የግብፅ የውሃ ሀብት እና መስኖ ሚኒስትር ሙሀመድ አብደል–አቲ፦ ‘የኢትዮጵያ የከብት እርባታ ከግብፅ እና ከሱዳን ድርሻ የበለጠ የውሃ ሀብት ይፈጃል‘ ስለዚህ ኢትዮጵያ አባይን መንካት የለባትም።
የአረብ ተንኮል መቼስ፣ ኢትዮጵያውያንን ምሳሌያዊ በሆነ መልክ በተዘዋዋሪ “ከብቶች” ማለቱ ሊሆን ይችላል። ከሆነም እውነቱን ነው፤ “ወላሂ!” ብሎ የሚምል መሪ የሥልጣን ወንበር ላይ መቀመጡ “ከብቶች” ሊያሰኘን ይገባል።
ያም ሆነ ይህ፡ ከግብጾች የዱር አህያነትና እብደት የከፋው ደግሞ የሕዳሴውን ግድብ አስመልክቶ በትናንትናው ዕለት በእንግሊዙ “ደይሊ ሜይል” ጋዜጣ ላይ የወጣው ሰፊ ዘገባ ነው። ርዕሱ፦
“በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ጦርነት ሊፈጥር የሚችለው ግድብ፤ በቻይና ኩባንያዎች የተገነባው የ 3 ቢሊዮን ፓውንድ አንጋፋ ፕሮጀክት መሙላት ስለጀመረና የአባይ ወንዝን ለመቀነስ ስለሚያሰጋው ውጥረት ተፈጥሯል፡፡“
“The dam that could start a war between Egypt and Ethiopia: Tensions rise as £3billion mega-project built by Chinese firms begins filling up – the Nile to a trickle”
ይህ ዘገባ እስካሁን ከሺህ በላይ አስተያየቶችን አግኝቷል። ለኢትዮጵያ–ነክ ዘገባዎች ይህ ያልተለመደ ክስተት ነው። ከዚህ በይበልጥ የሚያስገርመውና የሚያስቆጣው ደግሞ ዘጋቢው የተጠቀመባቸው ቃላት እና የአስተያየት ሰጭዎቹ አላዋቂነት፣ መረጃ–አልባነትና ለኢትዮጵያ ያላቸው ንቀት እና ጥላቻ ነው።
ለምሳሌ የዘገባው ፀሐፊ (ጠፍቶት አይመስለኝም) ሆን ብሎ እንዲህ ብሏል፦
“ኢትዮጵያ ከመኖሯ በፊት በ 1929 ዓ.ም ላይ የተፈረመ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነት ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ ብቸኛ መብት አላት የሚል ዋስትና ሰጥቷታል“
“The sticking point is a colonial-era treaty signed in 1929, before Ethiopia existed, which guarantees Egypt almost exclusive rights over the waters of the Nile.”
በተረፈ ግድቡን ከቻይና ጋር ለማያያዝ የታቀደው ነገር በአንባብያኑ ዘንድ ውጤታማ ሆኗል፤ አብዛኛዎቹ አስተያየቶች ቻይናን የሚኮንኑ ናቸውና። በተረፈ “ግብጽ ግድቡን በቦምብ መደብደብ አለባት ፥ “ግብጽ የእንግሊዝን ‘Lancaster‘ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን መግዛት አለባት“
የሚሉትን ፀረ–ኢትዮጵያ የሆኑ የጥላቻ ቃላትን ለማንበብ ይቻላል!
አዎ! ኤዶማውያኑ የዔሳው አሳሞች እና እስማኤላውያኑ የእስማኤል ፍየሎች ህብረት ፈጥረዋል በዲያብሎስ አንድ ናቸውና።