Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Archangel Michael’

ቅዱስ ምካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ፤ ዛሬም ቆመሃል በኪዳንህ ላሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2017

እርጉም የዲያብሎስ ልጆች በሴቶቻችን፣ በህፃናቶቻችንና በመላው ሕዝባችን ላይ ዘምተዋል፤ ማን ያየናል፣ ማን ያውቅብናል በማለት ሌት ተቀን ይፈታተኗቸዋል፤ ዲያብሎስን ድል የነሣህ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! የምስጋናን መሥዋዕት የምታዘጋጅ አንተ ነህና ጠላት ዲያብሎስ ተረማምዶ በእደ ፃዕረ ሞት ወገኖቻችንን እንዳያፍን በአፋቸው ላይ ጥበቃህን አጠንክር።

የቅዱስ ሚካኤል አምላክ ሆይ! በአርአያህ በአምሣልህ የፈጠርከን ሕዝቦችህን ሁሉ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውረን ለዘላለሙ አሜን።

ኅዳር ፲፪ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ በዓል

ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚመኑከመኤልአምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡ ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡

ስለዚህ ስለ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፤ ጠባቂነትና አማላጅነት ከአባቶቻቸው የተማሩትን በኑሮአቸው ያዩትን አባቶቻችን ጽፈዋል፡፡ ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከጻፉት አባቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፡

  • + ዮሐንስ አፈወርቅ
  • + ኤዎስጣቴዎስ ዘአንፆኪያ
  • + ቅዱስ መቃርዮስ
  • + ቅዱስ ያሬድ
  • + አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
  • + የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አባዲማቴዎስ ናቸው፡፡

እኛም የአባቶቻችንን አንደበት አንደበታችን አድርገን በኅዳር 12 ክቡር ገናና የሆነ ቅዱስ ሚካኤል ካደረጋቸውና ከሠራቸው ብዙ ተአምራት ውስጥ የተወሰኑትን በመልአኩ ተረዳኢነት እንዲህ ብለን እንናገራለን አንጽፋለን፡፡

ንግስት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ጣዖት የሠራችው ቤተ ጣዖት በእስክንድርያ ነበር፡፡ ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እስክንድርያው ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 – 326/ ዘመን ድረስ ነበር፡፡ እለ እስክንድሮስ ሊያጠፋው ሲነሣ ሕዝቡ ከልቡ ገና የአምልኮ ጣዖት ስላልጣፋ 18 ፓትርያርኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት፡፡ እለ እስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት በነበረው ዕለት የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እንዲያከብሩ አውጆ ቤተ ጣዖቱንም በቅዱስ ሚካኤል ስም ሰይሞ ቤተክርስቲያን አደረገው፡፡ ከዚህ በኋላ በቅዱስ ሚካኤልም ስም አብያተ ክርስቲያናት መታነጽ ጀመሩ በዓሉ በዚህ ቀን እንዲከበር ተወስኗል፡፡

እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ፡፡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው፡፡ መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው፡፡ ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ፡፡

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ፡፡ የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡

ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፡፡ በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፡፡››

በአንድ ዘመን ብዙ ሰዎች ከግብፅ አውራጃ መጥተው ወደ ባሕር ማዶ ሄዱ፡፡ ከባሕሩም በደረሱ ጊዜ በመርከብ ላይ ተሳፍረው ከየብሱ ጥቂት በራቁና ወደ ባሕሩ መካከል በደረሱ ጊዜ ጽኑ ነፋስ ተነሳባቸው ለመስጠም እስኪ ደርሱ ድረስ፡፡

የማዕበሉ ሞገድ እየጨመረ እየጸና ከፍ አለ፡፡ ታላቅም ማዕበል መጥቶ ሊገለብጣቸው ደረሰ፡፡ ፍጹም ጥፋትና ክፉ ሞት እንደ መጣባቸው ባዩ ጊዜ ጽኑ ሐዘን ያዛቸው፡፡ የሚያድናቸው የሚያጽናናቸው አጥተው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ብለው ጮኹ፡፡

‹‹የመላእክት አለቃቸው ግሩም ገናና የምትሆን ሚካኤል ሆይ የተአምራትና የይቅርታ መልአክ ነህና፡፡ ልዑል ቸርነቱን የሚገልጥብህ መልአክ ሆይ! እግዚአብሔር ፍቅሩን የሚያስታውቅብህ መልአክ ሆይ ወደኛ ተመልከት እርዳን፡፡ የተጨነቅን እኛን አድነን፡፡ ከመጣብን ሞትና ጥፋት እንድን ዘንድ ስለኛ ወደ ፈጣሪህ ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር ለምንልን፡፡ አሁን የሞት መጋረጃ ዓይናችንን ሸፍኖታልና፡፡ ፍጹም የጥፋት ጥላንም አይተናታልና›› ብለው በፍጹም ልቦናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ በመርከብ ውስጥ ያሉት ሁሉ ጽኑ ለቅሶ እያለቀሱ መራራ እንባ እያፈሰሱ ጮኹ፡፡

ከባሕር ጽኑ ማዕበል ከሞት ያድናቸው ዘንድ ያን ጊዜ በዚያች ሰዓት እግዚአብሔር የልቦናቸውን ሐዘንና ልመናቸውን ሰማቸው፡፡ ያን ጊዜም ይገዳቸው ዘንድ ቸር መልአኩን ሚካኤልን ላከላቸው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወረደ መርከቡን በእጁ ይዞ ሳበው፡፡ በመርከቡ ውስጥ ያሉትንም ወደ የብስ አወጣቸው፡፡ በደኅናቸው ተሻገሩ፤ ክፉ ነገር ጥቂትስ ስንኳ ፈጽሞ አላገኛቸውም፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ገናና የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ልመናውና አማላጅነቱ ፈጽሞ ይጠብቀን፡፡ ከጽኑ ጠላት እጅ በክንፎቹ ጋርዶ ይሰውረን፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

ምንጮች

-ድርሳነ ሚካኤል ዘኅዳር

-መጽሐፈ ስንክሳር ዘኅዳር

-የሐመር መጽሔት 1993 ዓም መጋቢትና ሚያዚያ

ቅዱስ ምካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ፤ ዛሬም ቆመሃል በኪዳንህ ላሉ። አሜን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ካኤል ሆይ ስለእኛ ስለሰው ልጆች በጌታ ፊት ቁምልን ምልጃና ጸሎትህ ተራዳእነትህ ጥበቃህ ለዘወትር አይለየን!! አሜን።

አስደናቂ አይደለም!? ላይ ያቀረብኩትን መልዕክት ከላኩ በኋላ፡ ቅዱስ ሚካኤልን ስጠራና ይህን ድህረገጽ ስከፍት፤ ያው የአምላኬ መልአክ በላዬ በራ፦

One Of The Biggest Alternative Media Networks In Italy Is Spreading Anti-Immigrant News And Misinformation On Facebook

______

Antivenom vs Venom | ሊቀ መላእክት ሚካኤል (Michael)በእነዚህ ገዳዮች ላይ ስይፉን ዘርግቶባቸዋል፤ ይገርማል ሁሉም ስማቸው በ “Mይጀምራል

  • ሜርከል (Merkel) ወደ ሞት እየሄደች ነው
  • ሙጋቤ (Mugabe) ወደ ሞት እየሄደ ነው
  • መንግስቱ (Mengistu) ወደ ሞት እየሄደ ነው
  • ሜይ (May) ወደ ሞት እየሄደች ነው
  • ማክሮን (Macron) ወደ ሞት እየሄደ ነው
  • ማንሰን (Manson) ሞተ
  • መሀመድ (Mohammad) ሞቷል
  • ሙስሊም (Muslim) እየሞቱ ነው

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

Simultaneous Muslim Attacks on Ethiopian and Egyptian Orthodox Christians at St. Michael Churches in Ethiopia & Egypt

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 22, 2016

[Daniel 12:1-3]

The End Times

At that time Michael, the great prince who protects your people, will arise. There will be a time of distress such as has not happened from the beginning of nations until then. But at that time your people—everyone whose name is found written in the book—will be delivered. Multitudes who sleep in the dust of the earth will awake: some to everlasting life, others to shame and everlasting contempt. 3 Those who are wise[a] will shine like the brightness of the heavens, and those who lead many to righteousness, like the stars for ever and ever.”

ArchAngelMichael2

Islamic terrorist attacked a group of Orthodox Christians who were attending morning prayers at St Michaels Church (Oromia Jimma Zone, Kunbi Wereda Kumbi). The attack took place during the early hours of 15th June 2016.

As per the available information, the attackers came from Addis Ababa and attacked the Christian faithful with swords. Two Christians were severely injured, along with 5 Muslims in the Village. One of the terrorists was arrested.

Patriarch Abune Mathias visited the injured who are now under treatment in Addis Ababa. The Ethiopian Patriarchate will cover the entire cost of the treatment and will make the necessary follow-up with the government.

Source

በጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት አደረሱ

Fanatic’ Muslim mob torches 80 Christian homes in Egypt over church rumour

AN ANGRY crowd destroyed dozens of Christian homes and properties in an Egyptian village last week in protest over rumoured plans to build a church.

The Muslim mob, which were described as “fanatic” by a terrified witness, began wreaking havoc at a Christian-owned building which was under construction.

The crowd believed it was set to be turned into a Christian church and took umbrage, setting fire to the building and other nearby Christian properties.

They also destroyed the construction materials and injured Christians who attempted to reason with them.

Christian resident Mousa Zarif said: “On Friday afternoon, following Friday noon prayer, a great deal of fanatic Muslims gathered in the front of the new house of my cousin, Naim Aziz, during its construction because of a rumour spread in the village that this building would be turned into a church.

They were chanting slogans against us. Among these slogans were: ‘By no means shall there be a church here.’”

Christian residents of the village of Al-Beida are currently forced to travel four miles to pray at the Holy Virgin and the Archangel Michael Coptic Orthodox Church.

When the church’s priest heard what was taking place in the village he rushed to the scene, where he was also set upon.

Zaire said: “They also intercepted the car of Father Karas Naser, the priest of the Holy Virgin and the Archangel Michael Coptic Church when he arrived at the village.

They attacked him but some moderate Muslims intervened, rescuing him from their hands and getting him out of the car.”

Police were called to the scene but either could not or refused to stop the destruction. The crowd continued to set homes and cars on fire in the presence of officers, and also gathered outside the doors to Christian buildings to perform their afternoon prayers on loudspeakers.

Anba Makarios, a Christian cleric for the region, said: “No one did anything and the police took no pre-emptive or security measures in anticipation of the attacks.

We are not living in a jungle or a tribal society. It’s incorrect for anyone to declare himself judge, police and ruler.”

Source

Egypt asks Israel to help solve Ethiopia’s Renaissance Dam crisis

__

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , | 1 Comment »

የኅዳር ሚካኤል — ብሩክ ዓመት በዓል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2014

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትከሚለው የንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደየሱስ መጽሐፍ የተወሰደ

ከከበረ ሰላምታ ጋር

የኅዳር ሚካኤልተብሎ በኅዳር ፲፪ ቀን የሚከበረው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓል ነው።

እግዚአብሔር፡ የእሥራኤልን ሕዝብ በሙሴ አማካይነት ከፈርዖን የባርነት አገዛዝና ከምድረ ግብፅ የሥቃይ ኑሮ ነጻ አውጥቶ መዓልቱን በደመና ሌሊቱንም በእሳት ዓምድ ከልሎ እየመራቸው የቀይ ባሕርንም በደረቅ ምድር አሻግሮ እየጠበቃቸው፡ ውኃውን ከዓለት አፍልቆ ኅብስተ መናውን ከሰማይ አውርዶ፡ ሥጋ አማረንቢሉም ድርጭቱን በነፋስ አዝንሞ እየመገባቸው እንደተንከባከባቸው ይታወቃል፡ በአምላካቸው ቸርነት ይደረግላቸው የነበረውን ያን ኹሉ የተራዳዒነት ተልእኮ ይፈጽምላቸው የነበረው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነበር። ይኹን እንጂ እነርሱ ለዚህ ኹሉ አምላካዊ ቸርነት ውለታቢሶች በመኾን ፈጣሪያቸውን አሳዘኑ፡ ይኸውም ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ወደተራራ ወጥቶ ለጥቂት ቀናት በሱባዔ መቆየቱን ምክንያት አድርገው፡ ካህን ወንድሙን አሮንን በፊታችን የምናስቀድመው ጣዖት ካልሠራህልንብለው አስጨንቀው ጣዖቱን ማሠራታቸውና ማምለካቸው ነው።

እነርሱ ሊጠፉበት የነበረውን የእግዚአብሔርን ቍጣ፡ ሙሴ በማለሟልነቱ አማልዶ ቢያስመልሳቸውም የእነርሱ ማለትም የእሥራኤል ልጆች ፍላጎት፡ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች፡ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ማምለክ ሳይኾን እንደአሕዛብ በሚታይና በሚዳሰስ ግዙፍ ነገር መኾኑን እግዚአብሔር ተመለከተ፡ እንዲህ ከኾነ ብሎም እርሱ እግዚአብሔር ቃሉን በጽላት ላይ ቀርፆ ያንም ጽላት በግእዝ ታቦትበሚባለው ሣጥን ውስጥ እንዲያስቀምጡት አዝዞ፡ በዚያ እንዲያመልኩት ታቦተ ጽዮንየተባለችውን ያቃል ኪዳን ምስክር ሰጣቸው። ከዚህ የተነሣ ጠላቶቻቸውን ድል ይነሡባት ዘንድ እንዲህ አድርጎ በሰጣቸው እርሱ ለእነርሱ በሚገልጽባት እነርሱም እርሱን በሚያመልኩባት በዚችው የጽላት ሕግ ሃይማኖትና ምግባር ጸንተው ይኼዱ ወይም አይኼዱ እንደኾነ ሊፈትናቸው አርባ ዓመታት ሙሉ በምድረ በዳ አንከራተታቸው። በዚያን ጊዜ ለእሥራኤል ሕዝብ አንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለኾንህ፡ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ እኔ በአንተ መካከል አልወጣምና በፊትህ መልአኬን እሰድዳለሁ!” ብሎ የመደበላቸው መልአክ፡ ቅዱስ ሚካኤል ነበረ። ይህ ኹሉ ዝክረ ነገር በኦሪት ዘጸአት መጽሓፍ ውስጥ ተመዝግቦ፡ ዛሬ ድረስ እንደሚነበብ ታውቃላችሁ።

በዚያን ዘመን እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ለአብርሃም ለይስሓቅና ለያዕቆብ የገባውን ቃል ኪዳን በማሰብ ለእሥራኤል ልጆች ያን የመሰለ ታዳጊነቱን በመልአኩ በቅዱስ ሚካኤል አገልጋይነት ያደርግ እንደነበረ፡ ዛሬ እውነተኞቹ እሥራኤል እኛ ስለኾንን ይህንኑ ተራዳኢነቱን ይፈጽምልናል!” ብለው የኢትዮጵያ ልጆች የቅዱስ ሚካኤልን በዓል፡ በዚህ ዕለት ያከብራሉ።

በአገራችን በኢትዮጵያ በዚሁ በኅዳር ሚካኤል ዕለት ካህናቱ በየቤተ ክርስቲያኑ ጸሎተ ዕጣን እየደገሙ የማዕጠንት ዕጣን የሚያሳርጉት ሕዝቡ በከተማ ቍሻሻ የኾነውን ነገር ኹሉ እየሰበሰበ የሚያቃጥለው በገጠርም በየእርሻው በተለይም በቆላ የሚኖረው ወገን ስለወባና ወረርሽኝ በየመሬቱ ላይ እሳት አንድዶ ጪስ የሚያጨሰው ኅዳር ታጠነየሚባለውን ይትበሃል ለማስታወስ ነው፡ የዚህም ምክንያት በራእየ ዮሓንስ ተጽፎ እንደሚነበበው፡ ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይየሚባሉት መላእክት ስለዓለሙ ኹሉ ደኅንነት በሰማይ በጽርሐ አርያም የምስጋናና የልመና ጸሎትን ከዕጣን ማዕጠንት ጋር በእግዚአብሔር መንበር ፊት ያለማቋረጥ የሚያቀርቡትን ሥርዓት የተከተለ ነው፡ እንደዚሁ ኹሉ እኛንም እግዚአብሔር በምድር ላይ ካለፈው ዓመት ከማናቸውም ዓይነት ሕማምና ደዌ፡ ቸነፈርና በሽታ ጠብቆ ስላዳነን፡ ከሚመጣውም እንዲጠብቀን በማለት በዚያ ሰማያዊ ሥርዓት እኛም፡ ኢትዮጵያውያን ለፈጣሪያችን ምስጋናችንንና ልመናችንን ይኸው እናቀርባለን፡ በቅርቡ፡ በአጼ ምኒሊክ ዘመን ደርሶ የነበረውን፡ የኅዳር በሽታየሚባለውን ከመሰለ በዓመቱ ውስጥ ተላላፊ የሰውና የከብት በሽታ ገብቶ፡ ሊያደርስ ከሚችለው ጥፋትና ዕልቂት አድነንለማለት።

በዛሬው በኅዳር ፲፪ ዕለት፡ ፪ሺ፯ ዓ.ም፡ ፲፫ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ህጻናት የልጅነት ልምሻ / ፖሊዮ ተላላፊ በሽታ መከላከያ ክትባት ይሰጣቸዋል። የዜናው ምንጭ አናዱሉ የተባለው የቱርክ የዜና ወኪል መሆኑ የሚገርም ነው። ይህችን ዕለት እናስታውስ! ኹሉን የሚያይ ቸሩ እግዚአብሔር ወገኖቻችንን / ልጆቻችንን ይጠብቅልን!

_

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

Rhodes Miracle: Archangel Michael Weeping Tears

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 11, 2013

Inhabitants of Rhodes, Greece, are talking about a miracle, having seen on Saturday morning an icon of the Archangel Michael weeping in the Sacred Church of the Archangel Michael in the Old Cemetery of Ialyssos.

At 2:00 PM Metropolitan Kyrillos of Rhodes went to the place himself where the icon can be found following reports from the faithful, in order to determine if this was a miracle or some other event.

The Metropolitan, after indeed verifying there were what looked like tears on the face of the Archangel, asked for the icon to be moved from the place it was hanging.

They then examined the back side of the icon as well as the wall on which it rested to determine if there was moisture which passed on to the icon.

Having established that this was impossible, the Metropolitan of Rhodes testified that this was in fact a miracle, and he asked that the icon be brought to the Sacred Church of the Dormition of the Theotokos in Ialyssos for public veneration, as well as to see if a change in environment would halt the phenomenon.

“We will move it to the big church to see how the phenomenon evolves,” Metropolitan Kyrillos told the faithful who had gathered in the small chapel.

The first to see the icon weeping were women who went on Saturday morning to open the church and who in turn informed the vicar of the church.

The vicar, Fr. Apostolos, informs us that the icon was constructed in 1896 and had recently undergone maintenance by the archaeological department.

As of today, the icon continues to weep in its new environment, sometimes stopping but then continuing again, and it is even reported that a second icon of the Archangel Michael is weeping from the original church as well. Large crowds have gathered to venerate the icon and have been anointed with the holy myrrh.

Source

Architectural Office reports Weeping Icon not Tampered

Rhodosreports  posted a letter from the Greek Architectural bureau that reports the results of their investigation of the wood, veneer, and paint of the icon made because of a request by the Metropolitan of Rhodes. It appears that the Metropolitan wants to conduct an adequate investigation of the phenomenon.

The scientists dispatched by the state found that the icon had not been tampered with in any way.

P.S:  The Four Ruling Archangels are Uriel, Gabriel, Raphael, Michael

Not only are the Four Archangels Uriel, Gabriel, Raphael, and Michael in charge of the Cardinal Directions and Four Elements, they also have part-time responsibilities in certain unique areas. In short, they are not just Archangels, but Patron Angels as well.

The Patron Angels most in vogue in the Ethiopian church are: St. Michael the Archangel, St. Gabriel, St. George, the Virgin Mary, St. John the Baptist, Tekla Haimanot, Gebre Menfese Kidus, St. Petros etc.

Michael means, ‘Like unto God’

REFERENCE: Daniel 10:13,12:1; Jude 1:9 and Revelation 12,8.

  • Insomnia- (Michael)
  • Repentance- (Michael, Uriel, or Raphael)
  • Righteousness- (Michael)
  • Snow- (Salgiel or Michael)
  • Truth- (Amitiel, Michael, or Gabriel)
  • Chaos- (Michael or Satan)
  • War- (Michael or Gabriel)

__

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

ቅ/ሚካኤል የአሥር ዓመት ዓይነ-ሥውር አበራ — Miracles of Archangel Michael

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 20, 2011

የአገራችንን ዓብያተ ክርስቲያናት ልዩና ቅዱሳዊ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል የቤተክርስቲያኖቹ ሕንፃዎች ዛፎችንና አእፅዋታትን ከተፈጥሮ ጋር በተስማማ መልክ አብቀለው ለምዕመናኑ አመች የሆነ ሁኔታ መፍጠር መቻላቸው ነው።

እላይ ቪዲዮው ላይ በከፊል እንደሚታየው ምዕመናኑ የቤተክርስቲያኖቹ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙት ውብ የተፈጥሮ ሣሮች፡ አበቦች ወይም ዛፎች አጠገብ በመሆን እንዲሁም ቀዝቀዝ ያለውንና ነፋሻማውን ንጹህ አየር እየተቀበለ ለፈጣሪው ጸሎቱን ያደርሳል።

ብዙ ዓብያተ ክርስቲያናትን በመላው ዓለም ተዘዋውሬ ለማየት በቅቻለሁ፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በቀላሉ ሊያገናኙ የሚችሉትና ለመንፈሳዊ ሕይወት በጣም አመቺ የሆኑ ዓብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ እንደሚገኙ አሁን ለመገንዘብ በቅቻለሁ። ይህን ለመሰለው ጸጋ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል። ምናልባት ይህ እድል አሁን በእጃችን ስላለ ላንገነዘበው እንችል ይሆናል፡ ሆኖም ግን በመልክአምድር እንደ አዲስ አበባ ከፍ ብለው በሚገኙ ቦታዎች ላይ የቤተክርስቲያኖች ቁጥር በዓለም በብዛት የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው። ይህ እራሱ እንደ አንድ ትልቅ ምልክት ሊሆነን ይገባል፡ ቤተክርስቲያን ልጆቿን ለመጭው ጊዜ እያዘጋጀች ነውና!

በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።” {ኢሳያስ 22}

/ሚካኤል የአሥር ዓመት ዓይነሥውር አበራ

የደወሌ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከድሬዳዋ ማሥራቃዊ ክፍል በኢትዮጵያና በጅቡቲ ወሰን አቅራቢያ በረሃማ በሆነችው ከተማ ነው።

በደወሌ በረሃማ ሥፍራ ላይ በተመሠረተው የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ተአምራት ታይቷል።

ከነዚህም አንድ ዓይነሥውር ከማየቱም በላይ ሁለተኛው ሊቀ መላእክት ቅ/ሚካኤል የተወሰደበትን ቆርቆሮ በተአምር ወደ ቤተ መቅደሱ መመለሱ ነው።

ዓያናቸው የበራው ግለሰብ አቶ ጥላሁን ታደሰ የሚባሉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ለዓይናቸው መታወር መነሻው በውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የቦኖ ውሃ አስቀጂ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ቢርካውን ሲከፍቱ እንደ ደም ያለ ነገር ይታያቸዋል ከዚህም ጋር የጋዜጣ ንባብ ሱስ ስለነበራቸው አዘውትረው ጋዜጣ ያነቡ ነበር። በእነዚህ ሁለቱ ምክንያቶች በየትኛው ዓይናቸው እንደጠፉ በትክክል ባይታወቅም ዓይናቸው ደም ካየበት ጀምሮ እየደከመ መምጣቱን በዝርዝር ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን እንዳስገነዘቡት ከልጅነቴ ጀምሮ ቅ/ሚካኤልን እወደዋለሁ አከብረዋለሁ እዘክረዋለሁ ግን ዓይኔ በመታወሩ ምክንያት ከሥራ ተወገድኩ ለመኖር ስል አንድ መሪ ልጅ ይዤ ከድሬዳዋ ደወሌ በመመላለስ የጫት ንግድ ጀመርኩ በዚህም ምክንያት በሄድኩ ቁጥር በረኸኛው ቅ/ሚካኤል በድርሳንህ እንደሚነገረው ብዙ ተዓምር ሠርተሃል በእኔም ላይ ተአምርህን አሳይ እለው ነበር። በንግዱ የዕለት ጉርሴን የዓመት ልብሴን በሚገባ እያገኘሁ የደወሌን ቅ/ሚካኤል አጥብቄ እማፀነው ነበር። ዕለቱ ማክሰኞ ሐምሌ 12 በዚሁ ዕለት የደወሌው ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተባርኮ እንደሚገባ ባለቤቴ ነገረችኝ እኔ ግን እጄም እግሬም በመተሣሠሩ ምክንያት አንቺ ሄደሽ አክባሪ አልኳት ሄዳ አክብራ ተመለሰች።

በዚሁ የቅ/ሚካኤል ዕለት ልጄን ይዤ ዳቦዬን አቅርቤ ከዘከርኩ በኋላ ከጐረቤቶቼ ጋር ጠበሉን ጸዲቁን ቀምሰን ቅ/ሚካኤልን አመስግነን ጐረቤቶቼ ሲወጡ ጋደም አልኩ እንቅልፍ ያዘኝ በእንቅልፍ ላይ እንዳለሁ አንተ አንተ የሚል የጥሪ ድምፅ ሰማሁ ድምፁም ተደጋግሞ መጣ ብድግ አልኩ ልጁን ብጠራው የለም ነገሩ ግራ አጋባኝ በቤቴ ወለል ላይ በመተከዝ እንዳለሁ አንተ አንተ አታየኝም እንዴ? አለኝ እኔም መልሼ እኔ እኮ ዓይን የሌለኝ በመሆኔ ላይህ አልችልም አልኩ፤ መልሶም እኔ የደወሌው የመቶ አለቃ ኃይለ ሚካኤል ነኝ እንዴት አታውቀኝም አለኝ እኔም በደወሌ የማውቀው መቶ አለቃ ገበየሁን ነው አልኩት ዕለቱ ቅ/ሚካኤል በመሆኑ ከልጅነት የምማፀነው ቅ/ሚካኤል ይሆናል በዬ አስብ ነበር።

ሆኖም የደወሌው መቶ አለቃ ኃይለ ሚካኤል ነኝ ሲለኝ ልቤ በደስታ እየመላ መጣ እሱም በመቀጠል የለበስኩት ምንድር ነው? የእኔስ መልክ ምን ይመስላል? ሲል ጠየቀኝ፤ እኔም የለበሰው ልብስ በኮከብ የተጥለቀለቀ መሆኑንና መልኩም ቀይ እንደሆነ ነገርኩት ከዚህ በኋላ ለ10 ዓመታት ብርሃን አጥቶ የኖረው ዓይኔ ለማየት በመታደሉ በደስታ ተመላሁ ከዚሁም ቀጥሎ መሉ እንደ ብርሃን የሚያበራው ይኽ ሰው በቀጥታ እያየሁት የወርቅ ኃብል በአንገቴ ላይ አጠለቀልኝ የዓይኔን ብርሃን አረጋግጦ የድሮውን የወታደሮች ካኪ ልብስ አለበሰኝ ወርቁንም ሆነ ልብሱን ለማንም እንዳትሰጥ በማለት አስጠነቀቀኝ ከእኔ ተሠወረ።

ከተሠወረ በኋላ ለእኔም ሆነ ለጐረቤቶቼ ነገሩ እውነት አልመሰለም ባለ 50 ባለ 25 ባለ 10 ሳንቲም ገንዘብ በእግሬ ሥር እየጣሉ ይኽ ምንድር ነው? እያሉ ፈተኑኝ ሁሉንም ነገርኳቸው ይህን ሲያረጋግጡ ደስታው ልዩ ሆነ።

እግዚአብሔር ይመስገን የቅ/ሚካኤል ተረዳኢነት አማላጅነት በሁሉም ሰዎች ዘንድ ለዘለዓለም ይኑር” ማለታቸውን የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በወቅቱ ገልጿል።

ከዚህም ሌላ ከባድ ነፋስ የተቀላቀለ ኃይለኛ ዝናብ ጥሎ በከተማ ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ሕንፃዎች ተሰነጣጠቁ፥ በላያቸው የነበረው የጣራ ቆርቆሮ የነፋሱ ኃይል ተገነጣጠሎ ሲወስድ ቀደም ሲል ከቤተ መቅደሱ ላይ ተወስዶ የነበረውና ግለሰቦች በራስ ወዳድነት ይጠቀሙበት የነበረው ቆርቆሮ በዚሁ ከባድ ነፋስ ተጭኖ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በመምጣት በቅጽረ ግቢው ውስጥ ተቀመጠ፤ የተወሰደው ቆርቆሮ ተመልሶ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በመገኘቱ ቅ/ሚካኤል የሠራውን ገቢረ ተአምር ሕዝበ ክርስቲያኑ በአድናቆት ተመልክቶታል።

___________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: