Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Afghan Minister’

በጀርመን የብስክሌት ተላላኪ የሆነው የአፍጋኒስታን ሚኒስትር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 1, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

በአፍጋኒስታን የቀድሞው የመገናኛ ሚኒስትር የነበሩት ሰይድ ሳዳት ባለፈው ዓመት ወደ አገሪቱ ከተዛወሩ በኋላ አሁን በምስራቅ ጀርመኗ ላይፕዚግ ከተማ ብስክሌት እየጋለቡ ምግብ ያቀርባሉ። የ ፵፱/49 ዓመቱ ፖለቲከኛ ሲናገሩ፤ “ለመንግሥት የሠራሁ ከፍተኛ ባለሥልጣን ስለነበርኩ አገር ቤት ያሉ አንዳንድ ሰዎች ዛሬ ምግብ አመላላሽ መሆኔን ተቃውመው ተችተውኛል። ተራ ሥራ እየሠራሁ ነው፤ እና የጥፋተኝነት ወይም የጸጸት ስሜት እንዲሰማኝ የሚያደርግ ምንም ነገር የለም። በፊት ሚንስትር ሆኜ ሕዝቤን ሳገለግል ነበር፤ አሁንም ምግብ በማቅረብ ሰዎችን እያገለገልኩ ነው።” ብለዋል።

“ከንቱ ኩራትን” ወዲያ አሽቀንጥሮ ወደ ቆሻሻ ቅርጫት የሚጥልና ጥገኛ ላለመሆን የሚጥር ጎበዝ ሰው ማለት እንዲህ ነው! በተቃራኒው ግን በታሊባኖቹ የተባረሩት የአፍጋኒስታን ፕሬዚደንት ግን ልክ እንደ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ሚንስትሮቹ ከሕዝባቸው የሠረቁትን ገንዘብ በጆንያ ተሸክመው በተባበሩት የአረብ ኤሚራቶች ወደገነቡት ወደ ዱባይ ቪላቸው ፈርጥጠዋል።

ትናንትና ንጉሥ ዛሬ ተራ ሰው የመሆን እጣ ፈንታ የሁላችንንም በር ሊያንኳኳ ይችላል።

✞✞✞[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፪፥፲፮]✞✞✞

የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።

✞✞✞[ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ ፲፪፥፪]✞✞✞

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

_______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Life, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: