Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2023
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘Challenges’

በሣር መካከል ያለች ውብ አበባ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 16, 2012

ዮሐንስና ቤተሰቦቹ ወደ አዲሱ ቤታቸው በመግባታቸውና በአካባቢው አቀማመጥ ለጥቂት ጊዜ ለመደመም የቤታቸው ፎቅ ላይ በመውጣታቸው ተደስተዋል።

ዮሐንስ ከልጁ ከሰምዖን ጋር ሲጨዋወት ከቆየ በኋላ “ለረዥም ዓመታት እንክብካቤ ያላገኘውን ይህ ሣር ምንድር ነው የምናደርገው?” በማለት ጠየቀው።

“የአትክልት ቦታውን ለማስዋብና ጥቂት አበቦች ለመትከል የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ።”

“ተመልከት ስምዖን፤ በሣሩ መካከል አንዲት ውብ ነጭ አበባ አለች።

“የታለች?”

“በስተቀኝ በኩል ከጎረቤታችን አጥር ወደ እኛ አንድ ሜትር ገባ ብላ አድጋለች።” አለ ዮሐንስ።

“በዚህ ሁሉ ሣር መካከል ማንም ሊመለከታት አይችልም። በጣም ውብ አበባ ናት። አበባዋ ብቸኛ አበባ ስለ ሆነች መጀመሪያ የምወስደው እርሷን ነው።”

ስምዖን በስተቀኝ በኩል ወዳለው የአትክልት ቦታ ሄደ። ይሁ እንጂ ሣሩ ረዣዥም ስለ ነበር አበባዋን ሊያገኛት አልቻለም። አባቱ ወደ ፎቁ እንዲወጣ ሲያደርገው ግን አገኛት። ይህችን የመሰለች ውብ አበባ በማግኘቱም ተደነቀ፡ ተደሰተ። ያደገችው በጎረቤታቸው የአትክልት ቦታ ውስጥ ሊሆን ይችላል ብሎም አሰበ።

“ይህችን የመሰለች ውብ አበባ በዚህ ረዣዥም ሣር መካከል ማግኘት ምንኛ ድንቅ ነገር ነው!”

“ስምዖን፤ እነዚህ አበቦች እኮ እግዚአብሔር የሚንከባከባቸውና ሥሮቻቸውን እስከ ሰማያት ድረስ የዘረጉ የአማኞች ነፍሳት ናቸው። እውነተኛ ክርስቲያን እግሮቹ በዚይ ዓለም ላይ ተተክለው የእግዚአብሔርን ሕልውና የሚናጸባርቅ አበባ ቢተክልም ሥሩን የሚሰድደው ወደ ሰማያት ነው። ለዚህ ነው አበባዋ ውብ የሆነችው” አለ ዮሐንስ

“…በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤ ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን።” (2ኛ ቆሮ 2:15-16)

መላው ዓለም በሣር ቢሸፈንም እንኳ በመካከሉ ውብ አበባ ለመኖሩ እርግጠኛ ነኝ።

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፦ አንተ በእያንዳንዱ ትውልድ ውስጥ ምክር አለህ።

ጌታዬ ሆይ፦ በሣር መካከል የበቀልሁ አበባ እሆን ዘንድ አድለኝ። ይህን  ካደረግህልኝ “

በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፤ እንዲሁ ወዳጄ በቆነጃጅት መካከል ናት።

እንደ ዱር እንኮይ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው።” (መኃ. 2:2-3) የሚለው ጣፋጭ ድምፅህን እሰማለሁና።

__

ኅዘን

በ ዲ/ን የሺጥላ ሞገስ

 • በግዴታ ማዘንና

 • በፈቃድ ማዘን

ኅዘን የሰው ልጅ አካላዊና ስሜታዊ ጉዳት ሲደርስበት እና ስቃዩ ሲገነፍል የሚከተል ክስተት ነው። በሁለተኛ ትርጉሙ ሰው ራሱን ከጠፋበት ሲያገኝ ያለበት ቦታ ትክክለኛ አለመሆኑን ሲገነዘብ የጥፋተኝነት ስሜት የተሰማውን ሕሊናውን ለማጠብና ለማሳረፍ በፈቃዱ በውስጡ የሚፈጥረው ለተሰማው የበደለኝነትና የጥፋተኝነት ስሜት የሚከፍለው ካሣ የፈቃድ ኅዘን የምንለው ነው።

በሰው ልጅ ሕይወት ላይ ከሚደርሱ ችግሮች አንዱ እና ከባዱ ኅዘን ነው። ኅዘን ውስጣዊ ስሜታችንን የሚቀጠቅጥና የሚያደቅ መዶሻ ነው። በእርግጥ ማናቸውም ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች የሚመሩን ወደ ሀዘን ነው። ይሁ እንጂ እያንዳንዳችን ላይ የሚደርስብን ኅዘን የስሜት ደረጃ ይለያይ ይሆናል። የግዴታ ኅዘን የምንለው ግን የጭንቀት መነሾ ወይም መበቀያ ሥር የምንለው ነው።

በግዴታ ማዘን

የኹከትና የጭንቀት መነሻ የምንለው እንዲህ ዓይነቱን ኅዘን ነው። በግዴታ እንድናዝን የምንገደድበትን አጋጣም የሚከስተውን ኅዘን። ይህ እንዴትና መቼ እንደሚገጥመን አስቀድሞ መገመት አይቻልም። ስለዚህ የሚከሰተውን ኅዘን ተቀብሎ ለማስተናገድ በቂ የመንፈስ ዝግጅት ላናደርግ ስለምንችል ኅዘናችንን ከባድና የጭንቀት መብቀያ ሥር ሆኖ በሕይወታችን ሊተከል ይችላል።

በክርስቶስ ሆኖ ብዙ የዚህን ዓለም ነገር ንቆ መኖር የዚህ ዓይነተኛ መፍትሔ ሲሆን በተጨማሪ የደረሰብን ኅዘን ሥር እንዳይሰድ የኅዘናችንን መፍትሔ እንጂ የኅዘናችንን ምክንያት አለማውጠንጠን ተገቢ ነው። እንዲሁም ኅዘናችንን እንዳንረሳ ዙሪያውን ከሚያራግቡ ነገሮች አጥብቆ መሸሽ ወይም እነዚያን ነገሮች ማራቅ ትልቅ እረፍት ይሰጣል።

በአንድ ወቅት አንዲት ሴት የንግድ ቦታዋ በእሳት አደጋ ወደመባት። ይህች ሴት የአንድ ልጅ እናት ስትሆን፡ አነስተኛ የንግድ ቦታ ነበራት። በእሳት አደጋ ከወደመባት በኋላ በከፍተኛ ኅዘን ተመታች። በአካባቢዋ ያሉና ጥቂት ዘመዶቿ እርሷን ለማቋቋም ያደረጉላት ዕርዳታ ከወደመው አምስት እጅ ሁለት እጅ እንኳ አይሆንም።

ስለዚህ ለዓመታት ያህል ጊዜ ታዝንና መጽናናትንም እንቢ አለች። ብስጭት፣ ጭንቀት፣ ለብቻ ማውራት የየዕለት ሥራዋ አደረገችው።

ከተወሰኑ ጊዜ በኋላ አንድ ልጇን አንጠልጥላ መንገድ ለመንገድ መዞርና ከማኅበረሰቡ ተገሎ ለመኖር ተገደደች።

ከዚህ ታሪክ የምንማረው ኅዘን በሕይወታችን ሥር እንዲሰድና በኋላም ጭንቀትን እንዲያበቅል እድል ላለመስጠት ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረግና መስዋዕትነት መክፈል እንደሚጠበቅብን እና ሁሉ በክርስቶስ ከንቱ ማድረግ እንደሚገባት ነው።

በእርግጥም በዚህ ዓለም ሁሉ ነገር ከንቱ ነው። አንድስ እንኳ ከእኛ ጋር ለዘላለም አይኖርም። ኅዘንም ቢሆን እንኳ።

“ከንቱ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል፡ ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድን ነው? ትውልድ ይሔዳል ትውልድ ይመጣል” (መ.መክ. 1:2)

__

Posted in Ethiopia, Life | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: