Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጻድቁ አቡነ ተክለሐይማኖት’

የዓለማችን ጥንታዊው ኤሊ ፲፻፺/190እና የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ቤ/ክ ኤሊ | አባታችን ምን እየጠቆሙን ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 3, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 😇 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

👉 ሙሉ ቪዲዮው ታች ይገኛል…

🐢 Tortoise – ♰ Tekle Haymanot ፤ ሁለቱም ስማቸው በ T/ፊደል ነው የሚጀምረው። የዓለማችን ጥንታዊ ኤሊ የሚኖረው ደግሞ በንግሥት እሌኒ ስም (St.Helena) በምትጠራዋ ደሴት ላይ ነው። ቅድስት እሌኒ የታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ እናቱና እግዚአብሔር ለበጐ አገልግሎት የጠራት ቡርክት ሴት (ንግሥት) ናት።

ንግሥት ዕሌኒ የጌታችንን መስቀል መስከረም ፲፮/16 ቀን ፫፻፳/320 . ም በዕጣን ጢስ ምልክት ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት ፲/10 ቀን አግኝታ በማውጣት ታላቅ ቤተመቅደስ ጎልጎታ ላይ ሠርታ በክብር አስቀመጠችው። ይህ መስቀልም ከዚያ ዕለት ጀምሮ እንደ ፀሐይ እያበራ ድውይ እየፈወሰ አጋንንት እያባረረ ልዩ ልዩ ተአምራት እየሰራ ሙት እያነሳ ዕውር እያበራ ተአምራቱን ቀጠለ፡፡ ይህንንም ከኃያላን ነገሥታት መካከል የፋርስ ንጉሥ መስቀሉን ማርኮ ፋርስ ወስዶ አስቀመጠው፡፡ በዚህ ጊዜ የአየሩሳሌም ምዕመናን የድሉን ዜና ሰምተው ስለነበር የአንድ ቀን መንገድ ያህል ሄደው በመቀበል ካህናቱ በዝማሬና በቸብቸቦ ወንዱ በሆታ ሴቱ በእልልታ ሆ ! እያሉና ችቦ አብርተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያኖችም ለመስቀል ችቦእያበሩ በዓሉን በሆታ በእልልታ በስብሐተ እግዚአብሔር የሚያከብሩት ይህንን ታሪካዊ ትውፊት በመከተል ነው፡፡

ብዙ የቤተክርስቲያን አባቶች እንደሚሉት ንጉሡ ሕርቃል ይህንን ታላቅ ድል ለማግኘትና የጌታን ቅዱስ መስቀል ከአሕዛብ / ከፋርሶች / እጅ ለማስመለስ የቻለው በዚያን ጊዜ አብያተ ክርስቲያንናት ሁሉ ለአንድ ሳምንት / አንድ ሱባዔ / ባደረጉትጾም ጸሎት ነው፡፡ ይህንንም ለማስታወስና ጌታን ለማመስገን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የግብጽ ኮፕቲክቤተክርስቲያን በየዓመቱ የዐቢይጾም / የጌታ ጾም / ከመጀመሩ አስቀድሞ ጾመ ሕርቃል ብለው አንድ ሳምንት ይጾማሉ፡፡ ፓትርያርክ ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው፡፡

ይህ ግማደ መስቀልም ለብዙ ዘመን በእስክንድርያ ሲኖሩ በግብጽ ያሉ እስላሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ ሔደ በእስክንድርያ የሚኖሩትን ክርስትያኖች ላይ ሥቃይ ያጸኑባቸው ጀመር፡፡ ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው መክረው ለኢትዮጵያዊው ዓጼ ዳዊት እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ ንጉሥ ሆይ ! በዚህ በግብጽ ያሉ እስላሞች መከራ አጽንተውብናል ኃይልህን አንሥተህ አስታግስልን ብለው ጠየቁት ዳግማዊ ዓጼ ዳዊትም ለመንፈሳዊ ኃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር አስገድዷቸው ሃያ ሺህ ሠራዊት አስከትለው ወደግብጽ ዘመቱ በዚህ ጊዜ በግብጽ ያሉ ኃያላን ፈሩ ተሸበሩ ንጉሡ ዳግማዊ ዳዊትም እንዲህ የሚል መልዕክት ለእስላሞቹ ላከ በተፈጥሮ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ካልታረቃችሁ ሀገራችሁን መጥቼ አጠፋለሁ የሚል ማስጠንቀቂያ ላከ፡፡

የንጉሡ መልዕክትም ለእስላሞቹ እንደደረሳቸው ፈርተው እንደ ጥንቱ በየሃይማታቸው ጸንተው በሰላም እንዲኖሩ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታረቁ፡፡ መታረቃቸውን ዓጼ ዳዊት ሰሙ በዚህም ጉዳይ ንጉሡ ደስ አላቸው፡፡ እግዚአብሔር አመሰገኑ በግብጽ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ከ አስራ ሁለት ሺህ ወቄት ወርቅ ጋር ደስታቸውን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለዳግማዊ ዳዊት በደብዳቤ አድርገው ላኩላቸው፡፡ ንጉሡም የደስታውንደብዳቤ ተመልክተው ደስ አላቸው ወርቁን ግን መልሰው በመላክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፉ፡፡ በግብጽ የምትኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች ሆኖ እንኳን ደስ አላችሁ የላካችሁልኝ 12,000 ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ፡፡ የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለም የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ በተቻለኝ ችግራችሁን ሁሉ አስወገድኩላችሁ አሁንም የምለምናችሁ በሀገሬ ኢትዮጵያ ረሀብና ቸነፈር ድርቅ ስለወረደብኝ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀልና የቅዱሳን አጽም ከሌሎች ክቡራን ዕቃዎች ጋር እንድትልኩልኝ ነው የሚል ነበር፡፡ በእስክንድርያም ያሉ ምዕመናን ይህ መልዕክት እንደደረሳቸው ከሊቃነ ጳጳሳትና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ጋር ውይይት በማድረግ ይህ ንጉሥ ታላቅ ክርስቲያን ነው፡፡ ስለዚህ ልቡን ደስ እንዲለው የፈለገውን የጌታችንን ግማደ መስቀል ከቅዱሳን አጽምና ንዋየ ቅዱሳት ጋር አሁን በመለሰው ወቄት ወርቅ የብርና የነሐስ የመዳብና የወርቅ ሣጥን አዘጋጅተን እንላክለት ብለው ተስማምተው በክብር በሥነ ሥርዓት በሠረገላና በግመል አስጭነው ስናር ድረስ አምጥተው ባስረከቧቸው ጊዜ በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እያሸበሸቡ በግንባራቸው እየሰገዱ በክብር በደስታ ተቀበሏቸው፡፡ መስከረም 16 በኢትዮጵያ ታላቅ ብርሃን ሌሊትና ቀን ሦስት ቀን ሙሉ ሲበራ ሰነበተ፡፡

ግማደ መስቀሉ ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ ሳይደርስ በድንገት ዓጼ ዳዊት ስናር ላይ አረፉ፡፡ ግማደ መስቀሉም የግድ በዚያው በስናር መቆየት አስፈለገው፡፡ ከዚህ በኋላ የሟቹ የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዓጼ ዘርዓ ያዕቆብ እንደነገሠ ወደ ስናር ሔደ ግማደ መስቀሉን ከሌሎቹ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር አምጥተው በመናገሻ ከተማቸው በደብረ ብርሃን ላይ ቤተመቅደስ ሠርተው ለማስቀመጥ ሲደክሙ በሕልማቸው አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል ወዳጄ ዘርዐ ያዕቆብ ሆይ መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ የሚል ሕልም አየ፡፡ ንጉሡም መስቀለኛ ቦታ እየፈለጉ በኢትዮጵያ አውራጃዎች ሁሉ በመፈለግ ከብዙ ቦታ አስቀምጠውት ነበር፡፡ ለምሳሌ በሸዋ በደርሄ ማርያም፣ በማናገሻ ማርያም፣ በወጨጫ መስቀሉን አሳርፈውት ነበር፡፡ ነገር ግን የመጨረሻውን ቦታ ባለማግኘታቸው በራዕይ እየደጋገመ መስቀሌን በመስቀለኛ ሥፍራ አስቀምጥ እያለ ይነግራቸው ነበር፡፡ ዓጼ ዘርዓ ያዕቆብም ለሰባት ቀን ሱባዔ ገቡ፡፡ በዚያም የተገለጸላቸው መስቀለኛውን ቦታ የሚመራህ ዓምደብርሃን ይመጣል አላቸው፡፡ እርሳቸውም ከዚያ እንደወጡ መስቀለኛውን ቦታ የሚመራ የብርሃን ዓምድ ከፊታቸው መጥቶ ቆመ፡፡ በዚያ መሪነት ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ ውስጥ ግሸን ከምትባል አምባ መርቶ አደረሳቸው፡፡ በእውነትምይህች ግሸን የተባለችው አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረጻት የተዋበች መስቀለኛ ቦታ ሆና ስላገኟት የልባቸው ስለደረሰ ደስ አላቸው፡፡ በዚያም አምባ ታላቅ ቤተመቅደስ ሰርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋየ ቅዱሳቱን በየመዓረጋቸው የክብርቦታ መድበው አስቀመጡዋቸው፡፡

ዘመኑም በ ፲፬/14 ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ ከእስክንድርያ ሀገር ከመስቀሉ ጋር በልዩ ልዩ ሣጥን ተቆልፈው የመጡትም ዝርዝር ስማቸው ጌታ በዕለተ ዓርብ ለብሶት የነበረው ቀይ ልብስ፣ ከሮም የመጣው ከለሜዳው፣ ሐሙት የጠጣበት ሰፍነግ / ጽዋ / ፣ ዮሐንስ የሳለውኩርዓተ ርዕሱ ስዕል እንዲሁም የተለያዩ የቅዱሳን አጽም፣ ከግብጽ ታላላቅ ገዳማት የተቆነጠረ አፈር፣ የዮርዳኖስ ውሃ ይገኛል፡፡

የስምህ መነሻ ፊደል የመስቀል ምልክት (♰)ለሆነው እና ክቡር ገናና ለሆነው ስም አጠራርህ ሰላም እላለው ። የወንጌል ተቀዳሚ ስም ማቴዎስ የተባልክ ተክለ ሐይማኖት ሆይ እንደ ችሎታዬ አመሰግንህ ዘንድ አንደበቴ ትፈታልኝ ዘንድ ድንግል ማርያምን እማልዳለሁ።” ገድለ ተክለ ሐይማኖት።

😈አረመኔው ግራኝ ልክ በተክለ ሐይማኖት ዕለት በአክሱም ጽዮን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነቱን ከፈተ፤ ለዋቄዮአላህሰይጣን የክርስቲያኖችን ደም የገበረበትን ዕለት እና ሥልጣኑን ለማደላደል በዓለ ንግሥናውንየሚያከብርበትን ዕለትም የመረጠው ሆን ብሎ በሰይጣናዊው ኢሬቻ ማግስት በዚሁ ዕለተ አቡነ ተክለ ሐይማኖት መሆኑን እናስታውስ

🐢 በዚህ በዛሬው የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት ሁለቱንም የዓለም ጦርነቶች ያየ የዓለማችን ጥንታዊው ኤሊ ፲፻፺/190ኛ የልደት ቀንን አክብሯል

በአዲስ አበባም ጥንታዊው አንጋፋ ዔሊ“ለቡ” ተብሎ በሚጠራው ሠፈር (እኔ ሠፈሩን “ተክልዬ” እለዋለሁ) ሚገኘው የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሐይማኖት ውብ ቤተ ክርስቲያን

💭 ኤሊ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ዘስጋ በመታደን ላይ ነች

የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ የተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ኤሊ ብዙ ገንዘብ ታስገኛለችበማለት ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን በማደን ላይ ያሉት አረመኔዎቹ የዋቄዮአላህ ጭፍሮች ወደ ኤሊ አደንም እየገቡ መሆኑ እየተነገረ ነው።

በበርካታ የሃገራችን ክፍሎች ኤሊ በርካታ ሚሊዮን ብሮችን ታስገኛለች በማለት አድኖ በአንድ ቦታ ማከማቸት እና የኤሊ ሕገወጥ ዝውውር እየተደረገ መሆኑ ተረጋግጧል።

አዲስ አበባን ጨምሮ፣ ሻሸመኔ፣ ሐረርጌ፣ ምዕራብ ኦሮሚያ እና አፋር ክልል ይህን መሰል ተግባር በስፋት እየተፈጸመ እንደሆነ መረዳት ተችሏል።

የዱር እንስሳዋን በተመለከተ በርካታ የተሳሳቱ መረጃዎች ይሰራጫሉ። ገንዘብ እናገኛለን በሚል በተሳሳተ መረጃ ኤሊ የሚያድኑት ሰዎች እጅግ ተፈላጊየምትባለዋን ኤሊ አድነው ካገኙ እስከ ፪፻/200 ሚሊዮን ብር ድረስ ዋጋ ታወጣለች ብለው ያምናሉ።

🐢 “እጅግ ተፈላጊ” የምትባለዋ ኤሊ የሚከተሉት ልዩ መለያዎች አሏት ተብሎ ይታመናል፤

  • እንደ ማግኔት ብረቶችን የመሳብ አቅም አላት፣
  • ንጹህ ውሃ ጎን ብትቀመጥ፤ ውሃው ይደፈርሳል፣
  • ጭለማ ውስጥ አንገቷ አንጸባራቂ ብርሃን ያወጣል፣
  • በካሜራ ምስሏ ሊነሳ አይችልም፣
  • በኤሊ ውስጥ ሜርኩሪ ይገኛል፣

እርኩስ የዋቄዮአላህ መንፈስ በሰፈነባት በዛሬዋ ኢትዮጵያ ዘስጋ ወራሪዎቹ የዘመናችን አማሌቃውያን እነዚህን ሐሰተኛ መረጃዎች በማሰራጨት የሰውን ልጅ ጨምሮ እነዚህንም ምስኪን እና ሰላማዊ የሆኑ የእግዚአብሔር ፍጥረታትን በማደን ላይ ናቸው።

ለፅንስትከ ተክለ ሐይማኖት ሆይ አስቀድሞ በማኅፀን ለተፀነስከው ፅንስትህና በታኅሣስ ፳፬/24 ቀን ለተውለድከው መወለድም ሰላም እላለሁ።

ለዝክረ ስምከ ተክለ ሐይማኖት ሆይ የስምህ የመነሻ ፌደሉ ትዕምርተ መስቀል ለሆነው ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ። እሱም ገናና የከበረ ስም ነው።

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ከአረጋዊ ተክል የተገኘህ አዲስ የተክል አበባ ነህ። የሌዊና የይሑዳ ካህናት ይህ ሰማያዊ መልአክ ነውን ወይስ ምድራዊ ሰው እያሉ ስለ አንተ ይደነቃሉ።

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ስግደትህ በማዕረገ መላእክት ደረጃ ነውና አከናውነህ የሠራሃት ጸሎትህ ባለ ዘመናችን ሁሉ ከጦርነትና ከጽኑ መከራ ሁሉ ጠባቂ ትሁነን።

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ መሥዋዕትን የምታሣርግ ታላቅ ካህን የእግዚአብሔር ባለሟል ነህና ቀንዶቹ ዓሥር ከሆኑ ከእባብ መተናኮልና አንደበቱ ሁለት ከሆነ ሰው ፀብ በክንፈ ረድኤትህ ሠውረህ አድነኝ።

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ልጆችህ በዚህ ዓለም ብዙ መከራ ቢያገኛቸውም በአንተ ዘንድ ፍጹም ሰላምና እረፍትን እንደሚያገኙ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ ከሐዲዎችን የምትበቀል ቄርሎስ የተባልክ አንተ ተክለ ሐይማኖት ነህ እኮን።

ቅዱሱ አባት ተክለ ሐይማኖት ሆይ፤ የሥላሴን አንድነት ሦስትነት በማስተማር ዓዋጅ ነጋሪነትህ ፍጹም ድንቅ ነው። እባቡን በእርግጫ አንበሳውን በጡጫ ብለው የሚያልፉ የሴትና የወንድ ደቀ መዛሙርት በጸጋ ወልድሃልና።

ያለምንም ተድኅሮ በሥላሴ ስም ይህን ሦስትነት አምናለሁ፤ በተንኮል ወንድማማቾችን እርስ በርስ የሚያባሉትን፣ ደንፍተው የሚያጠቁንን፣ ወዳጅ መስለው ሊያጠፉን የፈለጉትን የሚከተሉትን የጽዮንን ጠላቶች የእግዚአብሔር ቃል ይቅሰፋቸው፣ በተሣለ የመለኮት ሠይፍ አንገታቸውን ይቍረጣቸው፤ አሜን!!!

የአባታችን የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ረድኤትና በረከት፡ ምልጃና ጸሎት በሀገራችን በኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ አድሮ ይኑር፡ ሀገራችንን ሊያጠፋ የተነሳውን እርኩስ የዋቄዮአላህአቴቴ መንፈስን ያጥፉልን፤ ጠላቶቻችንን በእሳት ይጠራርግልን፤ ለዘላለሙ አሜን!

❖❖❖ ተክለ ሐይማኖት ፀሐይ ❖❖❖

የክርስቲያኖች መመኪያ

ተክለ ሐይማኖት ጻድቅ

የእንባችን ማበሻ

ከፈጣሪ የምታስታርቅ

ሰባሊ ወንጌል መናኝ

ሰማያዊ አርበኛ

በጸሎትህ ትሩፋት

ፀሐይ ያበራህ ለእኛ

ቅዱስ አባትችን ሆይ

ሀጢአታችን ስለበዛ

በቃልኪዳንህ አማልደን

በነፍሳችን ሁናት ቤዛ።

አደራ!

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይህንም ቤተ ክርስቲያን ያቃጠለው የዳግማዊ ግራኝ ሠራዊት ነው | ተክልዬን አልቻሏቸውምና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 30, 2020

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ

አዎ! ባለፈው ዓመት ላይ በደቡብ ጎንደር የሚገኘውን ታሪካዊ የአቡነ ተክለሐይማኖት ቤተ ክርስቲያን ያቃጠለውም የግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ሠራዊት ነው። እየመዘገብን ነው፤ እየቆጠርን ነው!

በግራኝ አብዮት አህመድ የሚመራው የብልግና ፓርቲ በኢትዮጵያ እና ሕዝቧ ላይ፣ በቤተ ክርስቲያኗ እና ቅዱሳን አባቶቿ ላይ መሳለቁን በድፍረት ቀጥሎበታል። እስኪ አስቡበት፤ ግራኝ አቢይ እና ፓርቲው የታሪካዊቷን ኢትዮጵያ ገጽታ ለመቀየርና ተዋሕዶ ክርስትናን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ቆርጠው ተነስተዋል።

ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ውዳቂ የብልግና ፓርቲ ልክ እንደ አልማርባዩ እናቱ ህወሃት“ኦርቶዶክስ ኋላ ቀር ናት፣ የብልጽግና እንቅፋት ናት፣ መወገድ አለባት” የሚል የፓርቲ ፕሮግራም ይዞ በኢትዮጵያ ብቅ በማለት ለኢትዮጵያ ሥልጣኔና በጣም ልዩ የሆነ ታሪካዊ ማንነት ከፍተኛ ስጦታ ያበረከተቸውን ቤተ ክርስቲያን ለመዋጋት ሲንጠራሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ደማችሁን አያፈላውምን? አያስቆጣችሁምን? ልክ ከአምስት መቶ አመታት በፊት በዘመነ ግራኝ አህመድ ቀዳማዊ ዘመን ኢትዮጵያና ቤተ ክርስቲያኗ እንዲደክሙ ከተደረጉ በኋላ በቱርክ የሚመሩት መሀመዳውያኑ ኢትዮጵያን ለማመሰቃቀል እንደበቁት ግራኝ አብዮት አህመድም መሃል ኢትዮጵያን በማዳከምና በማፈራረስ ላይ ይገኛል፤ ይህም በሶማሊያ፣ ሱዳን እና ጂቡቲ የተጧጧፈ ስልጠና በማድረግ ላይ ያለው የቱርኮችና አረቦች ሠራዊት ከሐረር እስከ አስመራ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ቤኒሻንጉል (ግድቡን)ያሉትን ቦታዎች ለመቆጣጠር አስፍስፎ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የእነ ግራኝ አህመድ ሳትሆን የአቡነ ተክለሐይማኖት ሀገር ናት፤ በዚህም ትልቅ ተስፋ አለን፥ ነገር ግን የሕዝባችንን የስቃይ ዘመን ማሳጠር የምንሻ ከሆነ ከእነ ዶ/ር አብዮት አህመድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አኝከን መትፋት ይኖርብናል። የእግዚአብሔርን ቅዱሳን መላዕክቱን እንዲሁም የእነ አቡነ ተክለ ሐይማኖትን እርዳታ የሚሻ ኢትዮጵያዊ በእነ ግራኝ አብዮት አህመድ ላይ ጥቃቱን ባፋጣኝ ማድረግ ይኖርበታል። ዘንዶው ሰውዬ እርኩስ መንፈስ እና መጥፎ እድል ነው ለሀገራችን ይዞ የመጣው፤ የዚህም መገለጫ የሆኑትን እስልምናን እና ግብረሰዶማዊነትን ለማስፋፋት የተላከ መሆኑ ዓይናችን እያየው፡ ጆሮዋችንም እየሰማው ነው። ይህ ሰው(መንፈሱ) ከእነ መንግስቱ ኃይለማርያም የባሰ አደገኛ ሰው ነውና በሚቀጥሉት ቀናትና ሳምንታት ይወገድልን ዘንድ የብጹእ አባታችንን አቡነ ተክለሐይማኖትን አማላጅነት እንዳይለየን ተግተን ልንጸለይ ይገባናል።

እዚህ ላይ ትንሽ ባክልበት፤ በደርግ ጊዜ መንግስቱ ኃይለማርያም ብዙ የኢትዮጵያ ህፃናትን ለግብረሰዶማዊ ሙከራ ወደ ኩባ/ ጓንታናሞ ልኳቸው ነበር፤ አንዷ ትንሽ ደሴት ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተዘጋጀች ነበረች። ይህን በተመለከተ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ደርሶባቸው ስለነበረው ጉድ እና እንዴት ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሄደው ለመፈውስ እንደበቁ ከጥቂት ዓመታት በፊት ኖርዌይ ላይ በነበረ ቆይታችን በሚያሳዝን መልክ አውስተውን ነበር።

የሚገርመው፤ ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ለመጀመር ግራኝ አብዮት አህመድ “ዳቦ፣ ፓርክ” ምናምን እያለ በመወራጨት ላይ ነው። የፋሺስት ደርግን የሕፃናት አምባ ምስረታ ዘመቻ የሚያዳንቁ ግብዞች አሉ፤ እነዚህ አልማርባዮች፤ አወቁትም አላወቁትም፤ የግብረሰዶማዊነት ተልዕኮ ያላቸው የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው። በጣም ያሳዝናል! ደርግ መጀመሪያ የሕፃናቱን አባቶች በሽብርና ጦርነት ሰበብ ካስገደለ በኋላ ልጆቻቸውን አሳዳጊአልባ በማድረግና በጎ ተግባር የፈጸመ ለማስመሰል የሕፃናት አምባ አቋቋምኩ፤ እንደ ኩባ ወደመሰሉ “ወዳጅ ሃገራት” ላኩ እያለ ሐይማኖት የሌላቸው፣ በዲያብሎሳዊው ግብረሰዶማውያን መንፈስ የሚያድጉ ሕጻናት ሊያደርጋቸው በግዙፍ ባጀት ሲያሳድግ ነበር። ዛሬም ግራኝ አብዮት አህመድ ሕፃናቱን ሰብስቦ “ገዳ” ላስተምራችሁ፣ ዳቦና ወተት ልቀልባችሁ” በማለት ላይ ነው።

ለእነዚህ ሁለት አውሬ የሲ አይ ኤ ቅጥረኞች (መንግስቱና አብዮት) አሁንም ሆይሆይ የምትሉ ሁሉ ጊዜው አብቅቷል፤ እናንተም የኢትዮጵያና እግዚአብሔር አምላኳ ጠላቶች ናችሁና አብራችሁ በእሳት ትጠረጋላችሁ፤ ጻድቁ አባታቻን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ሌት ተቀን በሚጠብቋት ሃገራችን ላይ በፈላጭ ቆራጭነት የመሳለቂያው ጊዜ እያከተመ ነው። ወዮላችሁ!

መታሰብያቸው ለዘላለም ከሚኖረው ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሐይማኖት ናቸው፤ ተክልዬ በዙሪያችን አሉ፤ እዚያ ላይ አሉ፣ በአፍሪቃ፣ እስያ፣ አውሮፓና አሜሪካ አየሮች ላይ አሉ፡፡ በጣም ታድለናል!

ሰባት ዓመት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሀገር፥ ለቤተክርስቲያን፥ ለምዕመናን እና ለዓለም ሁሉ የጸለዩት የቅዱሱ አባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት ረድኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተክልዬ የሃይማኖትን ገዳዮች ዛፍ ከሥሩ ይነቅሉታል ፥ የኢትዮጵያን ጠላትም በእሳት ይጠርጉታል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 1, 2020

አባታችን ተክልዬ፤ ልጅዎንና እህታችንን ተማሪ ሃይማኖትን በምን ዓይነት አሰቃቂ መልክ እንደገደሏት መዝግበዋልና፡ ተጨማሪ ወንጀል ከመፈጸማቸው በፊት ገዳዮቿን ዛሬውኑ ከምኒሊክ ቤተ መንግስት አውጥተው ኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ውስጥ ይክተቱልን። አሜን!

👉 መታሰቢያነቱ ለ እህታችን ሃይማኖት በዻዻ!

የአባታችን የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ረድኤትና በረከት፡ ምልጃና ጸሎት በሀገራችን በኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ አድሮ ይኑር፡ ሀገራችንን ሊያጠፋ የተነሳውን መንፈስ ያጥፉልን፤ ለዘላለሙ አሜን!

ተክለ ሐይማኖት ፀሐይ

የክርስቲያኖች መመኪያ

ተክለ ሐይማኖት ጻድቅ

የእንባችን ማበሻ

ከፈጣሪ የምታስታርቅ

ሰባሊ ወንጌል መናኝ

ሰማያዊ አርበኛ

በጸሎትህ ትሩፋት

ፀሐይ ያበራህ ለእኛ

ቅዱስ አባትችን ሆይ

ሀጢአታችን ስለበዛ

በቃልኪዳንህ አማልደን

በነፍሳችን ሁናት ቤዛ።

አደራ!

_______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተክልዬ የዋቄዮ-አላህን ዛፍ ከሥሩ ይነቅሉታል ፥ የኢትዮጵያን ጠላትም በእሳት ይጠርጉታል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 3, 2020

መታደል ነው፤ በእነዚህ የጾመ ነብያት ቀናት፡ ዛሬ የሐዋርያው አባታችንን፡ ማክሰኞ ደግሞ የቸሩ አምላካችንን ልደት እናከብራለን። እንኳን አደረሰን!

ተክለሐይማኖት ማለት “የሐይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ” ማለት ነው፡፡

ጻድቁ አባታችን በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ሕዝቡን ከኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ፣ ከክህደት ወደ ኃይማኖት ስለመለሱት በዚህም የተነሣ ለኢትዮጵያውያን ብርሃን ተብለዋል፡፡ በዚህም መሠረት፡ ከ1219-1222 .ም በከተታ ሦስት ዓመት ወንጌልን አስተማሩ፡፡ ቀጥለውም ዘጠኝ ወር በዊፋት አገልግሎታቸውን ፈጸሙ፡፡ ከ1223-1234 .ም ዳሞት በተባለው ስፍራ ወይም በወላይታ ሀገር ለ12 ዓመታት ሕዝቡን በማስተማር ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንንም አንጸዋል፡፡ በዚህ ሀገር ዲያብሎስ በዛፍ ላይ አድሮ “አምላክ ነኝ” እያለ ለረጅም ዘመናት ሕዝቡን በማሳት የሚጠቀምበትን ዛፍ በተአምራት ከሥሩ ነቅለው አፍልሰውታል፡፡

የዋቄዮአላህ ተከታዮችንም ዛፍ ፃድቁ አባታችን ከሥሩ ይንቀሉልን! ይህን አስመልክቶ እኔ በግሌ ያየኋቸው ብዙ የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ተዓምራት አሉ፤ በተለይ በዕለታቸው። ጻድቁ አባታችን እዚህ በስጋ እያሉ እንደነበራቸው በስድስት ብቻ ሳይሆን በስድስት ሚሊየን ክንፋቸው በሰዓት ስድስት ሚሊየን ኪሎሜትር ፍጥነት እስከ አሜሪካ እና ቻይና ድረስ በመብረር የ666ዲያብሎስን ዛፍ የመንቀል፣ ዘንዶውን የመግደልና የኢትዮጵያን ጠላቶች በእሳት የመጥረግ ኃይል እንዳላቸው 100% እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁ።

ዲያብሎስ ጠላት በእነዚህ የጾም ቀናትና ሳምንታት ሙጭኝ ብሎ ይፈታተነናል። በዛሬው ዕለት በሃገራችን በክርስቶስ ጠላት አህዛብ አማካኝነት እየተካሄደ ያለውን እንቅስቃሴ በሚገባ እንመዝግበው። ሕዝበ ክርስቲያኑ በመሀመዳውያኑ ጭፍጨፋና ግፍ የተፈጠረውን የተበዳይነትና ተጠቂነት፣ የቁጣና ሃዘን፣ ብሎም ለሰልፉ፣ ለተቃውሞና ለአመጽ የሚያነሳሳውን የወኔ መንፈስ ከተዋሕዶ ልጆች ለመንጠቅ/ለመስረቅ፤ በዚህም ለቀጣዩ ጂሃድ ይዘጋጁ ዘንድ የፈጠሩት ዲያብሎሳዊ እንቅስቃሴ ነው። ተጠቂነት/ተበዳይነት በበታችነት መንፈስ ለሚራመዱት ለመሀመዳውያኑ እና ለኦሮሞ ነን ባዮቹ በጣም ትልቅ መሣሪያቸው ነው።

እነዚህ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን እንዲሁም የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለተ ልደት የሆነውን የዛሬውን አርብ ዕለት ለእንቅስቃሴያቸው በድጋሚ መርጠውታል (ግድ ነው!) ፥ “የአዲስ አበባውን ኢሬቻ” እናስታውሳለን? በተክለ ሐይማኖት ዕለት ነበር። አዎ! ክርስቶስን ይጠሉታል፤ አቡነ ተክለ ሐይማኖትን ይጠሏቸዋል! ግራኝ አህመድን በጣም ይወዱታል (100%)። የአምላክህ እግዚአብሔርን፣ የሃገርህንና የተዋሕዶ እመንትህን ጠላት ለመለየት ከዚህ የበለጠ መለኪያ የለም። ስለዚህ የጠላቶቻችንን አረማመድ በጥሞና እንከታተለው፡ ተግባራቸውንም በደንብ እንመዝግበው፤ ከጨለማ ጋር ሕብረት መሰናከልንና መውደቅን ብቻ እንደሚያመጣ አይተናልና ከጨለማ ጋር አብሮ መሰለፉን እናቁም፤ ከመካከላቸው አንድ ወይም ሁለት ገለሰቦች “የኢትዮጵያን ባንዲራ” ስለያዙ ወይም “ኢቶቢያ! ኢትዮቢያ”(አዎ! መህመዳውያን “ኢትዮጵያ” እና “ኢየሱስ ክርስቶስ” ብለው በፍጹም አይጠሩም) በማለት የሚጽፉልንን የማስተኚያ ኪኒን አንውሰደው። ዲያብሎስም ሁለት መድኃኒት “ከሰጠ” በኋላ አንድ መርዝ ያክላል።

ዛሬ የደረሰን ትልቅ ዜና፦

ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በጋዛ ሰርጥ በኩርድ አማጺያን በቅርቡ ያስረሸናቸው እናት ኢትዮጵያን በሱዳንና የመን በኩል ለመተናኮል አቅዶ የነበረው ከፍተኛ የኢራን እስላም ሪፐብሊክ ባለሥልጣን በእሳት ተጠረገ። ቃሲም ሱሌማኒ ይባላል። ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉ!

አሁን የጂኒው ሳጥን ተከፍቷል፤ የኢትዮጵያ ጠላቶች እርስበርስ ይባላሉ፤ ይህ ገና ማማሞቂያው ነው። ሺያ እስላም ኤራን ሱኒ እስላም ጠላቷን ሳውዲን ልታጠቃ ትችላለች፤ ፈጠነም ዘገየም አንድ ቀን ማጥቃቷ አይቀርም፤ በመካከላቸው በሚደረገው የሚሳኤልና ሮኬት ልውውጥ የሁለቱም አገራት የነዳጅ ሜዳዎች ሙሉ በሙሉ ይጋያሉ፣ የአጋንንት መቀመጫ ዋሻዎቹ መካ እና መዲና በእሳት ተጠርገው ከምድር ገጽ ይጠፋሉ። ይህ ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው!

የአባታችን የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ረድኤትና በረከት፡ ምልጃና ጸሎት በሀገራችን በኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ አድሮ ይኑር፡ ሀገራችንን ሊያጠፋ የተነሳውን መንፈስ ያጥፉልን፤ ለዘላለሙ አሜን!

ተክለ ሐይማኖት ፀሐይ

የክርስቲያኖች መመኪያ

ተክለ ሐይማኖት ጻድቅ

የእንባችን ማበሻ

ከፈጣሪ የምታስታርቅ

ሰባሊ ወንጌል መናኝ

ሰማያዊ አርበኛ

በጸሎትህ ትሩፋት

ፀሐይ ያበራህ ለእኛ

ቅዱስ አባትችን ሆይ

ሀጢአታችን ስለበዛ

በቃልኪዳንህ አማልደን

በነፍሳችን ሁናት ቤዛ።

አደራ!

የቪዲዮው ምስል የሚያሳየን አዲስ አበባ “ለቡ” ተብሎ በሚጠራው ሠፈር (እኔ ሠፈሩን “ተክልዬ” እለዋለሁ) የሚገኘውን ውቡን የአባታችን የጻድቁ አቡነ ተክለ ሐይማኖት ቤተ ክርስቲያንን ነው።

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: