Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ፓስተር’

የእስስቱ ግራኝ ፓስተር፤ “በፍል ውሃ አጥምቁኝ ምንም አልሆንም!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2022

የፍል ውሃ ፓስተር

________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የረመዳን ጋኔን | በ አርባ ምንጭ ሀይቅ አጥማቂው ጴንጤ ፓስተር በአዞ ተገደሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 6, 2018

አስቃቂ ነው፤ ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

ቢቢሲ እንደዘገበው

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ በላንቴ ቀበሌ ልዩ ስሙ መርከብ ጣቢያበተባለ ስፍራ ከሀይቅ ዳር ቆመው መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩ ፓስተር በአዞ በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው ፖሊስ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ፓስተር ዶጮ እሸቴ የተባሉት የሃይማኖት አባት እሁድ ጠዋት 2 ሠዓት ተኩል አካባቢ ቁጥራቸው በግምት ሰማኒያ አካባቢ የሆኑ ተከታዮቻቸውን በሃይቁ ውሃ እያጠመቁ በነበረበት ሰዓት አደጋው እንደደረሰባቸው አቶ ከተማ ካይሮ የተባሉ የከተማው ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ ከተማ ስለ ክስተቱ ሲያስረዱ አጥማቂው የመጀመሪያውን ሰው አጥምቀው ሁለተኛውን ማጥመቅ ሲጀምሩ አዞው በድንገት በመውጣት የሚጠመቀውን ሰው ገፍትሮ ሲጥለው አጥማቂውን ግን ጎትቶ ወደ ውሃው ይዞት ሄዷልብለዋል።

የወረዳው ፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን እውነቱ ካንኮ በበኩላቸው ክስቱት መፈጠሩን አረጋግጠው፤ በወቅቱ በአካባቢው የነበሩ ዓሳ አስጋሪዎችና ወጣቶች በአዞው ጥቃት የተፈፀመባቸውን ግለሰብ ከአዞው ለማስጣል ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ እንደቀረ ተናግረዋል።

ዋና ሳጅን እውነቱ ምንም እንኳን የፓስተሩን ህይወት ማዳን ባይቻልም የአካባቢው ማህበረሰብ የሟች አስከሬን ከአዞው ለማስጠል እንደተቻለ ጨምረው አስረድተዋል።

የሟቹ ፓስተር ዶጮ እሸቴ የቀብር ሥነሥርዓትም ሰኞ እለት ተፈፅሟል።

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: