዙ ድካምና ውጣ ውረድ በኋላ ተራራውን ጨርሰው ከላይ ሲወጡ ግን አባጣ ጎባጣውን ሜዳና ገደሉን ያሳያል፡፡ ወንጌልንም በሚገባ ከተማሯት ጽድቅን ከኃጢአት ለይተን እንድናውቅ ታደርገናለች፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በደብረ ታቦር ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታል፡፡ ተራራ መሠረቱ ከመሬት አናቱ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ፤ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ራሷ በሰማይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹እኛስ ሀገራችን በሰማይ ነውና›› እንዲል /ፊልጵ. 320/፡፡

የደብረ ታቦር ተራራ ይህን ሁሉ ምስጢር የያዘ በመሆኑ በክርስትና ታሪክ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮት የተገለጠበት፣ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው፤ በምእመናንም ዘንድ ቡሔ ይባላል፡፡ የቡሔ በዓል ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ የያዘ በመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ልናከብረው ይገባናል፡፡

ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡

ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፤ የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡

ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር ይዞ የሚከወን ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፣ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡

የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡

ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ የት መጣ ግን በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ ምሳሌ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡

ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ቡሄ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡ ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

ምንጭ

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ብሩክ ቡሄ / Happy Buhe

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 20, 2016

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: