💭 ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።
❖❖❖[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፬፥፰፡፲፩]❖❖❖
“ቃየልም ወንድሙን አቤልን። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። እግዚአብሔርም ቃየልን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።”
የግራኝ አህዛብ ኦሮሞ ከቱርክና አረቦች ጋር አብሮ አማራውን ገደለው፥ አማራው ከግራኝ አህዛብ ኦሮሞ ፣ ከቱርክና አረቦች ጋር አብሮ ተዋሕዶ ትግራዋይ ወንድሙን ገደለው። ዋይ! ዋይ! ዋይ!
“እግዚአብሔርም ቃየልን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው?”
እያየነው እኮ ነው! የአቤል ደም ይጮኻል ቃኤልም ይቅበዘበዛል!የቃኤል፣ የእስማኤል፣ የዔሳው፣ የሳኦል፣ የኤልዛቤል፣ የሄሮድስ፣ የይሁዳ መንፈስ እንዲህ ያቅበዘብዛል። በየሜዲያው ይህን ያህል ከተቅበዘበዙ በየቤታቸውና በቤተሰቦቻቸው ዘንድ ሕሊናቸው ምን ያህል ይገርፋቸው ይሆን? ምን ያህልስ እንቅልፍ ይነሳቸው ይሆን? እኛንስ ደግመው ደጋግመው ለማታለል የማይሄዱበት እርቀት የለም፤ ግን እግዚአብሔርን እንዴት መፍራት ተሳናቸው? ምን/ማን አደፋፈራቸው? ለምን? ምክኒያቱም፤ ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው። በዲያብሎስ ተታልሎ ከክርስቶስ ፍቅር፣ ከወንድሙ ፍቅር ይልቅ ለራሱ ጠላት ባሪያ ለመሆን በመምረጡ ነው። እንግዲህ ለጊዜውም ቢሆን አለመታደል ህኖ፤ ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት የሰይጣን ጭፍሮች የሆኑት የዋቄዮ–አላህ–ዲያብሎስ ‘ነገስታት‘ ጠላቶቿ ናቸውና ነው!
አዎ! ዛሬ ወንድሞች በኅብረት ሊቀመጡ አልቻሉም፤ እንዲያውም ቃኤል ከእግዚአብሔር ጠላቶች ጋር አብሮ አቤልን በማሳደድና በመግደል ላይ መገኘቱ እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን መላው ዓለምን የሥራ ባልደረቦቼንና በዙሪያዬ ያሉትን ባዕዳውያን ሁሉ ነው ያስገረማቸው።
❖❖❖[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፫]❖❖❖
፩ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።
፪ ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን።
፫ በእርሱም ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።
፬ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ ዓመፅን ደግሞ ያደርጋል፥ ኃጢአትም ዓመፅ ነው።
፭ እርሱም ኃጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፥ በእርሱም ኃጢአት የለም።
፮ በእርሱ የሚኖር ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፤ ኃጢአትን የሚያደርግ ሁሉ አላየውም አላወቀውምም።
፯ ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።
፰ ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ኃጢአትን ያደርጋልና።
፱ ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ። ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን አያደርግም፥ ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።
፲ የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ የተገለጡ ናቸው፤ ጽድቅን የማያደርግና ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።
፲፩ ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት። እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤
፲፪ ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።
፲፫ ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ።
፲፬ እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል።
፲፭ ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።
፲፮ እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።
፲፯ ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?
፲፰ ልጆቼ ሆይ፥ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት አንዋደድ።
፲፱–፳ ልባችንም በእኛ ላይ በሚፈርድበት ሁሉ፥ ከእውነት እንደ ሆንን በዚህ እናውቃለን በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።
❖❖❖ በምዕራብ ትግራይ በወንድሞቻቸው አቤላውያን ላይ ከባድ ግፍ በመፈጸም ላይ ላሉትና ከአህዛብ ጋር ለተደመሩት አማራ ቃኤላውያን፤ ወዮላችሁ! የአቤል ደም እየጮኸ ነው!፦
👉 ወንድም ወንድሙን አያድንም፥ ሰውም አያድንም፤ ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥ ለዘላለም እንዲኖር፥ ጥፋትንም እንዳያይ፤ የነፍሳቸው ለውጥ ከብሮአልና፥ ለዘላለምም ቀርቶአልና። በልባቸውም ቤታቸው ለዘላለም የሚኖር፥ ማደሪያቸውም ለልጆች ልጅ የሚሆን ይመስላቸዋል፤ በየአገራቸውም ስማቸው ይጠራል። ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ። ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በአፋቸው እሺ ይላሉ።
❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፵፱]❖❖❖
፩ አሕዛብ ሁላችሁ፥ ይህን ስሙ፤ በዓለም የምትኖሩትም ሁላችሁ፥ አድምጡ፤
፪ ዝቅተኞችና ከፍተኞች፥ ባለጠጎችና ድሆች በአንድነት።
፫ አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም አሳብ ማስተዋልን።
፬ ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፥ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።
፭ ኃጢአት ተረከዜን በከበበኝ ጊዜ በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?
፮ በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በባለጠግነታቸውም ብዛት የሚመኩ፤
፯ ወንድም ወንድሙን አያድንም፥ ሰውም አያድንም፤ ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም፥
፰-፱ ለዘላለም እንዲኖር፥ ጥፋትንም እንዳያይ፤ የነፍሳቸው ለውጥ ከብሮአልና፥ ለዘላለምም ቀርቶአልና።
፲ ብልሃተኞች እንዲሞቱ፥ ሰነፎችችና ደንቆሮች በአንድነት እንዲጠፉ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንዲተዉ አይቶአል።
፲፩ በልባቸውም ቤታቸው ለዘላለም የሚኖር፥ ማደሪያቸውም ለልጆች ልጅ የሚሆን ይመስላቸዋል፤ በየአገራቸውም ስማቸው ይጠራል።
፲፪ ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ።
፲፫ ይህች መንገዳቸው መሰናክላቸው ናት፥ ከእነርሱም በኋላ የሚመጡ በአፋቸው እሺ ይላሉ።
፲፬ እንደ በጎች ወደ ሲኦል የሚሄዱ ናቸው፥ እረኛቸውም ሞት ነው፤ ቅኖችንም በማለዳ ይገዙአቸዋል፥ ውበታቸውም ከመኖሪያቸው ተለይታ በሲኦል ታረጃለች።
፲፭ ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።
፲፮ የሰው ባለጠግነት የቤቱም ክብር በበዛ ጊዜ አትፍራ፥
፲፯ በሞተ ጊዜ ከእርሱ ጋር ምንም አይወስድምና፥ ክብሩም ከእርሱ በኋላ አይወርድምና።
፲፰ በሕይወቱ ሳለ ነፍሱን ባርኮአልና ለሰውነቱ መልካም ብታደርግለት ያመሰግንሃል።
፲፱ ሆኖም ወደ አባቶቹ ትውልድ ይወርዳል፤ ለዘላለም ብርሃንን አያይም።
፳ አእምሮ የሌለው ክቡር ሰው እንደሚጠፋ እንስሶች መሰለ።
❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፵፯]❖❖❖
፩ እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ በአምላካችን ከተማ በተቀደሰ ተራራ ምስጋናው ብዙ ነው።
፪ በሰሜን ወገን በመልካም ስፍራ የቆመ የምድር ሁሉ ደስታ የጽዮን ተራራ ነው፤ እርሱም የትልቁ ንጉሥ ከተማ ነው።
፫ እግዚአብሔር በአዳራሾችዋ መጠጊያ ሆኖ ይታወቃል።
፬ እነሆ፥ ነገሥታት ተከማችተው በአንድነት መጥተዋል።
፭ እነርሱስ አይተው ተደነቁ፥ ደነገጡ፥ ታወኩ።
፮ መንቀጥቀጥ እንደ ወላድ ምጥ በዚያ ያዛቸው።
፯ በኃይለኛ ነፋስ የተርሴስን መርከቦች ትሰብራለህ።
፰ እንደ ሰማን እንዲሁ አየን በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል።
፱ አምላክ ሆይ፥ በሕዝብህ መካከል ምሕረትህን ተቀበልን።
፲ አምላክ ሆይ፥ እንደ ስምህ እንዲሁም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስጋናህ ነው፤ ቀኝህ ጽድቅን የተሞላች ናት።
፲፩ አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ የጽዮን ተራራ ደስ ይበለው፥ የአይሁድም ሴት ልጆች ሐሤት ያድርጉ።
፲፪ ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቍጠሩ፤
፲፫ በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፤ አዳራሽዋን አስቡ፤ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።
፲፬ ለዓለምና ለዘላለም ይህ አምላካችን ነው፥ እርሱም ለዘላለም ይመራናል።
_________________