✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፥፯]✞
፲፩ አቤቱ፥ የጣልኸኝ አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
፲፪ በመከራችን ረድኤትን ስጠን፤ የሰውም ማዳን ከንቱ ነው።
፲፫ በእግዚአብሔር ኃይልን እናደርጋለን፤ እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል።
😈 በአውሬው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የሚመራው የኦሮማራ አህዛብ ሠአራዊት ለዝርፊያ ከተሰማራባቸው ታሪካዊ ዓብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት አንዱ የደብረ ምሕረት ጨለቖት (ሀገረ ማርያም) ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ነው። ወረድ ብለን እንደምናነበው በረከታቸው ይደርብንና የሃገር ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ ከማረፋቸው በፊት በቦታው ላይ ያሉትን በርካታ የታሪክ ቅርሶች የዝመነ መሳፍንት ታሪክና ቅርስ ዝክር እና በዚያ ዘመን ቤተ ክርስቲያን የነበራትን ሕይወት ማስታዋሻ የሆኑ ሐብቶች መጠበቂያ የሚሆን ቤተ መዘክር የማሠራት እቅድ እንደነበራቸውና ይኽውም ከፍተኛ ድጋፍና ማበረታቻ እነሚያስፈልግ ገልጸው በአካል ተለይተውናል። ዛሬ ይዞታው ምን ላይ ይሆን? ታሪካዊ ቅርሶቹስ? የኦሮሞራ ቃኤላውያኑ እነዚህን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ቅርሶች ለመዝረፍ የብዙ ዓመታትና ዘመናት ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ዛሬ በፍሬዎቻቸው አውቀናቸዋል፤ ለዚህ የዘረፋ ተግባር ከኤዶማውያኑ የተማሩትን ስልት እና ጥበብ ተጠቅመዋል፤ የትግርኛን ቋንቋ ማጥናት ችለዋል። ከግራኝ እስከ ጉማሬው ብርሃኑ ነጋ ለፖለቲካው ድራማም ለሌብነቱና ለጭፍጨፋው ያመቻቸው ዘንድ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ስነ ልቦና፣ ባሕል፣ ህልም ብሎም የትግርኛን ቋንቋ ሳይቀር በሚገባ አጥንተዋል። እንደው ምስኪኗ አህያ አትሰደብብኝ እንጂ፤ “ከአህያ ጋር የዋለ ፈስ ተምሮ ይመጣል” እንዲሉ ከኦሮሞዎቹ “የኬኛ ቫይረስ” የተጋባበት የአማራው ልሂቅ ‘ልጅ ተድላ‘ “ቤተሰብ” በተሰኘው የግብዞች ስብስብ ፀረ–ትግራዋይ ሜዲያ “አክሱም የአማራ ሥልጣኔ እንጂ፤ የትግራዋይ አይደለም። ” ብሎ በመቀባጠር ተከታይ መንጋውን ሲያስደስት በዚህ ሳምንት ተመልክቸዋለሁ። ዋው!
እንግዲህ ይህ ግለሰብ የርዕዮት ሜዲያውን ትግራዋይ ‘ቴዎድሮስ ፀጋዬን‘ ልክ እንደ ሌሎች ብዙዎች የአማራ ልሂቃን (አቻምየለህ ታምሩ፣ ማስተዋል ደሳለው፣ ያሬድ ጥበቡ፣ ኢንጅነር ይልቃል፣ ሻለቃ ዳዊት፣ የኢትዮ360 “ኢሳቶች”፣ ዶ/ር ፍጹም አቻምየለህ፣ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ፣ ሄኖክ የማነ፣ የአብን አመራሮች ወዘተ)ለዓመታት ለኦሮማራ አጀንዳቸው ከተጠቀሙበት በኋላ ልክ በትግራይ ላይ ጦርነቱ በተከፈተ ማግስት “ዘወር በል!” ብለው ራቁት፤ ልክ በማግስቱ፤ ዋው! እንግዲህ ከቴዲ የሚጠብቁት ስለ ምኒልክ፣ ባልደራስ፣ በራራ እና ጥላሁን ገሠሠ እንዲናገር፤ ለአማራ ብቻ እንዲያለቅስ ነበር። ዛሬ እንዲያውም አንዳንዶቹ ይባስ ብለው ወደ ሜዲያዎቻቸው (የህወሃት ባሮሜትር አድርገውት)ለፈተና እየጋበዙ እነርሱ ፈራጆች ሆነው በፍርድ ቤት ችሎት እንደቀረበ ወንጀለኛ ሲሳለቁበት፣ ሲያዋርዱትና ሲፈርዱበት(በትግራይ ሕዝብም ላይ)ይታያሉ። የትግራይ ሕዝብ የመቶ ሰላሳ ዓመታት ታሪክን ነው የሚያሳየን፤ የኦሮማራዋ ‘ኢትዮጵያ ዘ–ስጋ‘ ትግራዋያን ለዘመናት ከተጠቀመችባቸው በኋላ ዛሬ አኝካ ተፋቻቸው። ህወሓቶች ከሠሯቸው ትልቅ ስህተቶች መካከል አንዱ እነዚህን ግብዞች በደንብ አለማሸታቸው ነው። ያው እየየን እኮ ኦሮሞው አማራውን በደንብ አድርጎ ሰልሚያሸውና ስለሚያርደው እኮ ነው ጸጥ ለጥ ብለው ለመገዛት ከኦሮሞዎቹ ጋር አብረው ትግራዋይን በመጨፍጨፍ ላይ ያሉት። እውነትም ‘አድጊ‘!
ልጅ ተድላ ያን እንደሚል ገና ለመጀመሪያ ጊዜ ከሦስት ዓመት በፊት እንዳየሁትና ልክ በፍራንክፈርት ጀርመን ተቀማጭነታቸው እንደሆነው የግራኝ ሞግዚት እንደ ‘ዶክተር ልዑል አስፋወሰን አስራተ ካሳ’ የኢሉሚናቲዎቹ ነፃ ግንበኞች/ፍሪሜሰንስ ወኪል እንደሆነ በደንብ ለመታዘብ በቅቼ ነበር። እነ ዘመድኩን በቀልን፣ ዶ/ር ራዶስ፣ ዶ/ር ዘበነ፣ መምህር ምሕረተ አብ እና በዋሽንግተን ዲሲ እና ቨርጂኒያ አካባቢ ያሉትን ቀሳውስት እና ካህናት ተብየዎች ሁሉ በፍላጎትም ተገደውም፤ አውቀውትም ሳዋቁትም በቴክኖሎጂ የእነዚህን ነፃ ግንበኞች ተልዕኮ የሚያሟሉ እንደሆኑ ለሰከንድ አልጠራጠርም።(በሲ.አይ.ኤ ዋና መቀመጪያ በሆነችው በቭርጂኒያ ባለፈው ዓመት ላይ በየከተሞቹ መንገዶች ኮቪድ19 ተከትሎ ማዕጠንት ለምን እንዲደረግ መፈቀዱን እናሰላስልበት) ለማንኛውም፤ በትግራይ ተዋሕዷውያን ላይ የሚካሄደው ጭፍጨፋ በጣም ብዙ ነገሮችን አሳይቶናል፤ ማን ምን እንደሆነ አስተምሮናል።
ለማንኛውም የኢትዮጵያም የተዋሕዶም ጠላት ማን እንደሆነ ዛሬ በግልጽ ታውቋልና የትግራይ አባቶች ከሥላሴ እርዳታ ጋር የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቅርሶች በጊዜው አሽሽተው ለመደበቅ በቅተዋል የሚል ዕምነት አለኝ።
“ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም”[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲]
❖❖❖ ጥንታዊው የደብረ ምሕረት ጨለቖት (ሀገረ ማርያም) ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ፣ ከባቢ መቐለ በ ፲፯፻፹፭/ 1785 ዓ.ም ተመሠረተ ❖❖❖
በ ፲፰/18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተመሰረተው የተለያዩ ነዋያ ቅዱሳትን የያዘው የጨለቖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን
ጨለቖት ትግራይ ክፍለ ሀገር በእንደርታ አውራጃ የሚገኝ ታሪካዊ ቦታ ነው። ይህ ቦታ ከመቀሌ በስተደቡብ ከሕንጣሎ ከተማ በስተሰሜን የሚገን ሲሆን እንደ ሰንሰለት በተያያዙ ተራራዎች የተከበበ ነው። የቦታው አቀማመጥ ወይና ደጋ ስለሆነ የአካባቢው አየር እንደየወቅቱ ይለዋወጣል። በክረምት ቀዝቃዛ ሲሆን በበጋ ወራት ደግሞ በጣም ይሞቃል።
በሰሜንና በደቡብ ጨለቖትን እየከፈለ ከምስራቅ ወይም ምዕራብ የሚፈስ ወንዝ አለ። ወንዙ በክረምት ወራት ይሞላል። በበጋ ግን መጠኑ የቀነሰ ውሃ የሚወርድበት ሲሆን ከሁለት ቦታ እየተነፈሰ ለመስኖ ተግባር ትልቅ አገልግሎት ይሰጣል።
የጨለቖት ነዋሪ ህዝብ ወንዙን ገድቦ የሚዘራቸው የእህል ዓይነቶች በቆሎ፣ ገብስ፣ ጢፍ፣ ስንዴ…የመሳሰሉት ሲሆን ከአትክልትና ፍራ ፍሬ ዓይነትም ጌሾ፣ ሽንኩርት፣ በርበሬ፣ ሎሚና ብርቱካን ወዘተ ተክሎ እያሳደገ ይጠቀማል።
❖ ሀገረ ማርያም ❖
ጨለቖት መጀመሪያ “ሀገረ ማርያም” ይባል ነበር። ሀገረ ማርያም የተባለበት ምክኒያትም በ፲፫/13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት አፄ ዐምደ ጽዮን ከጨለቖት በላይ ወደ ምስራቅ ባለ በሁለት ዳገት የተከበበ ጉድጓድ ቦታ ቤተ ክርስቲያን ሰርተው ታቦተ ማርያምን አስገብተው ሲያበቁ በዙርያዋ ያለውን መሬት በመስቀልና በዕጣን አስከልለው ያም ማለት መስቀልና ማዕጠነት ተይዞ የተሰጠው ርስት እየተዞረ ለታቦቲቱ አገልጋዮች ካህናት ማደሪያ ሰጥተው ሌሎች ባላባቶቹ ርስታችን ነው ብለው እንዳይካፈሉ በአዋጅና በውግዘት ይህች “ሀገረ ማርያም” ናት ብለው ስለሰየሟት “ሀገረ ማርያም” ተብላለች። ዳግመኛም ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ይዘው ሲመጡ ጨለቖት ውስጥ ስላደሩ መስቀሉ ያረፈበት ቦታ እስካሁን ድረስ ቤተ መስቀል ይባላል።
❖ ታላቅ ራእይ የተለጸበት ሱባኤ ❖
መምህር ገብረ ሥላሴ ማዶ ጭኽ በሚባል የቅዱሳን መጸለያ ቦታ ሱባኤ ገብተው ሲጸልዩ ከሰማይ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን እስከሚሠራበት ቦታ ቀስተ ደመና ተተክሎ ሦስት ጌቶች ቅዱሳን መላእክትን አስከትለው ሲወርዱና ቀስተ ደመናው በቆመበት ቦታ ሲያርፍ በራዕይ አዶ እርሳቸውም በሱባኤያቸው ወጥተው ያዩትን አምላካዊ ራእይ ለደጃዝማች ወልደ ሥላሴ ለብቻቸው ነገሯዋቸው። ደጃዝማችም በነገሩ እየተደሰቱ ከመምህር ጋር ሆነው ከሕንጣሎ ከተማ ወደ ሰሜን አቅጣጫ አፍጎል ወደ ሚባለው ቦታ መጥተው ከአደጉበት ጀመሮ እስከ ባሕርያቱ ድረስ በጥድና፣ በወይራ፣ በዋንዛም… የተሸነፈ ታላቅ ወንዝ አገኙ። መምህሩ እየመሩ በጫካው ውስጥ ለውስጥ አብረው ሲጓዙ ወለል ያለ መልክ ባዩ ጊዜ “ዝየ ይትሐነጽ ቤተ እግዚአብሔር”…ማለት የእግዚአብሔር ማመስገኛ ቤተ መቅደስ ከዚህ ይሠራል፤ በዚህ መልክ መካከል ያለው ቆት የሚባለው ትልቅ ዛፍም በጠቅላላ ለቤተ ክርስቲያኑ መዝጊያና መስኮት ይበቃል ብለው ነገርዋቸው።
ያን ጊዜ ቆት በሚባለው ትልቁ ዛፍ ስርም ሁለት አንበሶች ተኝተውበት ነበርና ደጃዝማች ወልደ ሥላሴ ደንግጠው ጦር ወርውረው ሁለቱን ገደሉዋቸው። በዱሩ ውስጥ ተሰውሮ ሲጸልይ የነበረው ባሕታዊ ወጥቶ መላእክት ገደልህ እንጂ እናብስት አልገደልህም ንስሐ ግባ ብሏቸው ተሰወረ። እርሳቸውም መምህራን በወሰኑላቸው ቀኖና መሠረት ኃጢአታቸውን ለማስተሰረይ ንስሐ ገብተናል ከዚህ በኋላ በአዋጅ በተሰበሰበው ሕዝብ ጫካው ተመንጥሮ ቆት የሚባው ትልቁ ዛፍ ተቆረጠ። ቤተ ክርስቲያኑ የሚሠራበት ቦታ ተስተካክሎ ተደለደለ።
❖ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ መመሥረት ❖
በዘመነ ማቴዎስ ሰኞ መስከረም ፱/9 ቀን 1785 ዓ.ም በጠቢባኑ መሪነት ከሦስት ክፍል ተከፍሎና ተለክቶ መሠረቱ ተቆፈረ የመሠረቱ ጥልቀት አስር ሜትር ሆኖ በጥቁር ድንጋይ ከተነጠፈ በኋላ በላይ ላይ አሞሌ ጨው እንደ ብሎኬት ተደርድሮ በንጣፍነት ተሠራ። እንዲህ የተደረገበት ምክንያትም ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራባቸው ዕንጨት ነክ የሆኑ እቃዎችና ዐምደ ወርቆች በምስጥ እንዳይበሉ ለመከላከል ነው። የቤተ ክርስቲያኑ መቅንና መድረክ ገብን መዝጊያ እንዲሁ በልዩ ልዩ ጌጥ የተሠሩ አአማድ የተዘጋጁት ከተቆረጠው ትልቁ የቆት ዛፍ ስለሆነ አናጢዎቹና ሠራተኞቹ ሕዝቡም ሁሉ ዛፍን ጨለቖት እያሉ በትግርና ቋንቋ አደነቁት “ጨለቖት” ማለት በአማርኛ ቋንቋ መልካም ቆት ማለት ነው፤ በብዙ ቀን በኋላም ቃሉን መሠረት በማድረግ ያገሩ ስም ጨለቖት ተብሎ ተጠራ።
❖ የቤተ ክርስቲያኑ ውስጣዊና አፍአዊ ቅርጽ ❖
የቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ክብ ሆኖ በሦስት ክፍል የተከፈለ ነው። ውስጣዊ ክፍል ቤተ መቅደስ መካከለኛው ቅድስት ሦስተኛው ደግሞ ቅኔ ማኅሌት ይባላል። ቤተ መቅደሱ ጸሎተ ቅዳሴ የሚደርስበት ቅዱስ ቁርባንና መስዋዕት የሚቀርብበት ነው። ከቀዳስያን በቀር ሌላ ሰው አይገባበትም። ሁለተኛው ክፍል ቅድስትም ቀሳውስትና ዲያቆናት ሰዓታትና ስብሐተ ፍቁር የሚያደርሱበት ምዕመናንም የኅሊና ጸሎት የሚጸልዩበት ነው። ቅኔ ማህሌቱም ሊቃውንትና መዘመራን ያሬዳዊ ማኅሌት የሚያደርሱበት ምዕመናንም የሚጸልዩበት ነው። በጉልላት ላይም ታላቅ መስቀል አለበት።
ቤተ ክርስቲያኑ ሊሠራ ሲል ወልደ ሥላሴ ታመው ስለነበር ፍጻሜውን ሳያዩ እንዳይሞቱ ከመስጋታቸው የተነሳ ሥራው በተጀመረበት ዓመት እንዲያልቅ ስለወሰኑ ወደ ላይ ያለው ከፍታ ከስፋቱ ጋር የተመዛዘነ አይደለም። ስለዚህ የተፈለገውን ያህል ወደ ላይ ሳይረዝም ባጭሩ ጥራው አልቆ ማክሰኞ ሐምሌ ፬/4 ቀን 1785 ዓ.ም ታቦቱ ገባ። የቅዳሴ ቤቱ በዓልም በታላቅ ክብር ከተከበረ በኋላ የቤተ ክርስቲያኑ ስመ ማዕረግ “ደብረ ተድላ” ተብሎ ተሰየመ።
❖ የቤተ መቅደሱ የግድግዳ ላይ ሥዕል ❖
የቤተ ክርስቲያኑ ስዕል የተሳለው ሠዓሊ አለቃ ኃይሉ በተባሉ ባለሙያ ነው። የተሳለውም ከሌላው ቦታ በተለየ መልኩ የመቅደሱና የቅድስቱ የውጭ ግድግዳ በሙሉ ሲሆን በቅድስቱ የውጭ ግድግዳ ዙሪያ የተሳለው አቡቀለምሲስ ዮሐንስ ያየው ራእይ ሁሉ ነው። በተለይም ከመቅደሱ ፊት ለፊት የምስለ ፍቁር ወልዳ ሥዕል ዕፁብ ድንቅ በሆነ ህብረ ቀለም የተሳለ ሲሆን በተለያዩ ጊዜ በመሰሉና ረዘም ያለ ጊዜ በመውሰዱ የራስ ወልደ ሥላሴ ስም አንዳንድ ጊዜ ደጃዝማች አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ራስ እየተባለ ተጽፎአል። በግድግዳው ላይ ብቻ ሳይሆን በየበሮቹ ላይ ያሉት ስዕሎች ሁሉ ሳይቀሩ ለተመልካች እጅግ የሚያስደንቁ ሆኖ ይታያል፡፤ የቤተክርስቲያኑ ሥ ዕልና በመስከረም ወር ፲፱፻፸፮/1976 ዓ.ም ተጀመሮ በ፯/7 ዓመታት ተፈጽሟል ይባላል።
❖ የቤተ ክርስቲያኑ ንዋያተ ቅድሳት ❖
👉 ከእንግሊዝ ንጉሥ ጊዮርጊስ ሣልሳዊ በስጦታ የተላኩት የሚከተሉት ናቸው፦
❖ የወይን ዘለላ የተቀረፀበት ባለ መክደኛ ድምፅ
❖ ትልቅ ቋሚ መስቀልና መዝሙረ ዳዊት
❖ የቅዱስ ጊዮርጊስ ምስል ከነፈረሱ
❖ መንገር ታቦት ዘውድና አክሊል
❖ ልዮ ልዩ የዜማ ስልት የሚያሰማ ባለምት ኦርጋኖን
❖ ልብሰ መንግስትና ሌሎችም በወርቅ ያጌጡ ብዙ አልባሳት
❖ ብዙ መስቀሎችና ከዕረፈ መስቀሎቻቸው ጋር
👉 ከእነዚህም አልባሳቱ በወርቅ ያጌጡ እቃዎቹም ከወርቅ የተሠሩ ናቸው። ራስ ወልደ ሥላሴም እነዚህን ስጦታዎች ሁሉ በምስጋና ተቀብለው በፊርማቸው ተረክበዋቸዋል። ከውጭ በመጡ አቡስትሊ በተባሉ ግብፃዊ ጠቢብ የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳትም የሚከተሉት ናቸው፦
❖ ክወርቅና ከብር የተሠሩ ዘውዶች
❖ መስቀሎች፣ ፃህልና ጽዋዕ
❖ ከበሮ፣ መቋሚያና ጸናጽል
❖ ልዩ ልዩ ያጌጡ አልባሳትና መነሳነስ
❖ የወይን ማጣሪያ ወንፊት
❖ የወርቅ ዙፋንና ወንበር፣ የሐር ምንጣፎች
ጠቢባኑ እነዚህን ሁሉ ሠርተው ለራስ ወልደ ሥላሴ አስረክበዋቸዋል። እርሳቸውም አይተው እጅግ ደስ ስላላቸው በሚልዮን የሚቆጠር ወርቅ ሸልመዋቸዋል ይባላል።
በቤተ ክርስቲያኑ ቤተ መጻሕፍትም ብዙ መጻሕፍት ይገኛሉ። በተለይም ከመጻሕፍቱ መካከል ሽፋኑ ወይም ገሉ በወርቅ የተለበሰ ወርቅ ወንጌልና የሦስት መቶ ዐስራ ስምንት ሊቃውንት ሥዕል ያለበት ሃይማኖት አበው ይገኙበታል።
❖ መደምደሚያ ❖
የ ጨለቖት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው በተደረገው ተአምራትና በተለገጸው ራዕይ መሠረት ነው። በተደረገው ተአምራት መባሉ መምህር ገብረ ሥላሴ የሁለት ቀን ሬማ ጸልየው ካስነሱ በኋላ ደጃዝማች ወልደ ሥላሴን ከእንግዲህ ወደዚህ አይምጡ በከተማዋ የሥላሴን ቤተ ክርስቲያን አሠርተው ከዚያ ይጸልዩ ብለው ስለመከርዋቸው ነው።
በአሁን ጊዜ የሃገር ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ በቦታው ላይ ያሉትን በርካታ የታሪክ ቅርሶች የዝመነ መሳፍንት ታሪክና ቅርስ ዝክር እና በዚያ ዝመን ቤተ ክርስቲያን የነበራትን ሕይወት ማስታዋሻ የሆኑ ሐብቶች መጠበቂያ የሚሆን ቤተ መዘክር የማሠራት እቅድ ያላቸው ሲሆን ይኽውም ከፍተኛ ድጋፍና ማበረታቻ የሚያስፈልገው ነው። (በረከታቸው ይደርብንና ብፁዕ አባታችን ከማረፋቸው በፊት የተጻፈ ነው)
በተገለጸው ራእይ መባሉም መምህር ገብረ ሥላሴ የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሚሠራበት ቦታ እንዲገለጽላቸው ሱባኤ በገቡ ጊዜ በቀስተ ደመና ምልክት ቦታው ስለታያቸው ነው። (የሉሲፈርን ባለ ሁለት ቀለማት ብቻ እና ባለ አምስት ፈርጥ ኮከብ ያረፈባቸውን ባንዲራ የምትይዙ ትግራዋይን ልብ በሉ! ዋ!)በተአምራትና በራእይ እየተመሩ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው የሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ ጥረት ያደረጉ ሁለቱ ሰዎች ራስ ወልደ ሥላሴና መምህር ገብረ ሥላሴ በዘርፍና ባለቤት ሙያ በስመ ሥላሴ መጠራታቸው ቤተ ክርስቲያኑን ለማሠራት መመረጣቸውን ስለሚያመለክት እጅግ ያስደንቃል። ስምን መልአክ ያወጣዋል እንዳሉ (ሉቃ. ፩፥፴፩) ብለው መምህር ያሬድ የታርክ ሐተታቸውን አጠቃሏል።
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፮]✞✞✞
፩ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤
፪ እግዚአብሔር ያዳናቸው፥ ከጠላቶች እጅ ያዳናቸው ይናገሩ።
፫ ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከባሕር፥ ከየአገሩ ሰበሰባቸው።
፬ ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ተቅበዘበዙ፤ የሚኖሩበትንም ከተማ መንገድ አላገኙም።
፭ ተራቡ ተጠሙም፥ ነፍሳቸውም በውስጣቸው አለቀች።
፮ በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው፤
፯ ወደሚኖሩበት ከተማ ይሄዱ ዘንድ የቀና መንገድን መራቸው።
፰ ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ምሕረቱም እግዚአብሔርን ያመስግኑ፤
፱ የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና።
፲ በጨለማ በሞትም ጥላ የተቀመጡ፥ በችግር በብረትም የታሰሩ፤
፲፩ የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ዐመፁ፥ የልዑልንም ምክር ስለ ናቁ፥
፲፪ ልባቸው በድካም ተዋረደ፤ ታመሙ የሚረዳቸውም አጡ።
፲፫ በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ በመከራቸውም አዳናቸው።
፲፬ ከጨለማና ከሞት ጥላ አወጣቸው፥ እስራታቸውንም ሰበረ።
፲፭ ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ምሕረቱም እግዚአብሔርን ያመስግኑ፤
፲፮ የናሱን ደዶች ሰብሮአልና፥ የብረቱንም መወርወሪያ ቈርጦአልና።
፲፯ ስለ ዓመፃቸው ሰነፉ፥ ስለ ኃጢአታቸውም ተቸገሩ።
፲፰ ሰውነታቸው መብልን ሁሉ ተጸየፈች፥ ወደ ሞትም ደጆች ቀረቡ።
፲፱ በተጨነቁ ጊዜም ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።
፳ ቃሉን ላከ ፈወሳቸውም፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው።
፳፩ ለሰው ልጆች ስላደረገው ተኣምራት ስለ ምሕረቱም እግዚአብሔርን ያመሰግኑ፤
፳፪ የምስጋና መሥዋዕትንም ይሠውለት፥ በእልልታም ሥራውን ይንገሩ።
፳፫ በመርከቦች ወደ ባሕር የሚወርዱ፥ በታላቅ ውኃ ሥራቸውን የሚሠሩ፥
፳፬ እነርሱ የእግዚአብሔርን ሥራ፥ በጥልቅም ያለችውን ድንቁን አዩ።
፳፭ ተናገረ፥ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፥ ሞገድም ከፍ ከፍ አለ።
፳፮ ወደ ሰማይ ይወጣሉ ወደ ጥልቅም ይወርዳሉ፤ ነፍሳቸውም በመከራ ቀለጠች።
፳፯ ደነገጡ እንደ ስካርም ተንገደገዱ፥ ጥበባቸውም ሁሉ ተዋጠች።
፳፰ በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው።
፳፱ ዐውሎንም ጸጥ አደረገ፥ ሞገዱም ዝም አለ።
፴ ዝም ብሎአልና ደስ አላቸው፤ ወደ ፈለጉትም ወደብ መራቸው።
፴፩ ለሰው ልጆች ስላደረገው ተአምራት ስለ ምሕረቱም እግዚአብሔርን ያመስግኑ።
፴፪ በአሕዛብ ጉባኤ ከፍ ከፍ ያድርጉት፥ በሽማግሌዎችም ሸንጎ ያመስግኑት።
፴፫ ወንዞችን ምድረ በዳ፥ የውኃውንም ምንጮች ደረቅ አደረጋቸው፤
፴፬ ከተቀመጡባት ክፋት የተነሣ ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት።
፴፭ ምድረ በዳን ለውኃ መቆሚያ፥ ደረቁንም ምድር የውኃ ምንጮች አደረገ።
፴፮ በዚያም ራብተኞችን አስቀመጠ፥ የሚኖርባትንም ከተማ ሠሩ።
፴፯ እርሻዎችንም ዘሩ ወይኖችንም ተከሉ፥ የእህልንም ሰብል አደረጉ።
፴፰ ባረካቸውም እጅግም በዙ፤ እንስሶቻቸውንም አላሳነሰባቸውም።
፴፱ እነርሱ በችግር በክፋት በጭንቀት ተዋረዱ እያነሱም ሄዱ፤
፵ በአለቶችም ላይ ኅሣርን፥ አፈሰሰ፥ መንገድም በሌለበት በምድረ በዳ አሳታቸው።
፵፩ ችግረኛንም ከችግሩ ረዳው፤ እንደ በጎች መንጋ ወገን አደረገው።
፵፪ ቅኖች ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፤ ኃጢአትም ሁሉ አፍዋን ትዘጋለች።
፵፫ ጥበበኛ የሆነና ይህን የሚጠብቅ ማን ነው? እርሱ የእግዚአብሔርን ምሕረት ያስተውላል።
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፰]✞✞✞
፩ አምላክ ሆይ፥ ምሥጋናዬን ዝም አትበል፥
፪ የኃጢአተኛ አፍና የተንኰለኛ አፍ በላዬ ተላቅቀውብኛልና፤ በሽንገላ አንደበትም በላዬ ተናገሩ፤
፫ በጥል ቃል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተሰለፉብኝ።
፬ በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።
፭ በመልካም ፋንታ ክፉን በወደድኋቸውም ፋንታ ጠላትነትን መለሱልኝ።
፮ በላዩ ኃጢአተኛን ሹም፤ ሰይጣንም በቀኙ ይቁም።
፯ በተምዋገተም ጊዜ ተረትቶ ይውጣ፤ ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት።
፰ ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፤ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ።
፱ ልጆቹም ድሀ አደግ ይሁኑ፥ ሚስቱም መበለት ትሁን።
፲ ልጆቹም ተናውጠው ይቅበዝበዙ ይለምኑም፥ ከስፍራቸውም ይባረሩ።
፲፩ ባለዕዳም ያለውን ሁሉ ይበርብረው፥ እንግዶችም ድካሙን ሁሉ ይበዝብዙት።
፲፪ የሚያግዘውንም አያግኝ። ለድሀ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።
፲፫ ልጆቹ ይጥፉ፤ በአንድ ትውልድ ስሙ ይደምሰስ።
፲፬ የአባቶቹ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ትታሰብ፤ የእናቱም ኃጢአት አትደምሰስ።
፲፭ በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ይኑሩ፤ መታሰቢያቸው ከምድር ይጥፋ።
፲፮ ምሕረትን ያደርግ ዘንድ አላሰበምና ችግረኛንና ምስኪንን ልቡ የተሰበረውንም ሰው ይገድል ዘንድ አሳደደ።
፲፯ መርገምን ወደደ ወደ እርሱም መጣች፤ በረከትንም አልመረጠም ከእርሱም ራቀች።
፲፰ መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፥ እንደ ውኃም ወደ አንጀቱ፥ እንደ ቅባትም ወደ አጥንቱ ገባች።
፲፱ እንደሚለብሰው ልብስ። ሁልጊዜም እንደሚታጠቀው ትጥቅ ይሁነው።
፳ ይህ ሥራ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሚያጣሉኝ በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ነው።
፳፩ አንተ ግን አቤቱ ጌታዬ፥ ስለ ስምህ ምሕረትህን በእኔ ላይ አድርግ፤ ምሕረትህ መልካም ናትና አድነኝ።
፳፪ እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
፳፫ እንዳለፈ ጥላ አለቅሁ፥ እንደ አንበጣም እረገፍሁ።
፳፬ ጕልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።
፳፭ እኔም በእነርሱ ዘንድ ለነውር ሆንሁ፤ ባዩኝ ጊዜ ራሳቸውን ነቀነቁ።
፳፮ አቤቱ አምላኬ፥ እርዳኝ፥ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።
፳፯ አቤቱ፥ እጅህ ይህች እንደ ሆነች፥ አንተም ይህችን እንዳደረግህ ይወቁ።
፳፰ እነርሱ ይራገማሉ አንተ ግን ባርክ፤ በእኔ ላይ የሚነሡ ይፈሩ፥ ባሪያህ ግን ደስ ይበለው።
፳፱ የሚያጣሉኝ እፍረትን ይልበሱ፤ እፍረታቸውን እንደ መጐናጸፊያ ይልበሱአት።
፴ እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰግነዋለሁ። በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ፤
፴፩ ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ በድሀ ቀኝ ቆሞአልና።
________________________________________
Like this:
Like Loading...