Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • March 2023
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘Calendar’

ኢየሱስ ክርስቶስ – መስቀል – ኮሮና – የፀሐይ ግርዶሽ – ላሊበላ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 21, 2020

👉 ነጥብጣቦቹን እናገናኛቸው

🌑 ኢየሱስ ክርስቶስ

🌑 መስቀል

🌑 አክሊል(Corona/ኮሮና)(ወታደሮችም ከእሾህ አክሊል ጐንጕነው በኢየሱሰ ራሰ ላይ አኖሩ)

🌑 ዓለት (ያም ዓለት ክርስቶስ ነበረ)

🌑 የላሊበላ ውቅር አብያተክርስትያናት በአፄ ላሊበላ ዘመን አለት(ድንጋይ)ተፈልፍለው የተሠሩ

🌑 የንጉሥ ላሊበላ የልደት ቀን (በጊታቸን የልደት ቀን ተወለዱ)

🌑 የፀሐይ ግርዶሽ

🌑 የኢትዮጵያ ዓመት ፪ሺ፲፪ ዓ.

🌑 የማያዎች የቀን መቁጠሪያ 2012 ዓ.ም

ድንቅ ድንቅ በጣም ድንቅ የሆነ ዘመን ላይ ነን። ግን እያየን ነው የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ (አህዛብ፣ መናፍቃን፣ ግብረሰዶማውያኑ፣ እነ ግራኝ አብዮት አህመድና የፈረንሳዩ ኢማኑኤል(አማኑኤል የሚል ስም ይዟል)ለላሊበላ የተለየ ትኩረት መስጠታቸው?

የፀሐይ ግርዶሹ የተከሰተበት ዕለት ልክ የዛሬ ዓመት ላይ ገዳይ አብይ የላሊበላን ልጅ ጄነራል አሳምነውንና ሌሎቹን ኢትዮጵያውያን ጄነራሎችን ለመግደል ከተዘጋጀበት ዕለት ጋር ተገጣጥሟል። ዘንድሮ ግን ጥይት ሳይተኩስ ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን በኮሮና ገድሎ ለመጨረስ ወስኗል። በኮሮና ሞተለሚባለው ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሞት የአብይ አህመድ አሊ እጅ አለበት(ዘር ማንዘሩ ይነቀል! ይጥፋ!)

____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ብዙዎችን ያስደነቀው የፀሐይ ግርዶሽ | ላሊበላ ነገሠ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 21, 2020

_________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መላው ዓለም የኢትዮጵያ ካላንደር ነው ትክክለኛው፤ ቅዳሜ ለ፲፮ ሰዓት እንፁም እያለ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 18, 2020

 • 👉 በመጨው እሑድ አሮጌው ዘመን ይፈጸማል፤ ኋለኛው ዘመን በአዲሱ ዘመን ይተካል
 • 👉 በ ፪ሺ፲፪ (2012) .ም ምድራችንን ከባባድ ፈተናዎች ገጥመዋታል

ምድራችን በእኛ አቆጣጠር በ ፪ሺ፲፪ (2012) .. በፈረንጆቹ 2020 .. ላይ በከባድ ፈተናዎች ውስጥ እያለፈች ነው። እጅግ ጥንታዊው ከ1200 ዓመታት በፊት የነበረው የማያ የዘመን ቀመር ዐዲስ ያልተለመደ ክስተት የሚጀምርበት ዑደቱ የሚጠናቀቅበት የተፈጥሮ አደጋዎች በዝተው የሚታዩበት 2012 ላይ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ብዙ ዓለም ዐቀፍ ተመራማሪዎች በፈረንጆቹ 2012 ላይ መስሏቸው ብዙ አስተያየት በጊዜው ሲሰጡ ቆይተው ነበር። 2012 የሚል አስፈሪ ፊልም ከማያ የዘመን ቀመር በመነሣት የፈረንጆቹ ፪ሺ፲፪ (2012) ከመድረሱ ፫/ 3 ዓመት ቀድሞ በ2009 ላይ በሆሊውድ ተሠርቶ በሮናልድ ኤመሪክ ዳይሬክት ተደርጎ ሁላችንም ተመልክተነዋል።

በፈረንጆቹ ፪ሺ፲፪ (2012) /ሚ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሦስት አፍሪቃውያን መሪዎች አርፈዋል/ተገድለዋል፤ ሆኖም ሌሎች ብዙ ክስተቶች ሳይከሠቱ የእኛው ፪ሺ፲፪ (2012) .ም ላይ እንገኛለን። ፪ሺ፲፪ (2012) ዓመት ግን ገና ከመጀመሩ ለዓለማችን በጣም አስደንጋጭ ነበር። በዚህ ዓመት በመላው ዓለም ኮሮናን ጨምሮ በርካታ አስደንጋጭና አስደናቂ ነገሮች በመታየት ላይ ናቸው።

በመጭው እሑድ ሰኔ ፲፬ / ፪ሺ፲፪ (14/2012 .) June 21 – 2020

ከኢትዮጵያውያን ጋር ዝምድና ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የሚነገርላቸው የአሜሪካዎቹ ማያዎች አሮጌው ዘመን ይፈጸማል፤ ኋለኛው ዘመን በአዲሱ ዘመን ይተካልይላሉ።

👉 ሰኔ ፲፬ / ፪ሹ፲፪ (14/2012 .) አቡነ አረጋዊ

ሁሉም ነገር ከኢትዮጵያ ቀመርና ከመጭው የፀሐይ ግርዶሽ ጋር መገጣጠሙ የሚገርም ነው።

🌑 ፪ሹ፲፪ /2012 .ም ግርዶሽ የሚታየው፡

 • ሰኔ ፲፬ / ፪ሺ፲፪ (14/2012 .) June 21 – 2020
 • በግርዶሹ 600 ሰዓት የሚፈጅ ጨለማ ይታያል፡፡
 • በመላ ኢትዮጵያ ይታያል፡፡
 • በተለይ ወለጋ፣ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ አላማጣ፣ ኢንጂባራ 98% ጨለማ ሆኖ ይታያል፡፡
 • የዓለምን አሰራር የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካን፣ የከፍተኛ የተፈጥሮ ኃይል ሊገኝ ይችላል ብለው ሳንቲስቶች ሀሳባቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡
 • ከምዕራብ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ ግርዶሹ ይታያል፡፡
 • ፀሐይ 98% ትሸፈናለች፡፡

🌑 የሚታይበት እና የሚያበቃበት፡

ከማዕከላዊ አፍሪካ ከኮንጎ ይነሳል፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ የመን፣ ፓኪስታን፣ ታይዋን፣ ንድና ቻይናን አቋርጦ ፓስፊክ ውቂያኖስ ላይ ያበቃል፡፡

🌑 ሙሉ ግርዶሹ የሚታይበት ወቅት

 • ከሌሊቱ ሰኔ 14/2012፲፬ / ፪ሺ፲፪ (14/2012 .) June 21 – 2020 .
 • – 1100 ሰዓት ይጀምራል፣
 • ከጠዋቱ 1245 እስከ ቀኑ 633

👉 ማስጠንቀቂያ፡

 • በዓይን ለማየት አይቻልም ዐይን ያሳውራል፣
 • በሱቅ ውስጥ የሚሸጥ መነጽር መጠቀም አይገባም፡፡
 • ለፀሐይ ግርዶሽ ተብሎ የተዘጋጀ መነጽር አለ፡፡
 • መነጽሩ አገር ውሰጥ አይገኝም፡፡
 • ለፀሀይ ግርዶሽ የሚሆን መነፀር አለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ጥንቃቄ ያድርጉ
 • ሲጨልም ማየት እንችላለን ነገር ግን ያለመነጽር ለማየት አንሞክር፣በጣም ጥንቃቄ ሊታከልበት ይገባል
 • ዐይናችን ሊፈስ ይችላል

የነገ ሰው ይበለን!

_______________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ትክክለኛው የዘመን አቆጣጠር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 31, 2010

 • ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ከሚለው የንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ መጽሐፍ የተወሰደ

በአረማዊነት ባህል፡ በክዋክብት ሥነ እውቀት ላይ የተመሠረተው የምዕራባውያን የዘመን አቆጣጠር፡ ከኢትዮጵያውያኑ የዘመን አቆጣጠር፡ የሚለይበት ባሕርይና አኹን ያለበት ቀውስ የደረሰበት ለምን ይሆን?

ኢትዮጵያውያን፡ በቅዱሱ ኪዳን ሃይማኖታቸው ላይ የመሠረቱትን፡ ይህን የጊዜ አቆጣጠር ሥርዓት፡ ምዕራባውያን፡ ኦርቶዶክሳውያን የተባሉት አብያተ ክርስቲያናት ጭምር፡ በአረማዊው፡ ዮልየስ ቄሣርና ጎርጎርዮስ (ግሬጎሪ) ፩፫ኛ በተባለው፡ በካቶሊካዊው ጳጳስ ስሞች እየሠየሙ፥ በየጊዜው እየለዋወጡና በመጨረሻ፡ ፰ ዓመታት ከ፲ ቀናት ያህል አክለውበት መቆየታቸው ይታወቃል። በዚህ የአቆጣጠራቸው ስልት፡ የጌታችን የኢያሱስ ክርስቶስን የልደት ቀን፡ ከ፬ እስከ፯ ዓመታት ለሚደርስ ዘመን፡ ከፍ አድርገው እንዲጨምሩ በመገደዳቸው፡ ይህን፡ ሰው ሠራሽ ቀውስ አስተካክለው ለማስታረቅ አቅቷቸው፡ እነሆ፡ እስካሁን ሲባዝኑ ይገኛሉ። በዚህ፡ በእነርሱው አቆጣጠር፥ ጌታ፡ የተወለደው፡ በ፬፥ በ፮ ዓመተ ምሕረት ላይ ሳይኾን አይቀርምከማለት በስተቀር፡ እርግጠኛውን ቀን፡ በቁርጥ ሊወስኑ ሳይቻላቸው ቀርቷል።

ይህ ቀውስ የተፈጠረባቸው፡ የጌታን የልደት ዓመት፡ አንድ ብለው መቁጠር ከጀመሩ በኋላ፡ ያ፡ የዓመተ ምሕረት መነሻ ዘመን፡ በአረማዊነት ዘመናቸው፡ ጁልያንበሚል ስምና በተለያየ ስልት ይጠቀሙበት በነበረው የአቆጣጠር ሥርዓታቸው፡ በ፬፥ በ፯ ዓመታት ላይ ውሎ ስላገኙት ነው።

ሌላው፡ ይህን ችግር የፈጠረባቸው ምክንያት፡ የምዕራባውያን የጊዜ አቈጣጠር፡ እንደ ኢትዮጵያውያኑ፡ በአንድ መሠረት ላይ ታንጾና በአንድ በተስተካከለ ሥርዓት ተቀምሮ የሚመራ ባለመኾኑ ነው። ይህንም፡ ከዚህ የሚከተለውን ማነጻጸሪያ ሓተታ በመመልከት መረዳት ይቻላል።

ኢትዮጵያውያን፡ የእግዚአብሔር ገነትተተከለባት፡ አዳምና ሔዋን የተፈጠሩባት አገራቸው የምትገኘው፡ በምድር ማዕከል ወይም መቀነት ክልል ውስጥ ስለኾነ፡ የጊዜ አቈጣጠራቸው ሥርዓት፡ መዓልቷና ሌሊቷ፡ ዓመቱን ሙሉ፡ በ፲፪፡ በ፲፪ ሰዓታት፡ እኩል በተከፈለበት የአሠፋፈር ስልት ላይ ተመሥርቶ፡ የባሕረ ሓሳቡ ቅመራ፡ ሥርዓቱን ጠብቆ፡ ያለችግር ይካኼዳል። ይኽውም፡ ወደኋላ፡ ወደረቂቃኑ ሳንኼድ፡ ከሣልሲት ተነሥተን፡ እስከ ዓመት ብንቈጥር እንኳ፡ ቀመሩ፡ የተስተካከለ ኾኖ እናገኘዋለን። ማለትም፡ ፷ (ስድሳ) ሣልሲታት፡ ፩ (አንድ) ካልዕት (second)፥ ፷ ካልዕታት፡ ፩ ደቂቃ፥ ፷ ደቂቃት፡ ፩ ሰዓት፡ ፳፬ ሰዓታት፡ ወይም ፷ ኬክሮስ፡ ፩ ዕለት፡ ፩፪ ሰዓታትን የያዘው፡ የብርሃን ጊዜ፡ መዓልት፥ ጨረቃ እንድትሠለጥንበት የተፈጠረችበት፡ ፩፪ ሰዓታትን የያዘው፡ የጨለማ ጊዜ፡ ሌሊትይባላል።

የመዓልቱ የጊዜ አቆጣጠር፡ የተፈጥሮውን ሥርዓት በመከተል፡ ከቀትር በፊትእና ከቀትር በኋላተብሎ፡ ፀሓይ፡ ጮራዋን በምትፈነጥቅበት፡ በንጋቱ ፩ ሰዓት ይጀምርና፡ በምትጠልቅበት፡ በምሽቱ ፲፪ ሰዓት ያበቃል፡ የሌሊቱም ጊዜ፡ እንደዚሁ፡ እስከእኩለ ሌሊት ድረስ፡ ከማታው፥ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ደግሞ፡ ከሌሊቱእየተባለ፡ ጨረቃ ከምትታይበት፡ ወይም ጨለማው ከሚጀምርበት፡ ከምሽቱ፡ ፩ ሰዓት ይነሣና፡ ጎህ በሚቀድድበት፡ በንጋቱ ፲፪ ሰዓት ይቆማል።

በዚህ መሠረት የተደለደለችው፡ አንዲቱ ዕለት፡ ሰባት ስትኾን፡ ፯ቱ ዕለታት፡ ፩ ሳምንት ይኾናሉ።

የምዕራብውያኑ ግን፡ እንዲህ አይደለም። ምዕራባውያን፡ የሰሜኑንና የደቡብን የመሬት ዋልታ ተከትለው፡ በሰሜንና በደቡብ ክፍላተ ዓለማት፡ የሚኖሩ በመኾናቸው፡ ኢትዮጵያውያን፡ ክረምት፥ መፀው፥ በጋ፥ ጸደይ እንደሚሉት፡ የእነርሱም ዓመት፡ Winter(ዊንተር) Spring (ስፕሪንግ) Summer (ሰመር) Autumn (ኦተምን) በተባሉ፡ በአራት የተለያዩ ወራት ተከፋፍሎ፡ በክረምቱ፡ ሌሊታቸው፡ እስከ ፭ ሰዓታት የሚጨምርበት፥ እንዲያውም፡ ወደሰሜኑም ኾነ ወደ ደቡቡ የመሬት ዋልታ ጫፍ እይተጠጉ በኼዱ መጠን፡ የሚቀነሱት፡ ወይም የሚጨመሩት ሰዓታት እያደጉ ይኼዱና፡ ወደ መጨረሻው ጽንፍ ላይ ሲደርስ፡ ከናካቴው፡ ፮ ወራት ሙሉ፡ ሌሊት ብቻ፥ ወይም መዓልት ብቻ ይኾናል።

ይህም ማለት፡ ይህ ኹኔታ፡ በሰሜኑና በደቡቡ ክፍላተ ዓለም፡ በዓመቱ ውስጥ፡ እንዲህ ስለሚፈራረቅ፡ የክረምቱ ብርዳማ ጠባይ፡ ቀደም ብሎ እንደተገለጸው፡ የሰሜኑን ክፍል በሚያጠቃበት ጊዜ፡ በደቡቡ ክፍል ደግሞ፡ የበጋው ፀሓያማ ጠባይ ይሰፍናል ማለት ነው።

ይህ ብቻ ሳይኾን፡ በዓመት፡ ሁለት ጊዜያት፡ በየ፮ ወሩ፡ የሰዓት አቆጣጠራቸውን፡ እንደየክፍለ ዓለማቸው አቀማመጥ፡ በ፩ ሰዓት ያሳድጉታል፡ ወይም በ፩ ሰዓት ይቀንሱታል።

በኢትዮጵያውያን ዘንድ፡ ፯ቱ የሳምንቱ ቀኖች፡ የእግዚአብሔር፡ የሥነ ፍጥረት ሥራው፡ በተራና በቅደም ተከተል የተካሄደባቸውንና በቅዱሳት መጻሕፍት የተመዘገቡትን የዕለታት ስም እንደያዙ፡ የአዳምና ሔዋን ቋንቋ በሆነው፡ በግእዝ፡ አሐዱአንድ፡ ወይም፡ መጀመሪያ ቀንለማለት፡ እሑድ፥ ቀጥሎ፡ ሁለት፥ ወይም፡ ሁለተኛ ቀንለማለት፡ ማግሰኞ፡ ቀጥሎ፡ አራት፥ ወይም፡ የሰንበት መግቢያ፥ ወይም፡ የሳምንቱ ጊዜ፡ የሚጠልቅበት ቀንለማለት፡ ስድስተኛው ቀንዓርብ፥ በሰንበት ጌታ፡ በኢያሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፡ ወደዘለዓለማዊነትከመለወጧ በፊት፡ ቀድሞ የነበረችበትን ሁኔታ ለማስታወስ፡ ሰባተኛዪቱን የሰንበት ቀንቅዳሜብለው ይጠርዋቸዋል።

ምዕራባውያን ግን፡ ለእነዚሁ የሳምንት ቀኖች፡ የሰጧቸውን የአረማውያን ጣዖታት አማልክቶቻቸውን ስም እንመልከት!

 • Sunday: Sun’s day (ሳንዴይ) ማለት የፀሓይ ቀን

 • Monday: Moon’s day (ማንዴይ) የጨረቃ ቀን፥

 • Tuesday: Tui’s day (ቱዩስዴይ)፡ ማለት፡ የጦርነቱ አምላክ፡ የቲዩ ቀን፥

 • Wednesday: Woden’s day (ዌድንስዴይ)፡ ማለት፡ የታላቁ አምላክ የውድን ቀን፥

 • Thursday: Thor’s day (ተርስዴይ)፡ ማለት፡ የነጎድጓዱ አምላክ፡ የቶር ቀን፥

 • Friday: Frigg’s day (ፍራይዴይ)፡ ማለት የታላቁ አምላክ፡ የዎድን ሚስት፡ የፍሪግስ ቀን፥

 • Saturday: Saturn’s day (ሳተርዴይ)፡ ማለት፡ የሰማዩ ኮከብ፡ የሳተርን ቀን።

በኢትዮጵያውያን ዘንድ፡ ፴ ዕለታት፡ ፩ ወር ሲኾኑ፥ ፲፪ ወራት እና ፭ ዕለታት ተሩብ ደግሞ፡ ፩ ዓመት ይኾናሉ። ፭ቱ ዕለታት ተሩብ፡ ጳጉሜይባላሉ። ጳጉሜ፡ የቃል ለቃል ትርጉሙ፡ ተውሳክጭማሪተረፍትርፍማለት ነው። ፲፪ቱ የምዕራባውያን ወሮች ግን፡ ፳፰፡ ዕለታትን፥ በየአራት ዓመቱም፡ ፳፱ ዕለታትን ከያዘውና (February – ፌብሩአሪ) ከሚባለው፡ ከአንደኛው ወር በቀር፡ እኩሌቶቹ፡ በ፴፥ የቀሩትም፡ በ፴፩ ዕለታት ተመድበው፡ ይህን በመሰለ የተዘበራረቀ መልክ ይቆጠራሉ።

በኢትዮጵያውያን በኩል፡ ከመስከረም እስከ ነሓሴ ድረስ ያሉት፡ ፲፪ቱ ወሮቻቸውና ጳጉሜ፡ እያንዳንዳቸው የሚጠሩበት ስም፡ ከእግዚአብሔር ከተሰጣቸው፡ የተፈጥሮ ጸጋቸው ጋር የተያያዘው ገጽታቸውን የሚያሳይ ትርጉም ያለው ሲኾን፡ በኢትዮጵያውያን የወራት አመዳደብ መሠረት፡ ከ September (ሴፕቴምበር) መስከረም እስከ እስከ August (ኦገሥት) ነሓሴ ድረስ ያሉት የምዕራባውያኑ ወሮቻቸው ግን እንደሳምንቱ ቀኖቻቸው ኹሉ፡ የተሠየሙት፡ በጣዖቶቻቸውና እንደአማልክት ይሰግዱላቸው በነበሩት ገዢዎቻቸው ስም ኾኖ ይገኛል።

ይኽውም፡ መስከረምን ከኢትዮጵያውያን፡ August(ኦገሥትን) ነሓሴን ደግሞ ከምዕራባውያን፡ ለምሳሌ ያህል ወስደን ብንመለከታቸው መስከረም፡ በኢትዮጵያኛ፡ ከረመወይም፡ ክረምትን አሳለፈከሚለው ግሥ ወጥቶ፡ ክረምቱ የሚያበቃበት፡ ማለትም፡ የዝናሙ ጠል አብቅቶ፡ የፀሓይ ብርሃን የሚፈነጥቅበት፡ የዓባይና የሌሎቹ ወንዞች ሙላት መጉደል የሚጀምርበትና ፍጥረቱ ኹሉ፡ ከተሸሸገበት በዓቱ እየወጣ፡ እርስ በርሱ የሚገናኝበት፡ አዲሱ ዓመት፡ የሚገባበት ማለት ነው። መስከረም ጠባየሚባለውም ለዚህ ነው። በምዕራባውያን ዘንድ ግን፡ August (ኦገሥት)፡ ስለወሩ ኹኔታ፡ ምንም ትርጉም የሌለው ኾኖ፡ እንደጣዖት ይመለክ ለነበረው፡ ለአረማዊው ርእሰ ነገሥት (Emperor): ለአውግሥጦስ ቄሣር፡ በመታሰቢያነት የተሰጠ ወር መኾኑን ብቻ ያስረዳል።

የኢትዮጵያውያን ዓመት የሚጀምረው፡ በመስከረም፡ የሚያበቃውም፡ በጳጉሜሲኾን፡ የምዕራባውያ ኑ ግን፡ በእነርሱ January (ጃንዋሪ)፡ ማለትም፡ በጥርይጀምርና፡ በDecember (ዲሴምበር)፡ ማለትም በታኀሣሥይጨርሳል። ስሙን በመታሰቢያነት፡ January (ጃንዋሪ) ብለው፡ ለዓመቱ የመጀመሪያ ወር የሰጡለት፡ Janus(ጃኑስ)፡ ለሮማውያን፡ ታላቁ ጣዖታቸው እንደነበረ፡ ቀደም ብሎ ተመልክቷል።

በኢትዮጵያውያን ዘንድ፡ ፬ ዓመታት፡ ፩ ዐውደ ዘመን ይኾናሉ። ይህም፡ እያንዳንዱ ዓመት፡ ፫፻፷፭ ከሩብ ዕለታት፡ ወይም ከ፮ ሰዓታት፡ ወይም ከ፲፭ ኬክሮስ ያለው ሆኖ፡ ዘመነ ማቴዎስዘመነ ማርቆስዘመነ ሉቃስእና ዘመነ ዮሓንስተብሎ ተሠይሟል፡ እነዚህ፡ የ፬ቱ ዓመታት ጳጉሜዎች ሰዓታት ሲደመሩ፡ ፩ ዕለት የሞሉና፡ በ፬ኛው ዓመት፡ በዘመነ ዮሓንስ መግቢያ፡ ፮ ዕለታት በመሆን፡ የባሕረ ሃሳቡ ቅመራ ይካተታል፡ የዘመን አቆጣጠሩም ዐውድ፡ እንዲህ በየአራት ዓመታቱ ይዘጋል።

ስለዚህ፡ የግሬጎሪወይም ግሬጎሪያንተብሎ የሚጠራው፡ የምዕራባውያን፡ የጊዜ አቆጣጠር ባህል፡ እንዲህ፡ ምስቅልቅሉ የወጣ በመሆኑ፡ በእርሱ ሰበብና ጠንቅ፡ ጽኑ የሆነው ሃይማኖታዊና ተፈጥሮአዊ መሠረት ያለው፡ የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት፡ ሊቃወስ ቀርቶ፡ ሊነካ እንኳ፡ ከቶ አይገባም።


Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: