በመስቀል አደባባይ ለተቃውሞ ሰልፍ እንዳትወጡ አሉን፣ ከዚያም ቦታውን ለማርከስ ሰይጣናዊውን ኢሬቻን አከበሩበት፤ አሁን የልብ ልብ ብሏቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ እየገቡ መተናኮስና መግደል ጀምረዋል። አዎ! ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቍ!
…ነጠብጣቦቹን…እናገናኝ፦
+++ ዕለተ መስቀል ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ግቢ ፥ በሬው ተጋድሞ ክፉኛ ይንቀጠቀጣል+++
መምህር ዘመድኩን በቀለ እንዳካፈለን፦
ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በሚገኘው በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የተደረገውን ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ደፋሩ የኦሮሚያ ፖሊስ በጉባኤው መምህር በመ/ር ምህረተ አብ ላይና በደብሩ አስተዳደር ላይ ያደረገውን ትንኮሳ እንደ ቀላል፣ እንደዋዛ አትመለከተው። ትናንት ፎሊስ ነፍሴ በአንድ ድንጋይ 100 ወፍ ለመምታት ነበር አቅዶ መጥቶ የነበረው። ፎሊስ ነፍሴ ከድንጋዩ ሌላም የሙቀት፣ የስሜት መለኪያ ቴርሞ ሜትርም ይዞ ነበር የመጣው። የ75 ሚልየን ኦርቶዶክሳዊያንን የልብ ትርታና ስሜት፣ የመምህሩንና የቤተክርስቲያኒቱንም አስተዳደር አቋምና ሙቀት ለመለካትም ነበር ዊኒጥዊኒጥ እያለ ዘው ብሎ መጥቶ የነበረው።
ፎሊስ ነፍሴ አስቀድሞ የጉባኤውን አዘጋጆች መረመሩ፣ ስሜታቸውንም ኮርኩረው በማስፈራራት መምህር ምህረተአብ እንዳይመጣና በጉባኤው ላይ ሳያስተምር እንዲመለስ እንዲያደርጉ ወተወቱአቸው፣ ቃታ ስበው አስፈራሩዋቸው። አዘጋጆቹ፣ የጉባኤው አስተባባሪዎችም መለሱላቸው አፍጥኑት፣ ሰማእትነት ብርቃችን ነው እንዴ? በማለት ቴርሞ ሜትሩን አከሸፉት።
ፎሊስ ነፍሴ በአስተናጋጆቹና በጉባኤው አስተባባሪዎች ላይ የዘረጋው የሙቀት መለኪያ እንደከሸፈ ሲያውቅ በቀጥታ ወደ ደብሩ አስተዳደር ቢሮ ገብቶ አለቃውን ከቤተ ክርስቲያን ውጪ አንድ ጊዜ እንዲያናግሩን ብለው በመጥራት ሌላ ዕድል ሞከሩ። አስተዳዳሪውም ከቢሮዬ አልወጣም። የሚፈልገኝ ቢሮዬ ይምጣ፣ ጉባኤውም በሰዓቱ ይካሄዳል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምናዘጋጀውን ጉባኤ የሚከለክለን አንዳችም ምድራዊ ሕግ የለም ብለው በአቋማቸው ጸኑ። ፎሊስ ነፍሴም ይሄኛው ሁለተኛው ቴርሞ ሜትሩም ዐይኑ እያየ እጁ ላይ ቋ ብሎ ተሰበረ።
ፎሊስ የመጨረሻ ሙከራውን በምእመናኑ ላይ ለማድረግ ሞከረ። ግርግር፣ የፖሊስ መዓት በአካባቢው እንዲተራመስ፣ ቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ በሮች ላይ የታጠቀ ሠራዊት በማፍሰስ፣ የህዝቡን ሀሞት ለማፍሰስ፣ በዚያውም የሙቀት መጠናቸውን ለመለካት በእጅጉ ጣረ። ጭራሽ ህዝቡ እንኳን ሊፈራ ፎሊስ የመጣው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ስላለ ለዚያ ጥበቃ እንጂ ጉባኤውን ለማጨናገፍ ነው ሳይል ወደ ጉባኤው ነጠላውን መስቀለኛ አጣፍቶ ተመመ። ፎሊስ ነፍሴ ቴርሞ ሜትሩን ይዞ ዊኒጥ ዊኒጥ ቢል ሰሚ አጣ። በሰጨው። ይሄም ከሸፈ።
የመጨረሻ ሙከራው ምህረተ አብን መተናኮል ነው። እኛ ፈቃድ ሳንጠየቅ፣ እኛ ሳናውቅ ይሄ ሁላ ሺ ህዝብ እንዴት ይሰበሰባል? ብሎ ኮማንደር ፍጹም ወበራ፣ በምህረተ አብ ላይ መንገድ ተዘጋ። ወደ ጉባኤው እንዳይመጣ ከመጣ ለሚፈጠረው ትርምስ ኃላፊነቱን እንዲወስድ በገደምዳሜ፣ በሾሬኔ ተነገረው። ይሄ የመጨረሻው የፎሊስ የሙቀት መለኪያ ዘዴው ነበር። “ እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” የሚለውን መመሪያ መጠቀሙ ነበር ፎሊስ ነፍሴ።
ዑራኤል በነበረው ጉባኤ መምህር ምህረተ አብ አሠፋ ስለ ሰማእታት ክብር አስተምሮ ነበር። በጉባኤው ላይ የነበሩ የ24 ቀበሌ ወጣቶች የዚያኑ ዕለት በታከለ ኡማ የፎሊስ ሠራዊት ተረሽነው የሰማእትነት አክሊልን ተቀብለዋል። ምህረተአብ ልቡ በጣም ተነክቷል፣ አልቅሷል፣ አዝኗል። የሰማእታቱ የቀብር ሥነሥርዓት ላይም ይሄው ስሜቱ በግልጽ ይነበብበት ነበር።
መመህር ምህረተ አብ በዘመነ ህወሓት በብቸኝነት ለአክራሪ እስላሞች መልስ በመስጠት የተጋፈጠ ወንድሜም መምህሬም ነው። ለጥያቄ ፎሊስ ጣቢያ በተጠራ ቁጥር በደስታ ሲሄድ አውቀዋለሁ። መምህር ምህረተ አብ ፓስተር ዳዊት በግልጽ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ደብዳቤ እንዲጽፍ ያስደረገም ጀግና ነው። ሲኖዶሱ ዝም ባለ ጊዜ ሁሉ ለቤተክርስቲያን አንደበት የሆነ የስስት ልጇ ነው። አይደክመውም፣ ታምሞ እንኳ ጉባኤ የቀረበትን ዘመን አላስታውስም።
እነ ዛኪር ፣ እነ አህመዲን ዲዳት አክራሪ የወሀቢይ እስላሞቹ በቤተ ክርስቲያን ላይ በተነሱ ጊዜ ብቻውን በሲዲም በቪሲዲም መልስ በመስጠት አንገታቸውንም የሰበረም መምህር ነው። ማስፈራሪያ፣ የእንገልሃለን ዛቻን ከቁብም ሳይቆጥር በፅንአት ቤተ ክርስቲያንን ያገለገለም ነው ምህረተ አብ።
ለእኔ ደግሞ ሲበዛ ወንድሜ ነው። በቅርብ አሳምሬ አውቀዋለሁ። ከመጀመሪያ የዐውደ ምህረት ላይ አገልግሎት ዘመኑ ጀምሮ አሳምሬ አውቀዋለሁ። “አለን” የሚለውን ዝማሬ በአንድ ላይ በእኔዋ “ ጌልገላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት” አማካኝነት በሠራንበት ወቅት ከስብከት ውጪ ያለውን ዕምቅ የግጥምና ዜማ ፀጋውንም በሚገባ አይቻለሁ። በስደት ዘመኔ ወቅት ለልጆቼ በቅርብ እንደ አባት እኔን ተክቶ በጉድለታቸው ሁሉ ይሞላ የነበረም ወንድሜ ነው። ሁሉ በከዳኝ ወቅት ከአጠገቤ የቆመ ያልተለየኝም ነው መምህር ምህረተ አብ። በእነ በጋሻው ደሳለኝ ክስ ስታሰርም ጠያቂዬ ነበር። ልጆቼ እንዳይርባቸው፣ ቤተሰቤ እንዳይበተን፣ እንዳይራብ እንዳይበተንም ያደረገም ወንድሜ ነው ምህረተ አብ። ሲበዛ ሃይማኖተኛ ነው።
በቅርቡ ወላይታ በነበረ ጉባኤ ላይ በ3 ቀን ጉባኤ የእነ ኢዩ ጩፋ መጫወቻ የነበሩና ከበረቱ፣ ከጋጣው ወጥተው የነበሩ የወላይታን ልጆች የተዋሕ በጎችን መመለሱ በፕሮቴስታንቶቹ ዘንድ ብዙም አልተወደደለትም። የማንቂያ ደወል ብሎ ይሄን ፍራሽ ጎዝጉዞ ጫትና ሺሻ ላይ የተወዘፈውን፣ የተዘፈዘፈውን የከተማ ወጣት የግዱን በእግዚአብሔር ቃል እየገረፈ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለስ ማድረጉንም ሰይጣን ዲያብሎስም አልወደደለትም። ምሮኮ ነጣቂ ነው ምህረተ አብ።
በንግሥ ቀን እንኳ ሰው የማይሞላባቸው፣ ሚልዮኖችን ውጠው ቅም የማይላቸው እነ ቦሌ መድኃኔዓለም። ጉርድ ሾላ ሲኤምሲ ሰዓሊተ ምህረት፣ አዲሱ ሚካኤል መርካቶ አውቶቡስ ተራ ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን አልፎ ዋናው መጋቢ መንገዱ እስኪዘጋጋ ድረስ ጉባኤ ማድረጉ ለሌሎች አሁን ፕሮጀክት ዘርግተው ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ለሚፈልጉ አካላት ፈጽሞ አልተመቻቸውም። ምቾት አልሰጣቸውም። ይበሰጫሉ። ኢትዮጵያን መውደዱ፣ ሰንደቋን ከፍአድርጎ ለብሶ መድመቁም ቋቅ የሚላቸው የትየለሌ ናቸው።
ምህረተ አብ እንደሌሎቹ አገልጋዮች አሜሪካና አውሮጳ ብቻ እየዞረ ኮሚሽኑን እየለቀመ ዘና ብሎ እንዲኖር የመንግሥትም የሰይጣንም ፍላጎት ነው። ምህረተ አብ ግን የአውሮጳም የአማሪካም ኑሮን አልፈለገውም። ልጁንና ሚስቱን አውሮጳ ለንደን ትቶ ከህዝቤ ጋር መከራን መቀበሉ ይሻለኛል ብሎ የተሻለውንና ከሁሉ የሚበልጠውን መርጦ ከወገኑ ጋር ከገጠር እስከ ከተማ መከራም ሆነ ደስታ ለመካፈል የቆረጠና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ላቡን ወዙን ለተዋሕዶ እያፈሰሰ ያለ ጀግና የተዋሕዶ ልጅ ነው። እስከአሁን በተቻለው ሁሉ እናት ቤተክርስቲያንን ሳይከዳ ከፊት መስመር ተሰልፎም ፍልሚያውን እየመራ ያለም ጀግና ሐዋርያ ነው።
በአሁን ሰዓት ከመምህር ምህረተ አብ በቀር ዐውደምህረቱ ላይ ሌላ ማን አለ? አንዳንዴ መምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴን፣ ሌላ ጊዜ መምህር ዘላለም ወንድሙን እንደ መስቀል ወፍ ብቅ ብለው ከምናይ በቀር ማን አለ? ምህረተ አብ ነው አሁን ከፊት መስመር እየተጋፈጠ ያለው። ፌስቡክን እየተጠቀመ፣ መረጃ እያስተላለፈ፣ ለህዝብ በቅርብ ተፈልጎ የሚገኘው ምህረተ አብ ብቻ ነው። እናም ይሄን በሰገነት ላይ ያለ መብራት ለማጥፈት ነው የኦሮሚያ ፖሊስ ትናንትና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በድፍረት ቴርሞ ሜትሩን ይዞ የመጣው።
እግዚአብሔር ያሳያችሁ፣ መድኃኔዓለም ያመልክታችሁ። በዚህ በየፌርማታው፣ በየገበያው፣ በየአውራጎዳናው፣ በየአውቶቡስና ታክሲ መያዣው፣ “ ኢየሱስን ካልተቀበላችሁ ሞተን እንገኛለን ” ብለው የፍንዳታ መዓት፣ የወጠጤ መዓት፣ በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ የፕሮቴስታንትና የወሀቢይ እስላሞች ሳይቀር የጆሮአችን ታምቡር እስኪበጠስ ድረስ እዬዬዬዬ እሪሪሪሪ ቋቀምበጭ እያሉ መከራ በሚያበሉን ዘመን በራሷ ዐውደምህረት ላይ ለምታደረግው ዘወትር የተለመደ ጉባኤ ፍቃድ አምጡ ማለት የጤና አይመስልም። ይሄ ከባድ ንቀት ነው። እጅግ ከባድ ንቀት ነው።
የመጨረሻውንም የሙቀት መለኪያ ልኬቷ ቋ እንቀጭ አድርጎ ፎሊስ እጅ ላይ ከሽ አድርጎ ምህረተአብ በታላቅ ክብርና ሞገስ ወጥመዱን ሰባብሮ፣ መረቡን በጣጥሶ የተለመደ አገልግሎቱን ሰጥቶ ጉባኤውን በሰላም ፈጽሟል። ዛሬስ እሺ ነገ ምን ሊኮን ነው? ዘንዶው ደፋር ነው ቱ ምን አለበሉኝ ቅድስተ ማርያም ሄዶ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያላወከ እንደሆን? ዛሬ ለስብከት ፍቃድ የጠየቀ ፎሊስ ነገ ለቅዳሴ አስፈቅዱኝ ያላለ እንደሆን ምን አለ በሉኝ። እነማን ናቸው የሚቀድሱት፣ ሰሞነኞቹስ እነማን ናቸው ያላለ እንደሆን ጠብቁ። በዚህ ድፍረቱ ገና ብዙ ታሪክ ያሳየናል።
ለማንኛውም አሁን ሁላችንም እንንቃ። ጎበዝ ጫትህን ትፋ። ሲጋራህን ጣል። ሀሺሽ ሺሻህን አስወግድ፣ አንቡላ ካቲካላህን አረቄ ድራፍትህን ድፋ። በየጋለሞታ ጭን ስር አትርመጥመጥ። ጹም፣ ጸልይ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመለስ። በዕድሜ እኩያህ በፀጋ አባትህ ከሆነው ከመምህር ምህረተ አብ ጎን ቁም። ንስሀ ግባ፣ ሥጋወደሙ ተቀበል። ተዘጋጅተህም ሁሉን ነገር ጠብቅ። አንተ የተኛህ በቶሎ ንቃ።
የፌስቡክ ላይ ፉከራ ብዙም አያዋጣም። ፍከራው ይቅርና መሬት ላይ ቁምነገር ለመሥራት ወስን። በዘወትር ጉባኤያት ላይ በአካል ተገኝ። ተማር፣ ዘምር፣ መስክር። አስቀድስ፣ ተቀደስ። ፀበል ጠጣ፣ ተጠመቅ፣ እምነት ተቀባ፣ በመስቀል ተዳሰስ፣ አንገትህ ላይ ማዕተብህን አጥብቀህ እሰር። በደንብ አጥብቅ እሰረው። በየሰፈሩ፣ በየቤትህ፣ ተሰባሰብ፣ ተመካከር። ተወያይ፣ ተነጋገር። እንደጤዛ ጠዋት ደምቀህ ረፋድ ላይ አትርገፍ። ጽና!!!
___________________________
Like this:
Like Loading...