የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኮሮናቫይረስ ምርመራውን ትክክለኛነት ከተጠራጠሩ አንድ ቀን በኋላ ለኮሮኔቫቫይረስ ምርመራ ሀላፊነቱን የያዘው የታንዛኒያ ብሔራዊ የጤና ቤተ–ሙከራ ከሃላፊነት ተነስቷል።
በብሔራዊ ላቦራቶሪ ውስጥ የተለያዩ እንስሳት ፣ ፍራፍሬዎችና የተሽከርካሪ ዘይት በምስጢር ከተሞከሩ በኋላ ፕሬዚደንቱ እንዳስታወቁት በፍየልና ፓፓያ ላይ የተካሄደው የኮሮና ፍተሻ አዎንታዊ ውጤቶችን በመመለሳቸው፤ ማለትም በኮሮናቫይረስ መለከፋቸውን በማስየቱ የሚደረገው ምርመራና የመርመሪያ መሣሪዎቹ ከንቱ ናቸው በዚህ መልክ ምርመራ ማድረግ አያስፈልግም ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም እንዳሉት በቫይረሱ ተለከፈዋል የተባሉት ሰዎች በበሽታው ላይታመሙ ይችላሉ። በቤተ ሙከራ መሣሪያዎች እና ቴክኒሻኖች ተአማኒነት ላይ ያላቸውን ጥርጣሬ በይፋ አሳይተዋል፡፡