Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘፪ሺ፲፩’

ዲያቆን ቢንያም፤ የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ተገቢውን ክብር ያልሰጠችው ታላቁ አባታችን ቅዱስ ያሬድ መጥቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2023

አዎ! ውጊያው ለአብዛኛው የዓለማችን ነዋሪ የማይታየውና የማይታወቀው መንፈሳዊ ውጊያ ነው። የተሠወረው ቅዱሱ አባታችን ያሬድ ሥራውን ይሠራል፤ የኢትዮጵያንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትናዋን የውስጥና የውጭ ጠላቶችን ያርበደብዳል። ዲያቆን ቢኒያም ወንድማችን እንዳሉን፤ ትክክለኞቹ ኢትዮጵያውያንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ሳይሆኑ ነን እያሉ በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ፣ በቅዱስ ያሬድ ልጆች ላይ እየዘመቱ ያሉት፣ ለራሳቸው/ለስጋቸው እንጂ ለሕዝባቸው፣ ለተተኪው ትውልዳቸው፣ ለሃይማኖታቸውና ለሃገራቸው የማይስቡ ከሃዲዎች ሁሉ ተግባራቸው ልክ እንደ አህዛብ ዓይነት ዲያብሎሳዊ ነውና፤ ጉዳቸው ፈልቷል፤ ወዮላቸው!

😇 የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ተገቢውን ክብር ያልሰጠችው ታላቁ አባታችን ቅዱስ ያሬድ፤

ብቸኛው የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ነው የሚገኘው፤ ይህም ታሪካዊው ሕንፃ ተገቢውን እንክብካቤ እያገኘ አይደለም! ለምን? ይህ የሚጠቁመን ከዳግማዊ ምንሊክ ጀመረው የነገሱት ነገሥታት ሁሉ የኢትዮጵያና ተዋሕዶ ክርስትናዋ ጠላቶች መሆናቸውን ነው።

አሳዛኙ ነገር እንዲህ ያለው ሊቅ ፣ ጻድቅና ቅዱስ የዜማና የመጻሕፍት ደራሲ የሆነው አባት ቅዱስ ያሬድ በሀገሩ በኢትዮጵያ የቀድሞው መንግሥት በስሙ ከሰየመለት የሙዚቃ ትምሕርት ቤት በቀር በክብሩ መጠን የተደረገለት አንድም ማስታወሻ የሚሆን ነገር በሀገሩ ላይ የለም። ይህ የሆነው ደግሞ የቅዱስ ያሬድም ሆነ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ትልቁ በደላቸው ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ ነው።

እስኪ ይታየን፤ በእውነት ከዳግማዊ ምንሊክ በኋላ የነገሡት ነገሥታቱና ገዢዎቹ ሁሉ ኢትዮጵያውያንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ቢሆኑ ኖሮ ለእነ ንግሥት ሳባ/ማከዳ፣ ነገሥታት ካሌብ፣ አብርሃ ወአጽበሃ፣ ቅዱስ ያሬድ፣ አፄ አምደ ጺዮን፣ አፄ ዮሐንስ፣ ራስ አሉላ ወዘተ ተገቢውን ክብር ሰጥተው ብዙ መታሰቢያ በሠሩላቸው ነበር። እነ ዳግማዊ ምንሊክና ኃይለ ሥላሴ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ቢሆኑ ኖሮ የግዕዝ ቋንቋን በትምህርት ቤት ደረጃ እንዲሰጥ ወይንም ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን በሞከሩ/በታገሉ ነበር። ግን በሉሲፈራውያኑ ዙፋን ላይ የተቀመጡ የኢትዮጵያ ጠላቶች ነበሩና ይህን ሊያደርጉ አይሹም ነበር። ሞኙን ሕዝባችንን ለማታለል ልክ “በዱባይ ቤተ ክርስቲያን አሠርቻለሁ” ለማለት እንደሞከረው እንደ አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ አንድ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ያሠሩና ኢትዮጵያውያን ነን!” ለማለት ይደፍራሉ።

ከዳግማዊ ምንሊክ እስከ ግራኝ ድረስ የዘለቁት የአራቱ ምንሊክ ዲቃላ ትውልዶች መሪዎች ሁሉ ተራ በተራ እያጭበረበሩ በአክሱም ጽዮን ላይ መዝመታቸውን እናስታውሰው። የሰሜኑን ክርስቲያን ሕዝብ ደግነትና ፍቅር እንደ ድክመትና ሞኝነት በመቁጠራቸው በእጅጉ ስተዋል። ይህ ደካማ ትውልድ ከተጠረገ በኋላ ሌላ ወንድ የሆነ ትውልድ በቅርቡ መነሳቱ እንደሆነ አይቀርም። ያኔ እስላም የለ፣ ዋቀፌታ ምንፍቅና ሁሉም ከሃገረ ኢትዮጵያ ተጠራርገው ይወጡ ዘንድ ግድ ይሆናል። በተለይ ኢትዮጵያ ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት ለገባችበት መቀመቅና ጥልቅ ውድቀት ከፍተኛውን አስተዋጽዖ ያበረከቱት እስልምና፣ ዋቀፌታ እና ፕሬተስታንታዊነት ናቸው። ሦስቱም በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና እና ቅዱስ ያሬድ ላይ ጂሃዳዊ ጦርነት ያወጁ የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር እርኩስ መንፈስ ስራዎች ናቸው።

ሃፍረተ-ቢሶቹና ቀማኞቹ ጋላ-ኦሮሞዎቹማ በድፍረት፤ ቅዱስ ያሬድ ኬኛ!” በማለት ላይ ናቸው። ከሦስት ዓመታት በፊት ልክ በዚህ በግንቦት ወር ላይ የቅዱስ ያሬድን ዜማ በአራዳ ቀለም ቀባብተው የሚያዜሙት፣ ቅዳሴውን በግዕዝ ሳይሆን በአጋንንታዊው ኦሮምኛ ቋንቋ የሚጸልዩትንና አቡነ ‘ናትናኤል‘ የተሰኙትን ኦሮሞን፤ ችኩሎቹ ወገኖችቻችን “የዘመናችን ቅዱስ ያሬድ!” እያሉ ሲጠሯቸው ስሰማ፤ ያየሁትን ነገር አይቻለሁና፤ ‘ኡ! ኡ!’ በማለት ቀጥሎ የሚታየውን የማስጠንቀቂያ ቪዲዮና ጽሑፍ አቅርቤ ነበር። ‘አቡነ‘ ናትናኤል ከትናንታ ወዲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን አለመሆናቸውንና በኦሮሙማ መርዝ የሰከሩ የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር ባሪያ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

እነ ቅዱስ ያሬድ ገና ብዙ ከሉሲፈር የሆኑትን ሰርጎ ገቦችን ያጋልጧቸዋል። ወዮላቸው!

👉 ወደዚህ ይግቡ፤ የድሮውን ቻኔሌን እነርሱው ስላዘጉት ቪዲዮውን በድጋሚ እልከዋለሁ፤

💭 “የፋሲካ የጸሎት መርሀ ግብሮችን ያስተላለፈውን የ ”ባላገሩ”ን የሉሲፈር ኮከብ አላያችሁምን?”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 16, 2020

የእዚህ እርኩስ መንፈስ ተላላኪ እባቡ ጋላ-ኦሮሞ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ከሁለት ዓመታት በፊት፤ “እኛ እኮ ወደ ትግራይ ብንዘምት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ማዕከል ስለሆነች አማራው በጭራሽ አይፈቅድልንም፣ አያሳልፈንምም” በማለት ያሰማውን መርዛማ ንግግር ሁሌ እናስታውስ፤ ምክኒያቱም ዳግማዊ ምንሊክም፣ ኃይለ ሥላሴም፣ መንግስቱ ሃ/ማርያምም፣ ኦቦ ስብሐት ነጋም ሕዝቡን እያታለሉ ለመጨፍጨፍ ተመሳሳይ ነገር ነበር ሲናገሩ የነበሩት

እስኪ ይህን ከሃዲ የዳግማዊ ምንሊክ ትውልድ ባግባቡ እንታዘበው፤ የትኛው ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ ነው ከባዕዳውያን የኢትዮጵያና ክርስትናዋ ታሪካዊ ጠላቶች ከሆኑት እስማኤላውያን አረቦች፣ ቱርኮችና ኢራኖች ጋር ሆኖ የቅዱስ ያሬድን ገዳማትንና አብያተ ክርስቲያናትን በአክሱም፣ በደብረ ዳሞ፣ ደብረ አባይ ወዘተ ሊያስጨፈጭፍ የሚደፍር/የሚችል? ትክክለኛ ኢትዮጵያዊ እና ክርስቲያን ይህን እንኳን ሊያደርገው በክፉ ቀን እንኳን በጭራሽ ሊያስበውም የማይችለው ከባድ የሃገር ጉዳይ ነው። ቅዱስ ያሬድን እንወድዋለን የሚሉትና ክብረ በዓሉንም ለማክበር የተነሱት ዶ/ር እና ፕሮፌሰር አፍቃሪ ወገኖች እንዴት ይህን ዲያብሎሳዊ ተግባር ሊደግፉት ቻሉ?

👉 ከዚህ በፊት ከቀረበው ጽሑፍ የተወሰደ፤

🎵 እነ ሞዛርት ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ በኢትዮጵያችን ተወለደ

Posted by addisethiopia /አዲስ ኢትዮጵያ on September 15, 2019

ቅዱስ ያሬድ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዜመው «ሀሌ ሉያ ለአብ፣ ሀሌ ሉያ ለወልድ፣ ሀሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፣ በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድር፣ ወበዳግም አርእዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ሲል ነበር። ይህን ዜማ ሲቀኝም ህዝቡ እሱን ለማዳመጥ ሀገር አቋርጦ ይመጣ እንደነበር መዛግብት ያስረዳሉ። ይህ ሁኔታም ያልተለመደ በመሆኑ እንደትንግርት ይቆጠር ነበር። የዜማው አወራረድ ተሰምቶ አይጠገብም። በዘመኑ የነበሩት ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል በቅዱስ ያሬድ መንፈሳዊ ዜማ በመደነቃቸው ዜማው በአዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ እንዲውል መፍቀዳቸው ይነገራል።

ያሬድ የንጉሡ የቅርብ ሰውና ወዳጃቸውም ነበር። እሳቸውም ሹመት ሊሰጡት ደጋግመው ጠይቀውታል። ይሁን እንጂ መንፈሱ በምናኔና ዓለምን በመናቅ የተሞላ ስለነበር ጥያቄያቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም። አንድ ቀን ግን ጻድቁ ቅዱስ ያሬድ ንጉሡን «በምናኔ በሰሜን ገዳም እንድኖር ይፍቀዱልኝ» ሲል ጠየቃቸው። እርሳቸውም ሀሳቡን ተቀብለው ፈቀዱለት። ቅዱስ ያሬድ በአክሱምና በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም ለረጅም ጊዜያት በትጋት ደቀ መዛሙርትንም በማፍራት አገልግሏል ።

ጻድቁም ወደ ሰሜን ተራሮች ወደ ራስ ደጀን ከመሄዱ በፊትም ታቦተ ጽዮንን ለመሰናበት ከመቅደስ ገባና ከመሬት ክንድ ከስንዝር ከፍ ብሎ በመቆም ዛሬ ሁላችን በውዳሴ ማርያም የጸሎት መጽሐፍ መጨረሻ ላይ የምንጸልየውን “አንቀፀ ብርሃን” የሚባለውን የምስጋና ጸሎት ንባቡን ከነ ዜማው ደርሶ ለቤተ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አበረከቶልን ከንጉሥ አፄ ገብረመስቀል ፈቃድ ያገኘው ጻድቁ ቅዱስ ያሬድም የመጨረሻዎቹን የዚህ ምድር ላይ ቆይታውን በሰሜን ተራሮች አካባቢ በበረዶማው የራስ ደጀን ተራራ ላይ ለማድረግ ሄዷል ። በዚያም በዋሻ ተቀምጦ በትጋሃ መላእክትና በተባሕትዎ በድንግልና ሲያገለግል ፤ ተተኪ ደቀመዛሙርትንም ሲያፈራ ቆይቶ በመጨረሻም ግንቦት ፩/1 ቀን በ፭፻፸፮/576 ዓም በተወለደ በ፸፩/71 ዓመቱ ተሰውሯል።

አሳዛኙ ነገር እንዲህ ያለው ሊቅ ፣ ጻድቅና ቅዱስ የዜማና የመጻሕፍት ደራሲ የሆነው አባት ቅዱስ ያሬድ በሀገሩ በኢትዮጵያ የቀድሞው መንግሥት በስሙ ከሰየመለት የሙዚቃ ትምሕርት ቤት በቀር በክብሩ መጠን የተደረገለት አንድም ማስታወሻ የሚሆን ነገር በሀገሩ ላይ የለም። ይህ የሆነው ደግሞ የቅዱስ ያሬድም ሆነ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ትልቁ በደላቸው ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ ነው ።

አቤት አቤት ቅዱስ ያሬድ አውሮፓዊ ቢሆን ኖሮ ብዬ ሳስብ ምን ሊያደርጉት እንደሚችሉ መገመት ብቻ ነው ። መንገዱ ፣ አደባባዩ ፣ ተራራው ፣ ትምህርት ቤቱ ፣ ቁሳቁሱ ሳይቀር በስሙ በተሰየመ ነበር ። አንድ ፒያኖ ይዘው ኦርኬስትራ ለመሩ ሰዎች ተአምር ለመፍጠርና ስማቸውን በመሸጥ የሀገር ገቢ ማግኛ ሲያደርጉ ሳይ እደነቃለሁ ። በጀርመን ሀገር በቦን ከተማ የቤትሆቨን ቤትን ለመጎብኘት ሄጄ ቅዱስ ያሬድን ሳስበው አልቅስ አልቅስ ነበር ያለኝ ። ሰው ቢልዮን ዶላር የሚያስገባለትን ሀብት ከመጋረጃ ጀርባ ደብቆ እንዴት በድህነት ይማቅቃል?? በቅዱስ ያሬድ አፍሮ በማያውቀው ፑሽኪን ይመጻደቃል ።

ኢትዮጵያ ለማታውቀው ፑሽኪን ለተባለ ሩሲያዊና ደጎል ለተባለ እንግሊዛዊው ግለሰቦች አደባባይ ስትሰይም ፣ ለአቶ ቸርችል ጎዳና ፣ ለጀናራል ዊንጌት ደግሞ ትምሕርት ቤት በመሥራትና በመሰየም ያልበላትን ስታክ ትታያለች ። በአቡነ አረጋዊ ስም ቡና ቤት ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቢራ ለመሰየም ግን ቅሽሽ አይላትም ፤ የሚጠየፍና ሃይ ባይም ትውልድ የለም ።

አንድ የውጭ ሀገር ሰው ኢትዮጵያ ሄጄ ስለ ቅዱስ ያሬድ ላጥና ቢል መከራውን ነው የሚበላው ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በሕይወት ለመኖሯ እና በምድር ላይ እንድትቀጥል ካደረጓት ነገሮች አንዱና ዋነኛው የቅዱስ ያሬድ ሥራዎች መኖር ነው ። ያለ ቅዱስ ያሬድ ሥራዎች ቤተክርስቲያናችን ማሰብ በራሱ ከባድ ነው የሚሆነው ። ቅዱስ ያሬድ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ፣ ለሊቃነ ጳጳሳቱ ፣ ለካህናትና ለዲያቆናቱ ፣ ለመዘምራኑም ሁሉ ፤ ሞገስ ፣ ክብር ፣ እንጀራም ጭምር ነው ። ነገር ግን ይኽን ሁሉ ለሆነላቸው ጻድቅ አንዳቸውም አስታውሰው ግዙፍ ነገር በስሙ ሊሠሩ ሲነሳሱ አይታዩም ።

ከዚህ ቀደም በአክሱም ከተማ በጻድቁ ቅዱስ ያሬድ ስም ዩኒቨርስቲ ይሠራል ተብሎ በገንዘብ ልመናው እኔም የተሳተፍኩበት ኮሚቴ ተቋቁሞ ብዙ ሚልየን ብር ከተሰበሰበ በኋላ የት እንደደረሰ መድኃኔዓለም ብቻ ነው የሚያውቀው ።

አሁን ግን ፈቃደ እግዚአብሔር በመድረሱ ጻድቁ ቅዱስ ያሬድ በመጨረሻው የምድር ላይ ቆይታው ብዙ ሊቃውንትን ባፈራበት በራስ ዳሽን ተራራ ላይ የሚገኘው ዋሻው በመጎሳቆሉ ፤ ቤተክርስቲያኑም በመፈራረሱ ፣ ቅርሶቹም ከአይጥና ከምስጥ ጋር ትግል መግጠማቸውን በማየታችን ይኽንን ችግር የሚቀርፍ ኮሚቴ በብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የሚመራና በሀገረ ስብኩቱ ሊቀጳጳስ በብፁዕ አቡነ ኤልሣዕ የበላይ ጠባቂነት እነ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስን ጨምሮ በዙ ሊቃውነተ ቤተክርስቲያንን ያካተተ አንድ ሀገር አቀፍ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩ ይታወቃል ።

እኔም በሀገሬ እያለሁ የዚሁ ኮሚቴ የህዝብ ግኑኝነት ኮሚቴው ኃላፊ ተደርጌም ተመርጬ ነበር ። ” ወይ ይሄ ነበር እንዲህ ቅርብ ነው ለካ “። ምንም እኔ አሁን ከኮሚቴው ጋር የመሥራት እድሉን ባይኖረኝም ኮሚቴው ግን ሥራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ይህንን በማየቴም እጅግ ደስተኛ ነኝ።

በራስ ደጀን ተራራ ላይ ፣ ቅዱስ ያሬድ የተሰውረበት ዋሻ ይታደሳል ። ሊፈርስ የደረሰው ቤተክርስቲያኑም በአዲስና በዘመናዊ መልክ ይሠራል ። የአብነት ትምህርትቤቱ የጥንቱን ሳይለቅ በዘመናዊ መልኩ ይገነባል ። የቅርሶቹ ማስቀመጫም የሚሆን እጅግ ዘመናዊ ሙዚየም ይገነባል ። ይህን ዓለም አቀፋዊ እቅድ በማቀድ ነው ይህ ኮሚቴ እንቅስቃሴ የጀመረው ። በመላው ዓለም ላይ ያሉ የቅዱስ ያሬድ ወዳጆችና ልጆች አንድ አንድ ቢር በነፍስ ወከፍ ቢያዋጡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የታቀደው እቅድ ሁሉ ፍጻሜውን ያገኛል።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ፃድቁ አባታችን ቅዱስ ያሬድ እዚህ ነው የተሠወረው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2023

🎵 በሰሜን ኢትዮጵያ በጠለምት ደብረ ሐዊ የሚገኘውና ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ድንቅ ገዳም ይህ ነው።

  • ቅዱስ ያሬድ የዜማ ሊቅ ብቻ አይደለም። አቡነ ያሬድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ነው።
  • አቡነ ያሬድ የመጽሐፍ መምህር(ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ነው።
  • አቡነ ያሬድ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ) ነው።
  • አቡነ ያሬድ ልዑለ ስብከት ነው።
  • አቡነ ያሬድ ሰማዕት ነው።
  • አቡነ ያሬድ ባሕታዊ ነው።
  • አቡነ ያሬድ መናኝ ነው።
  • አቡነ ያሬድ የሱራፌል አምሳያ ነው።
  • አቡነ ያሬድ ጥዑመ ልሳን ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ መዓርዒረ ዜማ ነው።
  • አቡነ ያሬድ ካህን (ካህነ ስብሐት) ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ መዘምር ዘበድርሳን
  • ቅዱስ ያሬድ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት)
  • ቅዱስ ያሬድ ዓርከ ሊቃውንት
  • አቡነ ያሬድ መንፈሳዊ ደራሲ ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ የኢትዮጵያ ብርሃን ነው።
  • አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ
  • እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ
  • ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ
  • ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ
  • አእምሮው የመጠቀ
  • ድርሰቱ የተራቀቀ

እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ የሱራፌል አምሳያቸው ነው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዱስ ያሬድን እንዲህ ሲል ያመሰገነው፦

የመንፈስ ቅዱስ ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል

ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤ ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት

ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ።

ቅዱስ ያሬድ አክሱም ጽዮንን እየተሳለማት ሣለ ክብርት እመቤታችን ለቅዱስ ያሬድ ተገልጣለት ቅዱስ ኤፍሬምንና ቅዱስ አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ አምጥታ ድርሰታቸውንና ቅዳሴያቸውን እንዲያሰሙት በማድረግ ቅዱስ ያሬድንም ዜማውን እንዲደርስ እረድታዋለች፡፡ ኹለቱንም ታላላቅ ቅዱሳን ነጥቃ ወደ ቅዱስ ያሬድ ካመጣቻቸው በኃላ “አንተ ውዳሴዬን፣ አንተ ቅዳሴዬን ነግራችሁት በዜማ ያድርስ” ብላቸው እነርሱም ለቅዱስ ያሬድ ነግረውት በዜማ አድርሶታል፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመልክ በመልኩ እያደረገ ዜማውን ደረሰው፡፡ ዜማውንም ሲጨርስ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ በያዘችው የብርሃን ባርካው ተስፋውን ነግራው ዐርጋለች፡፡

ይኽም የቅዱስ ያሬድ ድርሰቱ መነሻውም ሆነ መድረሻው ፍጹም መንፈሳዊ እንደሆነ ያሳያል። አባቶቻችንም ይኽን መንፈሳዊ መገለጥ በሥዕልም ጭምር ገልጠውታል። (ሽሬ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ይኽ ዓይነት ሥዕል ከሚገኙበት ገዳማት ውስጥ የሚገኘው አንዱ ነው።)

አቡነ ያሬድ ይባርክበት የነበረው የእጅ መስቀሉ በ1985 .ም በሆድ አደር ሌቦች አማካኝነት ተሰርቆ ከሀገር ወጥቶ ነበር። በፈረንሳይ ሀገር ለጨረታ ቀርቦ በ15 ሚሊዮን ዶላር ተሸጦ ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሰርቆ ከወጣ ከ18 ዓመት በኃላ በ2003 ወደ አገራችን ተመልሶ መጥቷል። ሊመለስ የቻለውም ሚስተር ዣክየተባሉ በጎ አሳቢ ሰው “…ይህን መስቀል ኢትዮጵያ ውስጥ ጎብኝቼዋለሁ፣ የኢትዮጵያ ንብረት ነውበማለት ወደ ሀገራችን እንዲመለስ ከሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልጆች ጋር በተደረገ ርብርብ ጨረታውን በ15 ሚሊዮን ዶላር አሸንፈው የአቡነ ያሬድን የእጅ መስቀል ወደ አገራችን መልሰውታል። አምላከ ቅዱስ ያሬድ

ክብር ያድልልን በእውነት!

አቡነ ያሬድ በምናኔ በኖረበት ቅዱስ ቦታ ላይ በስሙ ገዳም ተገድሞ መናንያን አሰረ ፍኖቱን ተከትለው ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ በረዶውንና ውርጩን ታግሠው በስሙ እየተማጸኑ ይኖራሉ፡፡ በቦታው እሁድ እሁድ ከመሬት ውስጥ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ቅዱስ ያሬድ መቋሚያውን ወርውሮ ያፈለቀው ፀበል ዛሬም አለ፡፡ ጻድቁ በተሰወረበት በደብረ ሐዊ ተራራ ላይ ብርድ በእጅጉ በጸናበትና በረዶ በሚፈላበት በዚያ አስቸጋሪ ቦታ ላይ እጅግ አስቸጋሪውን የአየር ጠባይ ተቋቁሞ በቦታው ላይ ቢያንስ 7 ቀን ሱባዔ የሚይዝ ካለ ራሱ ቅዱስ ያሬድ እንደሚገለጥለት በቦታው ላይ የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ።

አክሱም አቅራቢያ ቁጭ ብሎ ከትሏ ምሳሌ ወስዶ በተማረበት ቦታ ላይ አንዲት እናት ብቻዋን ለቅዱስ ያሬድ አስደናቂ ቤ/ክ በ2010 .ም አሠርታለታለች። ይኽም ለጻድቁ ለአቡነ ያሬድ ተስላ ስለቷ ደርሶላት እንደሆነ በቦታው ላይ ተነግሮናል። ይኽም ድንቅ ምስክርነት አቡነ ያሬድ ከዜማ ደራሲም በላይ መሆኑን አንድ ማሳያ ነው። በጸሎቱ ሀገርን የሚጠብቅ ባሕታዊ፣ በስሙ ለሚማጸኑት ሁሉ ከአምላኩ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን ደገኛ ጻድቅ መሆኑን አንድ ማሳያ ነው።

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሙሉ አካሏና ብርሃኗ የኾነው አቡነ ያሬድ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ ሞትን ሳያይ የተሰወረው በዛሬዋ ዕለት ነው። የከበረች በረከቱ ትደርብን! በጸሎቱ ይማረን!!!

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Saint Yared The Melodious: The Great African Christian Composer

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2023

😇 የቅዱስ ያሬድ ውብ ዜማ፡፤ ታላቁ ኢትዮጵያዊ / አፍሪካዊ ክርስቲያን የመንፈሳዊ ዜማ አቀናባሪ

  • 505 AD – 571 AD
  • Axumite Ethiopia
  • Ethiopian Christian Liturgical Chant
  • Pioneer of Musical Notation
  • Ten Melodic Notations For Spiritual Melodies

😇 The Feast of the Departure of Saint Yared

🎵 Ginbot ፲፩/11 (May 19) marks the departure of St. Yared, the great Ethiopian composer who lived in the 6th century. The Ethiopian Orthodox Church attributes its rich, age-old chant tradition to the Saint and commemorates his disappearance each year on this day.

St. Yared, who was named after the father of Enoch in the Bible (Genesis 5:18), was born in 505 E.C. in Axum to Abyud and Tawklia. After the death of his father, at the age of seven, his mother sent him to her priest brother named Gidewon to teach the lad and to look after him. As a child, St. Yared never seemed to succeed in his studies as he had difficulty understanding what his uncle taught him. At one point, he had even fled from Gidewon, an incident which led him to the turning point in his life.

While taking shelter under the shade of a tree, Yared saw a caterpillar (some claim an ant) trying to climb the tree. Despite its repeated failures, the insect finally managed to creep up the tree and ate its fruit. Yared drew an inspiration from the determination of the tiny creature and went back to his uncle to start learning afresh. His efforts then bore fruit and he managed to learn by heart whatever he was taught including both Old and New Testament with unbelievable brilliance, and grew in excellence as he grew older and older.

Saint Yared also gained melodic insight through divine revelation and composed melodious sacred melody which had never been heard before in this world. He created a system of chants in three modes (scores) called Ge’ez, Izil, and Ararary. There is no any sound system out of the category of the three modes of these hymns St Yared invented divinely. Saint Yared also wrote five volumes of chants for church services and celebrations. These volumes include The Book of Digua and Tsome Digua (chants for church holidays and Sundays services), The Book of Me’eraf (chants for major holidays, daily prayers and the season of fasting), The Book of Zimmare (chants to be performed after Mass) and The Book of Mewasit (chants for the dead). ST. Yared also created ten melodic notations for his spiritual melodies many centuries before the world-renowned composers Mozart and Beethoven.

Yared eventually became the father of Ethiopian traditional church education. He pioneered biblical interpretation, hymnody and liturgical dance, yet is best known for his musical compositions. His antiphonary books also contributed to the Qene poetry in classical Ethiopic.

There are two views among scholars of the church about the final days of St Yared’s life in this world. Some say he passed away while others contend that he disappeared like Saint Henok and Elijah the Prophet.

Despite that, every year on Ginbot 11 (May 19), the Ethiopian Orthodox Church marks the disappearance of the Saint who adorned its service with melodious sacred music.

According to Ethiopian tradition, God sent three white birds from heaven to Yared, foretelling him that he will learn to recite the hymnody of the 24 heavenly priests. Having seen the divine liturgy, Yared immediately began to compose poetic hymns and went to the sacred Zion Church of Axum. There, in the year 541, he offered praise to the Trinity and improvised the following hymn that connects creation, Sabbath and the Ark (Tabot):

In the beginning, God made the Heaven and the Earth; And having completed all, He rested on the Sabbath; And Said He to Noah at the onset of the Flood: “Build yourself an Ark by which you may be saved.”

Since classic Ethiopic manuscripts are revered as sacred objects of the church, Yared’s hymns and chants remained stable. However, his students introduced minor additions. Other scribes slightly revised the text and music notations.

The three dominant musical instruments in the liturgy are the prayer staff (Tau-cross), the sistrum and the drum.

The major Yaredic melodies represent persons of the Trinity:

  • The Ge’ez tune (not the classic Ethiopic language) symbolizes the Father. It is hard and stern.
  • The Izl melody is gentle and full of love. It is a representation of the Son.
  • The Araray tune, symbolizing the Holy Spirit, has a melancholic quality. It is used for occasions like Lent and funerals.

May the blessing of Saint Yared be with us all!

🎵 Musical notation

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Music | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መታሰብያቸው ለዘላለም ከሚኖረው ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 1, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 😇 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

😇 ሰባት ዓመት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሀገር፥ ለቤተክርስቲያን፥ ለምዕመናን እና ለዓለም ሁሉ የጸለዩት የቅዱሱ አባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት ረዲኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

፲፰፻፺፰ ዓ.የተመሠረተውና ውቡ የአዲስ አበባ ደብረአሚን አቡነ ተክለሐይማኖት ቤተክርስቲያን ፪ሺ፲፩ ዓ.

አረመኔው ግራኝና ኦሮሞ ሰአራዊቱ ግባቸውን መትተዋል፤ ከ፩ ሚሊየን በላይ ተዋሕዷውያንን ጨፍጭፈዋል፣ ገዳማቱንና ዓብያተክርስቲያኑን አፈራርሰዋል፤ ቀሪውን ደግሞ ለረሃብና በሽታ አጋልጠው እንዲዳከሙ አድርገዋቸዋል!

በአክሱም ጽዮን ላይ የሚካሄደው የዘር ማጥፋት ጦርነት ጥንታውያኑን ጽዮናውያንን የማጥፊያና የማዳከሚያ ጦርነት ነው። ዛሬም የምለው ነው፤ ኢአማኒያን የሆኑት የሕወሓት አመራሮችና ኦሮሞዎቹ የአክሱም ጽዮን ጠላቶች እነ ግራኝ አህመድ አሊ + ለማ መገርሳ + ጃዋር መሀመድ ይህን ጦርነት በጋራ ተናብበውና

የፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ የከፈተው ጦርነት ዋና ዓላማ መጀመሪያ የተጋሩ ጽዮናውያንን ከዚያም ተዋሕዶ አማራዎችን ከምድረ ገጽ አጥፍቶ እስላማዊት ኦሮሚያ ኤሚራትን ለመመስረት ነው! ይህን መላው ዓለም ተገንዝቦታል! ዛሬ ከእስራኤል ፕሬዚደንትና የአሜሪካ ልዑካን እስከ እባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ድረስ ሁሉም ወደ ባቢሎን ዱባይ ያመሩት ፩ኛ ‘ድላቸውን ለማብሰር’፣ ሁለተኛ ቀጣዩን ዲያብሎሳዊ ዕቅዳቸውን ለመተገበር ነው። አደገኛ ከሆኑት የፋርማ ኢንዱስትሪ ተቋማት መካከል “ፋይዘር” የተሰኘው የክርስቶስ ተቃዋሚ ኩባንያ በተለየ ና አውሬያዊ በሆነ መልክ ቀምሞ ያዘጋጃቸውን ክትባቶቹን ለብዙ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን እንደሚልክ በትናንትናው ዕለት አስታውቋል። ይህ ኩባንያ ዛሬ የኮሮና ክትባቶችን የሚያመርት ቍ. ፩ ኩባንያ ነው። ክትባቶቹ በተለይ የመንፈሳውያን ሰዎችን ማንነት ለመቀየር የሚያስችሉ መርዛማና ዘር-ለዋጭ ኬሚካሎችን መያዛቸውን ለአንዴም እንኳን መጠራጠር የለብንም።

ባጠቃላይ የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ሁሉም ዓለም አቀፋዊ አካላትና መንግስታት፤ “Thesis-Antithesis-Synthesis(ተሲስ ፣ ፀረፀረስታ እና ውህደት/መደመር)+ ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” የተሰኙትን የጀርመኑ ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል ያወጣቸውን ኋላ ቀር ዲያብሎሳዊ ሂደቶችን ተከትለው ነው ሁሌ የሚንቀሳቀሱት።

የሄግሊያን የቲሲስአንቲቴሲስሲንተሲስ ሂደት በፍሪሜሶነሪ/ነፃ ግንበኞች እና በሉሲፈሪያን ኢሶቴሪዝም/ምስጢረኞች ዘንድ ተቀባይነት ያለውን/ ያገኘውን የአልኬሚ፤ “Solve et Coagula (ፍታ እና አገናኝ)” የሚለውን መፈክር ያስተጋባል። ይህ በሜሶናዊ ኑፋቄ ከፍተኛ ደረጃዎች/ልሂቃን ዘንድ የተከበረው ገሃነማዊ ጣዖት በባፎሜት እቅፍ ላይ የሚታይ መፈክር ነው፣ በጣም ስልጣን ባላቸው የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮችና ስውር/ጥልቅ መንግስታት ዘንድም ተቀባይነት ያለው መፈክር ነው። በሄግሊያን ዲያሌክቲክስ፤ የክርስትና ሃይማኖት ተሲስንከአረማዊ መንፈሳዊነት እንደ ጸረ ቴሲስፀረፀረስታ ጋር ያጣመረ ሲሆን ይህም ከባቢሎናውያን ሚስጥራዊ ሃይማኖቶች ጋር በጣም ተመሳሳይ በሆነ ውህደት/መደመር ነው። “ክሪስላም/Chrislam ፣ አቃፊ ኢሬቻቅብርጥሴ ” እያሉ በጥንታውያን ክርስቲያን ሕዝቦች ላይ የሚዘምቱት ለዚህ ነው።

ችግሩን በጋራ ሆነው ጦርነቱን በመቀስቀስና ወንድማማቾችን በማባላት ፈጥረውብናል አሁን ምላሽ እየሰጡ ነው። መፍትሔው፤ “የክርስቶስ ተቃዋሚውን ልዑላችንን ተቀበሉ፤ የሉሲፈርን ባንዲራ አውለብልቡ (የሕወሓትን + ብእዴንን) ሃይማኖታችሁን፣ ባሕላችሁን፣ ቋንቋችሁን ተው! ፥ ገንዘቡን ፣ ምግቡን፣ ክትባቱን ሁሉ ከእኛ ነውና የምታገኙት እኛን ከተከተላችሁ ብቻ ነው ለእርዳታየምንደርስላችሁ…” እንግዲህ የፈጣሪን ሚና መጫወታቸው ነው። እነ ግራኝ አሁን ለትግራይ ሕዝብ፤ “እኛ ስንፈቅድልህ ነው እንጀራ፣ ውሃና መድኃኒት የምታገኘው ወዘተ” በሚል ድፍረትና እብሪት እራሳቸውን እንደ አምላክ መቁጠር ይጀምራሉ። ለእነዚህ የሰይጣን ጭፍሮች ሃሳቡ ብቻ ምን ያህል ማራኪ እንደሆነ እንታዘበው። ግን ወዮላቸው!

የኦሮሞ ብልጽግናዎች፣ የትግራይ ሕወሓቶችና የአማራ ብእዴኖች አስቀድመው የትግራይን ሕዝብ በምርጫ እና ፈንቅል በተባለው እንቅስቃሴ ሊፈትኑትና ሙቀቱንም ሊለኩት ድራማውን ሰሩ። አዝማሚያው ስላላማራቸውና በተለይ “ፈንቅል” የተሰኘው የሳምንታት እንቅስቃሴበአማራዎች ዘንድ ድጋፍ ማግኘቱን ከተገነዘቡ በኋላ ተደናግጠው፤ የዘር ማጥፋት ጦርነቱን ለመክፈት ተጣደፉ። ትግራይንም ሙሉ በሙሉ ዘግተውና ባዕዳውያኑንን ሳይቀር በማስገባት እየጨፈጨፉት ነው። በተጨማሪ የተለያዩ የማጭበርበሪያ ድራማዎችን እየሠሩ ጊዜ በመግዛት ሕዝቡን ለረሃብና በሽታ እንዲጋለጥ አደረጉት። አሁን የተረፈው የትግራይ ሕዝብ አማራጭ የለሽ እንዲሆን ከተደረገ በኋላ፤ “የሰላም ድርድር” ብለው ከፍተኛ ወንጀልና ግፍ የፈጸሙትን እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊንና ፋሺስት ኦሮሞ አገዛዙን፣ እንዲሁም ሕወሓቶችን፣ ሻዕቢያን፣ ብእዴንን፣ ኢዜማን፣ ቱርክ፣ ኤሚራቶች፣ ሶማሌዎችና ሌሎች አጋሮቻቸውን ሁሉ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከተፈጸመው በታሪክ ተወዳዳሪ የሌለው ግፍና ወንጀል ነፃ በማድረግ፤ ወደ ቀጣዩ ዙር የሕዝበ ክርስቲያኑን ቍጥር የመቀነሻ ዘመቻ ያመራሉ። ግን፤ ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ልጆችህ በዚህ ዓለም ብዙ መከራ ቢያገኛቸውም በአንተ ዘንድ ፍጹም ሰላምና እረፍትን እንደሚያገኙ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ከሐዲዎችን የምትበቀል ቄርሎስ የተባልክ አንተ ተክለ ሐይማኖት ነህ እኮን።

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ የሥላሴን አንድነት ሦስትነት በማስተማር ዓዋጅ ነጋሪነትህ ፍጹም ድንቅ ነው። እባቡን በእርግጫ አንበሳውን በጡጫ ብለው የሚያልፉ የሴትና የወንድ ደቀ መዛሙርት በጸጋ ወልድሃልና።

ያለምንም ተድኅሮ በሥላሴ ስም ይህን ሦስትነት አምናለሁ፤ በተንኮል ወንድማማቾችን እርስ በርስ የሚያባሉትን፣ ደንፍተው የሚያጠቁንን፣ ወዳጅ መስለው ሊያጠፉን የፈለጉትን የሚከተሉትን የጽዮንን ጠላቶች የእግዚአብሔር ቃል ይቅሰፋቸው፣ በተሣለ የመለኮት ሠይፍ አንገታቸውን ይቍረጣቸው፤ አሜን!!!

💭 ከሦስት ዓመታት በፊት የቀረበ ጽሑፍ፤

ሀገራችን ኢትዮጵያ የእነ ግራኝ አህመድ ሳትሆን የአቡነ ተክለሐይማኖት ሀገር ናት፤ በዚህም ትልቅ ተስፋ አለን፥ ነገር ግን የሕዝባችንን የስቃይ ዘመን ማሳጠር የምንሻ ከሆነ ከእነ ዶ/ር አብዮት አህመድ አሁኑኑ መራቅና ሂድ! ማለት ይኖርብናል። ዘንዶው ሰውዬ እርኩስ መንፈስ እና መጥፎ እድል ነው ለሀገራችን ይዞ የመጣው፤ የዚህም መገለጫ የሆኑትን እስልምናን እና ግብረሰዶማዊነትን ለማስፋፋት የተላከ መሆኑ ዓይናችን እያየው፡ ጆሮዋችንም እየሰማው ነው። ይህ ሰው(መንፈሱ) ከእነ መንግስቱ ኃይለማርያም የባሰ አደገኛ ሰው ነውና ቶሎ ይወገድልን ዘንድ የብጹእ አባታችንን አቡነ ተክለሐይማኖት አማላጅነት እንዳይለየን ተግተን ልንጸለይ እና ዳዊታችንንም አዘውትረን ልንደግም ይገባናል። እዚህ ላይ ባክልበት፤ በደርግ ጊዜ መንግስቱ ኃይለማርያም ብዙ የኢትዮጵያ ህፃናትን ለግብረሰዶማዊ ሙከራ ወደ ኩባ/ጓንታናሞ ልኳቸው ነበር፤ አንዷ ትንሽ ደሴት ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተዘጋጀች ነበረች። ይህን በተመለከተ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ደርሶባቸው ስለነበረው ጉድ እና እንዴት ደብረ ሊባኖስ ሄደው ለመፈውስ እንደበቁ ከጥቂት ዓመታት በፊት ኖርዌይ ላይ በነበረ ቆይታችን በሚያሳዝን መልክ አጫውተውን ነበር። ለእነዚህ ሁለት አውሬ የሲ አይ ኤ ቅጥረኞች አሁንም ሆይሆይ የምትሉ ቶሎ ንሰሐ ግቡ!

ሰባት ዓመት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሀገር፥ ለቤተክርስቲያን፥ ለምዕመናን እና ለዓለም ሁሉ የጸለዩት የቅዱሱ አባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት ረድኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

አባ አባ

አባ አባ ተክለሐይማኖት አብዬ//

በለኒ በለኒ ወልድዬ //

አዝማች

አባ አባ….እንኳን ሰው ምድሪቱ

አባ አባ….ፆም አያሳድርም

አባ አባአምላከ ተክልዬ

አባ አባብዬ አፍሬ አላውቅም

አባ አባምድራዊ መላክ ነህ

አባ አባየኢትሳ አንበሳ

አባ አባለደብረ ሊባኖስ

አባ አባአንተ ነህ ሞገሷ

አዝማች

አባ አባስማኒ ብያለሁ

አባ አባሳለ በሰማይ

አባ አባከኪሩቤል ተርታ

አባ አባሆነህ ስትታይ

አባ አባስምህም ሲጠራ

አባ አባገድልህ ሲነገር

አባ አባእጹብ ድንቅ ያሰኛል

አባ አባየተሰጠህ ክብር

አዝማች

አባ አባአባቴ እልሃለሁ

አባ አባ ልጄ ሆይ በለኝ

አባ አባየአባትና የልጅ

አባ አባፍቅርህ ይጽናልኝ

አባ አባንፍሮ ውሃ ጠጥቼ

አባ አባታምር አይቻለሁ

አባ አባእባብ እና ጊንጡን

አባ አባተረማምጃለሁ

አዝማች

አባ አባ… እለት በእለት ሂጄ

አባ አባ… ደጅ ስጠናው

አባ አባይሰማል ተክልዬ

አባ አባዛሬም ህያው ነው

አባ አባእንቆቅልሽ ፈቶ

አባ አባደስ አሰኝቶኛል

አባ አባየተክለሐይማኖት

አባ አባ… ብራኬው ደርሶኛል

_______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጽዮናዊው ንጉሥ አጽበሃ የመሠረቱት የ የካ ሚካኤል ዋሻ ቤተ ክርስቲያን | እርስቴን ለኦሮሞ ወራሪዎች አሳልፌ አልሰጥም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 22, 2021

St. Michael Church was in use from 320 to 1878 AD

💭 ይህን የአባቶቻችንን ታሪክ የምትሰሙ እና የምታነቡ ጽዮናውያን፤ ወራሪዎቹ ኦሮሞዎች አዲስ አበባን እና ደቡብ ኢትዮጵያን “ኬኛ” ሲሉ ስትሰሟቸው ደማችሁ አይፈላምን?፣ “ከላይ ሆነው የሚያዩን አባቶቻችን ይቆጣሉ፣ ያለቅሳሉ!” ብላችሁ አትደነግጡምን? በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ባለ ወቃማ ታሪክ የሆኑ የትግራይ ወገኖች እንደ ሕወሓት በመሳሰሉ ተዳጋጋሚና አላስፈላጊ የሆነ ስህተት በሚሠሩ ቡድኖች ማንነታቸውን እና ምንነታቸውን፣ ታሪካቸውን፣ ሃይማኖታቸውንና ምልክቶቻቸውን ሁሉ ልክ እንደ ዔሳው እንዲከዱ/እንዲተው/እንዲሸጡ እና ለጠላቶቻቸው እንዲያስረክቡ እየተደረጉ መሆኑ ነው። እስኪ ይታየን፤ እኔ መኪናየን ከእነ ቁልፉ ወይንም ጫማዬን መንገድ ላይ ትቼ ብሄድ እኮ መንገደኛው “የኔ ነው/ኬኛ” ብሎ ይወርሰዋል። አይደል?!

እንግዲህ ፳፯/ 27 ጥንታውያን የኢትዮጵያ ነገዶችን ጨፍጭፈው ከምድረ ገጽ ያጠፏቸው ወራሪዎቹ የዋቄዮ-አላህ አርበኞች የሆኑ ኦሮሞዎች/ ጋሎችም ወደ አብርሃ ወአጽበሐ እና ንጉሥ ዳዊት ከተማ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከመስፈራቸውና “ፊንፊኔ ኬኛ” የሚለውን የእባብ ገንዳ መዝሙራቸውን ከመጻፋቸው ከሺህ ዓመታት በፊት የታነጸውን ታሪካዊውን የየካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን / ዋሻን፤ አንድ ጽዮናዊ፤ እንደ አቶ ጌታቸው፤ “አይ እኛ ሥልጣን አንፈልግም፣ ግዛት ለመቀማት አይደለም ቅብርጥሴ” ማለት ሳይሆን የሚጠበቅበት፤ በቀጥታ እና በድፍረት፤ “አይ! ይሄ እኮ የአባቶቻችን እርስት ነው! እኛ ነን የሠራነው፣ ይህን እርስታችንን ለማንም ወራሪ አሳልፈን አንሰጥም፤ አርፈህ ትኖር ከሆነ ኑር አልያ ተጠራርገህ ትወጣ ዘንድ ግድ ይሆናል ወዘተ” የሚል ወገን ነው ዛሬ የሚያስፈልገው።

ዛሬ የእግዚአብሔር አብ ዕለት ነው፣ ወደ ጸሎት በምንገባበት ወቅት የወገኖቻችንን ሰቆቃና ለቅሶ በይበልጥ እየሰማን ነው፤ የአቤል ደም እየጮኸ ነው፤ የጽዮን ጠላቶች እየተርበተበቱ ነው፤ ግን የትም አያመልጧትም፤ ለዓመታት ስናስጠነቅቅ ቆይተናል፤ አሁን አንድ በአንድ በመለኮታዊ ሰይፍ የሚጠረጉበት ጊዜ ተቃርቧል፤ ቀጣዮቹን ቀናት በጥሞና እንከታተላቸው፤ የጽዮናውያን ድልና የዋቄዮአላህ አህዛብ ሽንፈት ወቅት በጣም እየተቃረበ ነው!

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን።

❖❖❖ ታሪካዊው የካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ዋሻ ቤተክርስቲያን ❖❖❖

በ፬/4ኛው ክፍለ ዘመን በአክሱም ንጉሥ በአጽበሃ ተመሠረተ

❖❖❖ የአንጋፋው ቀደምት እና ባለ ታሪክ የካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ዋሻ ቤተክርስቲያን ታሪክ ❖❖❖

ዋሻ ሚካኤል ከአዲስ አበባ በስተምስራቅ በኩል የካ ከፍለ ከተማ ውስጥ ያለ ጥንታዊ እና በከፊል ወጥ ከሆነ ዓለት ተፈልፍሎ የተሰራ ቤተክርስቲያን ነው። አዲስ አበባ ከሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ በስተጀርባ ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው ከፍታማ ቦታ ላይ ይገኛል። ምንም እንኳ የአካባቢው የቀደሙት ካህናት በ፬/4ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ቢናገሩም በአብዛኛው ሊሆን ይችላል ተብሎ የሚገመተው ግን በ፲፪/12ኛው ክፍለ ዘመን እንደተሰራ ነው።

👉 ታሪካዊ ተደራሽነቱ

የአክሱም መንግስትና የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን:- አብርሃና አጽብሃ የአክሱም መንግስትን በጋራ ይገዙ እንደነበር የተለያዩ መጽሃፍት ይገልፃሉ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጽሁፍም ይሄንን በተለያዩ መረጃዎች ይጠቅሳል፡፡ ክርስትናን ከተቀበሉ በኋላ እንደተፃፈ በሚነገረው የድንጋይ ላይ ፅሁፍ አብርሃና አፅብሃ የሚያስተዳድሩት አገር ግዛት ዝርዝር ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ዝርዝር እንደምንረዳው ግዛታቸው ሳባን /የመንን/፣ ኑባ /ሱዳንን/ እና ቤጃ /ደቡብ ግብጽ/ ድረስ ይደርሳሉ፡፡ ይህም እጅግ ሰፊ ግዛት እንዳላቸው ያስረዳል፡፡ ከየካ ሚካኤል የተገኘው /ያልታተመ/ መረጃ ይህንን ሀሳብ እንደሚከተለው ያጠናክራል።

በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ ወሰን በጣም ሰፊ ስለነበር ሁሉቱ ወንድማማቾች አክሱም ላይ ሆነው ሕዝባቸውን በቅርብ ለማስተዳደር ስለተቸገሩ እጣ ተጣጥለው ንጉስ አብርሃ አክሱም ላይ በመሆን ሰሜን ኢትዮጵያን፣ ንጉስ አጽብሃ ደግሞ ደቡብ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ሸዋ ውስጥ የረር ተራራ ላይ ቤተ መንግሥቱን ሰራ፡፡ በወቅቱ ቤተመንግሥቱን ለመሥራት ሲመጣ ማዕቀበ እግዚእ በሚባል ካህን ታቦት ሚካኤልን አሸክሞ አስመጥቶ ነበር፡፡ ይህንን አሸክሞ ያስመጣውን ታቦት ከየረር ተራራ በስተ ሰሜን አቅጣጫ ባስፈለፈለው ዋሻ ውስጥ እንዳስገባው ይገልፃል፡፡”

በትግራይ ክልል በአብርሃና አፅብሃ ቤተ ክርስትያን ውስጥ ከጅማ የአፅብሃ ሬሳ የመጣበት ነው የሚባለው የጠፍር አልጋ ይገኛል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ደቡብ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው አፅብሃ እስከ ጅማ መድረሱን ነው፡፡ ውቅር ቢተክርስቲያን መስራት ለአጽብሃ አዲስ አይደለም፡፡ በትግራይ ከውቁሮ ከተማ ፳/20 .. ርቀት ላይ ገረአልታ ውስጥ ገማድ በተባለ ስፍራ አብርሃና አጽብሃ ያሰሩት ነው የሚባል አብርሃ አጽብሃ በመባል የሚታወቅ ውቅር ቤተክርስቲያን ይገኛል፡፡ ቤተክርስቲያኑ ገዳም ነው፡፡

ከየካ ሚካኤል የተገኘው/ያልታተመ/ መረጃ እንደሚገልፀው በትግራይ ውቅሮ አካባቢ የሚገኘው የአብርሃና አፅብሃ ውቅር ቤተክርስቲያን ከዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው በመግለጽ ታሪኩን እንደሚከተለው ዘርዝሯል፡-

ከንጉስ አጽብሃ ጋር የመጣው ታቦት የገባበት ዋሻ የተፈጥሮ ዋሻ ሳይሆን በሰሜን ኢትዮጵያ እንደሚገኙት ከአንድ ቋጥኝ ድንጋይ ተፈልፍለው ከታነፁት ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ዓይነት በኢትዮጵያ ፊደል “ሀ” ቅርጽ የታነፁ ሲሆን በቤተክርስቲያን የፊደል ትርጉም “ሀ” ማለት “ህልዎቱ ለአብ እምቅድም ይትፈጠር ዓለም” ወይም “የአብ መኖር ከአለም አስቀድሞ ነው” ማለት ነው የሚለውን አባባል ለማስረዳት ተብሎ የታነፀ ነው ይላል፡፡” በሌላ በኩል አንዳንድ የታሪክ ተመራማሪዎች የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስቲያን በደቡብ ሸዋ ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ በአለምገና ቡታጅራ መንገድ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ ፷፮/66 ኪሎ ሜትር አካባቢ ከምትገኘው አዳዲ ማሪያም ውቅር አብያተ ክርስቲያን ጋር በመመሣሠሉና ይህ ደግሞ በንጉስ ላሊበላ ዘመን እንደ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በዚያ ዘመን የተሰራ ነው ይላሉ፡፡

በአዳዲ ማርያም የሚገኘው የታሪክ ማስታወሻ ንጉስ ላሊበላ የአዳዲ ማሪያምን ከቋጥኝ ድንጋይ እንደፈለፈለውና ሥራውን ሲጨርስ በራዕይ ተመርቶ ወደ ላሊበላ እንደተመለሰና እዚያ ሲደረሰ እንደሞተ ይተርካል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየሶስት ወሩ በሚያሳትመውና ሰላምታ ተብሎ በሚጠራው ቋሚ የበረራ መፅሄት ዊሊያም ዴቪድሰን የተባሉ የታሪክ ተመራማሪ የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስትያን የ፯፻/700 ዓመት እድሜ እንዳለውና አሰራሩም ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አሰራር ጋር እንደሚመሳሰል ይገልፃሉ፡፡

በየትኛው ዘመን እንደተሰራ ለማወቅ የአርኪዎሎጂ ጥናት መደረግ ስላለበት የነሱን የወደፊት የጥናት ውጤት መጠበቁ ወሳኝ ቢሆንም ከየካ ደብረሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ያገኘነው ያልታተመ ፅሁፍ የዋሻ ሚካኤል ውቅር ቤተክርስትኑ ከላሊበላ ጋር በማመሳሰል ማቅረብ የኢትዮጵያን ሀይማኖት ጥንታዊነት በሚፃረሩ ሀይሎች የሚወራ ነው በማለት ይቃወማሉ፡፡

አብርሃና አፅብሃ ከአባታቸው ታዜር ከእናታቸው ሶፍያ (አይዋል) ታህሳስ ፲፱/19ቀን ፫፻፲፪/312 .. ተወለዱ፡፡ አባ ሰላማ (አባ ከሣቴ ብርሃን) በ፳፰/28ኛ ዓመታቸው አጠመቁዋቸው፡፡ አብርሃና አጽብሃ ከአባ ሰላማ ጋር በመሆን ክርስትናን በግዛታቸው አስፋፍተዋል፡፡ በዘመናቸው ፷/60 አብያተ ክርስቲያናትን እንዳሳነፁና ከዚህም ውስጥ ፵፬/44 ቤተክርስቲያናት ፍልፍል ቤተክርስቲያናት ናቸው፡፡ በስማቸው ቤተክርስቲያን ታንፃል፡፡ በየወሩ በ፬/4ኛው ቀንና በየዓመቱ ጥቅምት ፬/4 በአክሱም ፅዮንና መርጦ ለማርያም ቤተክርስትያናት በዓላቸው ይከበራል፡፡

እንደ ነገሥታቱ ገድል በ፴፪/32ዐዎቹ ንጉሥ አጽብሃ በየረር ተራራ ላይ የገነባው ቤተ መንግሥትና ከቤተመንግሥቱ በስተ ሰሜን አቅጣጫ የተገነባው ውቅር ቤተክርስቲያን በአባ ከሣቴ ብርሃን የመጀመሪያው ጳጳስ ተባርኮ ተመረቀ፡፡

አብርሃና አጽብሃ የጀመሩትን ክርስትናን የማስፋፋት ሥራ በተከታዮችም ነገሥታት የቀጠለ ሲሆን በ፮/6ተኛው ክፍለ ዘመን በአፄ ካሌብና በአፄ ገ/መስቀል የንግስና ዘመን በበለጠ ተስፋፍቷል፡፡ በ፮/6ተኛው ክ/ዘመን በተለይ ዘጠኙ ቅድሳን ከመጡ በኋላ ክርስትናን የማሠራጨቱ ሥራ ይበልጥ ተስፋፍቷል፡፡

በአክሱም ዘመነ መንግስት ዮዲት ጉዲት የተባለች በአክሱም ግዛት ያሉትን አብያተ ክርስቲያናትና ቄሶችን ማጥፋት በጀመረች ጊዜ የአክሱም ፅዮንን ጨምሮ አንዳንድ ታቦታት ወደተለያዩ ቦታዎች ተሰደዋል፡፡ ምናልባት እነዚህ የፀረ ክርስትና ሰዎች አጽብሃ ወዳሰራው ውቅር ቤተክርስቲያን ቢመጡም ታቦቱን የእምነቱ ተከታዮች እስከ ፲፰፻፴፰/1838 ዓ.ም ድረስ ይዘው ሲሰደዱ እንደቆዩና በመጨረሻ ቡልጋ ውስጥ ከሚገኘው ኢቲሳ ተ/ሃይማኖት ገዳም የቅዱስ ሚካኤልን ጽላት እንዳመጡት ይነገራል፡፡

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር አብ ፥ የአጽናፈ ዓለሙ ፈጣሪ እና ገዥ ተዓምሩን በቅርቡ ያሳየናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 22, 2021

💭 በአስደናቂ ልዩ ጥበብ የተሠራውና “አዲሱ ገበያ” ተብሎ በሚጠራው ሠፈር የሚገኘው ውቡ የእግዚአብሔር አብ ቤ/ክርስቲያን ሕንፃ፤ አዲስ አበባ ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም።

💭 እንዲሁም ፳፯/ 27 ጥንታውያን የኢትዮጵያ ነገዶችን ጨፍጭፈው ከምድረ ገጽ ያጠፏቸው ወራሪዎቹ የዋቄዮ-አላህ አርበኞች የሆኑ ኦሮሞዎች/ ጋሎች ወደ አብርሃ ወአጽበሐ እና ንጉሥ ዳዊት ከተማ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከመስፈራቸውና “ፊንፊኔ ኬኛ” የሚለውን የእባብ ገንዳ መዝሙራቸውን ከመጻፋቸው ከሺህ ዓመታት በፊት የታነጸው ታሪካዊው የካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን / ዋሻ

ዛሬ የእግዚአብሔር አብ ዕለት ነው፣ ወደ ጸሎት በምንገባበት ወቅት የወገኖቻችንን ሰቆቃና ለቅሶ በይበልጥ እየሰማን ነው፤ የአቤል ደም እየጮኸ ነው፤ የጽዮን ጠላቶች እየተርበተበቱ ነው፤ ግን የትም አያመልጧትም፤ ለዓመታት ስናስጠነቅቅ ቆይተናል፤ አሁን አንድ በአንድ በመለኮታዊ ሰይፍ የሚጠረጉበት ጊዜ ተቃርቧል፤ ቀጣዮቹን ቀናት በጥሞና እንከታተላቸው፤ የጽዮናውያን ድልና የዋቄዮ-አላህ አህዛብ ሽንፈት ወቅት በጣም እየተቃረበ ነው!

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን።

___________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሰውን ሕይወት የሚያበላሹትና አገር የሚያጠፉት ክፉ መካሪዎች ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 13, 2020

የመጥምቁ የቅዱስ ዮሐንስን በዓል በማስመልከት የቀረበ ግሩም ትምሕርት

ሰይጣን አዳም አባታችንንና ሔዋን እናታችንን በገነት በነበሩበት ጊዜ በሥጋ ከይሲ (በእባብ አካል) ተሰውሮ ተሸሽጎ ክፉ ምክርን መክሮ አምላክ አታድርጉ ያላቸውን እንዲያደርጉ በማድረግ እግዚአብሔርን እንዲበድሉ ኃጢአት እንዲሠሩ ትዕዛዙን እንዲያፈርሱ አድርጓቸው እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምርናል።

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል ዓላማው ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት እንጂ ሰዎችን በእርሱ ዙሪያ መሰብሰብና መክበር አልነበረም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደሚነግረን «ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳ፣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ነገር ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይጎርፉ ነበር፡፡» /ማቴ.፫÷፭-፡፮/ እርሱ ግን «እኔ በውኃ ለንስሐ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡» እያለ ሰዎቹ እርሱን እንዲከተሉ ሳይሆን የጌታችንን መምጣት ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርግ ትምህርት ያስተምራቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

የመጀመሪያዎቹ ጌታችንን የተከተሉት ደቀመዛሙርት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ነበሩ፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን መታጀብ /በሕዝብ መከበብ/ ለሚያስደስተን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የእኛን ተከታዮች እንደ ፈሪሳውያን ለምንፈልግ አገልጋዮች ትልቅ ተግሳጽ ነው፡፡

እግዚአብሔር ከመልካም ምክር እንዲያገናኘን ክፉውን እና መልካሙን ምክር እንድለይ ማስተዋሉን እንዲሰጠን ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን!

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መንፈስ ቅዱስ በሰው ላይ አድሮ ጥበብን ይገልጣል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 7, 2020

እንኳን ለበዓለ ጰራቅሊጦስ በሰላም አደረሰን!

ጰራቅሊጦስ› የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት አንዱ የኾነው የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ስም ሲኾን፣ ትርጕሙም በጽርዕ (ግሪክ) ቋንቋ

  • 👉 ናዛዚ (የሚናዝዝ)
  • 👉 መጽንዒ (የሚያጸና)
  • 👉 መስተፍሥሒ (የሚያስደስት) ማለት ነው።

መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት በወረደበት ዕለት በቤተ ክርስቲያን የሚከበረው ይህ በዓል ‹በዓለ ጰራቅሊጦስ› ወይም ‹በዓለ ጰንጠቆስጤ› በመባል ይታወቃል። ‹ጰንጠቆስጤ› በግሪክ ቋንቋ በዓለ ኀምሳ፣ የፋሲካ ኀምሳኛ ዕለት፣ በዓለ ሠዊት (የእሸት፣ የመከር በዓል) ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፱፻፮፱፻፯)

ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካረገ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ሰባ ሁለቱ አርድእት፣ አምስት መቶው ባልንጀሮች እና ሠላሳ ስድስቱ ቅዱሳት አንስት በኢየሩሳሌም ከተማ በአንድነት ኾነው በጸሎት ይተጉ ነበር።

ጌታችን በሚያርግበት ጊዜ እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ፤ሲል ለሐዋርያቱ በሰጣቸው የተስፋ ቃል መሠረት በዐረገ በዐሥረኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል (ሉቃ. ፳፬፥፵፱)። ዅሉም በአንድ ቦታ ተሰባስበው ሳሉ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማለዳ እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ ወርዶ የነበሩበትን ቤት ሞላው። ከዚያም የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በዅሉም ላይ አረፉባቸው። በዚህ ጊዜ ዅላቸውም መንፈስ ቅዱስ ባደላቸው መጠን በየአገሩ ቋንቋዎች ዅሉ ተናገሩ (ሐዋ.፪፥፩)

ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ በዓል ዐሥራቱን፣ በኵራቱን፣ ቀዳምያቱን ካህናተ ኦሪት ስለሚቀበሉበት በብሉይ ኪዳን በዓለ ሠዊት ተብሎ ይከበር ነበር። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉበት በበዓለ ሠዊት ምትክ በዓለ ጰራቅሊጦስ ገብቶበታል። የበዓለ ትንሣኤ መነሻው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ማለትም በግብጽ፣ እስራኤል ከሞት የዳኑበት የመታሰቢያ በዓል እንደ ኾነው ዅሉ፣ ለበዓለ ጰራቅሊጦስም መነሻው ይኸው የአይሁድ የፋሲካ በዓል ነው። የአይሁድ ፋሲካ ከተከበረ ከሰባት ሳምንታት በኋላ በኀምሳኛው ቀን የሩቆቹ ከከተሙበት ወጥተው፣ የቅርቦቹ ከተሰባሰቡበት ተገናኝተው ለበዓሉ ፍጻሜ የሚኾነውን በዓለ ሠዊት (የእሸት በዓል) ያከብሩ ነበር።

ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ኾነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን

___________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

እነ ሞዛርት ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ በኢትዮጵያችን ተወለደ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 15, 2019

አውሮጳውያኑ የዜማ ሊቃውንት ሞዛርትና ቤትሆቨን ከመወለዳቸው ሺህ ዓመታት አስቀድሞ በኢትዮጵያችን የተወለደ ነው ሊቁ ማኅሌታይ አባታችን ቅዱስ ያሬድ። ጻድቁ የተወለደው በ505 /ም አክሱም ጽዮን አቅራቢያ ሲሆን አባቱ ይስሐቅ (አብድዩ ) እናቱም ክርስቲና (ታኡክልያ) ይባላሉ።

ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ

ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን:

ክብራችን: ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን?

አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም): ልቡናው የቅድስና ማሕደር:

ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው:: እስከ አርያም

ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ!

+ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት:- “ቅዱስ ያሬድ

ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ

ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ: ሙሉ አካሏ ነው

የጻድቁ ረድኤትና በረከት ከሀገራችን ከኢትዮጵያና ከህዝቧም ጋር ይሁን አሜን።

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith, Music | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

በየቦታው አገር የሚያጠፉት ክፉ መካሪዎች ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 14, 2019

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል ዓላማው ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት እንጂ ሰዎችን በእርሱ ዙሪያ መሰብሰብና መክበር አልነበረም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደሚነግረን «ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳ፣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ነገር ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይጎርፉ ነበር፡፡» /ማቴ.3÷5-6/ እርሱ ግን «እኔ በውኃ ለንስሐ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡» እያለ ሰዎቹ እርሱን እንዲከተሉ ሳይሆን የጌታችንን መምጣት ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርግ ትምህርት ያስተምራቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

የመጀመሪያዎቹ ጌታችንን የተከተሉት ደቀመዛሙርት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ነበሩ፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን መታጀብ /በሕዝብ መከበብ/ ለሚያስደስተን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የእኛን ተከታዮች እንደ ፈሪሳውያን ለምንፈልግ አገልጋዮች ትልቅ ተግሳጽ ነው፡፡

እግዚአብሔር ከመልካም ምክር እንዲያገናኘን ክፉውን እና መልካሙን ምክር እንድለይ ማስተዋሉን እንዲሰጠን ቅዱስ ፍቃዱ ይሁን!

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: