ዓለማችን በአጋንንት (ሰይጣን) ምልክቶች ተወራለች፡ እነዚህን ምልክቶች ፈለግንም አልፈለግንም በየቀኑ ሳናይ የምናልፍበት ሰዓት የለም። እነዚህን ምልክቶች ችላ ማለት ትልቅ ስህተት ብቻ ሳይሆን ሰይጣንን ለማገልገል ነፍሳቸውን ለሸጡት ተኩላዎችና ቀጣፊ ነጣቂዎች ወደ በረት እንዲገቡ በር መክፈትና እራስንም አሳልፎ መስጠት ነው።
በምንገኝበት ዘመናችን በግለሰቦች ላይ ተደጋግሞ የሚንጸባረቀው ሰይጣናዊ ምልክት ታች የምናየው ነው
ይህንንም ምልክት በተለይ፡ በባለሥልጣናት፣ በማናጀሮች፣ ለንዋይ በሚገዙ ወይም በገንዘብ አፍቃሪዎች ላይ፡ በሰዶማውያን – ባጠቃላይም በአጋንንት የተጠመዱ ግለሰቦች ላይ – ሲንጸባረቅ ለማየት እንችላለን።
Horned God Represents the horned god of witchcraft. Pan or Cernunnos. Note the thumb under the fingers and given by the right hand.
Horned Hand The sign of recognition between those in the Occult. When pointed at someone it is meant to place a curse. Note the thumb over the fingers and given by the left hand.
አጋንንት በመንፈሳቸው ሰው ላይ ሲያድሩ ዓይነተኛ መገለጫቸው ሰውነታዊ መንገላታትን ማሳየት ነውና፡ የእጅ እንቅስቃሴ ይህን ሁኔታ በግልጽ ይጠቁመናል። ስለዚህ፡ ለዚህ አደገኛ መንፈስ የተጋለጡት በጠበል፣ በጸሎት በቤተ ክርስቲያን ሥልጣን በእግዚአብሔር ስም ሊታሠሩና ኃይላቸው ሁሉ ሊነጠቅ ይገባዋል።
በጥንቆላው ዓለም ተወዳጅነት ካላቸው ምልክቶች አንዱ ባለ አምስት ማዕዘኑ ኮከብ (Pentagram) ነው። ይህም ምልክት መሬትን፡ ነፋስን፡ እሳትና ውሃን ባካባቢያቸው ከሚገኙት መናፍስት ጋር ያለውን ነገር ሁሉ የሚወክል ምልክት ነው። ይህን ምልክት በባንዲራዎቻቸው (ሰንደቅዓላማ)ላይ አስፍረው የሚገኙት ሁለት አገሮች ኢትዮጵያና ሞሮኮ ብቻ ናቸው።
ዋናዋናዎቹ ሰይጣናዊ የምስል ምልክቶች