Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘፪ሺ፲፭’

Double Moon During Hossana ( Palm Sunday ) Celebrations

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 9, 2023

🌿𝐇𝐚𝐩𝐩𝐲 𝐇𝐨𝐬𝐚𝐧𝐧𝐚 (𝐏𝐚𝐥𝐦 𝐒𝐮𝐧𝐝𝐚𝐲)!🌿

Hossana ( Palm Sunday ) is celebration of entry of Jesus to Jerusalem riding a donkey. Children in Jerusalem sang Hossana praising Jesus Christ. Source: cnewa.org. The day is celebrated in a peculiar way. It’s very common to see laity wearing cube shaped palm ring and wearing palm stripe on the head.

The Feast of Hosanna -Palm Sunday has been celebrated in Ethiopia since the earliest days of Christianity. Celebrated a week before Easter, the day marks the beginning of the Holy Week and commemorates the triumphal entry of Jesus Christ with his disciples into Jerusalem. On this day Ethiopian Orthodox laities wear headbands of palm leaves, a reminder of the palm leaves that were laid by a huge crowd of people when Jesus arrived at Jerusalem. The best place to observe this ceremony in Ethiopia is at Entoto St. Mary Church in Addis Ababa and St. Mary Zion Church in Axum, where on the 28th November 2020 Muslim soldiers from Ethiopia, Eritrea and Somalia armed by Iran, UAE and Turkey went on the rampage and massacred over 1000 Orthodox Christians.

Axum, a Holy City in Ethiopia’s northern Tigray region, whose main Church of Our Lady Mary of Zion is believed by Ethiopian Orthodox Christians to hold The Biblical Ark of Covenant.

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሆሣዕና ፳፻፲፫ ዓ.ም + የ፳፻፲፪ ዓ.ም ተዓምር በጨረቃ ላይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 9, 2023

🌴 ሆሣዕና በአርያም | ሰማያዊ ልዑል አምላክ ትሑት ሆኖ ተገለጠ 🌴

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሆሣዕና በአርያም | ሰማያዊ ልዑል አምላክ ትሑት ሆኖ ተገለጠ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 8, 2023

🌴 ሰውን ከወደቀበት የበደል ጉድጓድ ያወጣው ዘንድ እግዚአብሔር ክንዱን ወደ ዓለም ላከ፡፡ ሰው ሆኖ የተገለጠው የእግዚአብሔር ክንድ በጉድጓድ ተጥሎ የነበረን በዚያም በሥጋ በነፍስ፤ በውስጥ በአፍአ ቆስሎ የነበረ አዳምን በትህትና ሁለተኛ አዳም ሆኖ በሥጋ የቆሰለውን በለበሰው ሥጋ ቆስሎ;በነፍስ የታመመውን በትምህርት አዳነ፡፡ ከእርሱ አስቀድሞ ሰውን ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከባርነት ወደ ነፃነት የሚያመጣ ባለመኖሩ እርሱ ሁሉን የፈጠረ ሁሉን የሚያኖር እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ለሰው መድኃኒት ሆነ፡፡ በሞቱም መድኃኒትነትን አሣየ፡፡ በነቢይ መድኃኒተ ፈነወ እግዚአብሔር ለሕዝቡ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ መድኃኒትን ሰደደ፡፡ (መዝ.፻፲፥፱) ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፡፡

ክርስቶስ ባለ መድኃኒት ሆኖ በኃጢአት ለታመሙ ደቂቀ አዳም ሁሉ ሕይወትን ይሰጥ ዘንድ ወደዚህኛው ዓለም መጣ፡፡ በምድራዊ ሥርዓት እንደምናየው መድኃኒትና ባለ መድኃኒት እንደሚለያዩ አይደለም፡፡ ሁለቱንም እርሱ በመምጣቱ (ሰው በመሆኑ) ፈጸመ እንጂ፡፡ መድኃኒት አድርጎ ሥጋውን ደሙን የሰጠ እርሱ ነው፡፡ በካህናት አድሮ ሰው በንስሐ ሲመለስ መድኃኒት ወደሆነው ወደ ራሱ የሚመራ እርሱ ነው፡፡

ክርስቶስ መድኃኒት መሆኑ በሕማሙ እና በሞቱ ነው፡፡ በእመቤታችን ማኅፀን የተጀመረው የእርሱ መድኃኒትነት እና ፍቅሩ ፍፃሜውን ያገኘው በሕማሙ እና በሞቱ ነው፡፡ መሐሪ ንጉሥ እርሱ መሆኑን ይገልጥ ዘንድ በፈቃዱ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ከመግባቱ አስቀድሞ ከኢየሩሳሌም ፲፮ ያህል ምዕራፍ በምትርቀው በቤተፋጌ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ነበር፡፡

ከደቀ መዛሙርቱም ሁለቱን (ማለትም ጴጥሮስን እና ዮሐንስን) በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ ወዲያውም ወደ እርሷ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበትን ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ፡፡ (ማር ፲፩፡፪) በማለት አዘዛቸው፡፡ ዳግመኛም ሰው ወዳልገባባት የተዘጋች የምሥራቅ ደጅ ወደ ምትባል ወደ ድንግል መጥቶ ዘጠኝ ወር ማኅፀኗን ከተማ አድርጎ እንደኖረ፤ ማኅየዊት ከምትሆን ሕማሙ በኋላም ሰው ባልተቀበረበት መቃብር እንደተቀበረ፤ አሁንም ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት ማንም ሰው ያልተቀመጠባቸውን በሌላ መንደር የሚገኙ አህያንና ውርንጫን እንዲያመጡ ደቀመዛሙርቱን አዘዘ፡፡

የፍጥረት ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በልደቱ እስትንፋሷን የገበረችለትን አህያ አሁን ደግሞ በፈቃዱ ስለ ሰው ሁሉ ሊሞት ሲል ንጉሥነቱን ሊያስመሰክርባት ወደደ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ካለው ፲፮ ምዕራፍ አሥራ አራቱን በአህያ ላይ ሳይቀመጥ በእግሩ ሄደ፡፡ ከዚያም ሁለቱን ምዕራፍ በአህያ ላይ በመቀመጥ ከተጓዘ በኋላ የኢየሩሳሌምን መቅደስ ሦስት ጊዜ በውርጫዋ ላይ በመሆን ዞረ፡፡ በዚህም ለሰው ሁሉ ያለው ቸርነቱ፣ ሕግ የተሰጣቸው አይሁድ እና ሕግ ያልተሰጣቸው አሕዛብ ላይ እኩል ቀንበርን መጫን እንዳይገባ አጠየቀ፡፡

ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሄድ ብዙ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፣ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቆረጡ ያነጥፉ ነበር፡፡ (ማር. ፲፩፡፰)፡፡ ከዚያም ሰዎች ሆሣዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው (ማር. ፲፩፡፱) በማለት አመሰገኑ፡፡ ይህም ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን እኛ ክርስቲያኖች ቡሩክ ስሙ ለእግዚብሔር ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው፡፡ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ ክርስቶስም ምስጉን ነው በማለት የአብ እና የወልድን መስተካከልን ገልጸን ጌታን እናመሰግናለን፡፡ ጌታን የሚከተሉት ሰዎች ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር (ማር.11፲፩፡፲) ይኸውም በልዕልና፣ በሰማይ ያለ መድኃኒት፣ ከሰማይ የመጣ መድኃኒት ማለት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር እና መሓሪ መሆን በክርስቶስ ሕማም እና ሞት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተገልጧል፡፡ ክርስቶስ የተቀበለው ሕማም እና ሞት የእርሱን አምላክነት እና ንጉሥነት አልሸሸገውም፡፡ እንደውም ዙፋኑን መስቀል በማድረግ ንጉሥነቱን በመድኃኒትነቱ ገልጿል እንጂ፡፡ በነቢይ እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፣ እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፤ በምድር መካከልም መድኃኒትን አደረገ መዝ. ፸፫፤፲፪ ተብሎ የተነገረው እግዚአሔብር ድኅነትን በፈጸመበት ማዕከለ ምድር ሲሰቀል በመድኀኒትነቱ ንጉሥነቱን መግለጡን ያመለክታል፡፡ ዳግመኛም አንሰ ተሰየምኩ ንጉሠ በላዕሌሆሙ በጽዮን በደብረ መቅደሱ፤ እኔ ንጉሥ ሆኜ ተሸምኩ በተቀደሰው ተራራ ላይ (መዝ.፪፡፮) ተብሎ የተነገረው ኦርቶዶክሳውያን አበው እነርሱ (አይሁድ) ሰቅለነው ገድለነው ኋላ ፈርሶ በስብሶ ይቀራል ይሉኛል እንጂ እኔ ደብረ መቅደስ በምትባል በመስቀል ላይ ነግሻለሁ በማለት ይተረጉሙታል፡፡

ጌታ ንግሥናው ክብሩ የተገለጠበት ሆነ እንጂ መታመሙ እና መሞቱ ውርደት ክብሩንም የሚሸሽግ አይደለም፡፡ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማት ወልዱ ክብረ ወስብሐት፣ የልጁን ሕማማት ክብርና ምስጋና አድርጎ የሰየመ እግዚአብሔር ይመስገን አለ፡፡ እኛን ያከበረበት በመሆኑ ሕማሙ ክብር እንደተባለ እናስተውል፡፡ በመስቀል ላይ ሆኖም በቀኝ የተሠቀለው ወንበዴ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ (ሉቃ ፳፬ )በማለት ንጉሥነቱ መስክሮለታል፡፡ ለዚህ ነው ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በምስጋና መግባቱ መድኃኒትነቱን እና ንጉሥነቱን ያሳያል ያልነው፡፡ ዳግመኛም ሁሉን የያዘ ጌታ በአህያ ላይ መቀመጡ ትህትናው ያስረዳል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል ዲባ ዕዋለ አድግ ነበረ፡፡ በማለት ሰማያዊ ልዑል አምላክ ትሑት ሆኖ እንደተገለጠ ተናገረ፡፡

ጌታ ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ድንቅ የሆኑ እና ተአምራትን ለሰዎች አሳየ (ገለጠ)፡፡ እም ሆሳዕናሁ አርአያ ተአምረ ወመንክረ (ቅዳ. ጎርጎ.ዘኑሲስ) እንዲል፡፡ ይኸውም በአህያ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አእምሮ ጠባይዕ ያልቀናላቸው ሕፃናት ዕውቀት ተገልጾላቸው ሆሳዕና በአርያም እያሉ ጌታ በማመስገናቸው ነው፡፡ ዳግመኛም በከሃሊነቱ መናገር ለማይችሉ ዕውቀት ለሌላቸው ድንጋዮች ዕውቀት ተሰጥቷቸው መናገር ችለው ጌታን አመስግነዋል፡፡ እርሱ የባሕርይ አምላክ መሆኑ በሰውነቱም ቀድሞ በበደል ምክንያት ለሰው ከመገዛት ውጪ የሆኑ ፍጥረታት ዳግመኛ በሥጋዌ ለሰው እንደተገዙ ከዚህ ሁሉ ማስተዋል ይገባል፡፡

ጌታ ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ልጅነት እና ተአምራት ማድረግን ገለጸ፡፡ እም ሆሳዕናሁ አርአያ ጸጋ ወኅይለ እንዲል (ቅዳሴ ጎርጎ. ዘኑሲስ)፡፡ የእርሱ ማዳን ከሰው ተወስዶበት የነበረ የጸጋ ልጅነት እንዲመለስለት አድርጋ በልጅነት ላይ ገቢረ ተአምራት (ተአምራትን ማድረግ) ገልጿል፡፡ ይኸውም እርሱ በረድኤት አድሮባቸው ድንቅ ተአምራትን ለሚያደርጉ ቅዱሳን መሠረት ነው፡፡ በተጨማሪም ልጅነትን ካገኙ በኋላ በበደል ሲገኙ ለንስሓ የሚሆን እንባን ሠጠ፡፡ እምሆሳዕናሁ ወሀበ ፈልፈለ አንብዕ ለኅጥአን እንዲል (ቅዳሴ ጎርጎ. ዘኑሲስ) ይኸውም የበደሉትን ያከብራቸው ዘንድ፣ ኀጥአንን ከኃጢአታቸው ያነጻቸው ዘንድ እንዲሁም የሳቱትን በንስሐ ይመልሳቸው ዘንድ ነው፡፡

ዳግመኛም ጌታ መድኀኒት ከመሆኑ የተነሣ ለዕውራን ዳግመኛ ብርሃንን ሰጠ፡፡ ይኸውም ለጊዜው በተፈጥሮ ዐይን ተሰጥቷቸው የታወሩትን ፈውሶ በሥጋ ብርሃን መስጠቱ ሲሆን፤ ፍጻሜው ግን በነፍስ ዕውቀትን ከማጣት የተነሣ ዕውራን የነበሩትን ትምህርትን; ዕውቀትን ገለጸላቸው፡፡ ይኸውም የእርሱ ገንዘቡ ስለሚሆን አንድነት ሦስትነት፣ አምላክነቱን መድኃኒት መሆኑን ገለጠላቸው ማለት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዲ/ን ቢንያም፤ በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ምክኒያት በኢትዮጵያና በመላዋ ዓለም ከባድ ጦርነት አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 8, 2023

👉 ምስጋና ለ፦ ዲያቆን ቢንያም / Diyakon Binyam Frew። መልዕክቱ ከወር በፊት ነበር የተላለፈው።

አዎ! የዓለምን ጦርነት የምትመራው አክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ናት። የአውሎ ነፋሳቱንና የመሬት መንቀጥቀጡን አቅጣጫ መከተሉ ብቻ በቂ ማስረጃ ነው። አዎ! በሂደት፤ ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት፤ ላለፉት ላለፉት ሃምሳ ዓመታት፣ ላለፉት አምስት ዓመታት እየተሠራ ያለው በሕይወት የተረፈው ‘ኢትዮጵያዊ’ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እንዲጠላ ማድረግ ነው። ለዚህም ነው በቋንቁ ከፋፍለውና የሉሲፈራውያኑን ባንዲራ አስይዘው እርስበርስ በማባላት ላይ ያሉት።

ዛሬ፡ መላዋ ዓለም በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ስላለው ግፍና መከራ ዝም ጭጭ ብላለች፤ የስጋ ነገር ነውና ለወሬው ዩክሬን ትበልጥባታላች። እያየነው እኮ ነው። ምክኒያቱም፤ የመንፈሳዊውን ሕይወት በሚመለከት “በቀል የኔ ነው!” ያለን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላካችን ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ ተረክቦና ከቅዱሳኑ ጋር ሆኖ ሥራውን እየሠራ ስለሆነ ነው።

✞✞✞ የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ✞✞✞

❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፭፥ ፴፩፡፴፬]❖❖❖

የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።”

ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ(ማቴ ፳፭) ስለ ጌታችን ዳግም አመጣጥ እና በፍርድ ወንበር መቀመጥ ሲገልጽ «የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፤ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።» በማለት ጻድቃንን በበጎች፣ ኃጥአንን በፍየሎች መስሎ ጻድቃንን ለክብር በቀኝ፣ ኃጥአንን ለሃሳር በግራ ለይቶ ያቆማቸዋል። ቀጥሎም ጌታችን ክርስቶስ በፍርድ ቃል በቀኙ ያሉትን «እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።» ይላቸዋል። ነገር ግን ጻድቃን ብዙ መልካም ሥራ ሰርተው ሳለ ምንም እንዳልሰሩና እንዳላደረጉ ሆነው ከእግዚአብሔር ቸርነት የተነሳ ክብር እንደተሰጣቸው አውቀው በትህትና ቃል «ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣንይሉታል። እርሱም መልሶ በሕይወት ዘመናቸው ከእነርሱ ለሚያንሱት ያደረጉትን መልካም የቸርነትና ትህትና ሥራ እንደዋጋ ቆጥሮላቸው «እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት» ብሎ ጻድቃንን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሰዳቸዋል።

ነገር ግን በኃጥአን ላይ ከዚህ በተቃራኒ ፍርዱም ሆነ የእነሱም ምላሽ የተለየ ይሆናል። ጌታም እርሱን ባላመለኩት መጠንና ከሰይጣናት በተስማማ ሁኔታ መንገዳቸውን ባደረጉ ልክ እንዲህ በማለት ይፈርድባቸዋል፤ «እናንተ ርጕማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘለዓለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።» እነርሱ ግን ፍርዱን በመቃወም እንዲህ እያሉ ይከራከራሉ። «ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህምጌታችንም በምላሹ የርህራሄን ሥራ ለታናናሾቻችሁ አልሰራችሁም ፤ ያን አለመስራታችሁ ለኔ አለመስራታችሁ ነው ብሎ ወደ ዘለዓለም ቅጣት ይሰዳቸዋል።

ያቺ የፍርድ ቀን የዓለም ፍጻሜ ናት። በዛች ቀን መስማት እንጂ መመለስ መከራከር የለም። የዚያች ቀን የፍርድ ውሳኔ ዛሬ በምድር ላይ የምንፈጽመው የአምልኮና የመልካም ወይም የክፉ ምግባር ውጤት ነው። ዛሬ አካሄዳችንን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረግን ከእግዚአብሔር ጋር በተስፋዪቱ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እንሆናለን፤ዛሬ አካሄዳችንን ከዲያብሎስ ጋር ካደረግን ግን በግራ ከዲያብሎስ ጋር እንቆማለን፤ትሉ በማያንቀላፋ እሳቱ በማይጠፋ በገሃነም እሳት መኖር ግድ ይለናል። የዛሬ የአምልኮ አያያዛችን የፍጻሜውን ቀን ይወስነዋልና ዛሬ ሳናመነታ አኗኗራችንን እንወስን።

አባታችን አባ ዘወንጌል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለውን ነበር፦ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው” አሥር በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው የኢትዮጵያን ትንሣኤ ማየት የሚችለው” ያሉንም ትክክል መሆኑን እያየነው ነው። እንግዲህ የተበከለውና የቆሸሸው የምንሊክ አራተኛ ትውልድ ዲቃላ ሁሉ የመጽጂያ ሰፊ ጊዜና ብዙ አጋጣሚዎች ለመቶ ዓመታት ያህል ተሰጥቶት ነበር፤ ግን ዛሬም፤ አውቆቱም ሆነ ሳያውቀው፤ አብዛኛው “ኢትዮጵያዊ” 666 አውሬውን በማገልገል ላይ ነው። መላው ዓለምም ይህን አውቆታል! አሁን ጊዜው እያለቀ ነው! ይህ ማስጠንቀቂያ ከትግራይ አብራክ ለወጡትና እግዚአብሔርንና ጽዮን ማርያም እናቱን ለከዱት ለሻዕቢያዎችና ሕወሓቶችም ጭምር ነው። ወዮላቸው!

በትናንትናው ዕለት፤ አልጎሪዝሙ ጎትቶ ባመጣውና “ማገር” በተሰኘው ቻነል፤ ዶ/ር እና ፕሮፌሰር የተሰኘው አቶ ጌታቸው‘ (ሁሉም ስማቸው ጌታቸውነው፤ የትዕቢትና የዕብሪት ስም!) የተሰኘው ግለሰብ፤ “ወልቃይትንና ራያን በደማችን አስመልሰናል ቅብርጥሴ…!” ሲል ስሰማው የምጠጣው ውሃ ትን አለኝ። እነዚህ ዶ/ር እና ፕሮፌሰር ካባ የለበሱ ሃፍረተቢሶች፣ እብሪተኞች፣ ተንኮለኞች፣ ምቀኞችና ጸጸትአልባ የሉሲፈራውያኑ ቅጥረኞች/ወኪሎች አልማር ባዩንና ግትሩን መንጋቸውን ይዘው ሞኙን ሕዝብ በገፍ ለማስጨረስ ዛሬምደፍረዋል። በተለይ አሜሪካ ሆኖ እራሱን እያሳየ በየሜዲያው እየወጣ የሚለፍፈው ግብዝ ወገን ሁሉ አውቆትም ሆነ ሳያውቀው የሚሠራው ለሉሲፈራውያኑ ነው። እንግዲህ ለእነርሱም ወዮላቸው!

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፯፥፳፰]❖❖❖

እግዚአብሔር ፍርዱን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፤ ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፤ የኅጥኣን ዘር ግን ይጠፋል።”

👉 በሚቀጥሉት ዓመታት፤

  • እስከ ፲/10 ሚሊየን የሚሆኑ ጋላኦሮሞዎች ከኢትዮጵያ ምድር ይጠረጋሉ
  • እስከ ፲/10 ሚሊየን የሚሆኑ ኦሮማራዎች ከኢትዮጵያ ምድር ይጠረጋሉ
  • እስከ ፭/5 ሚሊየን የሚሆኑ ሶማሌዎች ከኢትዮጵያ ምድር/ ከአፍሪቃው ቀንድ ይጠረጋሉ
  • እስከ ፭/5 ሚሊየን የሚሆኑ አፋሮች ከኢትዮጵያ ምድር/ ከአፍሪቃው ቀንድ ይጠረጋሉ

በተቀረው ዓለም በጣም ብዙ ሕዝብ ይረግፋል፤ በተለይ ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ በሚቆጣጠሩት የዓለማችን ክፍል። እነ አሜሪካ ይጠፋሉ፣ እነ ቱርክ ኢራንና ሳውዲ አረቢያ ድራሽ አባታቸው ይጠፋል።

❖❖❖[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፪]❖❖❖

  • በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውኃ ወንዝ አሳየኝ።
  • በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።
  • ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥
  • ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።
  • ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፥ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
  • እርሱም። እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፥ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ።
  • እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ።
  • ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።
  • እርሱም። እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ።
  • ለእኔም። ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።
  • ፲፩ ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ አለ።
  • ፲፪ እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
  • ፲፫ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
  • ፲፬ ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።
  • ፲፭ ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።
  • ፲፮ እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።
  • ፲፯ መንፈሱና ሙሽራይቱም። ና ይላሉ። የሚሰማም። ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።
  • ፲፰ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን የትንቢት ቃል ለሚሰማ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፤ ማንም በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል፤
  • ፲፱ ማንምም በዚህ በትንቢት መጽሐፍ ከተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል፥ በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል።
  • ይህን የሚመሰክር። አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።
  • ፳፩ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው | ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 7, 2023

😇 ዛሬ ተወለደ ዛሬ ተወለደ የዓለም ቤዛ ወገኖቹን በደሙ ሊገዛ

🔔 ይህ የዛሬው የልደት በዓል፤ ታኅሣሥ ፳፱ / ጃንዋሪ 7 በ፤

  • ❖ ኢትዮጵያ (ኤርትራን ጨምሮ)
  • ❖ እስራኤል
  • ❖ ግብጽ
  • ❖ አርመኒያ
  • ❖ ጆርጂያ
  • ❖ ሩሲያ
  • ❖ ዩክሬን (በሉሲፈራውያኑ ሮማውያን ግፊት ከፊሉ ወደ ዲሴምበር 25 እየቀየረ ነው)
  • ❖ ቤላሩስ
  • ❖ ሞልዶቫ
  • ❖ ካዛክስታን
  • ❖ ሰርቢያ
  • ❖ ማኬዶኒያ
  • ❖ ሞንቴኔግሮ

ይከበራል

የቤተልሔም ኮከብ በመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን መሠረት ሦስቱን ጠቢባን ከምሥራቅ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ስፍራ የመራቸው ኮከብ ነው ፡፡

የቤተልሔም ኮከብ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስን ልደት ያመለክታል. በዚህ ምክንያት ነው ፣ በገና ወቅት ፣ ይህ ክስተት ሲዘከር ፣ የቤተልሔም ባህርይ ኮከብ በገና ዛፍ ላይ የተቀመጠው። የገና ዛፍን ይመልከቱ።

የቤተልሔም ኮከብ ከባለ አምስት ፈርጡ የሉሲፈር ኮከብ በመለየት ተቃራኒው ነው። የቤተልሔም ኮከብ ለእኛ ለክርስቲያኖች እንደ አማኝ ሕይወታችንን የሚመራ ብርሃን ፣ ተስፋ እና እምነት የሚወክል ነው። ይህ ኮከብ ዝነኞቹን ሶስት ጠቢባን ሰዎችን(ሰብዓ ሰገልን) የመራቸው ኮከብ ነው። ለዚህም ነው ለገና በዓል አከባበር እና መታሰቢያ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ምልክቶች አንዱ ይህ ኮከብ የሆነው።

ታዲያ ዛሬ የአማኑኤል ጌታችንን ልደት ፣ የእመቤታችንን ቅድሥት ማርያምንና የባለ እግዚአብሔርን በዓልን ስናከብር በከሃዲዎቹና ጨካኞቹ የሉሲፈራውያኑ አሽከሮች በእነ ግራኝ አብዮት አህመድ፣ ኢሳያስ አፈቆርኪና ደብረጽዮን አማካኝነት እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ላለፉት ሦስት ዓመታት የሚጨፈጨፉትን፣ የሚራቡትንና የሚሰደዱትን አክሱም ጽዮናውያንን ልናስታውሳቸውና ልናስብላቸው ዘንድ ግድ ነው። ዓለምና በዚህች ዓለም የባርነት ቀንበር ሥር የወደቁት የእኛዎቹ ቃኤላውያን ዝም ጭጭ ብለዋል፤ ይህም ግን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ሁሌም ከእነርሱ ጋር መሆኑን ነው የሚጠቁመን።

አዎ! ቅዱስ የሆነውን ብሶታችንን፣ ጩኸታችንና ለቅሷችንን ለእግዚአብሔር አምላክ እንጂ ለዚህች ዓለም ማሰማት/መስጠት አያስፈልገንም/የለብንም፤ አይገባትምና። የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ!

❖❖❖ ብሩክ የጌታችን ልደት በዓል!❖❖❖

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

✤ ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በበጎው ዘመን | ✤ ደብረ ሳሌም ቦሌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 12, 2022

😇 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ፡ የአዲስ ዘመን ምልክት

በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሰረት የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ በዓል የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በዓል ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ቅዱስ ዮሐንስ የአሮጌ (ብሉይ) ዘመን ማብቃት ብስራት፣ የአዲስ ዘመን መምጣት ማሳያ ሆኖ በቅዱሳት መጻሕፍት ስለሚታወቅ ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን መካከል ከነበሩት ቅዱሳን አበው አንዱ የሆነ፣ ከነቢያት እነ ነቢዩ ኢሳይያስ፣ ከመላእክት ቅዱስ ገብርኤልና ከካህናት አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት ነቢይና ሐዋርያ ነው፡፡ ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ቅኑት እንደ ገበሬ፣ ጽሙድ እንደ በሬ ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለገለ፣ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፣ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፣ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው፡፡

😇 የቅዱስ ዮሐንስ መዓርጋት

ቅዱስ ዮሐንስ በርካታ መዓርጋት አሉት፤ የተወሰኑትን ቀጥለን እንመለከታለን፤

  • መጥምቅ /መጥምቀ መለኮት/ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማጥመቁ
  • ነቢይ ከእኔ በፊት የነበረውና ከእኔ የሚበልጠው ይመጣል ብሎ ትንቢት በመናገሩ
  • ካህን ሕዝቡን በማጥመቁ
  • ወንጌላዊ ያስተማረው ትምህርት እንደነቢያቱ ይመጣል ይወለዳል ብቻ ሳይሆን መጥቷል፣ ተወልዷል፣ እነሆ በመካከላችሁ ቆሟል የሚል ለመሆኑ፤ እንደ ነቢያቱ ለቅጣት ምርኮን፣ ለስጦታ /ደስታ/ ምድረ ከነዓንን ሳይሆን ለቅጣት የዘለዓለም ሕይወትን፤ ለስጦታ መንግሥተ ሰማያትንና ገሃነመ እሳትን ማስተማሩ፤ የሥነ ምግባር ትምህርቱም እንደ ወንጌል ትሩፋትን የሚሰብክ በመሆኑ

ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በብሉይ ኪዳን እና በሐዲስ ኪዳን መሸጋገሪያ ላይ የነበረ ነቢይ በመሆኑ የዓመቱ መጀመሪያና የዘመን መለወጫ በዓል በሆነው መስከረም አንድ ቀን የእርሱ መታሰቢያ እንዲደረግበት፣ በዓሉም «ቅዱስ ዮሐንስ» ተብሎ እንዲጠራ አባቶቻችን ወስነዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው «ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ»፤ «መታሰቢያህ በርእሰ ዓውደ ዓመት ተጻፈ፤ በረከትህን አገኝ /እውሰድ/ ዘንድ «ባርከኝ» ብሎ ምሥጋናና ጸሎት ደርሷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልክአ ዮሐንስ ደግሞ «ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ» ይለዋል /ሠላም ለሥዕርተ ርእስከ/፡፡ «የመጥቅዕ እና የአበቅቴ ወላጅ፣ አስገኚ» ማለት ነው፡፡ ይህም ስም የተሰጠው የዓመቱ ክብረ በዓላት የሚውሉባቸው ቀናትና ዕለታትን ለማስላት የሚጠቅሙት መጥቅዕ እና አበቅቴ የሚባሉት ቁጥሮች በዚሁ በመስከረም አንድ ቀን ስለሚወጡ /ስለሚስሉ/ ነው፡፡

ሰማእት /ምስክር/ስለጌታችን አምላክነትና መድኃኒትነት እንዲሁም ስለ እውነት ስለመሰከረ፤ በመጨረሻም በአላውያን ነገሠታት እጅ ስለ ተገደለ፡፡

ከእነዚህ ሁሉ ስሞች የሚበልጠው ግን መጥምቅ /መጥምቀ መለኮት/ የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ ካደረጋቸውና ከሆናቸው ነገሮች ሁሉ የሚበልጠው አምላክን ማጥመቁ ነው፡፡ ጌታችንም ስለ እርሱ ክብር በተነገረ ጊዜ «እውነት እላችኋለሁ፤ ሴቶች ከወለዱአቸው ወገን ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም…» በማለት ይህንን ስያሜ አጽድቆለታል፡፡

😇 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ለእኛ

ቅዱስ ዮሐንስ በዘመኑ የነበሩ ሰዎችን ገሥጾና አስተምሮ ወደ እግዚአብሔር አቅርቧቸዋል፡፡ እኛስ በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች ከእርሱ ምን እንጠቀማለን? ሁለት ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

  • . ያስተምረናል፡፡
  • . ያማልደናል፡፡

. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ያስተምረናል

ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በቃሉ /በስብከቱ/፣ በሕይወቱ እና በአገልግሎቱ ዛሬ ድረስ ያስተምረናል፡፡

. በስብከቱ /በቃሉ/ ያስተምረናል

አንድ ሰው የድኅነትን ጸጋ /ስጦታ/ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለመቀበል ሦስት ነገሮች ያስፈልጉታል፡፡ እነዚህም እምነት፣ ምሥጢራትን መካፈል እና ምግባር ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በእነዚህ በሦስቱም ዙሪያ ትምህርቶችን ያስተምረናል፡፡

እምነት፡ቅዱስ ዮሐንስ «አብ ወልድን ይወዳል፤ ሁሉንም ነገር፤ በእጁ ሰጥቶታል፡፡ በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም» እያለ ምሥጢረ ን ምሥጢረ ሥጋዌን ያስተምረናል፤ ካላመንም የዘለዓለም ሕይወት እንደሌለን ይነግረናል፡፡

ምስጢራትን መካፈል፡ቅዱስ ዮሐንስ «መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፡፡»«ከእኔ በኋላ የሚመጣው በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ያጠምቃችኋል»«የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ» እያለ ምሥጢራትን /ምስጢረ ጥምቀት፣ ምስጢረ ንስሐን እና ምስጢረ ቁርባንን/ እንድንካፈል ያስተምረናል፡፡

ምግባር፡– «እናንት የእፉኝት ልጆች ለመሆኑ ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ፤ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤ … እነሆ ምሳር የዛፎችን ሥር ሊቆርጥ ተዘጋጅቷል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል፡፡» እያለ ምግባር እንድንሠራ ያስተምረናል፤ ያስጠነቅቀናል።

. በሕይወቱ ያስተምረናል

ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በሕይወቱ እግዚአብሔርን ያስደሰተ፤ «ከሴቶች ከተወለዱ የሚያህለው የለም» የተባለለት ስለሆነ አርአያ ልናደርገው፤ ለዚህ ክብር ያበቃውን ነገር ልንመረምርና በመንገዱ ልንከተለው ይገባናል፡፡ ከሕይወቱ ብዙ ልንማራቸው የሚገቡ ነገሮች ቢኖሩም ጥቂቶቹን ለጊዜው እንመልከት፡

ትሁት ነው፡ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ጌታ «ከሴቶች ከተወለዱት ወገን የሚያህለው የለም» እያለ ቢያመሰግነውም እርሱ ግን ያሉትን መልካምና ታላላቅ ነገሮች በሙሉ ችላ ብሎ «እኔ የጫማውን ማሰሪያ ልፈታ የማይገባኝ ነኝ» ይል ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ያሬድ «ዘወጠነዝ ትርሢተ ክብር ትሕትና ወፍቅር ትሕትና ወፍቅር ርእዮ እበዩ ለዮሐንስ…» እያለ የቅዱስ ዮሐንስ የክብሩ ጌጥ፣ የታላቅነቱ ምንጭ ትሕትናው እና እግዚአብሔርን ማክበሩ መሆኑን ይገልጻል፡፡ እመቤታችን በጸሎቷ «ትሁታንን ግን ከፍ ከፍ አደረጋቸው» [ሉቃ.፩፥፶፪] እንዳለችው እርሱ ትሁት ሲሆን እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ አከበረው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ትሕትና ግን ምንጩ ምንድን ነው?

ትሕትና ማለት ምንም ነገር የሌለው መሆን ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በባሕርይው ትሁት ነው፡፡ ጌታ «ከእኔ ተማሩ፣ እኔ ትሁት ነኝ» ይላል፡፡ የእግዚአብሔር ትሕትና ምንጩ ክቡር፣ ባዕለ ጸጋ መሆኑ ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ትሕትና ምንጭም ይኸው ነው፤ በእምነትና በምግባር ያጌጠ ባለ ብዙ ፍሬ ባለ ጸጋ መሆኑ ማንም ትሕትናን የሚፈልጋት ቢኖርም ማድረግ ያለበት ይህንኑ ነው፤ ባለብዙ ምግባር፤ ባለ ትልቅ እምነት መሆኑ፤ ያን ጊዜ ትሕትናው አብሮ ይመጣል፡፡

ሁለተኛው የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ትሕትና ምንጭ የእግዚአብሔርን ማንነትና ባሕርይ በሚገባ ማወቁ፤ የራሱን ማንነቱንና አቅሙንም መረዳቱ ነው፡፡ እኛም ትሕትናን ገንዘብ ልናደርግ ብንወድ የእግዚአብሔርን ማንነት፣ ባሕርይ፣ እና ክብር የተቻለንን ያህል ለማወቅ መጣር፤ ራሳችንንም ዘወትር መመርመር፣ ድካማችንን መረዳትና ይህንንም ደግመን ደጋግመን ለራሳችን መንገር አለብን፡፡

ጸጋውን ተጠቅሞ ፍሬ አፍርቷል፡ – ቅዱስ ዮሐንስ በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ነበር፡፡ እርሱም ይህንን ጸጋውን አትርፎበታል፤ሕዝቡም ካህናቱም አመጸኞች በነበሩበት በዚያ አስከፊ ዘመን [ሐዋ.÷፴፡፴፱] ጻድቅ ሆኖ ተገኝቷል፤ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም በረከት ሆኖ ነበር፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት ለዚህ የበቃው «የበረሃ እና የተራሮች ልጅ» በመሆኑና በብህትውና /በብቸኝነትና/ እና በትህርምት በመኖሩ ነው፡፡

እያንዳንዳችን ከጥምቀታችን ቀጥሎ በሚፈጸምልን ምሥጢረ ሜሮን አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ያድርብናል፡፡ ይህንን ተጠቅመን ሥራ ለመሥራት እኛም እንደ መጥምቁ የራሳችን በረሃ ያስፈልገናል፤ በትህርምትና ራስን በመግዛት መኖር አለብን፡፡

ይህንን ማድረግ የሚገባቸውና የሚችሉት በገዳም ያሉ ሰዎች ብቻ አይደሉም፡፡ በዓለም የምንኖር ሰዎችም ብቻችንን የምንሆንበትና በጸሎት፣ በተመስጦ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ፣ ራሳችንን በመመርመር የምናሳልፈው ጊዜ በመመደብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በወጣትነት ዘመኑ እንዳደረገው መኖሪያ ቤቶቻችንን ገዳማት ማድረግ እንችላለን፡፡ ሁኔታዎችን እያመቻቸን ወደተለያዩ ገዳማት እየሄድን ጊዜ ማሳለፍም ጠቃሚ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ምግባችንን፣ መጠጣችንን እና ልብሳችንን በልክ እያደረግን መጥምቁን ባለ ብዙ ፍሬ በሆነበት ጎዳናው ልንከተለው ያገባናል፡፡

በአግልግሎቱ ያስተምረናል፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ አገልግሎት ልንማራቸው የሚገቡ በርካታ ቁም ነገሮች አሉ በማለት የሚከተሉትን ይዘረዝራሉ፡፡

ቅድስ ዮሐንስ ያገለገለው ለአጭር /ከስድስት ወራት ብዙ ላልበለጠ/ ጊዜ ብቻ ቢሆንም በርካታ ሥራዎችን ሠርቶ አልፏል፡፡ እኛም አገልግሎታችንን ልንመዝነው የሚገባን በርዝመቱ ሳይሆን በጥልቀቱ፣ በውጤታማነቱ፣ በሚያፈራው ፍሬ እና በሚያመጣው ለውጥ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል ዓላማው ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት እንጂ ሰዎችን በእርሱ ዙሪያ መሰብሰብና መክበር አልነበረም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደሚነግረን «ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳ፣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ነገር ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይጎርፉ ነበር፡፡» [ማቴ.፫፥፭፡፮] እርሱ ግን «እኔ በውኃ ለንስሐ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡» እያለ ሰዎቹ እርሱን እንዲከተሉ ሳይሆን የጌታችንን መምጣት ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርግ ትምህርት ያስተምራቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

የመጀመሪያዎቹ ጌታችንን የተከተሉት ደቀመዛሙርት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ነበሩ፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን መታጀብ /በሕዝብ መከበብ/ ለሚያስደስተን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የእኛን ተከታዮች እንደ ፈሪሳውያን ለምንፈልግ አገልጋዮች ትልቅ ተግሳጽ ነው፡፡

«በማግስቱ ዮሐንስ ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር እንደገና በእዚያው ቦታ /ጌታችን በተጠመቀበት/ ቦታ ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚያ ሲያልፍ አይቶ «እነሆ የእግዚአብሔር በግ» አለ ሁለቱ ደቀመዛሙርትም ይህን ሲናገር ሰምተው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተከተሉት» [ዮሐ.፩፥፴፭፡፴፯]

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም በርካታ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት የነበሩና የእርሱን ጥምቀት የተጠመቁ ሰዎች በቀላሉ ወደ ክርስቲያኖች ማኅበር እንደተቀላቀሉ ይነግረናል፡፡ [ሐዋ.፲፰፥፳፬+ ፲፱፣ ፮፥፲፫፡፳፬]

ራሱም ይህንን አቋሙን እንዲህ በማለት ልብ በሚነኩ ቃላት እንዳጋለጠው ወንጌላዊው ዮሐንስ በወንጌሉ መዝግቦታል፡፡

ሰዎች ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥተው «መምህር፣ በዮርዳኖስ ከአንተ ጋር የነበረው፣ ስለ እርሱም የመሰከርክለት … ሰው ሁሉ ወደ እርሱ እየሄዳ ነው» ባሉት ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰ «ከላይ ካልተሰጠው በቀር ማንም አንዳች ሊቀበል አይችልም፡፡ «እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ» እንዳልሁ እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡ ሙሽራይቱ የሙሽራው ነች፡፡ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሟል፡፡ እርሱ ሊልቅ፤ እኔ ግን ላንስ ይገባል፡፡»

እውነት ነው፡፡ ሙሽራይቱ ቤተ ክርስቲያን የሙሽራው የክርስቶስ ነች፡፡ አገልጋዮች ሚዜ ናቸው፡፡ ሥራቸውም ሙሸራይቱን ወደ ሚዜው ማቅረብ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል በድፍረት ነው፡፡ እርሱ በነበረበት ወቅት ሔሮድስ አንቲጳስ የወንድሙን ሚስት አግብቶ የሚገሥጸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በበረሃው ሳለ ደፋር፣ ለሰው ፊት የማያደላ፣ መሆንን ተምሮ ነበርና ገብቶ ገሠፀው፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዲህ ይላሉ «ከአገልግሎቱ ሊያዘገየው ወይም ሊያስተጓጉለው የሚችል ቢሆንም እንኳን ተገቢውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አላለም፡፡ አስተሳሰቡም እንዲህ ነው «እግዚአብሔር እንዳገለግል ፈቃድ ከሆነ አገለግላለሁ፤ ካልሆነም የእርሱ ፈቃዱ ይሁን፡፡ ዋናው ነገር እውነትን መመስከር ነው» ቅዱስ ዮሐንስ ስለእውነት ራሱን አሳልፎ ቢሰጥም ከሞተ በኋላም ቢሆን የትምህርቱ ድምፅ ሄሮድስን ሲወቅሰው ኑሯል፡፡»

እውነት ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ከሞተ በኋላም ቢሆን ራሱ አስራ አምስት ዓመት ዙራ አስተምራለች፡፡ ሔሮድስም ከሞት ተነሥቶ የሚመጣ እስኪመስለው ድረስ ይፈራው እንደበር ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ጽፏል «በዚያን ጊዜ የአራተኛው ክፍል ገዢ የነበረው ሄሮድስ /አንቲጳስ/ ስለ ኢየሱስ ዝና ሰማ፤ ባለሟሎቹንም እንዲህ ከሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶ መጥቶአል ማለት ነው፤ ይህ ሁሉ ድንቅ ተዓምራት በእርሱ የሚደረገውም ለዚህ ነው» አላቸው፡፡ [ማቴ.፲፬፥፩፡፪]፡፡

😇 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ያማልደናል

ቅዱስ ዮሐንስ ዛሬ እኛን እግዚአብሔር ለወዳጆቹ በሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት በጸሎቱ ከእግዚአብሔር ያማልደናል፡፡

ቤተ ክርስቲያንም ዘወትር «ሰአል ለነ ዮሐንስ» «ዮሐንስ ሆይ ለምንልን»፤ ትለዋለች፤ «በአንተ ዮሐንስ መጥምቅ መሐረነ» «ስለ ዮሐንስ ስትል ማረን» እያለችም ትጸልያለች፡፡ እኛም ገድሉንና፣ መልኩን በመጸለይ፣ መታሰቢያው በሚደረግበት ጊዜም በስሙ ዝክር በመዘከር፣ ቸርነት በማድረግ በረከትን ለማግኘት ልንተጋ ይገባናል፡፡

«ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀመዛሙርቶቼ ስም ቢያጠጣ፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም» [ማቴ.÷፵፪]

«የቅዱስ ዮሐንስ ጸሎቱና በረከቱ ይደርብን! አማላጅነቱ ይደረግልን»

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: