Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Black white yellow’

ኮሮና ዘረኞችን አጋለጠቻቸው | Yellow hates Black but loves White hates Yellow + Black loves Yellow + White

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 22, 2020

ነጭቢጫንጥቁርን

እዚህ ይመልከቱ፦ https://www.bitchute.com/video/r15Aw4y681ma/

ኮሮና ጋኔን ናት ፥ ዘረኝነት ደግሞ የጋኔን አንዱ መገለጫ ነው፦

  • 👉 ቢጫ ጥቁርን ይጠላል ነጭን ይወዳል
  • 👉 ነጭ ቢጫን እና ጥቁርን ይጠላል
  • 👉 ጥቁር ነጭን + ቢጫን ይወዳል

ሰሞኑን በጀርመን አገር ያሉ ምግብ ቤቶች የመንግስት የኮሮና ቫይረስ ክልከላዎችን አብቅተው እፎይ በማለት እንደገና እንዲከፈቱ ሲፈቀድላቸው፤ የአንድ ታዋቂ ምግብ ቤት ፈረንሳዊ ኮከብ ምግብ አዘጋጅ፡ “ቻይናዎችን እዚህ አንፈልግም!” በማለት ቢጫ ሰዎችን ወደ ሬስቶራንቱ እንዳይገቡ በመከልከሉና ብዙዎችን በማስቆጣቱ ከማዕረጉ ላይ አንድ ኮከብ ቀነሰ።

ቀደም ሲል በቻይና ብዙ ጥቁሮች የዘረኝነት አድሎና ጥቃት እየደረሰባቸው ነበር። በአን ወቅት አንዲት ቻይና የቆየች ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት ወደ ገበያ ማዕከል መግባት ስትከለከል አብራት የነበረችዋ ነጯ ሴት ግን መግባት ተፈቅዶላት እንደነበር አይተናል። ብዙም ሳይቆይ በዘመነ ኦሪት እግዚአብሔር አምላክ በኢትዮጵያዊቷ ሲፖራ ምክኒያት የነብዩ ሙሴንና አሮንን እህት ማርያምን በዘረኝነቷ ገጽሶ ለምጻም እንዳደረጋት በዘመነ ኮሮናም ቻይናውያን ኢትዮጵያዊቷን ዲፕሎማት በማግለላቸው ይመስላል ሁለት ቻይናውያን ዶክተሮቻቸው ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ጠቁረው ተገኙ ፤ ኮሮና ሁሉንም ፩ ገጽታ ሰጠቻቸው ማለት ነው።

ኮሮና ሁሉንም ፩ አደረገቻቸው| ዘረኞቹ ቢጫ ቻይናውያን ጥቁሮች ሆነው ከእንቅልፋቸው ነቁ

በኮሮና ተጠቅተው የነበሩት ሁለት የቻይና ዶክተሮች ከማገገሚያ አልጋቸው ሲነቁ ቢጫው ቆዳቸው ሙሉ በሙሉ ጠቁሮባቸው ተገኘ።

እንግዲህ የእነዚህ ሁለት ዶክተሮች መጥቆር ሰሞኑን ቻይናውያን በጥቁር ሰዎች ላይ እያራገፉት ያለውን የዘረኝነትን ጋኔን “ዋ! ! ! !” እያሉ እራሳቸውን በመስተዋት እንዲያዩት ረድቷቸው ይሆናል።

በጣም የሚገርም ዘመን እኮ ነው፡ ጃል! ግን የዘረኝነትን ውጤቶች እያየን ነው? ነጮቹ ቻይናን በኮሮና ቫይረስ ከበከሏት በኋላ ሌት ተቀን ይኮንኗታል ፥ ቻይና ግን በሚሊየን ለሚቆጠሩ ቻይናውያን የአገሮቻቸውን በሮች ብርግድ አድርገው በከፈቱላት ጥቁር አፍሪቃውያን ላይ የዘረኝነትን መርዝ ትተፋለች። ለነገሩማ የምዕራብ እና ምስራቅ ኢአማንያን ሁሉም አብረው በአንድነት እየሠሩ ነው። ሁሉም ጥቁር አፍሪቃውያንን ከአህጉራቸው አስወግደው በአፍሪቃ ወይ ነጭንና ቢጫን ብቻ ለማስፈር ይሠራሉ ወይም ደግሞ አፍሪቃ የዱር አራዊቶችና ማዕድኖች መኖሪያ ብቻ እንድትሆን ይሻሉ። የተገለባበጠባት እርኩስ ዓለም።

እግዚአብሐር አምላክ ከሦስት ሺህ ሦስት መቶ ዓመታት በፊት ያስተማረን ይህን ነበር፤ የሰው ልጅ ግን ተምሮ ለመለወጥ ሰንፏል።

[ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፪፥]

  • ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።
  • እነርሱም። በውኑ እግዚአብሔር በሙሴ ብቻ ተናግሮአልን? በእኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን? አሉ፤ እግዚአብሔርም ሰማ።
  • ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።
  • እግዚአብሔርም ወዲያው ሙሴንና አሮንን ማርያምንም። ሦስታችሁ ወደ መገኛኛው ድንኳን ውጡ ብሎ ተናገረ፤ ሦስቱም ወጡ።
  • እግዚአብሔርም በደመና ዓምድ ወረደ፥ በድንኳኑም ደጃፍ ቆመ፤ አሮንንና ማርያምን ጠራ፥ ሁለቱም ወጡ።
  • እርሱም። ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።
  • ባሪያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው።
  • እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ፥ በምሳሌ አይደለም፤ የእግዚአብሔርንም መልክ ያያል፤ በባሪያዬ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለ ምን አልፈራችሁም? አለ።
  • እግዚአብሔርም ተቈጥቶባቸው ሄደ።
  • ደመናውም ከድንኳኑ ተነሣ፤ እነሆም፥ ማርያም ለምጻም ሆነች፥ እንደ አመዳይም ነጭ ሆነች፤ አሮንም ማርያምን ተመለከተ፥ እነሆም፥ ለምጻም ሆና ነበር።

_____________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Health, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: