Posts Tagged ‘ጸሎተ ሐሙስ’
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2022
VIDEO
✞✞✞ Day 6: Trial, Crucifixion, Death, and Burial on Good Friday
Friday’s events are recorded in Matthew 27:1-62, Mark 15:1-47, Luke 22:63, Luke 23:56, and John 18:28, John 19:37.
In the early morning hours, as Jesus’ trial was getting underway, Peter denied knowing his Master three times before the rooster crowed.
Good Friday is the most difficult day of Passion Week. Christ’s journey turned treacherous and acutely painful in these final hours leading to his death.
According to Scripture, Judas Iscariot, the disciple who had betrayed Jesus, was overcome with remorse and hanged himself early Friday morning.
Meanwhile, before the third hour (9 a.m.), Jesus endured the shame of false accusations, condemnation, mockery, beatings, and abandonment. After multiple unlawful trials, He was sentenced to death by crucifixion, one of the most horrible and disgraceful methods of capital punishment known at the time.
Before Christ was led away, soldiers spit on him, tormented and mocked him, and pierced him with a crown of thorns. Then Jesus carried His cross part of the way to Calvary and then a man named Simon was compelled to carry it the rest of the way. At Calvary, Jesus was again mocked and insulted as Roman soldiers nailed Him to the wooden cross.
Jesus spoke seven powerful statements from the cross, including “Father, forgive them, for they do not know what they are doing” (Luke 23:34, NIV), “Father, into your hands I commit my spirit” (Luke 23:46, NIV), and His last words were, “It is finished” (John 19:30).
Then, about the ninth hour (3 p.m.), Jesus breathed his last breath and died.
By 6 p.m. Friday evening, Nicodemus and Joseph of Arimathea took Jesus’ body down from the cross and lay it in a tomb.
_______ _______
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , Psychology , War & Crisis | Tagged: Addis Ababa , Aksum , Axum , መስቀል , ረቡዕ , ሰሙነ ሕማማት , ስቅለት , ስግደት , ቀዳም , ተዋሕዶ , ትንሣኤ , ትግራይ , አርብ , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , ኢየሱስ ክርስቶስ , እሑድ , ኦርቶዶክስ , ክህደት , ወንጀል , የኢየሱስ ፊልም , ይሑዳ , ጆርዳን ፔተርሰን , ገንዘብ , ጦርነት , ጸሎተ ሐሙስ , ጽዮናውያን , Christianity , Crucifixion , Ethiopia , Genocide , Good Friday , Holy Thursday , Holy Week , Jesus Christ , Jordan Peterson , Judas Iscariot , Passion Week , Saturday , Tewahedo Faith , The Cross , The Jesus Film , Tigray | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 20, 2022
VIDEO
❖❖❖ ጌታችን በጸሎተ ሐሙስ | ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን? ❖❖❖
ከኅፅበተ እግር በኋላ ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን ጌታችን እንዲህ ብሏቸዋል፤ “ ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን ? ዘወትር ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስ ስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው፡፡ የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው፤ ” ( ሉቃ . ፳፪፥፶፪ – ፶፫ ) ።
👉 የሰሙነ ሕማማት ሐሙስ ፮ ስያሜዎች
፩. ሕጽበተ እግር ይባላል ፪. የጸሎት ሐሙስ ይባላል ፫. የምስጢር ቀንም ይባላል ፬. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል ፭. የነጻነት ሐሙስ ይባላል ፮. አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል
_______ _______
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , Saints/ቅዱሳን , War & Crisis | Tagged: Addis Ababa , Aksum , Axum , መስቀል , ረቡዕ , ሰሙነ ሕማማት , ስቅለት , ቀዳም , ተዋሕዶ , ትንሣኤ , ትግራይ , አርብ , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , ኢየሱስ ክርስቶስ , እሑድ , ኦርቶዶክስ , ክህደት , ወንጀል , የኢየሱስ ፊልም , ይሑዳ , ገንዘብ , ጠላት , ጦርነት , ጸሎተ ሐሙስ , ጽዮናውያን , Ethiopia , Friday , Genocide , Holy Thursday , Holy Week , Jesus Christ , Judas Iscariot , Passion Week , Saturday , Tewahedo Faith , The Jesus Film , Tigray | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 20, 2022
VIDEO
❖❖❖ Holy Week – Day 5: Passover and Last Supper on Maundy Thursday ❖❖❖
Holy Week takes a somber turn on Thursday .
From Bethany, Jesus sent Peter and John ahead to the Upper Room in Jerusalem to make the preparations for the Passover Feast. That evening after sunset, Jesus washed the feet of his disciples as they prepared to share in the Passover. By performing this humble act of service, Jesus demonstrated by example how believers should love one another. Today, many churches practice foot-washing ceremonies as a part of their Maundy Thursday services.
Then, Jesus shared the feast of Passover with his disciples, saying:
“I have been very eager to eat this Passover meal with you before my suffering begins. For I tell you now that I won’t eat this meal again until its meaning is fulfilled in the Kingdom of God.” (Luke 22:15-16, NLT)
As the Lamb of God, Jesus was about to fulfill the meaning of Passover by giving his body to be broken and his blood to be shed in sacrifice, freeing us from sin and death. During this Last Supper, Jesus established the Lord’s Supper, or Communion, instructing his followers to continually remember his sacrifice by sharing in the elements of bread and wine (Luke 22:19-20).
Later, Jesus and the disciples left the Upper Room and went to the Garden of Gethsemane, where Jesus prayed in agony to God the Father. Luke’s Gospel says that “his sweat became like great drops of blood falling down to the ground” (Luke 22:44, ESV).
Late that evening in Gethsemane, Jesus was betrayed with a kiss by Judas Iscariot and arrested by the Sanhedrin. He was taken to the home of Caiaphas, the High Priest, where the whole council had gathered to begin making their case against Jesus.
Meanwhile, in the early morning hours, as Jesus’ trial was getting underway, Peter denied knowing his Master three times before the rooster crowed.
Thursday’s events are recorded in Matthew 26:17–75, Mark 14:12-72, Luke 22:7-62, and John 13:1-38.
_______ _______
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , Saints/ቅዱሳን , War & Crisis | Tagged: Addis Ababa , Aksum , Axum , መስቀል , ረቡዕ , ሰሙነ ሕማማት , ስቅለት , ቀዳም , ተዋሕዶ , ትንሣኤ , ትግራይ , አርብ , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , ኢየሱስ ክርስቶስ , እሑድ , ኦርቶዶክስ , ክህደት , ወንጀል , የኢየሱስ ፊልም , ይሑዳ , ገንዘብ , ጠላት , ጦርነት , ጸሎተ ሐሙስ , ጽዮናውያን , Ethiopia , Friday , Genocide , Holy Thursday , Holy Week , Jesus Christ , Judas Iscariot , Passion Week , Saturday , Tewahedo Faith , The Jesus Film , Tigray | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2021
VIDEO
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
👉 ማክሰኞ 👉 ሐሙስ 👉 ዓርብ 👉 ቅዳሜ 👉 እሑድ
በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የኢትዮጵያ ገዳም ግብጾች “መውረስ አለብን” እያሉ አሁን ኢትዮጵያውያን ምዕመናንን በመበጥበበጥ ላይ እንደሆኑ ከደቂቃዎች በፊት የደረሰኝ መልዕክት ይጠቁማል። ዋው ! በእርግጥም አጋንንቱ ተለቅቀዋል !
ሕማማተ እግዚእ ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ በገብርኤል ፣ ጸሎተ ሐሙስ በማርያም ፣ ዓርብ ስቅለት በኡራኤል ፣ ቅዳሜ ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ) በጊዮርጊስ እንዲሁም እሑድ ትንሣኤ በተክለ ሐይማኖት ዕለታት ሲውሉ ከ፸፫/73 ዓመታት በኋላ (፲፱፻፵/1940ዓ.ም)ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። ዘንድሮ በትግራይ ሕዝብና በአክሱም ጽዮን ላይ ጦርነት የታወጀው በእነዚህ ቀናት ነበር፤ በቅዱስ ጊዮርጊስና በአባታችን በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለታት።
👉 በ ፲፱፻፵/1940ዓ.ም የታዩ ቁልፍ ታሪካዊ ክስተቶች፦
☆ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከግብጽ ነፃ ወጥታ የራሷን ፓትርያርክ ትመርጥ ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ፤ በ፲፱፻፶፩/1951 ዓ.ም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ (ገብረ ጊዮርጊስ)ቀዳማዊ ሆኑ።
☆ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና ትቀላቀል ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ
☆ አይሁዶች በ ፪ሺ፱፻/2900 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበረ እና ሉዓላዊ ሀገር በመሆን ለእስራኤል ነፃነት አወጁ – እስራኤል አገር ሆነች
👉 እነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች ምንን እየጠቆሙን ይሆን?
❖ በኦሮማራው ንጉሥ አፄ ምኒልክ የተለያያኡት የትግራይ እና ኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ሰሜን ኢትዮጵያውያን መዋሐድና አንድ መሆን?
❖ የሰሜን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስረታ?
______________ ____________ _____________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith | Tagged: Addis Ababa , ልደታ ማርያም , ሰሙነ ሕማማት , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , ኢየሩሳሌም , ኢየሱስ ክርስቶስ , እስራኤል , ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት , ገዳም , ጸሎተ ሐሙስ , Ethiopian Orthodox , Faith , Holy Week , Jesus Christ , Maundy Thursday , Passion Week , St.Mary , Tigray , War | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 29, 2021
VIDEO
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
👉 ማክሰኞ 👉 ሐሙስ 👉 ዓርብ 👉 ቅዳሜ 👉 እሑድ
ሕማማተ እግዚእ ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ በገብርኤል ፣ ጸሎተ ሐሙስ በማርያም ፣ ዓርብ ስቅለት በ ኡራኤል ፣ ቅዳሜ ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ) በጊዮርጊስ እንዲሁም እሑድ ትንሣኤ በተክለ ሐይማኖት ዕለታት ሲውሉ ከ፸፫/73 ዓመታት በኋላ (፲፱፻፵/1940ዓ.ም)ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው። ዘንድሮ በትግራይ ሕዝብና በአክሱም ጽዮን ላይ ጦርነት የታወጀው በእነዚህ ቀናት ነበር፤ በቅዱስ ጊዮርጊስና በአባታችን በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለታት።
👉 በ ፲፱፻፵/1940ዓ.ም የታዩ ቁልፍ ታሪካዊ ክስተቶች፦
☆ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከግብጽ ነፃ ወጥታ የራሷን ፓትርያርክ ትመርጥ ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ፤ በ፲፱፻፶፩/1951 ዓ.ም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እና የመጀመሪያው ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስ (ገብረ ጊዮርጊስ)ቀዳማዊ ሆኑ።
☆ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር እንደገና ትቀላቀል ዘንድ ሂደቱ ተጀመረ
☆ አይሁዶች በ ፪ሺ፱፻/2900 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተባበረ እና ሉዓላዊ ሀገር በመሆን ለእስራኤል ነፃነት አወጁ ፥ እስራኤል አገር ሆነች
👉 እነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች ምንን እየጠቆሙን ይሆን?
❖ በኦሮማራው ንጉሥ አፄ ምኒልክ የተለያያኡት የትግራይ እና ኤርትራ ትግርኛ ተናጋሪ ሰሜን ኢትዮጵያውያን መዋሐድና አንድ መሆን?
❖ የሰሜን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምስረታ?
የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።
†ሐሙስ ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ
❖ በጸሎተ ሐሙስ የተፈጸሙ ተግባራት
በዕለተ ሐሙስ ከተፈጸሙ ዐበይት ተግባራት አንዱ መድኃኒታችን ክርስቶስ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው፤›› ብሎ አማናዊ ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ ነው (ማቴ. ፳፮፥፳፮-፳፰)። እንደዚሁም ይህ ዕለት ሰፊ ጸሎት የተደረገበት የጸሎት ቀን ነው። ጌታችን ሐሙስ ዕለት ወዙ እንደ ውኃና እንደ ደም ወርዶ መሬቱን ጭቃ እስኪያደርገው ድረስ መላልሶ ስለ ጸለየ ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› ተብሎ ተጠርቷል። ጌታችን የጸለየበትን ቦታም ወንጌላውያኑ በተለያየ ስያሜ ጠርተውታል፤ ማቴዎስና ማርቆስ – ‹ዐፀደ ወይን›፣ ‹ጌቴሴማኒ›፤ ሉቃስ – ‹ደብረ ዘይት›፤ ዮሐንስ – ‹ማዕዶተ ቄድሮስ›፣ ‹ፈለገ አርዝ›፣ ‹ዐፀደ ሐምል› በማለት ሰይመውታል (ማቴ.፳፮፥፴፮፤ ማር.፲፬፥፴፪፤ ሉቃ. ፳፩፥፴፯፤ ፳፪፥፴፱፤ ዮሐ. ፲፰፥፩)።
በተጨማሪም ይህ ዕለት (ሐሙስ) ያለ እርሱ ፈቃድ ሊይዙት እንደማይችሉ ለማስረዳት ጌታችን በመለኮታዊ ኃይሉ እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ካደረጋቸው በኋላ በይቅርታው ብዛት መልሶ በማስነሣት በፈቃዱ ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነው (ዮሐ. ፲፰፥፭-፰)። በዕለተ ሐሙስ ከተከናወኑ ዐበይት ተግባራት መካከል ሠራዔ ሕግ፣ ፈጻሜ ሕግ የኾነው ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕገ ኦሪትን እየፈጸመ አድጓልና በኦሪት ሥርዓት የሚፈጸመውን የመጨረሻውን በግዐ ፋሲካ (የፋሲካ በግ) ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መመገቡ አንደኛው ነው። ይሁዳ እንደሚያስይዘው ለሐዋርያት በምልክት ማስረዳቱ ሁለተኛው ሲኾን (ዮሐ. ፲፫፥፳፩)፤ እንደ አገልጋይ ራሱን ዝቅ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ደግሞ ሦስተኛው ነው።
❖ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር የማጠቡ ምሥጢር
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበ በኋላ ‹‹እናንተ መምህራችን፣ ጌታችን ትሉኛላችሁ፤ መልካም ትላላችሁ። እኔ ጌታችሁ መምህራችሁ ስኾን ዝቅ ብዬ እግራችሁን ካጠብኋችሁ እናንተም ዝቅ ብላችሁ የወንድሞቻችሁን እግር ልታጥቡ ይገባችኋል። ምሳሌ ኾኛችኋለሁና፤›› በማለት የትሕትና ሥርዓት ሠርቶ እነርሱም በሥራ እንዲገልጡት አዝዞአቸዋል (ዮሐ. ፲፫፥፲፭)። በግእዝ የተጻፈ አንድ ትርጓሜ ወንጌል ‹‹እዘርእ ፍቅረ ወትሕትና ውስተ አልባቢክሙ፤ ፍቅርንና ትሕትናን በልባችሁ እዘራለሁ፤›› እንዳላቸው ይናገራል።
ሠለስቱ ምእትም በአንቀጸ መነኮሳት ‹‹ወኢትትሐከይ ኀፂበ እግረ አኃው ሶበ መጽኡ ኀቤከ እስመ በእንተ ዛቲ ትእዛዝ ይትኀሠሥዎሙ ለእለ ያጸርዕዋ ለዛቲ ግብር ወለእመ ኮኑ ኤጲስ ቆጶሳተ እስመ እግዚአብሔር ኀፀበ እግረ አርዳኢሁ ቅድመ ወአዘዞሙ ከማሁ ይግበሩ፤ ወንድሞች ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እግራቸውን ማጠብን ቸል አትበል። ይህችን ሥራ ቸል የሚሏትን ስለዚህች ትእዛዝ ሥላሴ በፍዳ ይመረምሯቸዋልና። ኤጲስቆጶሳትም ቢኾኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቦ እንዲሁ ያደርጉ ዘንድ አዝዟቸዋልና፤›› (ሃይማኖተ አበው ፳፥፳፱፤ ፩ኛ ጢሞ. ፭፥፱-፲)።
የጌታችንን ትሕትና በተናገረበት ክፍል፣ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ‹‹የማይታዩ ረቂቃን መላእክቱ አደነቁ፤ ከልዑል ዙፋኑ ወርዶ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት ጊዜ አገልጋዮቹ መላእክት ደነገጡ። ትሕትና ወዳለበት ፍቅር የአሕዛብ እግረ ልቡናን ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ ብርሃናት ደነገጡ፤›› ይላል (ሃይማኖተ አበው ፹፰፥፰)። ፊልክስዩስም ‹‹ወኅፅበተ ፋሲካ ትትሜሰል በምሥጢረ ትሕትና ፍጽምት፤ የፋሲካ ኅፅበት ፍጹም በኾነ የትሕትና ሥራ ትመሰላለች፤›› ብሏል (መጽሐፈ መነኮሳት)።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ‹‹… ጌታችን ወደ ስምዖን ጴጥሮስ በደረሰ ጊዜ ጴጥሮስም ‹አቤቱ እግሬን የምታጥበኝ አንተ ነህን? አለው። እርሱም መልሶ ‹እኔ እግርህን ከላጠብሁህ አንተም ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም› አለው። ይህም ማለት ‹እኔ በአገልጋይ ምሳሌ እግርህን ካላጠብሁ አንተም ከበታችህ ላሉ ራስህን ዝቅ ማድረግ አትችልም። ራስህን ዝቅ ካላደረግህም የእነርሱ አለቃ መኾን አትችልም። በሰማያት ባለው መንግሥቴስ ከእኔ ጋር እንዴት አንድ ለመኾን ትችላለህ?››› በማለት ራሱ ትሑት ኾኖ ጴጥሮስን ትሑት ይኾን ዘንድ አጥብቆ እንደ መከረው ይናገራል።
በቅዱሳት መጻሕፍት መነሻነት ዘወትር በግልጥ ሲከናወን የኖረውን፤ አሁንም ባለ ማቋረጥ እየተከናወነ የሚገኘውን፤ ለወደፊትም የሚከናወነውን ቅዱስ የኾነውን የኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ሥርዓት ወደ ጐድን በመተው ግምታዊ ልማድን እየተከተለ ‹‹የሐዋርያት ጥምቀት በኅፅበተ እግር ነው፤ እኛ የዳነው በኅፅበተ እግር ነው፤›› የሚሉ ሰዎች አሉ። ቤተ ክርስቲያናችን ስታጠምቅም፣ ቅብዐ ቅዱስ ስትቀባም ከራስ ጀምራ ነው። በመጨረሻም በራስ ላይ እፍ ብላ መንፈስ ቅዱስን በማሳደር ነው እንጂ እግርን በማጠብ አጥምቃ አታውቅም።
ይኸውም ከሐዋርያት የተገኘ፤ ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣ ትውፊታዊና ቅዱስ ሥርዓት ነው እንጂ አሁን የተፈጠረ አዲስ ባህል አይደለም። ስለዚህም የጸሎተ ሐሙስ ኅፅበተ እግር ጥምቀት ሳይኾን ፍጹም ትሕትናን ሠርቶ ለማሠራት ጌታችን የፈጸመው ተግባር ነው። ይህንም ያለ ጥርጥር ልንቀበለውና ልንተገብረው ይገባል። ከዚህ ሌላ የሐዋርያት ጥምቀት አንዳንዶቹ ‹‹ተከተሉኝ›› ሲላቸው ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በበዓለ ኀምሳ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ነው ይላሉ። ይህ ዅሉ አባባል ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃነት ያልተደገፈ ግምታዊ አሳብ ነው እንጂ።
በዕለተ ሐሙስ በተከናወነው ኅፅበተ እግር ሐዋርያት እንደ ተጠመቁ የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው። ነገር ግን ይህ ኅፅበት መድኃኒታችን ክርስቶስ ወሰንና አቻ የሌለው ፍጹም ትሕትናውን የገለጠበት ምሥጢር እንጂ ጥምቀት እንዳልኾነ ብዙ መጻሕፍት ይስማማሉ። ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ መጻሕፍት በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ፍጹም ትሕትናውን ለመግለጥ እንደ ኾነ በማያሻማ ኹኔታ አረጋግጠዋል።
ሐዋርያት በዚህ ጊዜ (በኅፅበተ እግር) ተጠመቁ የሚል ግን ማኅበረ ሐዋርያት ከባስልዮስ መጽሐፍ አገኘን ብለው ከጠቀሷት አንዲቷ ጥቅስ በስተቀር ሌላ አልተገኘም። ከዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ቁም ነገር ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ አንድ ነው፤ ሃይማኖት አንዲት ናት፤ ጥምቀትም አንዲት ናት፤›› (ኤፌ. ፬፥፭) ባለው መሠረት ሠለስቱ ምእት በጉባኤ ኒቅያ በተናገሩት የሃይማኖት ጸሎት ‹‹ኀጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን›› (ሃይማኖተ አበው ፲፯፥፲፪) ከማለታቸውም ባሻገር ጥምቀት እንዳይደገም፣ እንዳይከለስ በፍትሕ መንፈሳዊ ከልክለዋል።
❖ ኅፅበተ እግር በቤተ ክርስቲያን
በየዓመቱ የሕማማት ሐሙስ በየአብያተ ክርስቲያናቱ፣ ዘወትር በየቀኑ በየገዳማቱና ትምህርት ቤቶች ለሚስተናገዱ እንግዶች ዅሉ ኅፅበተ እግር ይከናወናል። ኅፅበት ጥምቀት ነው ከተባለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠለስቱ ምእትም ኅፅበተ እግሩ ባለማቋረጥ ዅልጊዜ ሲተገበር (ሲከናወን) ሰዎች ዅሉ በየጊዜው ይጠመቃሉ ማለት ነው። ይህም ሐዋርያትና ሠለስቱ ምእት ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲፈጸም ከወሰኑ በአንድ ምላስ ሁለት ምላስ ያሰኛል። በአንዲት ቤተ ክርስቲያን የሚጣረሱ ተቃራኒ ሥርዓቶችን ማራመድ አይቻልምና። ከዚሁ ዅሉ ጋር ደግሞ የእግር መታጠብ ጥምቀት ከኾነ ጌታችን እግራቸውን አጥቦ ‹‹እንዲህ አድርጉ›› ብሎ አዞናልና አዲስ ተጠማቂዎችን አብሶም ሕፃናትን መላ አካላቸውን እያጠመቅን ለምን በቅዝቃዜ እናሰቃያቸዋለን? እግራቸውን ብቻ አጥበን ‹‹ተጠምቃችኋል›› እያልን አናሰናብታቸውም? እስኪ በማስተዋል እንመርምረው።
መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያከናወናቸው አምላካውያት ተአምራት እንዳይገለጡ ‹‹ይህን ለማንም እንዳትናገሩ፤›› እያለ አጥብቆ ይከለክል ነበር (ማቴ. ፰፥፬፤ ፱፥፴፤ ፲፮፥፳፤ ፲፯፥፲፱)። ይኸውም ገደቡ ካሣ እስከሚፈጸም እስከ ትንሣኤ ድረስ ኾኖ ከዚያ በኋላ ግን ተአምራቱ መነገር እንዳለበት ‹‹ወልደ እጓለ እመ ሕያው ክርስቶስ ከሙታን እስኪነሣ›› ብሎ ግልጽ አድርጎታል (ማቴ. ፲፯፥፲፱)። ይህንም ‹‹መከራን ከፊት አስቀምጦ፣ ደስታን፣ ክብርን መናገር ስለሚገባ ነው›› ብለው ሊቃውንቱ አትተውታል።
በዚህ አንጻር ጌታችን እስከ መስቀል ሞት ድረስ ከፊቱ ከባድ መከራ ተደግሶለት እያለ ‹‹በኅፅበተ እግር ሐዋርያትን አጠመቀ፤ ልጅነትን ሰጠ›› ማለት አያስሔድም። ምክንያቱም አንድ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን የሚያውጀው፤ ሹመት፣ ሽልማትን መስጠት የሚጀምረው ጠላቱን ድል አድርጎ መንግሥቱን ካደላደለ በኋላ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዓለሙን ያዳነውና ልጅነትን የሰጠው ዲያብሎስን በመስቀል ድል ከነሣው በኋላ ነው እንጂ በኅፅበተ እግር አይደለም።
ከኅፅበተ እግር በኋላ ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን ጌታችን እንዲህ ብሏቸዋል፤ ‹‹ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን? ዘወትር ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው። የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው፤›› (ሉቃ. ፳፪፥፶፪-፶፫)። ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበበት እና በአትክልት ቦታ ከጸለየበት ከሐሙስ ማታ እስከ ዓርብ እኩለ ቀን ድረስ ለመግለጽ እጅግ የሚከብድና የሚያሰቅቅ ሥቃይና መከራን በፈቃዱ ተቀብሏል።
ከዚህ አሰቃቂ መከራና ሞት በፊት ቅዱሳን ሐዋርያት ተጠመቁ፤ ልጅነትን አገኙ ማለት ከጋብቻ በፊት ልጅ መውለድ እንደ ማለት ከመኾኑም በላይ የዓለም ቤዛ የኾነውን የጌታችንን ሞት ከንቱ ዋጋ አልባ ማድረግ ነው። እንዴት ቢባል በክርስቶስ ክርስቲያን የተባለ በሙሉ ከሐዋርያት በተገኘ ልጅነት ነው፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በፊት በተከናወነ ኅፅበተ እግር ተጠመቁ ከተባለ ሞቱ ምንም ሥራ አልሠራም ማለት ነውና። ወገኔ ሆይ! ከዚህ በላይ እንደ ተገለጠው የዳንኸውና ልጅነትን ያገኘኸው በክርስቶስ ሞትና ደም እንጂ በእግር መታጠብ እንዳልኾነ ልታስተውል ይገባል።
____________ ___________ _____________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith | Tagged: Addis Ababa , ልደታ ማርያም , ሰሙነ ሕማማት , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , ኢየሱስ ክርስቶስ , ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት , ጸሎተ ሐሙስ , Holy Week , Jesus Christ , Passion Week , St.Mary , Tigray , War On Christianity | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2020
ከኅፅበተ እግር በኋላ ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን ጌታችን እንዲህ ብሏቸዋል፤ “ ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን ? ዘወትር ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስ ስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው፡፡ የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው፤ ” ( ሉቃ . ፳፪፥፶፪ – ፶፫ ) ።
👉 የሰሙነ ሕማማት ሐሙስ ፮ ስያሜዎች
፩ . ሕጽበተ እግር ይባላል
፪ . የጸሎት ሐሙስ ይባላል
፫ .የምስጢር ቀንም ይባላል
፬ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል
፭ . የነጻነት ሐሙስ ይባላል
፮ . አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል
👉 በጸሎተ ሐሙስ የተፈጸሙ ተግባራት
በዕለተ ሐሙስ ከተፈጸሙ ዐበይት ተግባራት አንዱ መድኃኒታችን ክርስቶስ “ ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው፤ ” ብሎ አማናዊ ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ ነው ( ማቴ . ፳፮፥፳፮ – ፳፰ ) ፡፡ እንደዚሁም ይህ ዕለት ሰፊ ጸሎት የተደረገበት የጸሎት ቀን ነው፡፡ ጌታችን ሐሙስ ዕለት ወዙ እንደ ውኃና እንደ ደም ወርዶ መሬቱን ጭቃ እስኪያደርገው ድረስ መላልሶ ስለ ጸለየ ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ጌታችን የጸለየበትን ቦታም ወንጌላውያኑ በተለያየ ስያሜ ጠርተውታል፤ ማቴዎስና ማርቆስ – ‹ዐፀደ ወይን›፣ ‹ጌቴሴማኒ›፤ ሉቃስ – ‹ደብረ ዘይት›፤ ዮሐንስ – ‹ማዕዶተ ቄድሮስ›፣ ‹ፈለገ አርዝ›፣ ‹ዐፀደ ሐምል› በማለት ሰይመውታል ( ማቴ . ፳፮፥፴፮፤ ማር . ፲፬፥፴፪፤ ሉቃ . ፳፩፥፴፯፤ ፳፪፥፴፱፤ ዮሐ . ፲፰፥፩ ) ፡፡
በተጨማሪም ይህ ዕለት ( ሐሙስ ) ያለ እርሱ ፈቃድ ሊይዙት እንደማይችሉ ለማስረዳት ጌታችን በመለኮታዊ ኃይሉ እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ካደረጋቸው በኋላ በይቅርታው ብዛት መልሶ በማስነሣት በፈቃዱ ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነው ( ዮሐ . ፲፰፥፭ – ፰ ) ፡፡ በዕለተ ሐሙስ ከተከናወኑ ዐበይት ተግባራት መካከል ሠራዔ ሕግ፣ ፈጻሜ ሕግ የኾነው ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕገ ኦሪትን እየፈጸመ አድጓልና በኦሪት ሥርዓት የሚፈጸመውን የመጨረሻውን በግዐ ፋሲካ ( የፋሲካ በግ ) ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መመገቡ አንደኛው ነው፡፡ ይሁዳ እንደሚያስይዘው ለሐዋርያት በምልክት ማስረዳቱ ሁለተኛው ሲኾን ( ዮሐ . ፲፫፥፳፩ ) ፤ እንደ አገልጋይ ራሱን ዝቅ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ደግሞ ሦስተኛው ነው፡፡
👉 ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር የማጠቡ ምሥጢር
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበ በኋላ “ እናንተ መምህራችን፣ ጌታችን ትሉኛላችሁ፤ መልካም ትላላችሁ፡፡ እኔ ጌታችሁ መምህራችሁ ስኾን ዝቅ ብዬ እግራችሁን ካጠብኋችሁ እናንተም ዝቅ ብላችሁ የወንድሞቻችሁን እግር ልታጥቡ ይገባችኋል፡፡ ምሳሌ ኾኛችኋለሁና፤ ” በማለት የትሕትና ሥርዓት ሠርቶ እነርሱም በሥራ እንዲገልጡት አዝዞአቸዋል ( ዮሐ . ፲፫፥፲፭ ) ፡፡ በግእዝ የተጻፈ አንድ ትርጓሜ ወንጌል “ እዘርእ ፍቅረ ወትሕትና ውስተ አልባቢክሙ፤ ፍቅርንና ትሕትናን በልባችሁ እዘራለሁ፤ ” እንዳላቸው ይናገራል፡፡
ሠለስቱ ምእትም በአንቀጸ መነኮሳት “ ወኢትትሐከይ ኀፂበ እግረ አኃው ሶበ መጽኡ ኀቤከ እስመ በእንተ ዛቲ ትእዛዝ ይትኀሠሥዎሙ ለእለ ያጸርዕዋ ለዛቲ ግብር ወለእመ ኮኑ ኤጲስ ቆጶሳተ እስመ እግዚአብሔር ኀፀበ እግረ አርዳኢሁ ቅድመ ወአዘዞሙ ከማሁ ይግበሩ፤ ወንድሞች ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እግራቸውን ማጠብን ቸል አትበል፡፡ ይህችን ሥራ ቸል የሚሏትን ስለዚህች ትእዛዝ በፍዳ ይመረምሯቸዋልና፡፡ ኤጲስቆጶሳትም ቢኾኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቦ እንዲሁ ያደርጉ ዘንድ አዝዟቸዋልና፤ ” ( ሃይማኖተ አበው ፳፥፳፱፤ ፩ኛ ጢሞ . ፭፥፱ – ፲ ) ፡፡
የጌታችንን ትሕትና በተናገረበት ክፍል፣ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ “ የማይታዩ ረቂቃን መላእክቱ አደነቁ፤ ከልዑል ዙፋኑ ወርዶ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት ጊዜ አገልጋዮቹ መላእክት ደነገጡ፡፡ ትሕትና ወዳለበት ፍቅር የአሕዛብ እግረ ልቡናን ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ ብርሃናት ደነገጡ፤ ” ይላል ( ሃይማኖተ አበው ፹፰፥፰ ) ፡፡ ፊልክስዩስም “ ወኅፅበተ ፋሲካ ትትሜሰል በምሥጢረ ትሕትና ፍጽምት፤ የፋሲካ ኅፅበት ፍጹም በኾነ የትሕትና ሥራ ትመሰላለች፤ ” ብሏል ( መጽሐፈ መነኮሳት ) ፡፡
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር “… ጌታችን ወደ ስምዖን ጴጥሮስ በደረሰ ጊዜ ጴጥሮስም ‹አቤቱ እግሬን የምታጥበኝ አንተ ነህን ? አለው፡፡ እርሱም መልሶ ‹እኔ እግርህን ከላጠብሁህ አንተም ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም› አለው፡፡ ይህም ማለት ‹እኔ በአገልጋይ ምሳሌ እግርህን ካላጠብሁ አንተም ከበታችህ ላሉ ራስህን ዝቅ ማድረግ አትችልም፡፡ ራስህን ዝቅ ካላደረግህም የእነርሱ አለቃ መኾን አትችልም፡፡ በሰማያት ባለው መንግሥቴስ ከእኔ ጋር እንዴት አንድ ለመኾን ትችላለህ ?”› በማለት ራሱ ትሑት ኾኖ ጴጥሮስን ትሑት ይኾን ዘንድ አጥብቆ እንደ መከረው ይናገራል፡፡
በቅዱሳት መጻሕፍት መነሻነት ዘወትር በግልጥ ሲከናወን የኖረውን፤ አሁንም ባለ ማቋረጥ እየተከናወነ የሚገኘውን፤ ለወደፊትም የሚከናወነውን ቅዱስ የኾነውን የኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ሥርዓት ወደ ጐድን በመተው ግምታዊ ልማድን እየተከተለ “ የሐዋርያት ጥምቀት በኅፅበተ እግር ነው፤ እኛ የዳነው በኅፅበተ እግር ነው፤ ” የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ስታጠምቅም፣ ቅብዐ ቅዱስ ስትቀባም ከራስ ጀምራ ነው፡፡ በመጨረሻም በራስ ላይ እፍ ብላ መንፈስ ቅዱስን በማሳደር ነው እንጂ እግርን በማጠብ አጥምቃ አታውቅም፡፡
ይኸውም ከሐዋርያት የተገኘ፤ ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣ ትውፊታዊና ቅዱስ ሥርዓት ነው እንጂ አሁን የተፈጠረ አዲስ ባህል አይደለም፡፡ ስለዚህም የጸሎተ ሐሙስ ኅፅበተ እግር ጥምቀት ሳይኾን ፍጹም ትሕትናን ሠርቶ ለማሠራት ጌታችን የፈጸመው ተግባር ነው፡፡ ይህንም ያለ ጥርጥር ልንቀበለውና ልንተገብረው ይገባል፡፡ ከዚህ ሌላ የሐዋርያት ጥምቀት አንዳንዶቹ “ ተከተሉኝ ” ሲላቸው ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በበዓለ ኀምሳ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ነው ይላሉ፡፡ ይህ ዅሉ አባባል ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃነት ያልተደገፈ ግምታዊ አሳብ ነው እንጂ፡፡
በዕለተ ሐሙስ በተከናወነው ኅፅበተ እግር ሐዋርያት እንደ ተጠመቁ የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ኅፅበት መድኃኒታችን ክርስቶስ ወሰንና አቻ የሌለው ፍጹም ትሕትናውን የገለጠበት ምሥጢር እንጂ ጥምቀት እንዳልኾነ ብዙ መጻሕፍት ይስማማሉ፡፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ መጻሕፍት በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ፍጹም ትሕትናውን ለመግለጥ እንደ ኾነ በማያሻማ ኹኔታ አረጋግጠዋል፡፡
ሐዋርያት በዚህ ጊዜ ( በኅፅበተ እግር ) ተጠመቁ የሚል ግን ማኅበረ ሐዋርያት ከባስልዮስ መጽሐፍ አገኘን ብለው ከጠቀሷት አንዲቷ ጥቅስ በስተቀር ሌላ አልተገኘም፡፡ ከዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ቁም ነገር ቅዱስ ጳውሎስ “ ጌታ አንድ ነው፤ ሐይማኖት አንዲት ናት፤ ጥምቀትም አንዲት ናት፤ ” ( ኤፌ . ፬፥፭ ) ባለው መሠረት ሠለስቱ ምእት በጉባኤ ኒቅያ በተናገሩት የሐይማኖት ጸሎት “ ኀጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን ” ( ሃይማኖተ አበው ፲፯፥፲፪ ) ከማለታቸውም ባሻገር ጥምቀት እንዳይደገም፣ እንዳይከለስ በፍትሕ መንፈሳዊ ከልክለዋል፡፡
👉 ኅፅበተ እግር በቤተ ክርስቲያን
በየዓመቱ የሕማማት ሐሙስ በየአብያተ ክርስቲያናቱ፣ ዘወትር በየቀኑ በየገዳማቱና ትምህርት ቤቶች ለሚስተናገዱ እንግዶች ዅሉ ኅፅበተ እግር ይከናወናል፡፡ ኅፅበት ጥምቀት ነው ከተባለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠለስቱ ምእትም ኅፅበተ እግሩ ባለማቋረጥ ዅልጊዜ ሲተገበር ( ሲከናወን ) ሰዎች ዅሉ በየጊዜው ይጠመቃሉ ማለት ነው፡፡ ይህም ሐዋርያትና ሠለስቱ ምእት ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲፈጸም ከወሰኑ በአንድ ምላስ ሁለት ምላስ ያሰኛል፡፡ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን የሚጣረሱ ተቃራኒ ሥርዓቶችን ማራመድ አይቻልምና፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋር ደግሞ የእግር መታጠብ ጥምቀት ከኾነ ጌታችን እግራቸውን አጥቦ “ እንዲህ አድርጉ ” ብሎ አዞናልና አዲስ ተጠማቂዎችን አብሶም ሕፃናትን መላ አካላቸውን እያጠመቅን ለምን በቅዝቃዜ እናሰቃያቸዋለን ? እግራቸውን ብቻ አጥበን “ ተጠምቃችኋል ” እያልን አናሰናብታቸውም ? እስኪ በማስተዋል እንመርምረው፡፡
መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያከናወናቸው አምላካውያት ተአምራት እንዳይገለጡ “ ይህን ለማንም እንዳትናገሩ፤ ” እያለ አጥብቆ ይከለክል ነበር ( ማቴ . ፰፥፬፤ ፱፥፴፤ ፲፮፥፳፤ ፲፯፥፲፱ ) ፡፡ ይኸውም ገደቡ ካሣ እስከሚፈጸም እስከ ትንሣኤ ድረስ ኾኖ ከዚያ በኋላ ግን ተአምራቱ መነገር እንዳለበት “ ወልደ እጓለ እመ ሕያው ክርስቶስ ከሙታን እስኪነሣ ” ብሎ ግልጽ አድርጎታል ( ማቴ . ፲፯፥፲፱ ) ፡፡ ይህንም “ መከራን ከፊት አስቀምጦ፣ ደስታን፣ ክብርን መናገር ስለሚገባ ነው ” ብለው ሊቃውንቱ አትተውታል፡፡
በዚህ አንጻር ጌታችን እስከ መስቀል ሞት ድረስ ከፊቱ ከባድ መከራ ተደግሶለት እያለ “ በኅፅበተ እግር ሐዋርያትን አጠመቀ፤ ልጅነትን ሰጠ ” ማለት አያስሔድም፡፡ ምክንያቱም አንድ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን የሚያውጀው፤ ሹመት፣ ሽልማትን መስጠት የሚጀምረው ጠላቱን ድል አድርጎ መንግሥቱን ካደላደለ በኋላ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዓለሙን ያዳነውና ልጅነትን የሰጠው ዲያብሎስን በመስቀል ድል ከነሣው በኋላ ነው እንጂ በኅፅበተ እግር አይደለም፡፡
ከኅፅበተ እግር በኋላ ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን ጌታችን እንዲህ ብሏቸዋል፤ “ ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን ? ዘወትር ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስ ስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው፡፡ የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው፤ ” ( ሉቃ . ፳፪፥፶፪ – ፶፫ ) ፡፡ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበበት እና በአትክልት ቦታ ከጸለየበት ከሐሙስ ማታ እስከ ዓርብ እኩለ ቀን ድረስ ለመግለጽ እጅግ የሚከብድና የሚያሰቅቅ ሥቃይና መከራን በፈቃዱ ተቀብሏል፡፡
ከዚህ አሰቃቂ መከራና ሞት በፊት ቅዱሳን ሐዋርያት ተጠመቁ፤ ልጅነትን አገኙ ማለት ከጋብቻ በፊት ልጅ መውለድ እንደ ማለት ከመኾኑም በላይ የዓለም ቤዛ የኾነውን የጌታችንን ሞት ከንቱ ዋጋ አልባ ማድረግ ነው፡፡ እንዴት ቢባል በክርስቶስ ክርስቲያን የተባለ በሙሉ ከሐዋርያት በተገኘ ልጅነት ነው፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በፊት በተከናወነ ኅፅበተ እግር ተጠመቁ ከተባለ ሞቱ ምንም ሥራ አልሠራም ማለት ነውና፡፡ ወገኔ ሆይ ! ከዚህ በላይ እንደ ተገለጠው የዳንኸውና ልጅነትን ያገኘኸው በክርስቶስ ሞትና ደም እንጂ በእግር መታጠብ እንዳልኾነ ልታስተውል ይገባል፡፡
__________ _________________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith | Tagged: ልደታ ማርያም , ሰሙነ ሕማማት , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , ኢየሱስ ክርስቶስ , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት , ጸሎተ ሐሙስ , Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith , Holy Week , Jesus Christ , Passion Week | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 24, 2019
VIDEO
በጸሎተ ሐሙስ የተፈጸሙ ተግባራት
በዕለተ ሐሙስ ከተፈጸሙ ዐበይት ተግባራት አንዱ መድኃኒታችን ክርስቶስ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው፤›› ብሎ አማናዊ ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ ነው ( ማቴ . ፳፮፥፳፮ – ፳፰ ) ፡፡ እንደዚሁም ይህ ዕለት ሰፊ ጸሎት የተደረገበት የጸሎት ቀን ነው፡፡ ጌታችን ሐሙስ ዕለት ወዙ እንደ ውኃና እንደ ደም ወርዶ መሬቱን ጭቃ እስኪያደርገው ድረስ መላልሶ ስለ ጸለየ ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ጌታችን የጸለየበትን ቦታም ወንጌላውያኑ በተለያየ ስያሜ ጠርተውታል፤ ማቴዎስና ማርቆስ – ‹ዐፀደ ወይን›፣ ‹ጌቴሴማኒ›፤ ሉቃስ – ‹ደብረ ዘይት›፤ ዮሐንስ – ‹ማዕዶተ ቄድሮስ›፣ ‹ፈለገ አርዝ›፣ ‹ዐፀደ ሐምል› በማለት ሰይመውታል ( ማቴ . ፳፮፥፴፮፤ ማር . ፲፬፥፴፪፤ ሉቃ . ፳፩፥፴፯፤ ፳፪፥፴፱፤ ዮሐ . ፲፰፥፩ ) ፡፡
በተጨማሪም ይህ ዕለት ( ሐሙስ ) ያለ እርሱ ፈቃድ ሊይዙት እንደማይችሉ ለማስረዳት ጌታችን በመለኮታዊ ኃይሉ እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ካደረጋቸው በኋላ በይቅርታው ብዛት መልሶ በማስነሣት በፈቃዱ ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነው ( ዮሐ . ፲፰፥፭ – ፰ ) ፡፡ በዕለተ ሐሙስ ከተከናወኑ ዐበይት ተግባራት መካከል ሠራዔ ሕግ፣ ፈጻሜ ሕግ የኾነው ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕገ ኦሪትን እየፈጸመ አድጓልና በኦሪት ሥርዓት የሚፈጸመውን የመጨረሻውን በግዐ ፋሲካ ( የፋሲካ በግ ) ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መመገቡ አንደኛው ነው፡፡ ይሁዳ እንደሚያስይዘው ለሐዋርያት በምልክት ማስረዳቱ ሁለተኛው ሲኾን ( ዮሐ . ፲፫፥፳፩ ) ፤ እንደ አገልጋይ ራሱን ዝቅ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ደግሞ ሦስተኛው ነው፡፡
_______ ______________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith | Tagged: ልደታ ማርያም , ሰሙነ ሕማማት , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , ኢየሱስ ክርስቶስ , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት , ጸሎተ ሐሙስ , Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith , Holy Week , Jesus Christ , Passion Week | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 4, 2018
VIDEO
በጸሎተ ሐሙስ የተፈጸሙ ተግባራት
በዕለተ ሐሙስ ከተፈጸሙ ዐበይት ተግባራት አንዱ መድኃኒታችን ክርስቶስ ‹‹ይህ ሥጋዬ ነው፤ ይህ ደሜ ነው፤›› ብሎ አማናዊ ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ ነው ( ማቴ . ፳፮፥፳፮ – ፳፰ ) ፡፡ እንደዚሁም ይህ ዕለት ሰፊ ጸሎት የተደረገበት የጸሎት ቀን ነው፡፡ ጌታችን ሐሙስ ዕለት ወዙ እንደ ውኃና እንደ ደም ወርዶ መሬቱን ጭቃ እስኪያደርገው ድረስ መላልሶ ስለ ጸለየ ዕለቱ ‹ጸሎተ ሐሙስ› ተብሎ ተጠርቷል፡፡ ጌታችን የጸለየበትን ቦታም ወንጌላውያኑ በተለያየ ስያሜ ጠርተውታል፤ ማቴዎስና ማርቆስ – ‹ዐፀደ ወይን›፣ ‹ጌቴሴማኒ›፤ ሉቃስ – ‹ደብረ ዘይት›፤ ዮሐንስ – ‹ማዕዶተ ቄድሮስ›፣ ‹ፈለገ አርዝ›፣ ‹ዐፀደ ሐምል› በማለት ሰይመውታል ( ማቴ . ፳፮፥፴፮፤ ማር . ፲፬፥፴፪፤ ሉቃ . ፳፩፥፴፯፤ ፳፪፥፴፱፤ ዮሐ . ፲፰፥፩ ) ፡፡
በተጨማሪም ይህ ዕለት ( ሐሙስ ) ያለ እርሱ ፈቃድ ሊይዙት እንደማይችሉ ለማስረዳት ጌታችን በመለኮታዊ ኃይሉ እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ካደረጋቸው በኋላ በይቅርታው ብዛት መልሶ በማስነሣት በፈቃዱ ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠበት ዕለት ነው ( ዮሐ . ፲፰፥፭ – ፰ ) ፡፡ በዕለተ ሐሙስ ከተከናወኑ ዐበይት ተግባራት መካከል ሠራዔ ሕግ፣ ፈጻሜ ሕግ የኾነው ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕገ ኦሪትን እየፈጸመ አድጓልና በኦሪት ሥርዓት የሚፈጸመውን የመጨረሻውን በግዐ ፋሲካ ( የፋሲካ በግ ) ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መመገቡ አንደኛው ነው፡፡ ይሁዳ እንደሚያስይዘው ለሐዋርያት በምልክት ማስረዳቱ ሁለተኛው ሲኾን ( ዮሐ . ፲፫፥፳፩ ) ፤ እንደ አገልጋይ ራሱን ዝቅ አድርጎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ደግሞ ሦስተኛው ነው፡፡
ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር የማጠቡ ምሥጢር
ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበ በኋላ ‹‹እናንተ መምህራችን፣ ጌታችን ትሉኛላችሁ፤ መልካም ትላላችሁ፡፡ እኔ ጌታችሁ መምህራችሁ ስኾን ዝቅ ብዬ እግራችሁን ካጠብኋችሁ እናንተም ዝቅ ብላችሁ የወንድሞቻችሁን እግር ልታጥቡ ይገባችኋል፡፡ ምሳሌ ኾኛችኋለሁና፤›› በማለት የትሕትና ሥርዓት ሠርቶ እነርሱም በሥራ እንዲገልጡት አዝዞአቸዋል ( ዮሐ . ፲፫፥፲፭ ) ፡፡ በግእዝ የተጻፈ አንድ ትርጓሜ ወንጌል ‹‹እዘርእ ፍቅረ ወትሕትና ውስተ አልባቢክሙ፤ ፍቅርንና ትሕትናን በልባችሁ እዘራለሁ፤›› እንዳላቸው ይናገራል፡፡
ሠለስቱ ምእትም በአንቀጸ መነኮሳት ‹‹ወኢትትሐከይ ኀፂበ እግረ አኃው ሶበ መጽኡ ኀቤከ እስመ በእንተ ዛቲ ትእዛዝ ይትኀሠሥዎሙ ለእለ ያጸርዕዋ ለዛቲ ግብር ወለእመ ኮኑ ኤጲስ ቆጶሳተ እስመ እግዚአብሔር ኀፀበ እግረ አርዳኢሁ ቅድመ ወአዘዞሙ ከማሁ ይግበሩ፤ ወንድሞች ወደ አንተ በመጡ ጊዜ እግራቸውን ማጠብን ቸል አትበል፡፡ ይህችን ሥራ ቸል የሚሏትን ስለዚህች ትእዛዝ ሥላሴ በፍዳ ይመረምሯቸዋልና፡፡ ኤጲስቆጶሳትም ቢኾኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቦ እንዲሁ ያደርጉ ዘንድ አዝዟቸዋልና፤›› ( ሃይማኖተ አበው ፳፥፳፱፤ ፩ኛ ጢሞ . ፭፥፱ – ፲ ) ፡፡
የጌታችንን ትሕትና በተናገረበት ክፍል፣ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግ ‹‹የማይታዩ ረቂቃን መላእክቱ አደነቁ፤ ከልዑል ዙፋኑ ወርዶ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያገለግል ባዩት ጊዜ አገልጋዮቹ መላእክት ደነገጡ፡፡ ትሕትና ወዳለበት ፍቅር የአሕዛብ እግረ ልቡናን ያቀና ዘንድ ግሩም እሳት በትሕትና መገለጡን ባዩ ጊዜ ብርሃናት ደነገጡ፤›› ይላል ( ሃይማኖተ አበው ፹፰፥፰ ) ፡፡ ፊልክስዩስም ‹‹ወኅፅበተ ፋሲካ ትትሜሰል በምሥጢረ ትሕትና ፍጽምት፤ የፋሲካ ኅፅበት ፍጹም በኾነ የትሕትና ሥራ ትመሰላለች፤›› ብሏል ( መጽሐፈ መነኮሳት ) ፡፡
አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ‹‹… ጌታችን ወደ ስምዖን ጴጥሮስ በደረሰ ጊዜ ጴጥሮስም ‹አቤቱ እግሬን የምታጥበኝ አንተ ነህን ? አለው፡፡ እርሱም መልሶ ‹እኔ እግርህን ከላጠብሁህ አንተም ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ የለህም› አለው፡፡ ይህም ማለት ‹እኔ በአገልጋይ ምሳሌ እግርህን ካላጠብሁ አንተም ከበታችህ ላሉ ራስህን ዝቅ ማድረግ አትችልም፡፡ ራስህን ዝቅ ካላደረግህም የእነርሱ አለቃ መኾን አትችልም፡፡ በሰማያት ባለው መንግሥቴስ ከእኔ ጋር እንዴት አንድ ለመኾን ትችላለህ ?››› በማለት ራሱ ትሑት ኾኖ ጴጥሮስን ትሑት ይኾን ዘንድ አጥብቆ እንደ መከረው ይናገራል፡፡
በቅዱሳት መጻሕፍት መነሻነት ዘወትር በግልጥ ሲከናወን የኖረውን፤ አሁንም ባለ ማቋረጥ እየተከናወነ የሚገኘውን፤ ለወደፊትም የሚከናወነውን ቅዱስ የኾነውን የኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ሥርዓት ወደ ጐድን በመተው ግምታዊ ልማድን እየተከተለ ‹‹የሐዋርያት ጥምቀት በኅፅበተ እግር ነው፤ እኛ የዳነው በኅፅበተ እግር ነው፤›› የሚሉ ሰዎች አሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ስታጠምቅም፣ ቅብዐ ቅዱስ ስትቀባም ከራስ ጀምራ ነው፡፡ በመጨረሻም በራስ ላይ እፍ ብላ መንፈስ ቅዱስን በማሳደር ነው እንጂ እግርን በማጠብ አጥምቃ አታውቅም፡፡
ይኸውም ከሐዋርያት የተገኘ፤ ከሐዋርያት ሲያያዝ የመጣ ትውፊታዊና ቅዱስ ሥርዓት ነው እንጂ አሁን የተፈጠረ አዲስ ባህል አይደለም፡፡ ስለዚህም የጸሎተ ሐሙስ ኅፅበተ እግር ጥምቀት ሳይኾን ፍጹም ትሕትናን ሠርቶ ለማሠራት ጌታችን የፈጸመው ተግባር ነው፡፡ ይህንም ያለ ጥርጥር ልንቀበለውና ልንተገብረው ይገባል፡፡ ከዚህ ሌላ የሐዋርያት ጥምቀት አንዳንዶቹ ‹‹ተከተሉኝ›› ሲላቸው ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ በበዓለ ኀምሳ መንፈስ ቅዱስ በወረደላቸው ጊዜ ነው ይላሉ፡፡ ይህ ዅሉ አባባል ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃነት ያልተደገፈ ግምታዊ አሳብ ነው እንጂ፡፡
በዕለተ ሐሙስ በተከናወነው ኅፅበተ እግር ሐዋርያት እንደ ተጠመቁ የሚናገሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ኅፅበት መድኃኒታችን ክርስቶስ ወሰንና አቻ የሌለው ፍጹም ትሕትናውን የገለጠበት ምሥጢር እንጂ ጥምቀት እንዳልኾነ ብዙ መጻሕፍት ይስማማሉ፡፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ መጻሕፍት በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ ፍጹም ትሕትናውን ለመግለጥ እንደ ኾነ በማያሻማ ኹኔታ አረጋግጠዋል፡፡
ሐዋርያት በዚህ ጊዜ ( በኅፅበተ እግር ) ተጠመቁ የሚል ግን ማኅበረ ሐዋርያት ከባስልዮስ መጽሐፍ አገኘን ብለው ከጠቀሷት አንዲቷ ጥቅስ በስተቀር ሌላ አልተገኘም፡፡ ከዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ቁም ነገር ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ አንድ ነው፤ ሃይማኖት አንዲት ናት፤ ጥምቀትም አንዲት ናት፤›› ( ኤፌ . ፬፥፭ ) ባለው መሠረት ሠለስቱ ምእት በጉባኤ ኒቅያ በተናገሩት የሃይማኖት ጸሎት ‹‹ኀጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን›› ( ሃይማኖተ አበው ፲፯፥፲፪ ) ከማለታቸውም ባሻገር ጥምቀት እንዳይደገም፣ እንዳይከለስ በፍትሕ መንፈሳዊ ከልክለዋል፡፡
ኅፅበተ እግር በቤተ ክርስቲያን
በየዓመቱ የሕማማት ሐሙስ በየአብያተ ክርስቲያናቱ፣ ዘወትር በየቀኑ በየገዳማቱና ትምህርት ቤቶች ለሚስተናገዱ እንግዶች ዅሉ ኅፅበተ እግር ይከናወናል፡፡ ኅፅበት ጥምቀት ነው ከተባለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሠለስቱ ምእትም ኅፅበተ እግሩ ባለማቋረጥ ዅልጊዜ ሲተገበር ( ሲከናወን ) ሰዎች ዅሉ በየጊዜው ይጠመቃሉ ማለት ነው፡፡ ይህም ሐዋርያትና ሠለስቱ ምእት ጥምቀት አንድ ጊዜ ብቻ እንዲፈጸም ከወሰኑ በአንድ ምላስ ሁለት ምላስ ያሰኛል፡፡ በአንዲት ቤተ ክርስቲያን የሚጣረሱ ተቃራኒ ሥርዓቶችን ማራመድ አይቻልምና፡፡ ከዚሁ ዅሉ ጋር ደግሞ የእግር መታጠብ ጥምቀት ከኾነ ጌታችን እግራቸውን አጥቦ ‹‹እንዲህ አድርጉ›› ብሎ አዞናልና አዲስ ተጠማቂዎችን አብሶም ሕፃናትን መላ አካላቸውን እያጠመቅን ለምን በቅዝቃዜ እናሰቃያቸዋለን ? እግራቸውን ብቻ አጥበን ‹‹ተጠምቃችኋል›› እያልን አናሰናብታቸውም ? እስኪ በማስተዋል እንመርምረው፡፡
መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ያከናወናቸው አምላካውያት ተአምራት እንዳይገለጡ ‹‹ይህን ለማንም እንዳትናገሩ፤›› እያለ አጥብቆ ይከለክል ነበር ( ማቴ . ፰፥፬፤ ፱፥፴፤ ፲፮፥፳፤ ፲፯፥፲፱ ) ፡፡ ይኸውም ገደቡ ካሣ እስከሚፈጸም እስከ ትንሣኤ ድረስ ኾኖ ከዚያ በኋላ ግን ተአምራቱ መነገር እንዳለበት ‹‹ወልደ እጓለ እመ ሕያው ክርስቶስ ከሙታን እስኪነሣ›› ብሎ ግልጽ አድርጎታል ( ማቴ . ፲፯፥፲፱ ) ፡፡ ይህንም ‹‹መከራን ከፊት አስቀምጦ፣ ደስታን፣ ክብርን መናገር ስለሚገባ ነው›› ብለው ሊቃውንቱ አትተውታል፡፡
በዚህ አንጻር ጌታችን እስከ መስቀል ሞት ድረስ ከፊቱ ከባድ መከራ ተደግሶለት እያለ ‹‹በኅፅበተ እግር ሐዋርያትን አጠመቀ፤ ልጅነትን ሰጠ›› ማለት አያስሔድም፡፡ ምክንያቱም አንድ መንግሥት ሕገ መንግሥቱን የሚያውጀው፤ ሹመት፣ ሽልማትን መስጠት የሚጀምረው ጠላቱን ድል አድርጎ መንግሥቱን ካደላደለ በኋላ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዓለሙን ያዳነውና ልጅነትን የሰጠው ዲያብሎስን በመስቀል ድል ከነሣው በኋላ ነው እንጂ በኅፅበተ እግር አይደለም፡፡
ከኅፅበተ እግር በኋላ ሊይዙት ወደ እርሱ የመጡትን የካህናት አለቆችን፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችንና ሽማግሌዎችን ጌታችን እንዲህ ብሏቸዋል፤ ‹‹ሌባን እንደምትይዙ በሰይፍና በጎመድ ልትይዙኝ መጣችሁን ? ዘወትር ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው፡፡ የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው፤›› ( ሉቃ . ፳፪፥፶፪ – ፶፫ ) ፡፡ ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበበት እና በአትክልት ቦታ ከጸለየበት ከሐሙስ ማታ እስከ ዓርብ እኩለ ቀን ድረስ ለመግለጽ እጅግ የሚከብድና የሚያሰቅቅ ሥቃይና መከራን በፈቃዱ ተቀብሏል፡፡
ከዚህ አሰቃቂ መከራና ሞት በፊት ቅዱሳን ሐዋርያት ተጠመቁ፤ ልጅነትን አገኙ ማለት ከጋብቻ በፊት ልጅ መውለድ እንደ ማለት ከመኾኑም በላይ የዓለም ቤዛ የኾነውን የጌታችንን ሞት ከንቱ ዋጋ አልባ ማድረግ ነው፡፡ እንዴት ቢባል በክርስቶስ ክርስቲያን የተባለ በሙሉ ከሐዋርያት በተገኘ ልጅነት ነው፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሞት በፊት በተከናወነ ኅፅበተ እግር ተጠመቁ ከተባለ ሞቱ ምንም ሥራ አልሠራም ማለት ነውና፡፡ ወገኔ ሆይ ! ከዚህ በላይ እንደ ተገለጠው የዳንኸውና ልጅነትን ያገኘኸው በክርስቶስ ሞትና ደም እንጂ በእግር መታጠብ እንዳልኾነ ልታስተውል ይገባል፡፡
ምንጭ
__ ____
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith | Tagged: ልደታ ማርያም , ሰሙነ ሕማማት , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , ኢየሱስ ክርስቶስ , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት , የካ ቅ/ሚካኤል , ጸሎተ ሐሙስ , Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith , Holy Week , Jesus Christ , Passion Week | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 13, 2017
ሚያዝያ ፬ ቀን ፳፻፱ ዓ . ም
ጸሎተ ሐሙስ በብሉይ ኪዳን
VIDEO
ጸሎተ ሐሙስ በብሉይ ኪዳን ለፋሲካ ዝግጅት ተደርጎበታል ( ማቴ . ፳፮፥፯ – ፲፫ ) ፡፡ ‹ፋሲካ› ማለት ማለፍ ማለት ነው፡፡ ይኸውም እስራኤላውያን በግብጽ ምድር ሳሉ መልአኩን ልኮ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የበግ ጠቦት እንዲያርድና ደሙን በበሩ ወይም በመቃኑ እንዲቀባ ለሙሴ ነገረው፡፡ ሙሴም የታዘዘውን ለሕዝቡ ነገረ፤ ዅሉም እንደ ታዘዙት ፈጸሙ፡፡ በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ መቅሠፍት ታዞ መልአኩ የደም ምልክት የሌለበትን የግብጻውያንን ቤት በሞተ በኵር ሲመታ፤ የበጉ ደም ምልክት ያለበትን የእስራኤላውያንን ቤት ምልክቱን እያየ አልፏል፡፡ ፋሲካ መባሉም ይህን ምሥጢር ለማስታወስ ነው ( ዘፀ . ፲፪፥፩ – ፳ ) ፡፡
በዚህ መነሻነት በየዓመቱ እስራኤላውያን በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በግ እያረዱ የፋሲካን በዓል ያከብራሉ፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም አስቀድማ ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች አገር እንደ መኾኗ ይህን ሥርዓት ትፈጽም ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳንም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ‹ፋሲካ› ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ጌታችን በዚህ በፋሲካ በዓል ራሱን የተወደደ ምሥዋዕት አድርጎ ደሙን ስላፈሰሰልን ነው፡፡ በደሙ መፍሰስም ሞተ በኵር የተባለ ሞተ ነፍስ ርቆልናል፡፡ ስለዚህም ክርስቶስን ‹ፋሲካችን› እንለዋን ( ፩ኛ ቆሮ . ፭፥፯፤ ፩ኛ ጴጥ . ፩፥፲፰ – ፲፱ ) ፡፡
የጸሎተ ሐሙስ ስያሜዎች
VIDEO
ጸሎተ ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን በርካታ ስያሜዎች አሉት፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን ነውና ‹ጸሎተ ሐሙስ› ይባላል ( ማቴ . ፳፮፥፴፮ – ፶፮ ) ፡፡ ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዅሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ የንጽሕና፣ የቅድስና አምላክ መኾኑን ያጠይቃል፡፡ ስለዚህም ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› ይባላል፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ሊቃነ ጳጳሳትና ቀሳውስት ‹‹ በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ፤ እኛም የአንተን አርአያነት ተከትለን የልጆቻችንን እግር እናጥባለን፤›› ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙ ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡
ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምሥጢረ ቍርባን በዚህ ቀን ተመሥርቷልና ዕለቱ ‹የምሥጢር ቀን› ይባላል፡፡ ይኸውም ጌታችን ኅብስቱንና ጽዋውን አንሥቶ ‹‹ ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ፤ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፤›› በማለት እርሱ ከእኛ፤ እኛም ከእርሱ ጋር አንድ የምንኾንበትን ምሥጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመኾኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የኾነ ዅሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡
መድኃኒታችን ክርስቶስ መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመኾኑ ይህ ዕለት ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ይባላል ( ሉቃ . ፳፪፥፳ ) ፡፡ ‹ኪዳን› ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ዅሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለ ኾነ ሐሙስ ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ተባለ፡፡
ይህ ዕለት ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ኾኖ መኖር ማብቃቱ የተገለጠበት፤ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለ ኾነ ‹የነጻነት ሐሙስ› ይባላል፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ‹‹ ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፡፡ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤›› በማለት ከባርነት የወጣንበትን፤ ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመኾኑ ሊቃውንቱ ‹የነጻነት ሐሙስ› አሉት ( ዮሐ . ፲፭፥፲፭ ) ፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች ሳይኾን ወዳጆች ተብለን በክርስቶስ ተጠርተናልና፡፡
በዚህ ዕለት እንደ ማክሰኞ ዅሉ ጌታችን በዮሐንስ ወንጌል ፲፬፥፲፮ የሚገኘውን ሰፊ ትምህርት ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡ የትምህርቱም ዋና ዋና ክፍሎችም ምሥጢረ ሥላሴን፣ ምሥጢረ ሥጋዌንና ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታንን ያካትታሉ፡፡ ጌታችን እነዚህን ትምህርቶች በስፋትና በጥልቀት መማር እንደሚገባ ሲያስረዳ፣ ለደቀ መዛርቱ ምሥጢሩን በተአምራት ሊገልጥላቸው ሲቻለው በሰፊ ማብራርያ እንዲረዱት አድርጓል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ያልገባቸውንም እየጠየቁ ተረድተዋል፡፡ ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን መማርና ያልገባንን ጠይቀን መረዳት እንደሚገባን ከዚህ እንማራለን፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠውም በዚሁ ዕለት ከምሽቱ በሦስት ሰዓት ነው ( ማቴ . ፳፮፥፵፯ – ፶፰ ) ፡፡
በጸሎተ ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸም ሥርዓት
VIDEO
በዚህ ዕለት ስግደቱ፣ ጸሎቱ፣ ምንባባቱ እንደ ተለመደው ይከናወናሉ፡፡ መንበሩ ( ታቦቱ ) ጥቁር ልብስ ይለብሳል፡፡ ጸሎተ ዕጣን ይጸለያል፤ ቤተ ክርስቲያኑም በማዕጠንት ይታጠናል፡፡ ሕጽበተ እግር ይደረጋል፡፡ ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ በየቤቱ ደግሞ ጉልባን ይዘጋጃል፡፡
ሕጽበተ እግር
ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ዲያቆኑ ሁለት ኵስኵስቶችን ውኃ ሞልቶ ያቀርባል፤ አንዱ ለእግር፣ አንዱ ለእጅ መታጠቢያ፡፡ ‹ጸሎተ አኰቴት› በመባል የሚታወቀው የጸሎት ዓይነት ይጸለያል፡፡ ወንጌል ተነቦ ውኃው በካህኑ ( በሊቀ ጳጳሱ ) ይባረክና የሕጽበተ እግር ሥርዓት ይከናወናል፡፡ ይኸውም ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ያሳየውን የተግባር ትምህርት ለማሳየት ነው ( ዮሐ . ፲፫፥፲፬ ) ፡፡ ከውኃው በተጨማሪ የወይራና የወይን ቅጠልንም ለሥርዓተ ሕጽበቱ ማስፈጸሚያነት እንጠቀምባቸዋለን፡፡ ምሥጢሩም የሚከተለው ነው፤
ወይራ ጸኑዕ ነው፡፡ ወይራ ክርስቶስም ጽኑዕ መከራ መቀበሉን ከማስረዳቱ በተጨማሪ እኛም ( እግራችንን የሚያጥቡን አባቶች እና የምንታጠበው ምእመናን ) መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ሥርዓተ ሕጽበቱን በወይራ እንፈጽማለን፡፡ የወይኑ ቅጠልም መድኃኒታችን ክርስቶስ በወይን የተመሰለ ደሙን አፍስሶ ለምእመናን የሕይወት መጠጥ አድርጎ መስጠቱን ለማዘከር በወይን ሥርዓተ ሕጽበትን እናከናውናለን ( ማቴ . ፳፮፥፳፮ ) ፡፡ በቀኝና በግራ የቆሙ ሊቃውንትም ‹‹ ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐጸበ›› እያሉ ይዘምራሉ፡፡ ይህ ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ሥርዓተ ቅዳሴው ተከናውኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ምእመናን ይቀበላሉ፡፡
ቅዳሴ
VIDEO
የጸሎተ ሐሙስ ቅዳሴ የሚከናወነው በተመጠነ ድምፅ ሲኾን፣ እንደ ደወል ( ቃጭል ) የምንጠቀመውም ጸናጽልን ነው፡፡ ልኡካኑ የድምፅ ማጉያ ሳይጠቀሙ በለኆሣሥ ( በቀስታ ) ይቀድሳሉ፡፡ ምክንያቱም ይሁዳ በምሥጢር ጌታችንን ማስያዙን ለመጠቆም ሲኾን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደ ነበር ለማስታወስ ነው፡፡ በመቀጠል ክብር ይእቲ፣ ዕጣነ ሞገር፣ ዝማሬ የተባሉ የድጓ ክፍሎች ተዘምረው አገልግሎቱ ይጠናቀቃል፡፡ ሕዝቡም ያለ ኑዛዜና ቡራኬ ይሰናበታሉ፡፡
ጉልባን
VIDEO
ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ በቤት ውስጥ ከሚፈጸሙ ተግባራት አንዱ ጉልባን ማዘጋጀት ነው፡፡ ጉልባን እስራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ በችኮላ መጓዛቸውን የምናስታውስበት ከእስራኤላውያን የመጣ ትውፊታዊ ሥርዓት ነው፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያ አብዛኞቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ ኪዳን መነሻ ስላላቸው ይህ ሥርዓት ዛሬም በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ ይከበራል፡፡
ጉልባን እስራኤላውያን ከባርነት በወጡ ጊዜ አቡክተው፣ ጋግረው መብላት አለመቻላቸውን ያስታውሰናል፡፡ በወቅቱ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መመገብ፤ ንፍሮ ቀቅለው ስንቅ መያዝ የመንገድ ተግባራቸው ነበርና፡፡ ይህን ታሪክ ለማሰብም በሰሙነ ሕማማት በተለይም በጸሎተ ሐሙስ ቂጣና ጉልባን ይዘጋጃል፡፡ በጸሎተ ሐሙስ የሚዘጋጀው ጉልባንና ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡፡ ይኸውም ጨው ውኃ እንደሚያስጠማ ዅሉ፣ ጌታችንም በመከራው ወቅት ውኃ መጠማቱን ለማስታወስ ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ምንጭ
___
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith | Tagged: ሕጽበተ እግር , ቤተ ክርስቲያን , ትንሣኤ , አምላክ , ኢትዮጵያ , ኢየሱስ ክርስቶስ , ወይንና ወይራ , ጉልባን , ጸሎተ ሐሙስ , ፋሲካ | Leave a Comment »