Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2024
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    2930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ወደ ክርስቶስ መምጣት’

ከጴንጤና እስልምና ወደ ተዋሕዶ | የአሜሪካዊቷ እህታችን ድንቅ ምስክርነት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 3, 2019

ቪድዮው ላይ፡ እህታችን (ሚያ ደብሪቱ) የሚከተሉትን ኃይለኛ ቃላት ስለ እራሷና ሙስሊም ስለነበረው ባሏ ቆንጆ በሆነ መልክ አካፍላናለች፦

እንዴት ተዋሕዶ ለመሆን በቃሽ የሚለው ጥያቄ ሁሌ ስጠየቀው የነበረው ጥያቄ ነው፤ አሁን

አጋጣሚውን በመጠቀም ይህን ቪዲዮ ሠርቻለሁ።

እኔ ፕሮቴስታንት ሆኜ ነበር ያደግኩት፤ በሳምንት ብዙ ጊዜ ቸርችእንሄድ ነበር።

ሳድግ መጠነኛ የሆነ አኗኗር ነበረን፤ በልጃገረድ ጊዜዬ በግሩፕ ሆነን ወደ ካናዳ እና ጃሜይካ እንጓዝና ስለመንፈሳዊው ህይወታችን እርስበርስ እንነጋገር ነበር ሁልጊዜ በክርስትና እምነት ተከብቤ እኖር ነበር።

ከፍተኛ ትምህርት ቤት እያለሁ አንዲት ልጃገረድ ተዋወቅኩ፤ ወዲያውም ልዩ እና ክርስቲያናዊ የሆነ ነገር እንዳላት ስለአየሁባት መንፈሴ ተነሳሳ።

ሰዎች አደነቋት አላደነቁት ግድ የማይሰጣት፡ በማንነቷ የምትተማመን እና እርግጠኛ የሆነች እንደሆነች ታዘብኩኝ።

በከፍተኛ ትምህርት ቤት ሁሉም ሰው ተወዳጅ መሆንን ይመኛል፤ ልጅቷ ግን አድናቆትን ማግኘት የማትፈልግ ሆና ሳያት ምን ይዛ ይሆን? በማለት እራሴን እጠይቅና እቀናባትም ነበር።

ከዚያም መነጋገር እንደጀመርን፤ ክርስቲያን ነሽን? የየትኛውስ ቤተክርስቲያን አባል ነሽ? በዬ ጠይቅኳት።

እርሷም የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ብላ መለሰችልኝ። ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚለውን ሰምቼው አላውቅም ነበር።

በተገናኘን ቁጥር ብዙ ጥያቄዎች እጭንባት ነበር፤ አቤት ትዕግስቷና ትህትናዋ!

ባወቅኳት ቁጥር ስለሷ የማወቅ ፍላጎቴ በጣም ጨመረ፤ በዚህ መልክ ስለተዋሕዶ

እምነት ትውውቅ አደረግኩ።

ከሰላማዊት ጋር አሁንም እንገናኛለን። ጠንካራ እምነት ያላት ሴት ናት፤ እስካሁን ድረስ ታበረታታኛለች፤ እርሷን በማወቄ እድለኛ ነኝ፤ ተባርኬአለሁ።

አሁን ባለትዳር ነኝ ልጆችም አሉኝ። በለቤቴ ለ20 ዓመታት ያህል የእስልምና ተከታይ ነበር። ከእርሱ ጋር ስንተዋወቅ፡ በሥላሴ ባምንም፡ ክርስትናን በደንብ አልተገብረውም ነበር።

የክርስቲያናዊ ሕይወት አልነበረኝም፤ ወደ ቤተክርስቲያንም አልሄድም፣ መጽሐፍ ቅዱስን አላነብም ነበር። ስለዚህ በወቅቱ ሙስሊሙን ሰው ማግባቴ እምብዛም አላሳሰበኝም። አክራሪ ሙስሊም ባይሆንም፤ ያው ሙስሊም ነበር።

አንድ ቤተሰብ እምነት ሊኖረው ይገባልና፡ አንድ ወቅት ላይ ሁለታችንም አምላክን በአንድ ላይ ሆነን መፈለግ ጀመርን።

ባለቤቴ ከኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ስለሚሠራ፤ ስለተዋሕዶ የመስማት እድሉ ነበረው፤ ነገር ግን ወደ ቤተክርስቲያናቸው ሄደን አናውቅም ነበር።

ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

ወደ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገባ የማይረሳና በጣም ልዩ የሆነ ስሜት ተሰምቶን ነበር፤ መዓዛው፣ መንፈሱሁሉም ሁኔታው መንግሥተ ሰማያዊ በሆነ ነገር የተከበብን ሆኖ እንዲሰማን አድርጎን ነበር።

ከዚህ በፊት እዚህ ቦታ ላይ ተገኝቼ አላውቅም፤ ግን ከቤተክርስቲያኑ ጋር የሚያያዝ ነገር እንዳለኝ የሆነ ልዩ መንፈስ በውስጤ ይነግረኝ ነበር።

ከዚያም እንደገና ወደቤተክርስቲያኑ መመጣት ፈለግን ቄሱ የቅድስት ቤተክርስቲያኗን መሰረታዊ ትምህርቶች እንደሚሰጡ ስንሰማ አላመታንም ወዲያው ቀጠሮ ያዝን።

ምክኒያቱም፡ በዕለቱ እግዚአብሔር ስለተናገረን ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ የተጠራን ሆኖ ስለተሰማን ነው። እንግዲህ ልዩ ስብከት በመስማታችን አይደለም የተማረክነው፤ እግዚአብሔር እዚህ በመገኘቱ እንጂ። እግዚአብሔር እዚህ እንዳለ እርግጠኞች ነን!

ይህችን ቤተክርስቲያን ምን ልዩ ያደርጋታል?

ሌሎች ቸርቾች ውስጥ መንፈሳዊመሳይ ከሆነ እብደት የፈለቀ ጩኸትና ጭብጨባ፣ ዳንኪራና ጭፈራም የበዛበት ነገር ታዝበናል፤

በተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ግን ይህ የለም፤ በጣም እውነተኛና ኃይለኛ የሆነ ነገር አለ፤ ይህን የመሰለ ተሞክሮ ገጥሞን አያውቅም፤ ባሌም ወዲያው፦ “ማነው ክርስቶስ? ማነው ኢየሱስ?” እያለ መጠየቅና መመርመር ጀመረ።

ምክኒያቱም፡ በሌላ ቦታ በሕይወቴ ያለተሰማኝ ነገር ነው እዚያ ቦታ ተሰምቶኝ የነበረው። በሕይወቴ ብዙ ቸርቾችን ጎብኝቻለሁ፤ እዚህ የተሰማኝ ግን ሌላ ቦታ ተሰምቶኝ አያውቅም።

ቀጣይ እርምጃዎችን መውሰድ

የቤተክርስቲያኗ መሰረታዊ ትምህርቶች የሚሰጡበትን ክፍል በየሰንበቱ ሳናቋርጥ መከታተል ጀመርን፤ በጣም ልዩ የሆነ ጊዜ ነበር። ቀስበቀስ ስለ ተዋሕዶ እምነት የበለጠ እውቀት ከመሠረቱ አንስቶ መገብየት ቻልን።

ስለ ጥምቀት፣ ንስሐ ስለመግባትና ስለ ሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ተማርን። እነዚህን ምስጢራት የተከተለ ሕይወት በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ተረዳን። ክርስቲያኖች ይህን ዓይነት ሕይወት ነው መኖር ያለባቸው።

ወንጌልን መስበክ

ኦርቶዶክሶች በየቦታው፣ በየጎረቤቱ፣ ትምህርት ቤቱና ሥራ ቦት መስበክ መቻል አለብን። ሰላማዊት ወንጌል ሰባኪ አልነበረችም፣ ግን ጣቷን ማካፈል የምትወድ ወጣት ሴት ነበረች። ዓይነ አፋር ብትሆን፣ እምነቷን ለማካፈል ፈቃደኛ ባትሆንና ብታመነታ ኖሮ እኔ አሁን ያለሁበትን ሕይወት አላገኝም ነበር። እግዚአብሔር ነው ከእርሷ ጋር ያገናኘኝ።

እምነታችንን መኖር ይገባናል፣ ፍቅርን ማሳየት አለብን። አስፈላጊ ሲሆን ብቻ መናገር ይኖርብናል፤ ስለ እምነታችን ሁሉንም ነገር ለሁሉም ሰው መናገር አይጠበቅብንም።

ልዩ ምስጋና

በዚህ አጋጣሚ ማሕበረ ቅዱሳንን እንዲሁም ኒውዮርክና ኒው ጀርሲ ያሉትን የቅዱስ ገብርኤልና ቅ/ ሥላሴ ዓብያተ ክርስቲያናት ከልብ አመሰግናለሁ። ሁሌ ስንበት ሰንበት ወደዚያ በደስታ እሄዳለሁ።

ቦስተንም ያሉ ወንድሞችና እህቶች ከቤተሰቤ የበለጡ ቤተሰቦቼ ናቸው። ብዙ ረድተውኛል። ክፍሌ እና ፀሐይ፣ ቀሲስ እስክንድር እና ቆንጆ ቤተሰቡ፣ ቀሲስ ኃይለ ገብርኤል፣ ኤደን እና ቤተሰቦቿ፣ ሀማላ፣ ቲዋን ሁላችሁንም በጣም እወዳችኋለሁ፤ በስም ያልጠራኋችሁም፤

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »