Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2019
ለመጪው የጳጳሱ የሞሮኮ ጉብኘታቸው የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲሱ አርማ በእስላማዊው ጨረቃ የተከበበውንና የተጣመመውን የአዲስ ዘመን መስቀልን እንዲያሳይ ተደርጓል። ከቫቲካን ቢጫ፣ ከእስልምና ደግሞ ቀይ እና አረንጓዴ በመውሰድ፡ መስቀሉና ግማሽ ጨረቃዋ የኢትዮጵያን ቀለማት፤ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ያንጸባርቃሉ። ይህ የጳጳሱ አዲስ አርማ ብቻ አይደለም፤ ሮማን ካቶሊኮች እ.አ.አ በ1960 ዓመታት ላይ በ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ላይ ለአንድ ዓለም ሃይማኖት ምስረታ መሰረቱን ከጣሉበት ዕለት አንስቶ በተቻላቸው መጠን “ክርእስላም”/ “Chrislam” የተሰኘ የእነርሱን ክርስትና እና እስልምናን ያጣመረ አዲስ ሉሲፈራዊ ሃይማኖት ለመመስረት እየታገሉ ነው። ሙከራውንም በናይጄሪያ ነበር ቀደም ሲል የጀመሩት፤ ቩዱ + እስልምና + ካቶሊክ ተደበላልቀው ማለት ነው። ይህ የጳጳስ ፍራንሲስኮ አርማ ለዚህ አዲስ ሃይማኖትም እንደ አርማ በይፋ ያገለግላል።
በአዲሱ ዓለም አቀፋዊ አገዛዝ የሚነገረው አዲሱ አምላክ ሉሲፈር ነው!
ኢትዮጵያን አንዴም ጎብኝተው የማያውቁት (አንድም የሮማ ጳጳስ አልጎበኛትም)ጳጳሱ ከጥቂት ቀናት በፊት በአራብ ኤሚራቶች ከኢማማሞች ጋር ተሳስመው ነበር የተመለሱት፤ አሁን ደግሞ በቅርቡ ሁለት አውሮፓውያን ሴቶች በሙስሊሞች እንደ ዶሮ በታረዱባት ሞሮኮ የክርስቶስ ጠላት ከሆኑት ኢማሞች ጋር ለመተቃቀፍ በመጪው ማርች 30 ወደዚያ ያመራሉ።
_____________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: መናፍቅ, ምንፍቅና, ሮማን ካቶሊክ, ቫቲካን, አርማ, ክሪስላም, የኑፋቄ ትምህርት, የኢትዮጵያ ቀለማት, ጳፓስ ፍራንቸስኮ, Chrislam, Christianity, Crescent & Cross, Heresy, Heretic Pope, Logo, Pope Francis, The Vatican | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 30, 2018
አቤት ቅሌት!
ኢሉሚናቲው ጳጳስ ፍራንቸስኮ እንዳሉት ከሆነ “ንስሐ የማይገቡ ኃጢአተኞች ከሞት በኋላ አይቀጡም፤ ይልቁንም ነፍሳቸው ጨርሳ ትጠፋለች እንጂ”።
ከአንድ ኢ–አማኝ ፈላስፋ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ “የኃጢአተኞች ነፍስ ከሞቱ በኋላ ምን ይሆናል?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነበር ይህን ቅሌታማ ነገር የተናገሩት።
ይህ አባባላቸው በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ካቶሊኮችን አስቆጥቷል
በሁኔታው የተደናገጠቸው ቫቲካን በሪፖርቱ ውስጥ የተጠቀሱት ጥቅሶች አጠያያቂ እንደሆኑ በማስተባበል ላይ ትገኛለች።
ተጨማሪ ለማንበብ…
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: መናፍቅ, ምንፍቅና, ሮማን ካቶሊክ, ቫቲካን, የኑፋቄ ትምህርት, ገነትና ሲዖል, ጳፓስ ፍራንቸስኮ, Christianity, Heaven and Hell, Heresy, Heretic Pope, Pope Francis, The Vatican | Leave a Comment »