ባለፈው በሳምንት እስልምናን አልፈልግም በማለቷ ቤተሰቦቿ እንደሚገድሏት በመፍራቷ ከሳውዲ አረቢያ ያመለጠችው ወጣት ራሃፍ ሞሃመድ አል ኩኑን በባንግኮክ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ የቁም እስረኛ ነበረች፤ የሳውዲ መንግስትም ክትትል አድርጎባት አባቷን እና ወንድሟን በመላክ ወደ ሳውዲ በግድ እንድትመለስ ሞክሮ ነበር፥ አልተሳካም፤ በመላው ዓለም ድጋፍ አግኝታ ስለነበር አሁን በካናዳ መንግስት ጥገኝነትን አግኝታ ትናንትና ወደ ቶሮንቶ ለመብረር በቅታለች።
ወጣት ሳውዲዎች አገራቸውን ለቀው መውጣት ሲሹ፥ አንበጦችና በረሮዎች ደግሞ ወደ መካ ሃጅ ያደርጋሉ!
ልክ እንደ እርሷ ተመሳሳይ የሆነ ሁኔታ ላይ ያሉ በጣም ብዙ ሴቶች አሉ፤ የእኛንም እህቶች ጨምሮ ፥ ዓለም ግን ቸል ብሏቸዋል!
ጎበዟ ወጣት እስልምናን አልፈልግም፤ በድንኳን መሸፋፈኑንም አልሻም በማለት ከእስልምና ባርነት ነፃ ስትወጣ፥ የኛ አገር መሀመዳውያን ሴቶች ደግሞ ፓርላማ ውስጥ ሳይቀር ተሸፋፍነው በመግባት ባርነቱን መርጠዋል። የተዘበራረቀበት ዓለም!