Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ፈረሰኛው’

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለጣዖት አልንበረከክም ለንጉሡም አልታዘዝም በማለቱ የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ፥ የኛዎቹ “ካህናት” ግን ለዋቄዮ-አላህ ጣዖት ተንበረከኩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 😇 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

ሃላል የሚለው የእስልምና ቃል “ሄሌል/ሄል” ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሉሲፈር/ሰይጣን ነው። እንዲያውም ቱርኮች “ሄሌል” ነው የሚሉት።

❖❖❖[፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፰]❖❖❖

  • ፲ አንተ እውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይታነጽበትምን?
  • ፲፩ በአንተ እውቀትም ይህ ደካማ ይጠፋል፥ እርሱም ክርስቶስ የሞተለት ወንድም ነው።
  • ፲፪ እንዲህም ወንድሞችን እየበደላችሁ ደካማም የሆነውን ሕሊናቸውን እያቆሰላችሁ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።
  • ፲፫ ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም።

❖❖❖[፩ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፲፥]❖❖❖

  • ፲፬ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ።
  • ፲፭ ልባሞች እንደ መሆናችሁ እላለሁ፤ በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ።
  • ፲፮ የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?
  • ፲፯ አንድ እንጀራ ስለ ሆነ፥ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና።
  • ፲፰ በሥጋ የሆነውን እስራኤል ተመልከቱ፤ መሥዋዕቱን የሚበሉ የመሠዊያው ማኅበረተኞች አይደሉምን?
  • ፲፱ እንግዲህ ምን እላለሁ? ለጣዖት የተሠዋ ምናምን ነው እላለሁን? ወይስ ጣዖት ምናምን እንዲሆን እላለሁን?
  • ፳ አይደለም፤ ነገር ግን አሕዛብ የሚሠዉት ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር ማኅበረተኞች እንድትሆኑ አልወድም።
  • ፳፩ የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም።
  • ፳፪ ወይስ ጌታን እናስቀናውን? እኛስ ከእርሱ ይልቅ እንበረታለንን?
  • ፳፫ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም።

በቱርክ የሚገኘውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ከጎበኙ በኋላ ብዙ ሙስሊሞች ከጨለማ ወደ ክርስቶስ ብርሃን እየነጎዱ ነው!

የክርስቶስ ተቃዋሚ ግብጻውያን ሙስሊሞች ግን ረመዳን ሲያፈጥሩ፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት አደረሱ፤ መስቀሉን ጣሉት

ከኢትዮጵያ ጠባቂ እረኞች አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው ፥ ዛሬ ከጣዖት አምላኪ መሀመዳውያን ጋር ለሉሲፈር የተሰዋውን ምግብ ለመብላት ፈቃደኞች የሆኑት “አባቶች” ግን ለኢትዮጵያ ፥ ለቤተክርስቲያኗ እና ለበጎቿ ጠባቂዎች ስላይደሉ ሁሉም እንደ አላውያን፣ ፈሪሳውያን እና ሳዱቃውያን ነው ሊቆጠሩ የሚገባቸው።

ለዚህ ለሕዝብ ክርስቲያኑ ቅዱስ ለሆነው የዳግማዊ ትንሣኤ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ክቡር ዕለት የኢትዮጵያና ተዋሕዶ ክርስትናዋ ቀንደኛ ጠላት የሆነው የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር አምላኪው የኦሮሞ አገዛዝ በደንብ ሲዘጋጅበት ነበር።

ልክ በካቶሊኮች ዘንድ ውስጥ ላለፉት መቶ ዓመታት ፕሮቴስታንቶችና ሰዶማውያን ተሰግስገው በመግባት ቤት

ቤተ ክርስቲያናቸውን እንደበከሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ፕሮቴስታንት መናፍቃን፣ ጣዖት አምላኪ ዋቄፈናዎችና አላውያን ተሰግስገው በመግባት ዛሬ በግልጽ ለምናየው ድፍረት፣ ውርደት፣ ቅሌትና የጥፋት ርኩሰት በቅተናል።

እስኪ ይታየን፤ “አባቶች” የተባሉት የክርስቶስን የእግዚአብሔር አብ ልጅነት፣ አምላክነቱን፣ ስቅለቱንና ትንሣኤውን ከካዱት የክርስቶስ ተቃዋሚ መሀመዳውያን ጋር አንድ ላይ ሲመገቡ፤

  • ❖ ያውም በዳግማዊ ትንሣኤ ዕለት
  • ❖ ያውም በታላቁ ሰማዕት በቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት
  • ❖ ያውም አንድ ሚሊየን የሚሆኑ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት የጥንት ስልጣኔ እና የሃይማኖት መገኛ፣ የጽላተ ሙሴ/ የቃል ኪዳኑ ታቦት ቤትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሠረት በሆነችው በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ በተጨፈጨፉበት ማግስት
  • ❖ ያውም በብዙ ሚሊየን የሚሆኑ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ለረሃና ጥሜት በተጋለጡበት ወቅት
  • ❖ ያውም የገዳማት እና አድባራት የሆኑ ታሪካዊ እና ሀይማኖታዊ መጽሐፍት እና ማህደሮች በተዘርፉበትና በወደሙበት ማግስት።
  • ❖ ያውም ብዙ የሃይማኖት አባቶች ፣ ዲያቆናት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶችና የሃይማኖት ተማሪዎች፣ ሕፃናት እንዲሁም ምእመናን በተለይም በእነዚያ በቅዳሴና መንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የነበሩ ቀሳውስትና ካህናት እንደ እንስሳት በአህዛብ ሰአራዊት ከተጨፈጨፉ በኋላ።
  • ❖ ያውም ታሪካዊውን የደብረ ዳሞ ገዳምን እና የመቀሌው ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ በትግራይ የሚገኙ ሁሉም ገዳማት እና የሃይማኖት ትምህርት ቤቶች ማለት ይቻላል በክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ፣ በታሪካዊ ጠላቶቻችን አረቦች፣ ቱርኮች፣ ኢራኖች ድሮኖች፣ አውሮፕላኖች እና በከባድ መሳሪያዎች በቦምብ ከተደበደቡ በኋላ።

እግዚኦ! እግዚኦ! እግዚኦ!

እንግዲህ ዛሬ ለጨፍጫፊውና ለበዳዩ ሙስሊም ጉዳይ መግለጫ ለማውጣትና ለሉሲፈር የተሰዋው ምግብ ጎን ለመመገብ የደፈሩት በአክሱም ጽዮን ላይ የፀረ-ክርስቲያን ዘመቻው ልክ እንደጀመረ ዝምታውን በመምረጣቸውና እስካሁን ድረስ በረሃብና በበብሽታ ለሚረግፈው ተዋሕዶ ክርስቲያን ትንፍሽ እንኳን ለማለት የማይሹት “አባቶች” ከላይ እስከ ታች፡ ሁሉም ኢትዮጵያንና ቤተክርስቲያኗን ለማፍረስ ከዚህ አረመኔ ኦሮሞ አገዛዝ ጋር ተናብበው በጋራ እየሠሩ መሆናቸውን ዛሬ ማረጋገጥ እንችላለን።

ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ልጆች አስቀድሞ ይህን ሁሉ የጥፋት ርኩሰት ያመጣባችኋል ያላቸው በዙሪያቸው ምድሪቱን ሁሉ ከበው የሚኖሩትን አህዛብን ነው። ስለዚህም ደግሞ ከአህዛብ ጋር ምንም ዓይነት ህብረትና አንድነት እንዳይመሰርቱ ይህ ርኩሰት ከመፈጸሙ በፊት አስቀድሞ አስጠንቅቋቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለእስራኤል ልጆች የተስፋይቱን ምድር ከማውረሱ በፊት በምድሪቱ ይኖሩ የነበሩት አህዛብ ስለምን ከምድሪቱ እንደሚባረሩም አስረድቷቸዋል። አህዛብ በድሪቱ ውስጥ ያደርጉት ስለነበረውና ጥፋትና ሞት ስላመጣባቸውም ርኩሰት በግልጽና በዝርዝር ነግሯቸዋል። ደግሞም ይህ ርኩሰትና ኃጢአት ወደ እነርሱ ይመጣበት ዘንድ ስላለው መንገድም አሳውቋቸዋል። ልክ እንደ ከነዓን ምድር እንደ እስራኤል ሁሉ ኢትዮጵያም እግዚአብሔርን በማያውቁና በእግዚአብሔር ህግ በማይኖሩ የዋቄዮ-አላህ አህዛብ ዙሪያዋን የተከበበች ብቸኛዋ የክርስትና ምድር ናት።

ኢትዮጵያውያን የተሰጣቸውንና ለእግዚአብሔር ልጆች የሆኑበትን ኪዳን አፍርሰው በዙሪያቸው ካሉትንና በወራሪ መልክ እንዲገቡ ከፈቀዱላቸው የዋቄዮ-አላህ የጥፋት ህዝቦች ጋር በመዳቀል፣ አንድነትና ህብረት መፍጠራቸውንና እነዚያ የጥፋት ህዝቦች የሚያደርጉትን የምኞት ርኩሰት በተቀደሰችው ምድር ውስጥ መፈጸማቸውን ነው። ስለዚህም ርኩስታቸውና ዓመጻቸው ደግሞ እንደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ኢትዮጵያውያንም “ምናለበት? ይሁንብን፣ አሜን!” ብለው የገቡት የመርገም ኪዳን (ህግ) በተለይ ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት ተፈጻሚ ሆኖባቸዋል። ቅጣቱም እግዚአብሔር አምላክ “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት ላንተ አይሁኑልህ።” በማለት የሰጣቸውን ህግና ሥርዓት ስለጣሱ ነው። ምክኒያቱም ይህ ህግ ዋናው የሐይማኖቱ መሠረት ነውና። ሌሎች ኃጢአቶች ይቅር ሊባሉ የሚችሉ ቢሆንም አህዛብና ሌሎች ብዙዎች የሚያመልኳቸውን አማልክት በማምለክ የሚሆነው ኃጢአት ግን ይቅር የማይባልና እጅግ ከባድ ቅጣት የሚያስከትል ጥፋት ነው።

💭 እስኪ የእነዚህን ከሃዲ ፈሪሳውያን የቤተ ክህነት አባላት ተግባር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሕይወት ጋር እናነጻጽረው፤

✞✞✞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሰማዕትነት በመጽሐፈ ስንክሳር ✞✞✞

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሚያዝያ ሃያ ሦስት በዚች ቀን ፀሐይና የአጥቢያ ኮከብ የተባለ ታላቅና ክቡር የሆነ የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ የምስክርነት ፍጻሜ ሆነ፡፡

የዚህም ቅዱስ አባቱ መስፍን ነው፡፡ ስሙም አንስጣስዮስ ይባላል፡፡ ከቀጰዶቅያ አገር ነው፡፡ የእናቱም ስም ቴዎብስታ ይባላል ከፍልስጥዔም አገር ናት ታናሽ ሆኖ ሳለ አባቱ ዐረፈ፡፡

ሃያ ዓመትም በሆነው ጊዜ የአባቱን ሹመት ሊቀበል ወደ ንጉሥ ዱድያኖስ ዘንድ ሔደ፡፡ ንጉሡም ጣዖትን እንዲአመልኩ ሰዎችን ሁሉ ሲያስገድዳቸው አገኘው፡፡

ይህንንም አይቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ እጅግ አዘነ በእርሱ ዘንድ ያለውን ገንዘቡን ሁሉ ለድኾች፣ ለምስኪኖች ሰጠ ባሮቹንም ነፃ አወጣቸው፡፡

ከዚህ በኋላ በንጉሥ ፊት ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነ፡፡ ንጉሡም አባበለው ብዙ ቃል ኪዳንም ገባለት እርሱ ግን አልተቀበለውም፡፡

ለመስማት እንኳ የሚያስጨንቅ ሥቃይን አሠቃየው ጌታችን ግን ያጸናዋል ቍስሉንም ያድነዋል ሦስት ጊዜም እንደሚሞት እርሱም እንደሚአስነሣው በአራተኛውም የምስክርን አክሊልን እንደሚቀበል ነገረው፡፡ ቃል ኪዳንም ሰጠው ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ ይሆን ዘንድ በተጋድሎና መከራ በመቀበልም ጽኑዕ በሆነ ሥቃይም ሰባት ዓመት እንደሚኖር መላእክትም እንደሚአገለግሉት ነገረው፡፡

ንጉሡም ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለመታዘዙና ባለመመለሱ እጅግ አዘነ፡፡ ስለዚህም አትናስዮስ የሚባል ታላቅ ሥራየኛ አመጣ፡፡ እርሱም መርዝን ቀምሞ በጽዋ መልቶ አስማት ደግሞ እንዲጠጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው፡፡ ወዲያውኑ የሚሞት መስሎት ነበር፡፡ ቅዱሱም ያንን ጽዋ ጠጣው ምንም ጉዳት አልደረሰበትም፡፡

ያ መሠርይም በክብር ባለቤት በጌታ በኢየሱስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ ከእርሱም ጋር ሌሎች ብዙዎች ሰዎች በሰማዕትነት ሙተው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ ቁጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ ነፍስ ነው፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስም በዱድያኖስና በሰባ ነገሥታት ፊት በቆመ ጊዜ በዚያም የተቀመጡባቸው የዕንጨት ወንበሮች ነበሩ፡፡ ቅዱሱንም እሊህን የተቀመጥንባቸውን ወንበሮች እንዲበቅሉ እንዲአብቡና እንዲአፈሩ ታደርጋቸው ዘንድ ከአንተ እንሻለን አሉት፡፡ በዚያን ጊዜ ጸለየ እንዳሉትም አደረጋቸው ይህንንም ድንቅ ሥራ አይተው ቍጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ በጌታችን አመኑ፡፡

ከዚህም በኋላ ቅዱሱን ወስደው በጐድጓዳ ብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት፡፡ አቃጥለው አሳርረውም ሥጋውንና ዐጥንቱን ፈጭተው አመድ አድርገው ከረጅም ተራራ ላይ በተኑት፡፡ ጌታችንም ነፍሱን ወደ ሥጋው መልሷት ደግሞ አስነሣው፡፡ ወደ ነገሥታቱም ተመልሶ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ስም ሰበከ፡፡ ቍጥር የሌላቸው አሕዛብ አይተው አደነቁ በጌታችንም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ፡፡

ነገሥታቱም ደግመው ሙታኖችን ብታሥነሣ አምላክህ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በእርሱም እናምናለን አሉት፡፡ ቅዱሱም ጸለየ ከጒድጓድም ውስጥ ወንዶችና ሴቶችን ጐልማሶችንም አስነሣላቸው እነዚያም በክብር ባለቤት በጌታችን ስም አስተማሩ የገሀነምንም ወሬ ተናገሩ ጥምቀትንም ተቀብለው ተመልሰው ዐረፉ፡፡

ከሀድያን ነገሥታት ግን ሙታንን ያስነሣህ አይደለም የረቀቁ ሰይጣናትን አሳየህ እንጂ ብለው ተከራከሩ፡፡ ከዚያም ከጭንቀታቸው ብዛት የተነሣ ከአንዲት ድኃ ሴት ዘንድ አስጠበቁት እርሷም እንጀራ ልትለምንለት ወጣች የእግዚአብሔርም መልአክ በላዩ ከበጎ ነገር ሁሉ የተመላ ማዕድን አቀረበለት፡፡ የዚያች መበለትም የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍን አበቀለ ታላቅ ዛፍም ሆነ፡፡

ያቺም መበለት በተመለሰች ጊዜ የቤቷ ምሰሶ ቅርንጫፍ አብቅሎ ታላቅ ዛፍ እንደሆነ ስለ ማዕዱም ይህን ታላቅ ምልክት አይታ የክርስቲያኖች አምላክ ሰው ተመስሎ ወደ እኔ መጣ አለች፡፡ ቅዱስም እኔ አምላክ አይደለሁም፡፡ የአምላክ ባሪያ ነኝ እንጂ አላት፡፡ እርሷም እንዲህ ብላ ለመነችው የአምላክ አገልጋይ ከሆንክ ቸርነትህ እንድትደርሰኝ እለምንሃለሁ፡፡ ዕውር ደንቆሮ ዲዳ ጐባጣ የሆነ ልጅ አለኝና ታድንልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ ስለ ጌታችን እምነትም አስተማራትና በመስቀል ምልክት አማተበው ያን ጊዜም አየ፡፡ ቅዱሱም በሌላ ጊዜ እንዲሰማ እንዲናገርና እንዲሔድ እንዲአገለግለኝም እኔ እሻለሁ አላት፡፡

በዚያን ጊዜ ንጉሡ በአገሩ ሜዳ ውስጥ ሲዘዋወር ያቺን ዛፍ አይቶ አደነቀ ስለ እርሷም ጠየቀ ቅዱስ ጊዮርጊስ በእርሷ ዘንድ የተቀመጠባት የዚያች መበለት የቤቷ ምሰሶ እንደሆነ ነገሩት፡፡ ንጉሡም ተቆጣ ቅዱሱንም ከዚያ ወስዶ አስገረፈው በመንኰራኵርም አበራዩት ሙቶም ከከተማ ውጭ ጣሉት ጌታም ከሞት አስነሣው ወደ ነገሥታቱም ተመለከተ ንጉሡም አይቶ ደነገጠ ስለ ሕይወቱም አደነቀ፡፡

ከዚህም በኋላ ይሸነግለው ዘንድ ጀመረ በመንግሥቱ ላይም ሁለተኛ ያደርገው ዘንድ ቃል ገባለት ቅዱስ ጊዮርጊስም እየዘበተበት ነገ በጥዋት ለአማልክቶችህ መሥዋዕትን አቀርባለሁ አንተም ሕዝቡ እንዲሰበሰቡ እዘዝ እኔ ስሠዋ እንዲአዩ አለው፡፡ ንጉሡም ዕውነት የሚሠዋ መስሎት ደስ አለው ወደ ቤተ መንግሥቱም እልፍኝ አስገብቶ አሳደረው፡፡

ለጸሎትም ተነሣ የዳዊትንም መዝሙር አነበበ የዱድያኖስ ሚስቱ እለስክንድርያ ንግሥት ሰምታ ቃሉ ደስ አሰኛት የሚያነበውንም ይተረጒምላት ዘንድ ለመናቸው፡፡ እርሱም እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ሰው እስከሆነበት ጊዜ የሆነውን ሁሉ ሊያስረዳትና ሊያስገነዝባት ጀመረ፡፡ ትምህርቱም በልቡዋ ተቀርጾ በክብር ባለቤት በጌታችን አመነች፡፡

በማግሥቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ለአማልክት ሲሠዋ ለማየት ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ ዐዋጅ ነጋሪ ዞረ የቤቷን ምሰሶ ያበቀለላት ያቺ መበለት ሰምታ ዕውነት መስሏት እጅግ እያዘነች ልጅዋን ተሸክማ እያለቀሰችም ወጣች፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስም በአያት ጊዜ ፈገግ አለ ልጅሽን በምድር ላይ አኑሪው አላት፡፡ ከዚያም ልጅዋን ጠርቶ ወደ አጵሎን ሒድ ወደእኔም ይመጣ ዘንድ በክብር ባለቤት በጌታዬ ኢየሱስ ስም እዘዘው አለው፡፡ ያን ጊዜ ያ ልጅ ድኖ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዳዘዘው ወደ ጣዖቱ ቦታ ሒዶ አዘዘው፡፡ በጣዖቱ ያደረ ያ ርኵስ መንፈስም ከማደሪያው ወጥቶ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አለት መጥቶ እኔ ሰውን ሁሉ የማስት እንጂ አምላክ አይደለሁም ብሎ በሕዝቡ ሁሉ ፊት አመነ፡፡ ቅዱሱም ትውጠው ዘንድ ምድርን አዘዛትና ወዲያውኑ ዋጠችው ጣዖታቱንም ከአገልጋዮቻቸው ጋራ አጠፋቸው ንጉሡም ከወገኖቹ ጋር ዐፈረ፡፡

ብስጭትና ቁጣንም እንደተመላ ወደ ንግሥት ሚስቱ ዘንድ ገባ፡፡ እርሷም አምላካቸው ጽኑዕና ኃያል ነውና ክርስቲያኖችን አትጣላቸው አላልኩህምን አለችው፡፡ ይህንንም ከእርስዋ ሰምቶ በእርሷ ላይ እጅግ ተቆጣ ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ እምነት የከበረ ጊዮርጊስ እንደአስገባት አወቀ፡፡

ከዚህም በኋላ ከከተማ ውጭ እንዲጐትቷትና በመጋዝም እንዲሰነጥቋት አዘዘ፡፡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለች፡፡

በዚያም ጊዜ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሥራ ነገሥታቱ ሁሉም ደነገጡ ኀፍረት ደግሞ እንዳይጨምርባቸው ከእርሱም እንዲአርፍ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ እንዲጽፍ ንጉሥ ዱድያኖስን መከሩት፡፡

ያን ጊዜም የክቡር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፡፡ ድል አድራጊ ጊዮርጊስም እጅግ ደስ አለው፡፡ እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገሥት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ወዲያው እሳት ወርዶ ከሠራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገሥታት አቃጠላቸው፡፡

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተገልጾ ብዙ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ በምድር መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ እኔ ኃጢአቱን ሁሉ እደመስሳለሁ በመከራም ውስጥ ሁኖ በባሕርም ሆነ በየብስ ወይም በደዌ በስምህ የሚለምነኝን እኔ ፈጥኜ ከመከራው አድነዋለሁ፡፡ ይህንንም ጌታችን ተናግሮ በክብር ወደ ሰማይ ወጣ፡፡

ከዚህ በኋላ ራሱን ዘንበል አድርጎ በሰይፍ ቆረጡት በመንግሥተ ሰማያት አክሊላትን ተቀበለ፡፡ ከአገልጋዮቹም የቀሩት ሥጋውን ወስደው በልብስ ጠቀለሉት ወደሀገሩ ልዳም ወሰዱት፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ሠርተው በውስጥዋ አኖሩት ከእርሱም ቍጥር የሌላቸው ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የቅዱስ ጊዮርጊስም በረከቱ ረድኤቱ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ከሥጋና ከነፍስ መከራ ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን፡፡

  • ሃገራችን ቅጥሩዋ ተደፈረ፣ አላዊያን እጅግ በረቱብን፤ ደማችን በከንቱ ፈሰሰ፣
  • የትናንቶቹ አባቶቻችን እኮ አንተን መከታ አድርገውና ታቦትክን ይዘው ነበር አያደረጉት!

❖ ❖ ❖ ተአምር ሠሪው ሰማዕት ሆይ ፤ ፈዋሴ ዱያን እንደመሆንህ ከወፍ በሽታ ፈውሰህ የምታድን ነህና ልምናችንን ጸሎታችንን ዘወትር ቸል ሳትል ስማን ከሱ በሺ የሚቆጠሩ ልዩ ልዩ ነገሮች ይተላለፋሉና።

ኃያሉ ጊዮርጊስ ሆይ፤ ድካም የማይሰማህ ትጉህ ገበሬ ነህና ዳግመኛ እንዳያጣሉንና እንዳይተናኮሉን ጠላቶቻችን እንደ ጢስ አጥነህ፤ እንደ ጉም አብነህ ፈጥነህ አጥፋቸው። በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን በመናፍቃንና በአላውያን ዘንድ የመፈራትን ግርማ እንዳጎናጸፍከው ከእኛ የተዋሕዶ ልጆችም በግዙፍ አካልና በረቂቅ መንፈስ ሊተናኰሉን በሚመጡ ጠላቶቻችን ላይ ድል የመንሣትን አክሊል አቀዳጀን። አሜን።

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ኮከብ ክብርየተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፯(ሰብዓ)ነገሥታትን ደምስሰው እንዳጠፏቸው፡ የተነሱብንን የጽዮንን ተቃዋሚዎች፣ የኔንም/የኛንም ጠላቶች ሁሉ ይደመስሱልን ዘንድ እማፀናለሁ።

የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ መንጋው 😈 ሁሉ በመለኮታዊ ሰይፍ ይጨፍጨፉ፣ ነበልባላዊ በሚሆን ቃላችሁ ሥልጣናችሁ ይንደዱ ይቃጠሉ፣ በሲዖል የጨለማ አዝቀት ውስጥ ይዝቀጡ ወይም ይስጠሙ፣ ኅዘን ከላያቸው አይራቅ፣ ትካዜም ከልባቸው አይጥፋ።

የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ መንጋው 😈 ሁሉ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ከምድረ ገጽ ላይ እንዲጠፉ የሚፈልጉ ናቸውና እነሱን ራሳቸውን እንደቃየልና ይሁዳ በዱርና በበረሃ በታትኗቸውና ሲቅበዘበዙ ይኑሩ።

ያለምንም ጉድለት በሥላሴ ስም ይህን ሦስትነት አምናለሁ፤ እያታለሉና በእንግዳ ተመስለው አክሱም ጽዮንን ያጠቋትን የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ መንጋው 😈 ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል መቅ ያውርዳቸው፣ በተሣለ የመለኮት ሠይፍ አንገታቸውን ይረደው። አሜን! አሜን! አሜን!❖ ❖ ❖

🐎 የፈረሰኛው ሰማእት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና ምልጃ አይለየን!✞

______________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅ/ ጊዮርጊስ | በፅዮን ተራራ ላይ የቆመው በግ የጥንቱን እባብ ሰይጣንን ያጠፋዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2022

የጠፋውን ሰላምና አንድነት በእርሱ ለሚያምኑት ሁሉ ይመልሳል

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 😇 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

ሃገራችን ቅጥሩዋ ተደፈረ፣ አላዊያን እጅግ በረቱብን፤ ደማችን በከንቱ ፈሰሰ፣

የትናንቶቹ አባቶቻችን እኮ አንተን መከታ አድርገውና ታቦትክን ይዘው ነበር ድል ያደረጉት!

❖ ❖ ❖ ተአምር ሠሪው ሰማዕት ሆይ ፤ ፈዋሴ ዱያን እንደመሆንህ ከወፍ በሽታ ፈውሰህ የምታድን ነህና ልምናችንን ጸሎታችንን ዘወትር ቸል ሳትል ስማን ከሱ በ የሚቆጠሩ ልዩ ልዩ ነገሮች ይተላለፋሉና።

ኃያሉ ጊዮርጊስ ሆይ፤ ድካም የማይሰማህ ትጉህ ገበሬ ነህና ዳግመኛ እንዳያጣሉንና እንዳይተናኮሉን ጠላቶቻችን እንደ ጢስ አጥነህ፤ እንደ ጉም አብነህ ፈጥነህ አጥፋቸው። በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን በመናፍቃንና በአላውያን ዘንድ የመፈራትን ግርማ እንዳጎናጸፍከው ከእኛ የተዋሕዶ ልጆችም በግዙፍ አካልና በረቂቅ መንፈስ ሊተናኰሉን በሚመጡ ጠላቶቻችን ላይ ድል የመንሣትን አክሊል አቀዳጀን። አሜን።

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ኮከብ ክብርየተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፯(ሰብዓ)ነገሥታትን ደምስሰው እንዳጠፏቸው፡ የተነሱብንን የጽዮንን ተቃዋሚዎች፣ የኔንም/የኛንም ጠላቶች ሁሉ ይደመስሱልን ዘንድ እማፀናለሁ።

የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ መንጋው 😈 ሁሉ በመለኮታዊ ሰይፍ ይጨፍጨፉ፣ ነበልባላዊ በሚሆን ቃላችሁ ሥልጣናችሁ ይንደዱ ይቃጠሉ፣ በሲዖል የጨለማ አዝቀት ውስጥ ይዝቀጡ ወይም ይስጠሙ፣ ኅዘን ከላያቸው አይራቅ፣ ትካዜም ከልባቸው አይጥፋ።

የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ መንጋው 😈 ሁሉ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ከምድረ ገጽ ላይ እንዲጠፉ የሚፈልጉ ናቸውና እነሱን ራሳቸውን እንደቃየልና ይሁዳ በዱርና በበረሃ በታትኗቸውና ሲቅበዘበዙ ይኑሩ።

ያለምንም ጉድለት በሥላሴ ስም ይህን ሦስትነት አምናለሁ፤ እያታለሉና በእንግዳ ተመስለው አክሱም ጽዮንን ያጠቋትን የጽዮን ጠላቶች የሆኑትና በጽዮን ልጆች ላይ በጣም ብዙ ግፍ ያደረሱት የዋቄዮአላህ ጭፍሮች እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እና ተከታይ መንጋው 😈 ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል መቅ ያውርዳቸው፣ በተሣለ የመለኮት ሠይፍ አንገታቸውን ይረደው። አሜን! አሜን! አሜን!❖ ❖ ❖

🐎 የፈረሰኛው ሰማእት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና ምልጃ አይለየን! ✞

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኃያሉ ጊዮርጊስ የተዋጋላትና ተዋሕዷውያን ደማቸውን ያፈሰሱባት ኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን እርስት ናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2020

አዎ! ተራራዎቿ እና ሜዳዎቿ ፣ አፈሮቿ እና ውሃዎቿ ፣ ደኖቿ እና አታክልቶቿ ሁሉም የተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ደም የፈሰሰባቸው ውድ የቤተ ክርስቲያን ንብርቶች ናቸው። ስለዚህ ለማረስ፣ ሕንፃ፣ መንገድና አደባባይ ለመሥራት ዓለማዊው መንግስት ነው የቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ማግኘት ያለበት። እስኪ በአዲስ አበባ ብቻ ተመልከቱት፤ የት ነው አንድ ዜጋ ንጹሕ አየር፣ ንጹህ ውሃ፣ ንጹህ ፍቅርና ደስታን የሚያገኘው? ልክ እንደዚህች በሚያምር ደን እንደተከበበችው እንደ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ባሉት የተቀደሱ ሥፍራዎች አየደለምን? ግን አደራ! የሠፈሮቹንም ስም “ፈረንሳይ”፣ “ጀርመን” ፣ “ፒኮክ” ፣ “ቼችኒያ” ወዘተ በማለት ጠላትን ለወረራ አንጋብዝ!

ተአምር ሠሪው ሰማዕት ሆይ ፤ ፈዋሴ ዱያን እንደመሆንህ ከወፍ በሽታ ፈውሰህ የምታድን ነህና ልምናችንን ጸሎታችንን ዘወትር ቸል ሳትል ስማን ከሱ በኢ የሚቆጠሩ ልዩ ልዩ ነገሮች ይተላለፋሉና።

ኃያሉ ጊዮርጊስ ሆይ፤ ድካም የማይሰማህ ትጉህ ገበሬ ነህና ዳግመኛ እንዳያጣሉንና እንዳይተናኮሉን ጠላቶቻችን እንደ ጢስ አጥነህ፤ እንደ ጉም አብነህ ፈጥነህ አጥፋቸው። በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን በመናፍቃንና በአላውያን ዘንድ የመፈራትን ግርማ እንዳጎናጸፍከው ከእኛ የተዋሕዶ ልጆችም በግዙፍ አካልና በረቂቅ መንፈስ ሊተናኰሉን በሚመጡ ጠላቶቻችን ላይ ድል የመንሣትን አክሊል አቀዳጀን። አሜን።

የፈረሰኛው ሰማእት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና ምልጃ አይለየን!

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: