Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • January 2023
  M T W T F S S
   1
  2345678
  9101112131415
  16171819202122
  23242526272829
  3031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጽላት’

የብሪታኒያ ቅሌት | የኢትዮጵያ ቀሳውስት የተሠረቀውን ቅዱስ ታቦት መጎብኘት ተከለከሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 2, 2019

ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት በመቅደላ ጦርነት ወቅት ከኢትዮጵያ በብሪታኒያ ጄነራል ናፒይር የተሠረቀው ቅዱስ ታቦት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ጥረት ቢደረግም እንግሊዛውያን ግን ዛሬም ለመመለስ ፈቃደኞች አይደሉም።

በሃገረ ብሪታኒያ በጣም ቁልፍ እንደሆነ በሚነገረለትና በነጻ ግንበኞች በተገነባው ህንጻ፡ በዌስትሚኒስተር አቤይ ውስጥ ከመንበሩ ጀርባ ተደብቆ ይገኛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀጳጳሳት ዌስትሚንስተር ቤተክርስቲያን በሚገኘው ታቦት አቅራቢያ ቅዳሴ ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ፈቃድ እንዲያገኙ ለንደን የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት ብዙ ሙከራ አድርገዋል፥ ግን አልተሳካላቸው።

ዲያቆን ሳሙኤል ብርሃኑ የዌስትሚንስተር አቤይ አስተዳዳሪዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀጳጳሳትን ጉብኝት ሊያስትናግዱ ባለመቻላቸው የተሰማቸውን ሃዘኔታ እንደሚከተለው ገልጠዋል፦

በ ፳፩ ኛው መቶ ዘመን የባህላዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ይህን ያህል ግድየለሾች ይሆናሉ፤ እንዲህ የመሰለ አመለካከት ሊኖራችሁ ይችላል ብዬ አላምንም ነበር። ለመወያየት እንኳ ፈቃደኞች አይደሉም

እንደሚታወቀው ታቦቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሠረት ሲሆን የቤተክርስቲያንን ሕንፃ የሚባርክና የሚቀድስ ነው።

እንደ ክርስቲያን ይህን ዓይነት አስተያየት እንዴት ይይዛል?የቤተክርስቲያን በር እንዴት ይዘጋብናል? የዌስትሚንስተር አቤይ አቀራረብ በጣም አሳፋሪነው – በተለይ የዌስትሚንስትር ቤተክርስቲያን እራሷ ለመጸለይ ፈቃድ አለመስጠቷ ተጨማሪ ቅሌት ነው።

ይሁን! ለጊዜው ግድየለም፡ አባቶች! ብሪታኒያ ቅዱስ ታቦታቱን ለኢትዮጵያ ሀገራችን መመለስ ፈርታለች፤ ምክኒያቱም ራቁቷን ትቀራለችና፣ ታላቋ ብሪታኒያ ታንሳለችና፤ ተስጥቷት የነበረውን ኃይልና ሞገስ ትነጠቃለችና። እንደ እኔ ከሆነ ብሪታኒያ ታላቅ ለመሆንና አብዛኛውን የዓለማችንን ክፍል ለመቆጣጠር የበቃችው፣ እንግሊዝኛ ቋንቋዋ የዓለም ሁሉ መነጋገሪያ ቋንቋ ለመሆን መቻሉ እንዲሁም ብሪታኒያ በአንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች ድል አድራጊ ለመሆን የተቻላት የተዋሕዶ ታቦታትን በእጆቿ ስላስገባቻቸው ነው።

በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ሀገራችንን የወረረችው፥ በትምህርት ቤት ለመማር እንደተገደድነው ፥ የታሠሩትን ዜጎቿን ለማስፈታት(ማታለያ False Flag Operation ነበር)ሳይሆን፤ እነዚህን ታቦታት ለመስረቅ ነው። መጽሐፈ ሄኖክን ከኢትዮጵያ ሰርቆ የሄደውን ሌባውን ነፃግንበኛ ጀምስ ብሩስን ቀደም ሲል ለስለላ ልከውት ነበር።

ግን የብሪታኒያ እና አጋሮቿ የክብርና ታላቅነት ዘመን ኢየሱስ ክርስቶስን መክዳት ከጀመሩበት ሰዓት አንስቶ ቀስበቀስ እየመነመነ መጥቷል። ለዚህም ነው እስልምና እንደ መቅሰፍት ሆኖ እየተላከባቸው ያለው። እባቦቹ ትውልደ ፓኪስታን የለንደን ከንቲባ እና የአገር ውስጥ ሚንስትር እስከመሆን በቅተዋል። በቅርቡ ደግሞ የክርስቶስ ተቃዋሚ ከሆነችው ቱርክ የመጀመሪያው የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ይሾማል። ለንደንንን ለፓክሲታን መንፈሳዊ ወንድሙ አስርክቦ ገለል ያለው የቀድሞው የለንደን ከንቲባና የቱርኩ ፖለቲከኛ አሊ ከማል የልጅ ልጅ የሆነው ቦሪስ ጆንሰን ወስላታዋን ተሪዛ ሜይን ይተካት ይሆናል።

ካሁን በኋላ የምዕራባውያኑ ምርጫ በኮሌራ እና ወረርሽኝ መሃከል ነው፤ ንስሐ ገብተው እካልተመለሱ ድረስ ሃገራቱን የሚያጠነክርና የሚጠቅም ሰው ከእንጊድህ አያገኙም።

___________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በመቅደላ ውጊያ ከኢትዯጵያ የተዘረፉትና በለንደን የሚገኙት ፲፩ ታቦታት “በውሰት” ሊመለሱ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2019

የብሪቲሽ ብሄራዊ ሙዚየም ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት በነበረው የመቅደላ ውጊያ በእንግሊዝ ወታደሮች ተዘርፈው የተወሰዱት እነዚህ ታቦታት በውሰት ሊመልስ ነው።

የሙዚየሙ ሀላፊዎች ጽላቶቹን በመመለሱ ረገድ ሀሳቡን እንደሚጋሩትና የህግ ጉዳይ ሆኖ በነፃ ለመመለስ መወሰን ባይችሉም ታቦቶቾን በረጅም ጊዜ ብድር ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ በቦታው ለተገኙት ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ በሙዚየሙ የሚገኙ ታቦታት ለኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ልዩ ክብርና ቦታ ያላቸው ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙባቸው ህያው በመሆናቸው ወደ ትክክለኛ ቦታቸው እንዲመለሱ ጠይቀው ነበር

ከእነዚህ ፲፩ ታቦታት መካከል ፱ኙ ከእንጨት ሲሆኑ ፪ቱ ደግሞ ከድንጋይ ናቸው። ሁሉም በእዚህ የብሪቲሽ ሙዚየም ድብቅ የዕቃ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው እንደተቀመጡና እስከ ዛሬ ድረስ፤ ኃላፊዎቹንም ጨምሮ፤ ማንም ከፍቶ እንዳላያቸው ተጠቁሟል። ታቦታቱ ላይ ምናልባት የተቀረፀ መስቀል ሳያርፍባቸው አይቀርም ተብሏል።

በሌላ በኩል የሙዚየሙ ሃላፊዎች ኢትዮጵያን መጎብኘትና አብረው ለመሥራት እንደሚፈልጉ፣ ወደፊት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡም የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ ገልጸዋል

የኢትዮጵያ ቅርሶች በአብዛኛው በእንግሊዝ፣ በጀርመንና በጣልያን አገር ነው የሚገኙት።

መቅደላ ወይም በአሁኑ ስሙ አምባ ማርያም የሚባለው አምባ፣ ወሎ ውስጥ የሚገኝ በአጼ ቴወድሮስ ዘመን ለዋና ከተማነት ታጭቶ በመካከሉ በእንግሊዞች ጦርነት ወቅት የተቃጠለ ከተማ ነው።

የእንግሊዝ ጦር ውድ ብራናዎችን፣አክሊሎችን፣መስቀሎችን፣የወርቅ ዋንጫዎችን፣የንጉሳዊያንና የቤተ ክርስትያን ቁሳቁሶችን ጋሻና የመሳሰሉትን ቅርሶችን በመዝረፈ ፲፭ ዝሆኖችንና ፪፻ በቅሎዎችን ለማጓጓዣነት ተጠቅመው እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ። ወሰዱ።

በጣም ይገርማል! እግዚአብሔር የሰጠንን የራሳችንን ንብረት በብድር መልክ ሊሰጡን ነው። ለመሆኑ ይህን ኢትዮጵያ የተረሳችበትን ቀውጥ ጊዜ ለምን መረጡ? ዓብያተክርስቲያናት በሚቃጠሉበትና በሚዘረፉበት ዘመን? ይህ ንብረት የመንግስት ሳይሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅርስና ንብረት ስለሆነ በቀጥታ የሚመለከታት ቤተክርስቲያንን ነው፤ ለምንድን ነው መንግስት ወይም የባሕል ሚንስቴር እዚህ ላይ እጁን የሚያስገባው? ምን ዓይነት ተንኮል ታስቦ ይሆን?

ወይስ ያለፈውን እና መጪውን “ቴዎድሮስን” ፈርተው ይሆን? የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል አለማየሁ በዊንድሶር ቤተመንግሥት በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው የተቀበረው። ከሁለት ሣምንታት በፊት የስሴክስ ልዑልን የወለደችው የእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰብ አዲስ ደም፡ ልዕልት ሜጋን ሜርክል ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ የጋብቻ ሥነ ሥርዓቷን የፈጸመችው የልዑል አለማየሁ አጽም በሚገኝበት በዚሁ በውንድሶር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ነው።

ባለፈው ሣምንት ኢትዮጵያዊ ዝርያ ያለባት የብሪታኒያ ንግሥት ኤልሳቤጥ የልዑል አለማየሁን አጽም ለኢትዮጵያ አልመልስም ብላ ነበር። ይገርማል! እዚህ ያንብቡ

ለማንኛውም ቅዱስ ታቦታቱን ይመለሱልን እና ሕዝባችንን አደንዝዞና አሥሮ ያለውን እርኩስ መንፈስ ካገራችን ያጥፉልን! እነርሱ ለክፋት አስበውት ሊሆን ይችላል እግዚአብሔር ግን ለበጎ ያደርገዋል

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን!

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አለም (ዲያብሎስ) “ማየት ማመን ነው” ይለናል | እግዚአብሔር ደግሞ “ማመን ማየት ነው” ብሎ ያስተምረናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2017

ኃይለኛ ጦርነት ላይ ነን!!!

መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” [ኤፌሶን ፮፡፲፪]

 • ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ. – (ተክለሃይማኖት ነው) ሰበታ የሚገኘው የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደመ።

 • ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፱ ዓ. ስለዚህ ቆሼ አስከፊ ቆሻሻ ሽታ እንዲሁም አካባቢው በመስጊድ ጩኽት ስለመበከሉ፤ ብሎም ዲያብሎስ እንደዚህን በመሳሰሉት መሰናክሎች በኩል ምዕመናኑን እየተዋጋ ከቤተክርስቲያን በማራቅ ከክርስቶስ ለመለየት እነደሚሞከር አወሳን።

 • መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፱ ዓ. በተለምዶ ቆሼ ሚባለው ስፍራ የተከሰተው አሳዛኝና አስደንጋጭ ዜና በመላው ዓለም መነጋገሪያ ለመሆን በቃ።

ሰበታ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ስትወድም ጽላቶ ግን በተአምር አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተገኝተዋል

ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ. (ተክለሃይማኖት ነው) እማሆይ ፩ | ጽላቶ አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው መገኘታቸው ”ተአምር” እንደሆነ በስፍራው የነበሩትና የአይነ ምስክር የነበሩት እማሆይ ወለተኪዳን ለ ሸገር ኤፍ ኤምናግርው ነበር።

ሰበታ የሚገኘው የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደመ። ሁለት ጽላቶች አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው መገኘታቸው ” ተአምር” እንደሆነ በስፍራው የነበሩ የአይን እማኝ ተናገሩ። ቃጠሎው በአገለጋዮች ስህተት የተነሳ እንደሆነም ተመልክቷል። የቃጠሎው መንሥኤ በግልጽ አልታወቀም።

ኢትዮ አዲስ እማሆይ ወለተ ኪዳንን በማነጋገር እንዳስተላለፈው ከሆነ በቃጠሎው ንዋየ ቀድሳት፣ አልባሳት፣ ቅዱስ መጽሃፍት፣ ሙዳየ ምጽዋትና ሙሉ መቀደሱ አመድ ሆኗል። ለሊቱን በሰበታ ኤሌክትሪክ ተቋርጦ ስለነበርና በእለቱ ቀዳሴ የሚደረገው ከሰዓት በኋላ በመሆኑ ፣ ማለዳ ኪዳን ለማድረስ የገቡ አገልጋዮች ጀነሬተር አብርተው ነበር። እናም ኪዳን አድርሰው ሲጨርሱ ያበሩትን ጀነሬተር ሳያጠፉ ይወጣሉ። ከዛም ቀኑ አቀራቢያ በሚገኘው የተክለዬ አርሴማ ቤተክርስቲያን ታቦት ስለሚወጣ ለአገልግሎት ወደዛ ያመራሉ።

እማሆይ እንዳሉት እንደተለኮሰ የተረሳው ጀኔረተር ይፈነዳና ቤተክርስቲያኑ ውስጥ እሳት ይነሳል። ቤተ ክርስቲያኑንን ሙሉ በሙሉ ያቃጥላል። ” በሚያሳዝን ሁኔታ ” አሉ እማሆይ ” በሚያሳዝን ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኑ ዓመድ ሆነ” በመቀጠል ግን ” የእግዚአብሔርር ተአምር” ሲሉ ድንቅ የሆነ ነገር ተናገሩ፤ እንዲህ አሉ ” የእመቤታችን እና የአቡነ አረጋዊ ጽላቶች ከእነ አልባሳታቸው እሳት የሚባል ነገር አልነካቸውም”

‹‹ይህ ዅሉ የደረሰው በእኛ ኀጢአት ነው የደብሩ አገልጋይ ካህናትና የአካባቢው ምእመናን ጥላቻንና መለያየትን በማስወገድ፤ ከኀጢአት በመራቅ፤ በፍቅር፣ በሰላምና በአንድነት በመኾን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት እናገልግል” የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳዳሪ መልአከ ሕይወት ሐዋዝ ተስፋ

ከታነጸ ጥር 3 ቀን አራተኛ ዓመቱን የሚይዘው የሰበታ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ላይ ስለደረሰው ቃጠሎ ዝግጅት ክፍሉ የሚመለከታቸውን ሃላፊዎች አላናገረም። ይህ ዘገባ እሰከታተመበት ሰዓት ድረስ ለቃጠሎው መነሻ ነው በሚል አዲስ መረጃ አልደረሰንም። በወቅቱ የእሳት አደጋ ስለመደረሱም ሆነ ስላደረገው ጥረትም የተባለ ነገር የለም። ቤተ ክርስቲያኑ ለወደፊት ገዳም እንዲሆን እቅድ እንደነበር እማሆይ ተናገረዋል።

ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፱ ዓ. እማሆይ ፪ | እግዚአብሔር ወንድ አይልም ሴት አይልም፡ የሚፈልገው ቅን ልቦና ነው። እነ ገብረክርስቶስን፡እነ አቡነ አረጋዊን የመረጠ አምላክ ሲመርጥ ሴት ወንድ አይልም።

የሉሲፈር አገልጋይ ለመሆን የመረጣችሁት “ፊሚኒስቶች” ልብ በሉ!

ከሁለት ወራት በፊት፡ ልክ በዛሬው በጻድቁ አቡነ አረጋዊ ዕለት፡ “ቆሼ” አጠገብ በምትገኘው የ አቡነ አረጋዊ እና ገበረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የእማሆይ እናታችንን ግሩም ትምህርት ለመከታተል በቅቼ ነበር። በዚህች ዕለት የተከሰተው ድርጊት ሁሉ እስካሁን ድረስ በጣም ያስገርመኛል፤ ይደንቀኛልም። እማሆይ ቪዲዮው ላይ የሚከተሉትን ትምህርት አካፈሉን፦

እግዚአብሔር የሚባርክ ጳጳስ ከመንበሩ፣ እውነተኛ ዳኛ ከሃገሩ አያጥፋብን! የቸርነቱን ሥራ ይስራልን! የሚባርክ ጳጳስ ከመንበሩ ያላሳጣን አምላክ ምስጋና ይድረሰው። አባቶቻችን አንድ ጳጳስ ለማግኘት፡ ያውም ከግብጽ ቋንቋው የማይታወቅ ጳጳስ ለማግኘት ስንት መከራ ነበረባቸው!? አሁን በየቦታው፡ በየክፍለሀገሩ ጳጳሳት፣ ቅስና ድቁና፣ ስልጣንነት የሚሰጡ ጳጳሳት ያበዛልን አምላክ ምስጋና ይድረሰው! የነሱ ለቅሶን ስቃይ ቆጥሮ በኛ በክፉው ዘመን ጳጳሳቱን አበዛልን።”

በ እማሆይ ስብከት መሃል፡ ጋኔናዊው የመስጊድ አዛን ጩኽት ከበስተጀርባቸው ልክ ሲለቀቅ፡ እማሆይ፡ “እየሰማችሁ ነው?„ አሉና፡ አሳላቸው (0654)። የሰውን መረበሽ ተመልከቱ። በነገራችን ላይ፡ እስራኤል ይህን ጩኽት እየከለከለች ነው፤ ኢትዮጵያ ልብ በይ! እማሆይ አለፍ ካሉ በኋላም፡ “መነኮሳትንም ጳጳሳትንም ሰይጣን እንዳያስታቸው ይጠብቅልን!„ አሉና አንዶት ቆንጆ የጥምቀት ግጥም አነበቡ። ዲያብሎስም ድል ተመታ! ሁሉም እዚህች ትንሽ ቪዲዮ ላይ ይታያል፤ ይሰማል!

ተመልከቱ የዲያብሎስን ተንኮል። መስጊዱ፡ ከጻድቁ አቡነ አረጋዊ እና ገብረክርስቶስ ቤተከርስቲያን ጎን መጥቶ በቅርብ ነው የተሠራው፤ የመጮሂያው ምሰሶም ከቤተክርስቲያኗ እና ከአካባቢው ህንፃዎች ከፍ ብሎ ነው የተተከለው፤ ልክ እንደ “ቆሼ” ይህም ቤተክርስቲያኗንና ህዘብ ክርስቶስን ለመረበሽ ታስቦ መቀመጡ ነው፤ በእውነት ሰይጣን ከቤተክርስቲያን አይርቅም። እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ አይኖርም። የመሰናክሉ ብዛት፣ የጠላታችን ተንኮልና ምቀኝነት ሁልጊዜ በጣም ያስገርመኛል። ጦርነት ላይ፤ ከባድ ጦርነት ላይ ነው የምንገኘው። በርግጥ ጦርነታችን ስጋ ከለበሱት ወገኖቻችንን ጋር አይደልም፡ መንፈሳዊ ባሕርይ የያዘ ነው። ሆኖም፡ የጠላታችን የዲያብሎስ ርኩስና የክህደት መንፈስ በተለይ በእነርሱ ላይ በይበልጥ ያደረ በመሆኑ፡ በውነት የምንወዳቸው ከሆነ፡ ቢቻል ወደ ክርስቶስ እንዲመለሱ መታገል፡ ካልሆነና ካልተቻለ ደግሞ መራቅና ማራቅ ግድ ነው። አሊያ ህዝበ ክርሲትያኑ እየደነዘዘና መንፈሱ እየደከመ ስለሚመጣ፡(ተልዕኳቸውም ይህ ነው!) ሁሉም ነገር ለነርሱም ለኛም አደገኛና መራራ ነው የሚሆነው።

የእማሆይን ትምህርት ከተከታተልኩ በኋላ፡ ከአንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ በሳል ወጣት ወንድማችን ጋር ለሁለት ሰዓት ያህል በተለያይ አስገራሚ ርዕሶች ላይ ስወያይ ነበር። በተለይ ስለቆሼና አካባቢውን ስለከበቱ ሙስሊሞችና መስጊዶቻቸው። እኚህ ወጣት ለዚህችም ሆነ ለሌሎች ዓብያተክርስቲያናት ባቅራቢያ ከሚገኙት የሙስሊሞች ዳቦ ቤቶች ዳቦ እንደሚገዙ ሲነግሩኝ፡ “እንዴ! ለምን ከሙስሊም ቤት ዳቦ ለቤተክርስቲያን ይመጣል? እንዴት? የኛ ዳቦ እኮ ሕብስትም ነው፤ ትክክል እኮ አይደልም! ስጋ ቤቶቹ መከፋፈላቸው ያለ ምክኒያት ነበርን?„ ስላቸው፤ ወዲያው ነቃ ብለውና በመገረም፤ “እስካሁን ለምን እዚያ እንደምንገዛ አስበንበት አናውቅም፡ ቅርበቱ ነበር የታየን፡ ምን ሆነን ነበር? ይህ እኮ አልጠፋንም ነበር፤ግን አደንዝዘውን ይሆን?„ በማለት ሁለተኛ ከዚያ እንደማያመጡ ቃል ገቡልኝ።

መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፱ ዓ. በቆሼ አደጋ ከሞቱት ወገኖች መካከል በኢየሱስ ያልዳኑትና፡ በወቅቱም፡ ርኩሱን ቁርዓን ሲቀሩ የነበሩት ህፃናት ይገኙበታል

ስለ “ቆሼ” አሳዛኝ አደጋ ዛሚ ኤፍ ኤምባቀረበው ትረካ ላይ፤ “ቆሼ በአካባቢው ነዋሪዎች፡ ደሪወይም አባታችንየሚል ቅጽል ስም ሰጥተውታል።” አለን፡ ጋዜጠኛው ወንድማችን ግዛቸው። “አባታችን”፡ ልብ በሉ። ቀጠል ያደርግና እዚያው አብረው ሲኖሩ የነበሩ ሙስሊም ሎተሪ ሻጭ ህፃናት “ቅዱስ” ቁርአን እየቀሩ ህይወታቸው እንዳለፍ ያወሳልናል።

እዚህ ላይ ሁለት የምያሳዝን ነገር ነበር የታዘብኩት፦

1. እነዚህ ሙስሊም ህፃናት “ክርስቶስ አልተወለደም! አልተሰቀለም!” የሚለውን ርኩሱን ቁርዓን እየቀሩ፡ እና አምላካችንን ክርስቶስን ሳይቀበሉ፡ሳይድኑ ህይወታቸው ማለፉ፣

2. እንደ ጋዜጠኛ ግዛቸው ያሉ እስላም ያልሆኑት ወገኖቻችን ርኩሱን ቁርዓን ለምን “ቅዱስ” እንደሚሉት ነበር እጅግ በጣም ያሳዘነኝ።

እኛ፤ አንድ አባት ነው ያለን፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። አንድ ቅዱስ መጽሐፍ ነው ያለው፡ እርሱም መጽሐፍ ቅዱሳችን ነው። ሙስሊሞቹ ቅዱሱን መጽሐፋችንን ሲጸርፉት፣ ሲኮንኑት እንጂ፤ ሲያሞግሱት ወይም “ቅዱስ” ብለው ሲጠሩት ሰምተን እናውቃለንን? በጭራሽ!

ይህ ታሪክ ሌላ ምንን አስታወሰኝ፤ እዚህ ተመልከቱ – ከሁለት ዓመት በፊት በሜዲትራኒያን ባህር ጀልባ ላይ ተሳፍረው ለተሻለ ህይወት ወደ አውሮፓ ሲጓዙ በውሃው ላይ ማዕበል ተነሳ። ከዚያም ክርስቲያን አፍሪቃውያኑ ጸሎት ሲጀምሩ አብረዋቸው የነበሩት ሙስሊሞች ጸሎታችሁ ነው ማዕበል ያስነሳው በማለት የነበሩትን 10 ክርስቲያኖች ገድለው ለአሳ ቀለብ እንዲሆኑ ወደ ውሃው አሽቀነጠሯቸው። (አንበሣን ፈርቼ ዛፍ ላይ ብወጣ ነብር ጠበቀኝ)አንርሳ! ታዲያ አሁን በ ቆሼ የነበሩት ሙስሊሞች ቁራን ሲያቀሩ፡ ህዝበ ክርስቲያኑ እናንተናችሁ ያመጣችሁት ብሎ ሊያጠፋቸው ይሞክር ነበርን? በፍጹም፡ የማይታሰብ ነው! ለመሆኑ ስንቶቻችን ነን በቀን አምስት ጊዜ ለአላሃቸው የሚያደርጉት ጸሎት ግማሹ እኛን ክርስቲያኖችን እና አይሁዶችን የሚረግሙበት ጸሎት እንደሆነ የምናውቅ? እዚህ ተመልከቱ። አንዱ ወገናችን ይህን ስነግረው እና የጸሎቱን ጽሑፍ ሳሳየው፡ “አ አ ኧረረግ!„ አለና ራሱን ስቶ እስከ መውደቅ ደርሶ ነበር። እነርሱ ድግምቱንና መተቱን ባገኙት አጋጣሚ ሁላ፡ በዓይጦች ሳይቀር፡ እንደሚያደርጉብን አንዳንዶቻችን ደርሰንበታል፤ ሆኖም ስጋቸውን አይደለም የምንዋጋው፡ ያደረባቸውን ርኩስ መንፈስ እንጂ። ይህን መንፈስ በእረኛችን በእግዚአብሔር ስም፣ ከመለአክቶቻችንና ከቅዱሳኖቻችን ጋር አብረን እንዋጋዋለን።

በነገራችን ላይ፡ ቆሼ ተነስቶ የመናፈሻ ፓርክ ለመስራት እቅድ መኖሩ ሰሞኑን ተገልጦ ነበር። ይህ ትልቅ ነገር ነው፡ እንደ ተዓምርም ሊወሰድ የሚገባው ጉዳይ ነው። ወገኖቻችን ህሊና እንዲገዙ ለረዳቸው ቸሩ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው!!

በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችኋል፤ በስሜም ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፡፡ በዚያን ጊዜ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን በመካድ ይሰናከላሉ፤ አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ሰዎችም እርስ በርሳቸው ይጣላሉ፡፡ ብዙ ሃሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤ ከክፋት ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች፡፡ እስከ መጨረሻ በትዕግስት የሚጸና ግን ይድናል፡፡ ለሕዝቦች ሁሉ ምሥክር እንዲሆን ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል በመላው ዓለም ይሰበካል፤ በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል፡፡” [ማቴ. 24፥ 9–14]

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የቅዱስ ሚካኤልን ጽላት ወደ መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እንዲገባ ምክንያት ከሆኑትና ራዕዩን ካዩት አባት ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 19, 2017

ከ መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽሕፈት ቤት የተገኝ

በዚህ ጽሑፍ የቅዱስ ሚካኤልን ጽላት ወደ መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን እንዲገባ ምክንያት የሆኑትን አባት የአቶ በለጠ ዘነበን ታሪክና ስለታያቸው ራዕይ የሰጡንን ቃለ ምልልስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፦

መንበረ ልዑል

በመጀመሪያ ለመጠይቅ ፈቃድዎን ስለሰጡን በእግፍዚአብሔር ስም እናመሰግናለን። የት እና መቼ ተወለዱ?

አቶ በለጠ

የተወለድኩት ሰሜን ሸዋ ግድምና ኤፍራታ ወረዳ በምትባል አነስተኛ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ በ1921 .. ነው።

መንበረ ልዑል

ትምህርት መቼና የት ተማሩ?

አቶ በለጠ

በአስር ዓመቴ ወደ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በመግባት የዲቁና ማእረግ ተቀብያለሁ። እንዲሁም መስተጋብዕ አርባዕት ተምሬ አርያም ላይ ስደርስ ልብስና ስንቅ ስላለቀብኝ ወደ እናትና አባቴ ተመለስኩ።

መንበረ ልዑል

ትምህርት ካቋረጡ በኋላ ህይወትዎ ምን ይመስላል?

አቶ በለጠ

ትምህርቴን ባቋረጥቁ በዚያው ወቅት ክረምት ላይ ቀኑ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሰዎች መተት ሰርተውብኝ ለ፫ ዓመታት ያህል አእምሮዬ በመቃወሱ በእግር ብረት ታስሬ በደብረ ሊባኖስና ሚጣቅ አማኑኤል ፀበል ስጠመቅ ቆይቼ ትንሽ ተሻለኝ። ከህመሜ ካገገምኩ በኋላ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ በመሄድ ወደ ካራ ቆሬ የሚያደርሰኝ መኪና እየፈለግኩ ሳለ “አሥመራ አሥመራ” የሚል አዎቶብስ አገኘሁ። መኪናው ውስጥ ገብቼ አስመራ ምጽዋ ወደሚባለው ቦታ ደረስኩ፡ እዛም ከሠራዊቱ ጋር የምገኘውን ምግብ እየበላሁ እኖር ጀመር። ነገር ግን ህመሙ ስላገረሸብኝ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ። አዲስ አበባም ለ፯ ዓመት ቆይቼ ወደ ትውልድ ሀገሬ በመመለስ ትዳር መስርቼ ለ፪ ዓመታት ያህል ቆየሁ። ነገር ግን ህመሙ ስለተመለሰብኝ ወደ አዲስ አበባ በድጋሚ መጣሁ።

መንበረ ልዑል

አዲስ አበባ በሚኖሩበት ወቅት መተዳደሪያዎት ምን ነበር?

አቶ በለጠ

አዲስ አበባ እንደመጣሁ የካርታ ስራ ድርጅት በሚባል መስሪያ ቤት በቀን ሰራተኛነት ተቀጥሬ መስራት ጀመርኩ። እዚያ ትንሽ ጊዜ ከሰራሁ በኋላ የተሻለ ስራ በማግኘቴ ወደ መዘጋጃ ቤት በጥበቃነት ተቀጥሬ እየሰራሁ እያለ መንጃ ፈቃድ ለማውጣት ቻልኩኝ። ከመዘጋጃ ቤት በመውጣት በሹፌርነት መስራት ጀመርኩ። ነገር ግን ብዙም በስራው ሳልገፋበት ትቸው ወጥሁ። በዚህ መካከል አንድ ህልም አየሁ።

መንበረ ልዑል

በወቅቱ የታየዎት ህልም ምን ነበር?

አቶ በለጠ

ነገሩ እንዲህ ነው። በህልሜ ፃድቁ አባታች ኤዎስጣቴዎስ መቅደሳቸውን እንድሰራ ሲያዙኝ አየሁ። እኔም ቤተክርስቲያን የሚሆን ቦታ እየፈለኩ እያለ ስኔ12 2001 .. ምሽት ላይ ቅዱስ ሚካኤል በህልሜ ታየኝ። ህልሙም ምስካየ ግዙናን አስቀድሼ ስመለስ 6ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ በር ላይ ሚዛንና ሰይፍ የያዘ ሰው ወደ አንደኛ በር ይጠቁመኝ ነበር። ብንን ስል ከሌሊቱ ዘጠኝ ሆኗል። ይህ ነገር ከዛን ጊዜ ጀምሮ በየወሩ3 ወይም 4 ጊዜ “ተናገር!“ እያለ ያዘኛል። እኔ ግን አቅም የለኝም ምን ብዬ ልናገር ስል፡ “ነፃ አውጣኝ መታሰሩ ይበቃኛል!“ እያለ እየመላለሰ ይነግረኝ ነበር።

እኔም ይረዱኛል ብዬ በማስባቸው ባለሀብቶችና ታዋዊ ሰዎች ብጠቁምም መፍትሄ ሳላገኝ ድካም ብቻ ሆኖ ቀረ።

መንበረ ልዑል

የዚህ ህልሞዎት መጨረሻ ምን ሆነ?

አቶ በለጠ

የሚረዳኝ ሰው ባጣሁበት ሰዓት አሁን በህይወት ለሌሉት ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ደብዳቤ ድፊእ ጉዳዩን ስከታተል እሳቸውም በህይወተ ሥጋ ስለተለዩ በዚህም ምክንያት ከ ፫ አመት በኋላ እንደገና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጉዳዩን አመለከትኩ። ወደ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ ተመርቶ እየተመላለስኩ ጉዳዩን ስከታተል በ፪ሺ፱ ዓ.. መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ከ፱ ዓመታት በኋላ ጉዳዩ መስመር እየያዘ መሆኑን ሰማሁ። በስተመጨረሻም፡ ህዳር ፲ ፪ሺ፱ ዓ.. ማለዳ በክብር ወደ ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ እንዲገባ ሆነ። በወቅቱም ከተሰማኝ ደስታ የተነሳ እያነባሁ ነበር።

መንበረ ልዑል

በመጨረሻ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት አለ?

አቶ በለጠ

በመጨረሻ የማስተላልፈው መልዕክት ይህንን ነገር ሁሉ በዓይኔ ላሳየኝ ለፈጣሪ ክብር ምስጋና ይሁን፡ እንዲሁም በዚህ መንፈሳዊ ስራ የተራዱኝን ሁሉ አምላከ ቅዱስ ሚካኤል ዋጋቸውን ይክፈልልኝ እያልኩኝ አሁንም ለጊዜው የማልናገረው ብዙ ነገር አለኝ።

መንበረ ልዑል

አባታችን አቶ በለጠ ቅዱስ ሚካኤል በእርስዎ ላይ አድሮ የገለጠውን ተዓምር ስላካፈሉን በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን፤ እግዚአብሔር ይስጥልን።

ታላቁ ደብር መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ወቅት

የ ፺፫ አመታት ዕድሜ ባለጸጋ የሆነው ታላቁ ደብር መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በዘመናት ብዙ ታሪካዊ ሂደቶችን አልፎ ከአሁኑ ትውልድ ደርሷል። የቤተክርስቲያኑ ታሪክ እንደሚያስረዳው ወደ ቅጽረ ቤተክርስቲያኑ የሚመጡት የንጉሳውያን ቤተሰብ ብቻ በመሆናቸው ምዕመናኑ ደብሩን የሚያውቁበት እድል አልነበራቸውም። ለዚህም ይመስላል ለመጀመሪያ ጊዜ ታቦተ ህጉ ለክብረ በዓል የወጣው ከተተከለ ከ፶፫ አመት በኋላ ሚያዝያ ፴ ፲፱፻፷፱ ዓ.ም መሆኑ እንዲሁም የቅዱስ ሚካኤል በዓል ህዳር ፲፪ ፲፱፻፸ ዓ.ም መከበር መጀመሩ ከህዝቡ እይታ የራቀ መሆኑ አንዱ ማሳያ ነው። ቢሆንም በደብሩ የታሪክ ጉዞ ውስጥ በርከት ያሉ ጥቧን አባቶች የተገኙ ሲሆን እንዲሁ አሁንም በቀደሙት አባቶች መንፈስ የሚጓዙ ሥጋቸው ለነፍሳቸው የተገዛላቸው አንጋፋ አባቶች የሚገኙበት ታላቅ ደብር ነው።

ይህም ደብር ፻ኛ አመቱን በቅርብ አመታት ለማክበር በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ይገኛል።

በአመት ውስጥም ጥቅምት ፴ እና ሚያዝያ ፴ የሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ አመታዊ ክብረ በዓል እና ህዳር ፲፪ ፣ጥር ፲፪ ፣ ሰኔ ፲፪ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት በደብሩ ይከበራል። በተጨማሪም ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉበት በዓለ ሃምሳ በጽርሐ ጽዮን እንደሆነ ይታወቃል። ይህም የሐዋርያውና የሰማዕቱ ወንጌላዊ ማርቆስ እናት ቤት መሆኑን የሊቃውንት መጽሐፍት ይመሰክራሉ። ይህንንም አብነት በማድረግ “በዓለ ሃምሳ” ከቅዱስ ማርቆስ ታሪክ ጋር በማስማማት በታላቅ ድምቀት በደብሩ ይከበራል።

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: