የትናንትናውን ቀን ምዕራባውያኑ “የሴቶች ቀን” ይሉታል። ሜዲያው ሁሉ ሊያወራለት የሚገባው ታሪካዊ ቀን ነበር። በትናንትናው ዕለት እህቶቻችን ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ጋር ሙሉ በሴቶች የተከናወነ ጉዞ ወደ ሩቋ አርጀንቲና አካሂደው ነበር። በዋና ከተማዋ ቡዌኖስ አይሬስ የአርጀንቲና ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸው ነበር። እህቶቻችን ለሦስተኛ ጊዜ ነው በዚህ መልክ ሲበሩ።
በሌላ በኩል ደግሞ፡ የእህቶቻችን ጠላቶች የሆኑት ሳውዲዎች ሴቶቻቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ መኪና እንዲነዱ በትናንትናው ዕለት ፈቀደውላቸው ነበር።
ሳውዲዎች ወደታች ቁልቁል ያያሉ፤ ገና በምድር ላይ ናቸውና!
የኢትዮጵያ ሴቶች ግን ወደሰማይ ያያሉ፤ ክንፍ አውጥተውም መብረር ይችላሉ!!!
በሴቶች ብቻ የበረረ ዓየር መንግድ የኢትዮጵያ ብቻ ነው። ለሴቶች መብት እንቆማለን የሚሉት ም ዕራባውያን እንኳን ተመሳሳይ ተግባር ፈጽመው አያውቁም።
ይህ በጣም ኃይለኛ ምስልነው፤ ብዙ ነገሮችን የሚናገርና የሚያስደንቅ የንፅፅር ምስል ነው!!!
እህቶቻችን ለእነዚህ አረቦች በፍጹም፣ በጭራሽ የበታች ሆነው መኖርና መሥራት የለባቸውም!
International Women’s Day – a comparative story of symbolic nature the Medias avoid to report on:
Ethiopian Women Fly High — Ethiopian Airlines honors March 8, 2018 sends all women crew to Buenos Aires, Argentina – while Saudi Women are still crabbing their way across the desert.
This is for a 3rd time that the all female Ethiopian crew is making history.
A woman from Spain, Estefania Aguirre, did a video recently mocking “International women’s day” and said that the women marching are an embarrassment to all women:
______