Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Atse Yohannes’

የአፄ ዮሐንስ እና የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 30, 2011

 

*ከማሞ ውድነህ*

ካለፈው የቀጠለ

 

አሁንኮ አባታችን ያቀረቡልዎ ክስ የደንከልን በር ለሃይማኖት ተግባር ነው ብላችሁ ከገዛችሁ በኋላ ለንግድ ሥራና ለመንግሥት መገልገያ እንዲሆን አደረጋችሁ፤ የትንባሆ ነገር በሕዝቡ ዘንድ እንዲለመድ አድርጋችኋል ነውና ለዚህ መልስ ይስጡብለው ጠየቋቸው።

አባ ማስያስ በጸጉር የተሸፈነ የዱር ድመት የመሰለ ፊታቸውን ወደ ዕጨጌው ዘወር አድርገው፤

እሳቸውኮ እኛን በሆነ ባልሆነ የሚወነጅሉን አገራችሁ ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር ተወዳጅታ በጥበብ እንዳትኮራ እንደ እነርሱ በመሳሰሉ ከእስክንድርያ በሚላኩ ሰባኪዎች አማካይነት አገራችሁ የግብጽ ጥገኛ ሆና እንድትኖር ከግብጽም ፈቃድ እንዳትወጣባቸው፡ በዚህ አገሩ የሚኖሩ እስላሞች ክርስቲያይኖች እንዳይሆኑባቸው የግብጽ ከዲብ ባለሟልነት እንዳይቀርባቸው ብለው ነውብለው ሲሳለቁ ዕጨጌውን ቁጣ ቱግ አድርጎ አስቆጣቸውና፤

ስሙ ወይ ማስያስ! ማንነትዎንኮ አሳምሬ ደርሼበታለሁ! የጣሊያኑ ንጉሥ ነፍስ አባት አይደሉም? ይህን ያምናሉ? ወይስ ይክዱኛል?” ብለው አፈጠጡባቸው።

ይኽ ነገር እውነት ነው?” ብለው ዮሐንስም ተጨመሩ። የችሎቱ ፍጥጫ ከአባ ማስያስ ላይ ተከመረ።

ብሆንስ ምንድነው ነውሩና ጥፋቱ?” አሉና አባ አንገታቸውን ደፉ።

ነውሩና ጥፋቱማብለው እጨጌም አባን ገለማምጠው፡ የችሎቱንም ሁኔታ ቃኝተው ክርክራቸውን ቀጠሉበት። ነውሩና ጥፋቱማ እንደ አባትነትዎ ከንጉሥዎ አጠገብ ሆነው መምከርና ማስተማር ሲገባዎ በወንጌል ስም፡ በክርስቶስ ስም ከሰው አገር ገብተው ሃይማኖት እየበረዙ ወንድምና ወንድም ለማፋጀት ተንኮል እየሠሩ መገኘትዎ ነውብለው ሲመልሱላቸው ችሎቱ ይበል ይበልብሎ አስተጋባላቸው።

አፄ ዮሐንስ አንገታቸውን አቀርቅረው ሲተክዙ ቆዩና በሆዳቸው ውስጥ ሲጤስ የነበረውን ንዴት ደጋግመው በመተንፈስ ካስወጡት በኋላ፤

እኮ ለዚህስ የሚሰጡት ምላሽ አለዎት?” ብለው ጠየቋቸው የዐይኖቻቸውን ቅንድቦች ዘግተው።

የንጉሥ ነፍስ አባትነት ከሀገራቸው ወጥታችሁ አታስተምሩ ብሎ አይከለከልም፡ እርሳቸውስ የከዲቡብለው ተናግረው ሳይጨርሱ እጨጌ አቋረጧቸውና፤

ጃንሆይ! በዚህ ችሎት የምትገኙ መኳንንትና ሊቃውንት! ልብ በሉልኝ! ‘ስሱ ሲበላ ይታነቃል! ሐሰተኛ በአነጋገሩ ይታወቃል እንዲሉ፥ የግብጽን ጦርና የመኳንንት ወስላቶች የምትረዱስ እናንተ አይደላችሁም? እውነተኞቹ የወንጌል ሰባኪዎች ከሆናችሁ ቀደም ሲል የቱርክ ጦር ዛሬም ግብጾች ክርስቲያኑን ሁሉ እስላም ካልሆንክእያሉ ሲያስጨንቁት ለምን አልገላገላችሁም?” ብለው አንገታቸውን አሰገጉባቸው።

እኮ? የደንከልን የባሕር በርስ ለንግድና ለወታደር ተግባር እንዲውል አሳልፋችሁ አልሰጣችሁም? የትንባሆ ዘርስ በእርሻ ላይ እየዘራችሁ ሕዝቡን እያስለመዳችሁት አይደለም? ለግብጥ ጦርና እኔን ካሎረፉ ወስላቶችስ ጥግና ጋሻ ሁናችሁ የለም? ይህን ሁሉ ታምናላችሁ? ትክዳላችሁ?” ብለው አፄ ዮሐንስም ቁጣና ፍጥጫ ጨመሩበት።

 

Continue reading…AtseYohannesNegusMenilik2

 

 

 

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

የአፄ ዮሐንስ እና የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 27, 2011


*ከማሞ ውድነህ*

የእስበሳችን ነገር ያለ ማክረሩ ነው የሚሻለው። ጠንካራ ክንድና ብርቱ ትኩረት የሚገባው ግን እንደ አዞ ከውሀ ውስጥ ብቅ የሚለው ነው (አሉላ አባነጋ)

አፄ ዮሐንስ ከጉራዕ ጦርነት በኋላ ሐማሴን ውስጥ ሰነባብተው ወደ ዐደዋ ከመመለሳቸው በፊት የሰሜን ኢትዮጵያ በር የተከበረና የታፈረም እንዲሆን ሲሉ ደጃዝማች ኃይሉ ተወልደ መድኅንና ራስ ባርያውን በገዥነት ሲሾሙ፡ ስመጥሩውን አዋጊያቸውን ሊጋባ አሉላን በራስነት ማዕረግ አስኮፍውሰና አስጊጠው ከመረብ ማዶ ያለውን አገር በጦር አበጋዝነት እንዲጠብቁ ሾሙዋቸው። ከዚያ በኋላም የአፄ ዮሐንስ ትልቁ የሥራ ምዕራፍ የኢትዮጵያን የውስጥ ጉዳይ ማደላደልና ማለሳለስ አንድነቷን ማጽናትና ሕዝቡ ፍትሕ አግኝቶ አርሶና ነግዶ እንዲተዳደር የማድረጉ ጉዳይ ነበር።

ይህን ዓላማቸውን ሊያደናቅፉባቸው እንደሚችሉ አሥግተዋቸው ከነበሩት ሁኔታዎችም ጋር መፋጠጡን ተያያዙት። በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የውስጡን ተቀናቃኝ ቀርቶ የውጭውንም ወራሪ ጠላት ከአንዴም ሁለቴ ኃያሉ ክንዳቸውን ስለአሳረፉበት ለጊዜው ረጭ ብሎላቸዋል። በምዕራብና በመካከል ኢትዮጵያም በኩል የቤገምድር የወሎና የጐጃም ሁኔታ ጋብ ብሎላቸዋል። የጥርጣሬና የሥጋት ትኩረታቸውን የሳበባቸው ግን ሸዋ ሆነ። የወጣትነት ጓደኛቸውና ምስጢረኛቸው ምኒልክ አፄተብለው ቁጥሩ እስከ ሰባ ሺህ በሚደርስ ሠራዊት ጐልብተው፡ ከሸዋም አልፈው ወሎንና ጐጃምን ለመደረብ ከሚያስፈራሩበት ደረጃ ላይ ወጥተዋል።

አፄ ዮሐንስ ግን፡ የምኒልክን ሁኔታ አንሥተው ከመኳንንቶቻቸውና ከጦር አበጋዞቻቸው ጋር በሚወያዩበት ሰዓት ሁሉ ደጋግመው የሚያነሡት ጉዳይ ነበራቸው።

ዋናው ሥጋቱና ችግሬ የሠራዊቱ ብዛት አይደለም። ለዚህ ለዚህስ እኔም ላቅ ያለ እንጅ ከእርሱ ዝቅ ያለ ሠራዊት የለኝም። ግን እንደዚያ ማሳያ እንደሚሉት የሰይጣን መልእክተኛ የመሰለ ፈረንጅ ከአጠገቡ አስቀምጦ፡ ከነሙንዚንገር ጋርም የሚያደርገው መላላክና መስማማት ነው።

ከዚያ ሌላ ደግሞ እነዚህ ሚሲዮኖችም በዚያ በኩል ገብተዋል፡. ዋናው ዓላማቸውም ምኒልክን አሳስተውና ጦር አስመዝዘው ከኔ ጋር ለማጋጨት መሆኑን አላጣሁትም። ግዴለም የማደርገውን ዐውቃለሁእያሉ ዛቻ አዘልና ትካዜለበስ አነጋገር ያሰሙ ነበር። እርግጥም ነው በዚያ ዘመን ፒዬር አርኖ የተባለ ፈረንሳዊ በዘይላ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ የምኒልክ ባለሟል ሆኖ የእርሳቸውንም መልእክት ይዞ ወደ ግብጽና ፈረንሣይ እየሔደ ዮሐንስን ለመጣል ትልቅ መሣሪያ ይሆናችኋልእያለ ያሽቃብጥ ነበር። ከእርሱም ሌላ ደግሞ በምሕጻረ ቃል አባ ማስያስእየተባለ የሚጠራው ሎሬንዞ ጉልየሞ ማሳያ የሚባለው የሮማ ካቶሊክ ሚሲዮን አባል በሸዋና በከፋ ውስጥ ድርጅቱን አቋቁሞ የምኒልክን ባለሟልነትም አትርፎ ከሚሲዮናዊነቱ ይልቅ በዲፕሎማቲክና በስለላው ሙያ ተሠማርቶ ዮሐንስንና ምኒልክን ለማራራቅና ለማጋጨት በመካከላቸው ገብቶ ነበር።

እነዚሁ ሁለቱ አውሮጳውያን የምኒልክን ጉልበት ከዮሐንስ ጉልበት የጠነከረ ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት ሲከታተሉት የነበሩት ዮሐንስም ክንዳቸውን በቀላሉ የማይታጠፍ ለማድረግና ምኒልክንም ለማስገበር ሲሉ የሠራዊታቸውን ቁጥር እስከ አንድ መቶ ሺህ ከአደረሱት በኋላ፥ ክዚሁ ውስጥ እስከ ዐርባ ሰባት ሺህ

የሚደርሰውን ልዩ ልዩ መሣሪያዎች አስታጠቁት። ከጉንደትና ጉራዕ ጦርነቶች የተገኘው ቀላል መካከለኛና ከባድ መሣሪያም የበላይነታቸውን ያረጋገጡበት ዋናው ትጥቃቸው ነበር።

ከመሣሪያው ጥራትና ብዛትም ሌላ በአጼ ተክለ ጊዮርጊስና በግብጾች ላይ ያገኙት ድል ዝናቸውንና ጥንካሬያቸውን አበሻ መሬት አውጥቶ በአፍሪቃ፡ በእስያና በአውሮጳ ውስጥ አስተጋብቶላቸው ነበር። በአሜሪካም ውስጥ ቢሆን፡ የኛ የጦር መኮንኖች ያዘመቱትን የግብጽን ጦር ድል ያደረገ ብርቱ ንጉሥየሚል ጸጸትለበስ ታዋቂነት አትሮላቸው ነበር።

ታዲያ እንደዚያ ሆኖ ስሙ የገነነ ሠራዊት ሸዋ የገባ እንደሆነ ሊያደርስ የሚችለውን ብርቱ ጉዳት አስቀድመው የተረዱትና የተጠነቀቁበት ከጐልማሳው ምኒልክ ይልቅ አዛውንቱ አጐታቸው ዳርጌ ንበሩ። ጉዳዩን በቀላሉ አትዩት፤ በየልቦናችሁ ምከሩበትና በእርቅ ይለቅሲሉ አዛውንቱ ጦር ጠማኝይሉ የንበሩት የምኒልክ የጦር አበጋዝ ግን፤

ወይ እሳቸው መጥተው፥ ያለዚያ እኛ ዘምተንባቸው ሳንሞካከር እንዴት አስቀድመን እንገብራለንእያሉ ምኒልክን ይወተዉቱ ነበር።

በዮሐንስ ቤተ መንግሥት እንደአባት ይታዩ የንበሩት ራስ አርአያም በበኩላቸው፤

የሁለት ወንድማማች ጠብ ማንን ጐድቶ ማንን ይጠቅም ይመስላችሁ? ኢትዮጵያን እኮ ነው የሚያዳክማት! ኢትዮጵያን እኮነው የሚያሳንሳት! ኢትዮጵያን እኮ ነው የጠላቶቿ መሳቂያ የሚያደርጋት! ታሪክ ይወቅሰናል፤ ትውልድ ያፍርብናል፤ ታቦትና መስቀል አስይዘን ካህናትን ወደ ምኒልክ እንስደድ እንጂ ጦር መምዘዙን አልስማማበትምእያሉ የእህታቸውን ልጅ ከነጦር አበጋዞቻቸው ይቆጡ ነበር።

 

 

Continue reading…AtseYohannesNegusMenilik

 

 

 

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: