ይህን ዜና ሳይ፡ “እንዴ ፕሬዚደንት ትራምፕ አዲስ ኢትዮጵያን ይከታተላሉ እንዴ? አማርኛ ይችላሉ እንዴ?” አሰኘኝ!
የጥቁር ሕዝቦችን የመብት ትግል እንቅስቃሴ ያወደመው ወስላታው ኦባማ የመለመላቸው አራት ዱርየ ሴቶች በመቅለብለብ ላይ ናቸው። እነዚህ አራት የአሜሪካ ተዋካዮች ምክር ቤት ዓባላት፤ ሶማሊቷ ኢልሃን ኦማር፣ አሌክሳንድርያ ኮርቴዝ፣ ራሺዳ ትላይብ እና አያና ፕሪስሊ ናቸው። እነዚህ አራት ሴቶች (2 ሙስሊሞች ፣ 2 ኮሙኒስቶች) አሜሪካን ለማጥፋት በባራክ ሁሴን ኦባማ ቀስቃሽነት የተጠራውን ኤሊዛቤላዊ ቡድንን መስርተዋል።
አንዳንዶች እነዚህን አራት ሴቶች አሜሪካን የሚጠሉ ኮሙኒስቶች ናቸው ይሏቸዋል፤ ነገር ግን ከኮሙኒስትነትም አልፈው እስላማዊ ናቸው፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ መንፈስ ያደረባቸው ጋለሞታዎች ናቸው።
እነዚህ ምስጋና–ቢስ “ሴቶች” አሁን በጣም የሚያሳፍሩ ነገሮችን በመቀበጣጠር ላይ ናቸው። በመጭው ዓመት በሚደረገው የፕሬዚደንት ምርጫ ላይ ፕሬዚደንት ትራምፕን ለመርታት የዲሞክራቲክ ፓርቲው ምንም ዓይነት ዕድል የለውም። እነዚህ አራት “ሴቶች” በባራክ ኦባማ እየተዘጋጁ ያሉት ግን ለ2024 ዓ.ም የአሜሪካ ምርጫ ነው።
ከዚህ ቀደም እንዳወሳሁት ሶማሊቷ ኢልሃን ኦማር በኢትዮጵያ ላይ እየደረሰው ባለው ግፍ ሳቢያ ለአሜሪካ የተላከች መቅሰፍት ናት፤ ሰለዚህ በ 2024 ዓ.ም ላይ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚደንት ሆና ብትሾም አይግረመን፤ ነገሮች ከምናስባቸው በላይ ናቸው።
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከጥቂት ቀናት በፊት ለእነዚህ ሴቶች “አሜሪካን የማትወዱና፣ እዚህ በመኖራችሁ የሚከፋችሁ ከሆነ፤ አሜሪካን በመልቀቅ ወደ መጣችሁበት ብልሹ ሃገራት መመለስ ትችላላችሁ” ማለታቸው ትክክል ናቸው። ሃገር–ወዳድ መሪ ማለት እንዲህ ነው። የሩሲያው ፕሬዚደንት ፑቲንም ለቼችኒያ ተገንጣዮች “ይህች ሃገር ሩሲያ ናት፣ ቋንቋችን ሩሲያኛ ነው፤ የማትቀበሉ ከሆነ ሩሲያን ለቃችሁ ውጡ” ብለዋቸው ነበር። እኔም የኢትዮጵያ መሪ ብሆን ኖሮ እንድነ ጀዋር ኢትዮጵያዊነትን የማይቀበሉትን ወሮበሎች ሁሉ፡ “ኢትዮጵያን ልቀቁ!” እላቸው ነበር፤ ደግሞም ከብዙ መስዋዕት በኋላ በቅርቡ ይህ መምጣቱ የማይቀር ነው።