Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጳጳስ ፍራንሲስኮ’

ጀግናው የግሪክ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ለሮማው ጳጳስ ፍራንሲስኮ፤ “ፓፓ፤ መናፍቅ ነህ!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2021

👉ገብርኤል 👉ማርያም 👉ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉ዮሴፍ 😇መድኃኔ ዓለም

አቴንስ ከተማ ፤ ቅዳሜ ዕለት የሮማው ጳጳስ ጉብኝት በኦርቶዶክስ ግሪክ፤ አንድ የግሪክ ኦርቶዶክስ አባት ለሮማው ጳጳስ ፍራንሲስኮ፤ “ጳጳስ አንተ መናፍቅ ነህ! ሰላሳ ሺህ ሕፃናትን (በፈረንሳይ ብቻ) ደፍራችኋል!” ብለው ጮኹ።

ጀግናው የግሪክ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ የሮማውን ጳጳስ ፍራንሲስኮን በዚህ መልክ ከገሰጿቸው በኋላ እንዲህ አሳዛኝ በሆነ መልክ በፖሊስ ተወስደዋል።

መናፍቁ ጳጳስ ፍራንሲስኮ የምስራቅ እና ምዕራባዊ አብያተ ክርስቲያናትን “አንድ ለማድረግ/ለመጠቅለል” በሚያደርጉት ሥራ የግሪክን የሮማ ካቶሊኮችን ለመጎብኘት ቅዳሜ እለት ግሪክ ገብተዋል።

እንዲህ ያሉ ጀግና አባት መድኃኔ ዓለም ይስጠን። ዓለም ተስፋ ያደርግባቸው የነበሩት “ትሁቶቹ” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ “አባቶች”ተገቢ ባልሆነ ዝምታቸው አውሬውን ነው እያገለገሉ ያሉት።

👉 የሚገርም ነው፤ በትናንትናው ዕለት ይህን በድጋሚ አቅርቤው ነበር፤

💭 Elder Paisios’ Amazing Prophecies About Turkey | ግሪካዊው በረኸኛ ጻድቅ አባ ፓይስዮስ፤

“አብዛኛዎቹ ቱርኮች ይጠፋሉ፤ ያለ እግዚአብሔር በረከት የተገነባ ሕዝብ ስለሆኑ ይደመሰሳሉ”

💭 ትንቢተኛው የግሪኩ አባ ዘወንጌል‘ | ቱርክ የምትባል አገር አትኖርም፤ በቅርቡ ትፈራርሳለች

✞✞✞“ኦርቶዶክስ በመሆናችን እግዚአብሔር ይረዳናል” አባ ፓይሲዮስ✞✞✞

በረኸኛው/ደገኛው ቅዱስ ኣባታችን ኣባ ፓይሲዮስ (..1924-1994)ቅድስናቸው በሁሉም ግሪኮች ዘንድ የታወቀው፤ ፖለቲከኞች ፣ አገልጋዮች ፣ ዓለማውያን ፣ መነኮሳት ፣ ካህናት ፣ ጳጳሳት በኤጂያን ባሕር ዙሪያ ስለሚሆነው ነገር ሁሉ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ተነጋግረዋል።

የወደፊቷን ግሪክ እጣ ፈንታ ለማየት እስኪበቁ ድረስ አባታችን ቀናትን እና ሌሊቶችን በጸሎት ያሳለፉ ነበር። ለግሪክ ፣ ለግሪካዊነትና ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ፣ ልባዊና ጥልቅ ጭንቀት እንዳላቸው ለሚቀርቧቸው ሁሉ ያወሱ ነበር።

💭 በቪዲዮው ከተካተቱት የአባታችን ትንቢታዊ መልዕክቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

👉 ቅዱስ ኮስማ እንደተነበዩት ሩሲያውያን ከላይ ጣልቃ ይገባሉ፤ ግሪኮች ቁስጥንጥንያን/ኢስታምቡልን በአምላክ ፈቃድ ያስመልሳሉ።

👉 ቱርክ በአጋሮቿ ትፈራርሳለች፤ ቱርኮች የተቀቀለውን ስንዴ በወገባቸው ዙሪያ አኑረዋል፤ የግሪክ ሠራዊት ወደ ቁስጥንጥንያ/ኢስታምቡል ያመራል

👉 ቱርክ በ፮/6 ማይሎች ርቀቶች(የግሪክን የክልል ውሃ)መቃረቧን በዜና ሲሰሙ ከዚያ ጦርነት ይከተላል፤ መርከቦቿም ይደመሰሳሉ።

👉 ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ። የቱርክ መጨረሻ መጀመሪያ ይሆናል።

👉 ቁስጥንጥንያ/ኢስታምቡል ለግሪክ ትመለሳለች፤ በሩሲያ እና በቱርክ መካከል ጦርነት ይከሰታል፤ በመጀመሪያ ቱርኮች ያሸንፉ ይመስላቸዋል ነገር ግን ይህ የእነሱ መጥፊያቸው ይሆናል።

👉 ቱርኮች ይጠፋሉ ። እነሱ ያለ እግዚአብሔር በረከት የተገነባ ህዝብ ስለሆኑ ይደመሰሳሉ።

አንድ ሦስተኛው ቱርኮች ወደ መጡበት የቱርክ ጥልቀት ይመለሳሉ። አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ክርስቲያን ስለሚሆኑ ይድናሉ ፣ ሦስተኛው ደግሞ በዚህ ጦርነት ይገደላሉ። ግሪኮች፣ አርመኖችና ኩርዶች ቱርክን ይከፋፈሏታል።

👉 የቀደመው የቱርክ ትውልድ በአዲስ የፖለቲከኞች ትውልድ ይተካል። በእግዚአብሔር ላይ እምነት እና ተስፋ እስካለ ድረስ ብዙ ሰዎች ይደሰታሉ። በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ውስጥ የሚሆነው ሁሉ ይህ ነው። ጊዜው ደርሷል።

👉 እንግሊዞች እና አሜሪካውያን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ቁስጥንጥንያን ለግሪክ ይሰጧታል። ቱርኮች ግሪክን ይተናኮላሉ፤ ማዕቀብ ይከተለላል፤ ዘመነ ረሃብ ይመጣል። ግሪኮች ይራባሉ።

👉 ከቱርክ ትንኮሳ በኋላ ሩሲያውያን ወደ ቢስፎረስ ባሕር ይወርዳሉ፣ እኛን ለመርዳት ሳይሆን፣ ሌሎች ፍላጎቶች ስላሏቸው እንጂ።

👉 በሩሲያውያን እና በአውሮፓውያን መካከል ታላቅ ጦርነት ስለሚኖር ብዙ ደም ይፈስሳል። ግሪክ በዚያ ጦርነት ውስጥ የመሪነት ሚና አለመጫወቷ ትልቅ በረከት ነው። ምክኒያቱም በአውሮፓውያን መካከል በሚደረግ ጦርነት የሚሳተፍ ሁሉ ይጣፋልና ነው።

👉 ቱርኮች ይመቱናል ግን ግሪክ ከፍተኛ ጉዳት አይደርስባትም፤ ቱርኮች በአገራችን ላይ ከፈፀሙት ጥቃቶች ብዙም ሳይቆይ ሩሲያውያን ቱርኮችን ይመቱና ያፈርሷቸዋል፤ ልክ አንድ ወረቀት ተቀዳደደው ይፈራርሳሉ።

👉 ሩሲያ ቱርክ ከወደመች በኋላ እስከ ፋርስ ባሕረ ሰላጤ ድረስ ጦርነቱን ትቀጥላለች፣ ወታደሮቿም ከኢየሩሳሌም ውጭ ይቆማሉ።

👉 ከዚያ የምዕራባውያኑ ኃይሎች ሩሲያውያን ወታደሮቻቸውን ከእነዚህ ቦታዎች እንዲያስወጡ ማሳሰቢያ ይሰጣሉ።

👉 ግን ሩሲያ ኃይሏን አታወጣም ፣ ከዚያ የምእራባዊያን ኃይሎች እነሱን ለማጥቃት ወታደሮችን መሰብሰብ ይጀምራሉ።

👉 የሚፈነዳው ጦርነት ዓለም አቀፋዊ ይሆናል እናም የሩሲያውያንን ኪሳራ ያስከትላል፤ ግዙፍ መተራረድ ይኖራል ፣ ከተሞቹ የፈራረሱ መንደሮች ይሆናሉ።

👉 ግሪክ በዚያ ጦርነት ውስጥ አትሳተፍም፤ የቁስጥንጥንያው ገዢ በእኛ በኩል ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ይሆናል።

የቱርክ መጥፋት ለግሪኮች ትልቅ እርካታ ይሆናል፤ ቁስጥንጥንያ ለግሪኮች ትመለሳለች።

የፀሎት እና ቅዳሴ ሥነ ስርዓት በቅድስት/ሃጊያ ሶፊያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደገና ይጀምራል።

ልክ እንደ ዛሬዎቹ ‘ኢትዮጵያውያን’ባዮች ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ፤ አርሜኒያውያንም ከ፻ ዓመታት በፊት ከሚበላቸው አውሬ ጎን ተሰልፈው ነበር

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሮማው ጳጳስ ከእኛዎቹ በልጠው ለትግራይ ጸሎት ያደርሳሉ | “ረሃብን መታገስ የለብንም!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 13, 2021

💭 የቫቲካን መልዕክት፦

የሁሉንም ህሊና የሚፈታተን አደጋ፤ በትግራይ ያለው የረሃብ ደወል። ፍራንችስኮስ ከአንጀሉስ በኋላ ባደረጉት ሰላምታ በጭፍጨፋው ለተጎዱት የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሚኖሩ ሕዝቦች “ሰላም ለኪ” አቅርበዋል። “ረሃብን መታገስ የለብንም” ብለዋል

Una tragedia che interpella la coscienza di tutti: l’allarme alimentare nel Tigray. Nel saluto post Angelus, Francesco recita un’Ave Maria per la popolazione della regione dell’Etiopia colpita da violenze. L’appello a non tollerare che si muoia di fame.

👉 እንግዲህ ይህ ከG7 ጉባኤ ጋር በተናበበ መልክ የቀረበ መልዕክት መሆኑ ነው። ግን ይሁን እስኪ!

ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ምነው ጠፉ?

ከዚህ በፊት ኤርትራ ውስጥ ያሉት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካርዲናሎች ኤርትራውያን ከትግራይ ተሰርቀው ወደ ኤርትራ የሚገቡትን ቁሳቁሶች እንዳይገዙ ት ዕዛዝ በማስተላለፍ ከትግራይ ሕዝብ ጋር እንደሚሰለፉ ገልጠው ነበር፤ ያውም በኢሳያስ አፈቆርኪ ግዛት። የኛዎቹስ ሰባት ወራት እንደ ሞእተ ሰው “ጭጭ” ብለዋል።

የአገር ውስጥ ሜዲያዎች ለሆዳቸው ያደሩ ፈሪ ጥንቸሎች ስለሆኑ ይህን ማድረግ እንደማይፈልጉና እንደማይችሉ ግልጽ ነው፤ ግን የውጭ ሜዲያዎች ለምንድን ነው አቡነ ማትያስን ለቃለ መጠይቅ የማይጋብዟቸው? የትግራይ ጉዳይ እኮ አንዴ ብቻ ተነግሮበት በዝምታ የሚታለፍና ቸል የሚባልበት ጉዳይ አይደለም። የቤተ ክህነት ግድየለሽነትና ከግራኝ ጋር ተደማሪነት፣ የኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ብሔሮች ዝምታና ከግራኝ ጋር ተደማሪነት፣ የሜዲያዎች ሽርሙጥና እና ከግራኝ ጋር ተደማሪነት ናቸው ጭፍጨፋው፣ አስገድዶ መድፈሩ፣ ረሃቡና ስደቱ እንዲቀጥል እርዳታ እያደረጉለት ያሉት። እኔ ሁሉንም መጠራጠር ጀምሬአለሁ/ ግዴታየም ነው፤ ከእግዚአብሔር አምላኬ እና ቅዱሳኑ በቀር ከላይ እስከ ታች ማንንም አላምንም! ሁሉም ተናብበው የእግዚአብሔርን ልጆች ለማጥፋት በጋራ እየሠሩ ነው። የትም ዓለም እኮ ታይቶ የማይታወቅ ክስተት ነው ዓለም እየተገነዘበው ያለው። ብጹእነታቸው ከሳምንታት በፊት ከዘመድኩን በቀለ ጋር በስልክ እንዲነጋገሩ በመገደዳቸው/በመደረጋቸው በጣም ነበር ያዘንኩት!

_________________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life, News/ዜና | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ካቶሊኮች መሰከሩ | ጣልያን የዋቄዮ-አላህ ጣዖት አምልኮን በመፍቀዷ የኮሮና መቅሰፍት መጣባት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 29, 2020

👉 ፓቻማማ + አቴቴ + ሺቫ

ይህ የጣልያን አሳዛኝ ሁኔታ የሚያስተምረን ነገር ቢኖር ከተመሳሳይ መቅሰፍት ለመዳን መስቀል አደባባይ ላይ የተተከሉትን የኢሬቻ ዛፎች ዛሬውኑ ቁረጡ። አዲስ አበባ፣ ደብረዘይት፣ ናዝሬት መላዋ ኢትዮጵያ ከዋቄዮ አላህ፣ ከኢሬቻ ቃልቻ ቆሽሻ መንፈስ በፍጥነት መጽዳት እንዳለባቸውና መመለክና መፈራት ያለበት ብቸኛ አምላክ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ነው። በመሰቀልደመራ ወቅት በመስቀል አደባባይ ሲፈረግጥ የነበረው በሬ እኮ እንደ አንድ ምልክት ሊሆነን በተገባ ነበር።

ዋቄዮአላህ የፈጠራቸው ሴት አማልክት በአፍሪቃ /በኦሮሞዎቹ አቴቴ፣ በደቡብ አሜሪካ አማዞናስ ዙሪያ ፓቻማማበህንድ ሺቫ ከእነ ሦስት ልጆቿ/ቹ፤ ሳትቫ፣ ራጃስ፣ ታማስ። ሁሉም የአልላት፣ አልኡዛ እና አልማናት አቻዎች መሆናቸው ነው።

የጨረቃው አምላክ አላህከፀሐይዋ አምላክ ጋር ተጋብቶ ያስገኛቸው ልጆች በአንድነትም “የአላህ (ሴት) ልጆች” የተባሉ ሦስት አማልክት ስምም፦

👉 አልላት

👉 አልኡዛ

👉 አልመናት

ነበር፡፡

👉 ..አ ጥቅምት 4 ቀን 2019 .. – ጣዖት አምልኮ ሥነስርዓት በቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስኮ እና ሌሎች ቀሳውስት በቫቲካን የአትክልት ስፍራዎች ላይ ያካሄዱት የዛፍ ተከላ ሥነስርዓት።

***በዓላቱ – መስከረም/ጥቅምት ላይ ተከታትለው ይውላሉ***

(ኢሬቻ + ሺቫ(ሙሩጋን) + ዱርጋ (ሴት የዛፍ አምላክ) + ፓቻማማ + ሃሎዊን)

በአምልኮ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከአማዞን የመጡ ሰዎች ሁለት ከእንጨት የተሠሩ እርጉዝ ሴቶች ሐውልቶች(ፓቻማማ)ጳጳሱ ፊት ተንበርክከው ሲያመልኩ ይታያሉ።

በዛፍ ተከላ ሥነ ስርዓት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የጣዖቷን ፓቻማም ሐውልት ባረኳት

👉 ካርዲናል በርክ ጳጳስ ፍራንሲስኮን ወቀሱ፦

ታዋቂው የአሜሪካ ካርዲናልና የቫቲካን ከፍተኛ ዳኛ ሬይመንድ በርክ፦ የደቡብ አሜሪካው የአማዞን ሲኖድ ያመጣት ጣዖት ፓቻማማ፣ እና የዛፍ ተከላ ሥነስርዓቱ አጋንንታዊ ኃይልን በቫቲካን አስገብተውብናል፤ ከፓቻማማ ጋር ሰይጣን ቤተ ክርስቲያን ገባ፤ ብቸኛዋ ወላዲተ አማልክ ድንግል ማርያም ናት። ከዚህች ጣዖት ጋር የመጣው የሰይጣን መንፈስ ከቫቲካን ይወገድ ዘንድ በክርስቶስ ስም መጸለይ ያስፈልጋል፤ የቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ከእነዚህ የክፋት ኃይሎች መጽዳት አለበት።ሲሉ ብሶታቸውን ገና ኮሮና ከመታወቋ በፊት አሰሙ።

👉 የእስልምና ጣዖት አምልኮ በቫቲካን

ሮማን ካቶሊኮች እ..አ በ1960ዎቹ በ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ላይ ለአንድ ዓለም ሃይማኖት ምስረታ መሰረቱን ከጣሉበት ዕለት አንስቶ በተቻላቸው መጠን “ክርእስላም”/ “Chrislam” የተሰኘ የእነርሱን ክርስትና እና እስልምናን ያጣመረ አዲስ ሉሲፈራዊ ሃይማኖት ለመመስረት እየታገሉ ነው።

👉 ይህ በቫቲካን ታይቶ አይታወቅም፦

አንድ የቱርክ ኢማም ንግግር አድርግ ተብሎ ሲጋበዝ፤ ክርስቲያኖችን እና አይሁዶችን የሚረግመውንና አልፋቲሃየተሰኘውን የእስልምና ፀሎትክፍል “ እንደ እባብ እየነዘረ ለቀቀው።

👉 ሁለተኛው የፊሊፒንስ ካቶሊክ ቄስ፦

ጣዖታቱ ፓቻማማ” + “አቴቴ” + “ዮጋ” + “ሃሪ ፖተር” + “አላህቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባታቸው ሰይጣን ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖችን በአጋንንቱ ሊበክላቸውና ሊለክፋቸው በቅቷል።

እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ፡፡[ዘጸ ፳፥፪፡፫፟]

የሚለውን ትዕዛዝ በመሻራችን ነው ኮሮናየመጣችብን።

ቸሩ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከዋቄዮአላህ መንፈስ እና ከታዘዘው መቅሰፍት ሁሉ ይጠብቅልን! ለዘለዓለሙ አሜን!

👉 ገነ ማስተዋሌ ነው፦

ቪዲዮው ልክ የ2200 ደቂቃዎች እርዝመት አለው። ፳፪ / 22 ማክሰኞ ይውላል– ኡራኤል

በዚህ ዕለት ምን ይከሰት ይሆን?

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Health, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በኢትዮጵያ ያገለገሉ የመጀመሪያው የካቶሊክ ኤጲስ-ቆጶስ በኮሮና ሞቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 28, 2020

ጣልያናዊው ኢጴስቆጶስ “አቡነ አንጄሎ ሞረሺ” ይባሉ ነበር። በደቡብ ኢትዮጵያ በዲላ እና ጋምቤላ ያገለገሉ ሲሆን ወደ ጣልያን ከተመለሱ በኋላ ነበር በኮሮና ቫይረስ የተያዙት። ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

የሚያሳዝን ነው፤ እስከ አሁን በአጠቃላይ ፷/ 60 የካቶሊክ ቀሳውስት በኮሮና ሞተዋል፤ ግን ለምን ጣልያን? ለምን ካቶሊኮች፣ ለምን ፕሮቴስታንትና ሙስሊም በሆኑት ሃገራት? እንግዲህ እስከ አሁን በይብለጥ እየተጠቁ ያሉት እንደ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዊዲ አረቢያና ቱርክ የመሳሰሉት ሙስሊም ሃገራት፣ እንደ ጣልያን፣ ስፔይን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ብሪታኒያ እና ዩ.ኤስ አሜሪካ የመሳሰሉት የካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት ሃገራት ናቸው።

ግብዝነት እንዳሆንብን እና በይበልጥ እንዳይፈታተነን መጠንቀቅ ቢኖርብንም፤ አሁን ባለው መጠይቅ ያለብን በአውሮፓ እንኳን ለምን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ግሪክ፣ ቆጵሮስ ሩሲያ፣ ጆርጅያ፣ አርሜኒያ፣ ቡልጋርያ፣ ሩማኒያ ወይም ሰርቢያ እስካሁን የኮሮና ሰለባ የሆነ ሰው የለም። ለምን? እንዴት?

ለወገኔ እንደ ማጽናኛ የምለው በተቀደሱት የኢትዮጵያ ተራራዎች እንደ አዲስ አበባ ከባሕር ከሁለት ሺህ ሜትር በላይ ከፍታ ባላቸው ቦታዎች ኮሮና ቫይረስ ድርሽ የማለት አቅም ያለው አይመስለኝም። በተጨማሪ በእነዚህ ቦታዎች ወባ አለመኖሩ የሚጠቁመን ነገር አለ።

_______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Health, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሮማ ካቶሊኩን ጳጳስ ኮሮና ያዘቻቸው እንዴ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 27, 2020

ጳጳስ ፍራንሲስኮ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁትን በትናንትናው ዕለት ህመምተኞች በጎበኙ ማግስት “በጉንፋን ነገር” መታመማቸው ተዘገበ።

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል የኢሳያስ አፈወርቂ ቫይረስ በአስመራ አውሮፕላን ማረፊያ አገታቸው፤ ባለፈው ሳምንት ካርዲናሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ስላለው ፀረክርስትና ዘመቻ ማሳሰቢያ ነገር በመስጠታቸው ኢሳያስና አብዮት አህመድ የጠነሰሱት-እሳቻውን-የማሳፈሪያ ሤራ ይመስላል። ያሳዝናል!

ፍራንሲስኮስ ደግሞ ባለፈው መስከረም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መግቢያ ሰሞን በቫቲካን የደቡብ አሜሪካ “ህንዶች” የኢሬቻ ጣዖት አምልኮ ዛፍ ከተከሉበት ዕለት ጀምሮ ቀንድ በማብቀል ላይ ናቸው (በሌላ ቪዲዮ አቀርበዋለሁ)። ታዲያ አሁን የዚህ የኮሮና መቅሰፍት ሰለባ ሆነው ይሆን? ለማንኛውም ሁሉም እየተከሰተ ያለው ሃገራችን በቅዱስ ጊዮርጊስ እየተመራች በፋሺስት የጣልያን ሠራዊት ላይ ድል የተቀዳጀችበት ፩፻፳፬/124ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ለማክበር በምንዘጋጅበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያ ስታነጥስ መላዋ ዓለም ጉንፋን / ኮሮና ይይዛታል!

____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ | እንግዳ ነገር ፣ ቅርፅ መቀየር? | የቫቲካኑ ጳጳስ ሴትዮዋን አጮሏት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 2, 2020

የቫቲካኑ ጳጳሳ ፍራንሲስኮ ባለፈው ማክሰኞ በቫቲካኑ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከያዘቻቸው ሴት እጅ ነፃ ለማውጣት የሴትየዋን እጅ በመመንጠቅ በቁጣ ሲያጮሉት ይታያሉ።

ድርጊቱ ከመከሰቱ በፊት ሴትየዋ በመስቀል ምልክት ፊቷን አማትባ ነበር። የ 83 ዓመቱን ጳጳስ እጅ እንደያዘች ልትነግራቸው የፈለገችው ነገር ነበር፡ ነገር ግን ምን ልትነገራቸው እንደፈለገች ግልፅ አይደለም።

ቪዲዮው ላይ አንዳንድ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች ይታያሉ። አንድ ከየት እንደመጣ እና የማን እንደሆነ የማይታወቅ እጅ ሰተት ብሎ ሲገባ ይታያል። ልክ ይህ እጅ ሲገባ ጳጳሱ ፊታቸው ሲቀያየርና የተለየ ሰው ሆነው ይታያሉ። ሌላዋ ሴት ደግሞ ደም የለበሰ ቀይ እጅ አላት።

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ

ገጽ 18-21

ወደ ጣራው በኩል ኮሽታ ድምፅ ሳያሰማ ስፍፍፍፍእያለ ወርደና በዝግታ መድረኩ ላይ እርፍፍፍ.…አለ። ፊቱ የሰው ነው። ከአንገቱ በታች ሲታይም የሰው ቅርፅና የሰው የሰውነት ክፍሎችን ሁሉ ያካተተ ተክለ ቁመና ያለው ነው። ነገር ግን አጠቃላይ አቋሙን ግዝፈቱ ሰው እንድላሆነ የሚያስታውቅ ነው። የቆመው እንደ ሰው በእግሮቹ ነው፤ ነገር ግን ሁለቱ እግሮቹ በጣም ወፋፍራምና አብረቅራቂ ቆዳ ያላቸው ዘንዶዎች ናቸው። ከወደ ጭኑ ወፈር፥ ከወደ ባቱ ቀጠን ያሉ የቆሙ ዘንዶዎች እግር ሆነውታል። እጆቹ ደግሞ እግር የሆኑት የወፋፍራም ዘንዶዎች ልጆች የሆኑ ይመስል በመጠንና በውፍረት ከእነሱ አንሰው ነገር ግን የቆዳ ቀማቸውና ዘንዶነታቸው እንዳለ ሆኖ ነው የሚታዩት።

የዘንዶ ቅርፅና ቆዳ ካለው ጡንቻና ክንዱንም አልፎ ከሚገኘው ቅርፅ ቀጥሎ ያሉት የእጆቹ መዳፎችም እንደ እግሮቹ ሁሉ የሰው የመሰሉና በመዳፍ ስፋትና በጣት ርዝመት ብቻ ከሰው ዘገግና ሰፋ ይሉ ከመሆናቸው በቀር ሌላ እንግዳ ነገር አይታይባቸውም። እነሱም ባለ አምስት ጣት ናቸው።..…

.… ሂደቱ በዚህ አይነት እንደቀጠለ በነበረ ጊዜም ይህ ምንነቱ ያልለየ ነገር በመጣበት አኳኋን፤ ኮሽታ ድምፅ ሳይሰሙ ሀይማኖታዊ ልብሳቸውን እንደለበሱና በአንድ እጃቸው የወርቅ መቋሚያቸውን እንደጨበጡ፤ ያንን ከእንቁና ከወርቅ የተሰራ የአራስ አክሊላቸውን እንደደፉ በቀይ ካባ አጊጠው የቫቲካኑ ዋና ጳጳስ ከተፍ አሉ።፡እንዲሁ ኮርኒሱ ሳይበሳ ከላይ ወርደው ያለ አንዳች ድንጋጤ በደመቀ ፈገግታ ተውጠው ሲወርዱና በተጫሙት ቀይ ምቹ ጫማ የመድረኩን ወለል ሲረግጡ ተሰብሳቢዎች እያዩዋቸው የነበረ ቢሆንም፤ አንዳቸውም የመገረም ሁኔታ አልተንፀባረቀባቸውምና ጉዳዩ የተለመደ መሆኑን ማረጋገጥ ተቻለ።.…

ጳጳሱ አንድ እጃቸውን አንስተው የተቀመጡ ምልክት አሳዩዋቸው። የG8 አገአት መሪዎችም በድንፋታ የታጀበ ምስጋናቸውን ደምድመው በየወንበሮቻቸው ቁጭ አሉ። የቫቲካኑ ጳጳስም ተስብሳቢዎችን አስቀምጠው በትለየ ቋንቋና ለማንም ባልተሰማ ሹክሹክታ ለዚያ ቀድሟቸው ለመጣው ዘንዶ ለበስ ሰው ጎንበስ ብለው አነበነቡና እጅ ነስተው ቀና አሉ። ይህንን አድርገውም ሌላ ቃል ሳይናገሩ በመጡበት አኳኋን ወደ ላይ ተነሱና ተንሳፈው ሄዱ። ኮርኒሱና ጣራው ክፍትም ክድንም ሳይል እንዲሁ አሳለፋቸው። ጳጳሱ ከሄዱ በኋላ እንዲሁ ባረፈበት ቦታ እንደቆመ እንደ ሞዴሊስት ተገትሮ በልዩ ፈገግታ በጎንዮሽ ተሰብሳቢዎችን በማየት ብቻ ተወስኖ የነበረው ሰው መሳይ አካል በዝግታ መድረኩ ላይ መንጎማለል ጀመረ። ወዲያውም አስገምጋሚ ድምፅ ከአንደበቱ ወጣ። የሚናገረው በጠራ እንግሊዝኛ ነው።

ክብር ለሀያሉ አባቴ!” ሲል በከባድ ድምዕ ጀመረ።

አሜን!” የሚል የጋራ ጪኸት አሰሙ።

ሁላችሁም በአንድነት ውጪያችሁን አብሩ!” አላቸው።ሁሉም በአንድነት አይኖቻቸውን ለስድስት ሴኮንድ ያህል ጨፍነው ቆዩና ገለጡ ሲገልጡም የተለመዱ ጥቋቁርና ጥምዝ የሆኑ አጫጭር ቀንዶቻቸው በየግንባሮቻቸው ግራና ቀኝ ወጡ።ቀጠለ፤ አሁን ደግሞ ውስጣችሁን ለማብራት ተመሳሳይ ነገር በእጥፍ አድርጉ!” ሲል፤ ታዳሚዎች ለአስራሁለት ሴኮንድ ያህል አይኖቻቸውን ጨፍነው ገለጡ። ሆኖም ያዩት አዲስ ነገር አልነበረ። ወዲያው ግን፤

እርስ በርሳችሁ ተያዩሲላቸውና ሲተያዩ፤ በጉጉት ይጠብቁት የነበረው ነገር በየግንባሮቻቸው ላይ ተፅፎአቸው አዩ። በአብረቅራቂ የኩል ቀለም 666 የሚል ምልክት ተፅፎባቸው ሲያዩ ማመን አቃታቸው። አመስግኑ! አባቴን አመስግኑ!” ተባሉ።

እንግዲህ ጳጳስ ፍራንሲስኮ እና ግራኝ አብዮት አህመድና ታማኝ ተደማሪዎቹ ላይ ተጽፎባቸው የሚታየውም ይኸው 666 የሚለው ምልክት ነው።

ይህ 1667ኛው ቪዲዮዋችን ነው!

_______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቡልጋሪያ | ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የካቶሊኩን ጳጳስ ፍራንሲስኮን አላስተናግድም አለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 6, 2019

በራሳቸው በካቶሊኮች ዘንድ የተጠላውና መናፍቅ የሆነው የቫቲካን ጳጳስ ፍራንሲስኮ ከቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች ጋር ለመገናኘት እሁድ ዕለት ወደ ቡልጋሪያ በመጓዝ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ጋር የጋራ የጸሎት አገልግሎት የማክበር ተስፋ ነበረው። ነገር ግን የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ አባቶች ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር ጸሎት ለማድረግ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ገልጠዋል።

የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት በዛሬው ዕለት በሶፊያ ከተማ ከጳጳሱ “ለሰላም ፀሎት” ማድረጊያ ሥነ ሥርዓት ጋር እንዲቀላቀሉ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል፤ በተለይ በዚህ “የሰላም ጸሎት” ላይ የሙስሊም መሪዎች መካፈላቸውን የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶችን አላስደሰታቸውም።

የቡልጋሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለብዙ ዘመናት በፀረክርስቶሷ ኦቶማን ቱርክ እና በኮሙኒዝም ጭቆና ቀንበር ብዙ ፈተናን ያየች ቤተክርስቲያን ናት።

ከሦስት ዓመታት በፊትም ጳጳስ ፍራንሲስኮ በኦርቶዶክስ ጆርጂያ ተመሳሳይ ዕጣ ደርሶት ነበር።

የቡልጋሪያ አባቶች ውሳኔ ትክክለኛ ነው። ይህ ግራ የተጋባ ጳጳስ አንድ የዓለም ሃይማኖት (በቫቲካን መሪነት) ለመመሥረት በመጣደፍ ላይ ነው፤ ለዚህም ነው መሀመዳውያኑ በማስጠጋት ላይ ያለው፣ ለዚህም ነው በሚሊየን የሚቆጠሩ መሀመዳውያን “ስደተኞች” አውሮፓን እና አሜሪካን እንዲያጥልቀልቁ ድጋፉን የሚሰጠው። ወደ ቡልጋሪያም የሄደው ያው ቡልጋሪያ በሯን ለሙስሊም ስደተኞች እንድትከፍት ለመገፋፋት ነው።

ለሰላም ፀሎት” በሚል ሰበብ በአገራችንም የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች በአንድ ላይ ሲሰባሰቡ እያየን ነው፤ ይህ ትልቅ ስህተት ነው፤ ከሰይጣን ጋር ሆኖ ለሰላም ፀሎት ማድረግ አይቻልም፤ ቅጥፈት ነው! እራስን ማታለል ነው!

ሰሞኑን አንዳንድ አስገራሚ ነገሮችን እያየን ነው፤ ለምሳሌ የበዓል ወቅትን ወይም ልዩ መርሃ ግብሮችን በመጠቀም እንደ እነ መጋቢ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ የመሳሰሉትን ታዋቂ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችከሙስሊም ኡስታዞችና ሸሆች ጋር መድረክ ላይ ወይም ስቱዲዮ ውስጥ በአንድ ላይ እንዲገናኙና በአገራችን ሁኔታ ላይ ተመሳሳይ መልዕክት እንዲያስተላልፉ እየተደረገ ነው፤ ከጀርባው ትልቅ ተንኮል አለ፤ “ሁሉም ሃይማኖቶች አንድ ናቸው፣ አንድ ነን፣ በሉሲፈር መሪነት ዓለም አቀፋዊ የሆነ አንድ ሃይማኖት መመሥረት አለብን” የሚል አጀንዳ ያለው ነው።

[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፲፬]

ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እጅግ በጣም የሚገርም ነው | በዛሬው ዕለት የሮማው ጳጳስ ፍራንሲስኮ ስለ ንቅሳት የሚከተለውን ተናግረዋል፦

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 21, 2018

ንቅሳትን አትፍሩ፣ ለበርካታ አመታት ኢሬቴራውያን/ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች እና ሌሎችም በግምባራቸው ላይ መስቀል ያደርጋሉ

ዋውውው!

Don’t be afraid of tattoos, for many years ERITREAN / ETHOPIAN Christians and others have gotten tattoos of THE CROSS on their foreheads.

Pope Francis Gives His Blessing for Tattoos

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: