Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጨለማ’

ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው፤ አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 13, 2022

❖❖❖[፪ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፪]❖❖❖

  • ፩ ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤
  • ፪ ብዙዎችም በመዳራታቸው ይከተሉአቸዋል በእነርሱም ጠንቅ የእውነት መንገድ ይሰደባል።
  • ፫ ገንዘብንም በመመኘት በተፈጠረ ነገር ይረቡባችኋል፤ ፍርዳቸውም ከጥንት ጀምሮ አይዘገይም ጥፋታቸውም አያንቀላፋም።
  • ፬ እግዚአብሔር ኃጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥
  • ፭ ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን አድኖ በኃጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውኃ ካወረደ፥
  • ፮ ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥
  • ፯-፰ ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥
  • ፱-፲ ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን፥ በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤
  • ፲፩ ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም።
  • ፲፪ እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤
  • ፲፫ የዓመፃቸውን ደመወዝ ይቀበላሉ። በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፤ ነውረኞችና ርኵሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤
  • ፲፬ ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትንም የማይተዉ ዓይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።
  • ፲፭ ቅንን መንገድ ትተው ተሳሳቱ፤ የባሶርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከተሉ፤ እርሱ የዓመፃን ደመወዝ ወደደ፥
  • ፲፮ ነገር ግን ስለ መተላለፉ ተዘለፈ፤ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን እብድነት አገደ።
  • ፲፯ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው እነዚህ ውኃ የሌለባቸው ምንጮች በዐውሎ ነፋስም የተነዱ ደመናዎች ናቸው።
  • ፲፰ ከንቱና ከመጠን ይልቅ ታላቅ የሆነውን ቃል ይናገራሉና፥ በስሕተትም ከሚኖሩት አሁን የሚያመልጡትን በሥጋ ሴሰኛ ምኞት ያታልላሉ።
  • ፲፱ ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው። አርነት ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጡአቸዋል፤ ሰው ለተሸነፈበት ለእርሱ ተገዝቶ ባሪያ ነውና።
  • ፳ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።
  • ፳፩ አውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና።
  • ፳፪ ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ። የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

The Sun Disappeared & The Day Turned into Darkness in Antichrist Turkey

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2021

💭 A terrible storm hits Antalya, Turkey – which is waging a NATO green-lighted Drone Jihad – unleashing war crimes against the two most ancient Christian nations of the world: Armenia and Ethiopia

💭 በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ፀሀይ ጠፋች፤ ቀኑም ወደ ጨለማ ተለወጠ

በኔቶ ፈቃድ የድሮን ጂሃድ የምታካሂደው ቱርክ በከባድ አውሎ ንፋስና ጎርፍ ተመታች ፥ በሁለቱ ጥንታዊ የዓለማችን የክርስቲያን ሃገራት በአርሜኒያ እና ኢትዮጵያ ላይ የጦር ወንጀል እየፈፀመች ያለችው ቱርክ አቅበቅዝብዟታል፤ ከአባሪዎቿ ጋር መጥፊያዋ ተቃርቧል።

[Luke 21:25]

There will be signs in sun and moon and stars, and on the earth dismay among nations, in perplexity at the roaring of the sea and the waves„

[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩፳፭]

“በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤”

ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፤ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ።”

[ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ ፪፥፰]

፩ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፤

፪ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘላለምም ጀምሮ እንደ እነርሱ ያለ አልነበረም፥ ከእነርሱም በኋላ እስከ ብዙ ትውልድ ድረስ እንደ እነርሱ ያለ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።

፫ እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም።

፬ መልካቸው እንደ ፈረስ መልክ ነው፥ እንደ ፈረሶችም ይሮጣሉ።

፭ በተራራ ላይ እንዳሉ ሰረገሎች ድምፅ፥ ገለባውንም እንደሚበላ እንደ እሳት ነበልባል ድምፅ፥ ለሰልፍም እንደ ተዘጋጀ እንደ ብርቱ ሕዝብ ያኰበኵባሉ።

፮ ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፤ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቍራል።

፯ እንደ ኃያላን ይሮጣሉ፥ እንደ ሰልፈኞችም በቅጥሩ ላይ ይወጣሉ፤ እያንዳንዱም በመንገዱ ላይ ይራመዳል፥ ከእርምጃቸውም አያፈገፍጉም።

፰ አንዱ ካንዱ ጋር አይጋፉም፥ እያንዳንዱም መንገዱን ይጠበጥባል፤ በሰልፍ መካከል ያልፋሉ፥ እነርሱም አይቈስሉም።

፱ በከተማም ያኰበልላሉ፥ በቅጥሩም ላይ ይሮጣሉ፤ ወደ ቤቶችም ይወጣሉ፥ እንደ ሌባም በመስኮቶች ይገባሉ።

፲ ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፤ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ።

፲፩ እግዚአብሔርም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ይሰጣል፤ ሰፈሩ እጅግ ብዙ ነውና፥ ቃሉንም የሚያደርግ እርሱ ኃያል ነውና፤ የእግዚአብሔርም ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነውና ማንስ ይችለዋል?

፲፪ አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።

፲፫ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።

፲፬ የሚመለስና የሚጸጸት እንደ ሆነ፥ ለአምላካችሁም ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቍርባን የሚሆነውን በረከት የሚያተርፍ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

፲፭ በጽዮን መለከትን ንፉ፥ ጾምንም ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ፥

፲፮ ሕዝቡንም አከማቹ፥ ማኅበሩንም ቀድሱ፥ ሽማግሌዎቹንም ሰብስቡ፥ ሕፃናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ፤ ሙሽራው ከእልፍኙ፥ ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ።

፲፯ የእግዚአብሔርም አገልጋዬች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ። አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብ መካከል። አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ? ይበሉ።

፲፰ እግዚአብሔርም ስለ ምድሩ ቀና፥ ለሕዝቡም ራራለት።

፲፱ እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን። እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፥ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።

፳ የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረበዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፤ እርሱም ትዕቢትን አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ።

፳፩ ምድር ሆይ፥ እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አድርጎአልና አትፍሪ፥ ደስም ይበልሽ፥ እልልም በዪ።

፳፪ እናንተ የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድር በዳው ማሰማርያ ለምልሞአልና፥ ዛፉም ፍሬውን አፍርቶአልና፥ በለሱና ወይኑም ኃይላቸውን ሰጥተዋልና አትፍሩ።

፳፫ እናንተ የጽዮን ልጆች፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር የፊተኛውን ዝናብ በጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ ቀድሞውም የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።

፳፬ አውድማዎችም እህልን ይሞላሉ፥ መጥመቂያዎችም የወይን ጠጅንና ዘይትን አትረፍርፈው ያፈስሳሉ።

፳፭ የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።

፳፮ ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።

፳፯ እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።

፳፰ ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤

፳፱ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ፤

፴ በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።

፴፩ ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።

፴፪ እንዲህም ይሆናል፤ የእግዚአብሔር ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምስራች የሚሰበከላቸው ይገኛሉ።

________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ ኡራኤል | የኮከቧ ብርሃን አንበሳን ያሳያል | ዋ! ግማሽ ጨረቃ! ዋ! ፒኮክ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 1, 2020

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ

ኮከብ እንደ ፀሐይ የራሷ ብርሃን አላት፤ ታበራለች ፥ ጨረቃ ግን ብርሃን ትሰርቃለች እንጅ የራሷ ብርሃን የላትም፣ ጨለማ ናት።

ኡራኤል የሚለው ስም `ኡርእና ኤልከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ኡራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃንማለት ነው። በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ የተመሰረቱ ገዳማት በቅዱስ ኡራኤል መሪነት ነው።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፱፡፩፥፪]

ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል። ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።

የቅዱስ ኡራኤል ፀሎት በያለንበት ይድረስ!

_________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አርሲ ነገሌ | ጨለማው በቡሄ ብርሃን ድል ተነሳ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 19, 2020

በመጨረሻም ብርሃን ጨለማን ድል ይነሳል፤ የብርሃነ መስቀሉ ልጆች የዋቄዮአላህን የድቅድቁ ጨለማ አርበኞች ከአርሲ እና ኦሮሚያ ከተባለው ህገወጥ ክልል ጠራርገው ያስወጧቸዋል።

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ፀረ-ኢትዮጵያው የፋሽስት ኦሮሞ ሠራዊት ጡንቻውን ለአዲስ አበባ አሳየ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 31, 2019

___________________________

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የፀሐይ ግርዶሽ ፥ ጋኔን ፀሐይን በላት | የዋቄዮ አላህ እና የሰው አጋንንት አሁን ለማጥፋትና ለማሳት ተዘጋጅተዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 26, 2019

ተጠንቀቁ!!! ዲያብሎስ ሰይጣን ብርሃንን እየተዋጋ ነው።

ባለፈው ጊዜ ሊሲፈራውያኑ አሽከራቸውን ግራኝ አብዮት አህመድ አሊን የሸለሙት ሙሉ ጨረቃ እስክትወጣ ድረስ በመጠበቅ ነበር፤ አሁን ደግሞ የፀሐይ ግርዶሽ ተከስቶ ጨለማ በሚሰፍንበት ወቅት በህዝበ ክርስቲያን ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ከአጋንንት መናኸሪያ ከሳውዲ መካ ትዕዛዝ ተላልፏል። በትናንትናው ዕለት የአክሱም ኃውልትን የሚመለከት ቪዲዮ ያቀረብኩት በምክኒያት ነበር ማለት ነው፤ በጊዜው አላወቅኩትም ነበር። እንደሚታወቀው ጣዖት አምላኪዎቹ፡ የአክሱም ኃውልትን ጫፍ/ራስ ለሳባውያን አምላክ አልማቃህየግማሽ ጨረቃ ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጓል። ይላሉ። እንግዲህ የጨረቃ አምላክ “አልማቃህ” የሙስሊሞች አምላክ ነው ማለት ነው። በአክሱም መስጊድ የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው አንዱ ምክኒያት ይህ ነው።

[፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፭፥፰፡፱]

በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።

[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፲፪፥፯፡፰]

ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው። ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፪፥ ፩፡ ፱]

ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።

እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።

ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥

ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።

አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።

ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።

በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።

ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ከ42 ዓመታት በፊት ቀይ-ሽብር ሰፍኖ በነበረበት ዘመን መብራት በኒው-ዮርክ ጠፍቶ እንደነበረው ዛሬም ተደገመ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 14, 2019

ባቢሎናውያኑ ለሃገራችን ገንዘቡን እና ድጎማውን ሲነፍጉን፣ በአዲስ አበባ ትራንስፎርመሮችን ሆን ብለው ሲያሰርቁና መብራትን ሲከለክሉን የባቢሎን ኒው ዮርክ ትራንስፎርመሮች መፈንዳት ጀመሩ። ዋው!

በትናንትናው ዕለት በኒው ዮርክ ከተማ ሙሉ በሙሉ መብራት በመጥፋቱ ለብዙ ሰዓታት የቆየ ጨለማ ሰፍኖ ነበር፣ የምድር ባቡሮች ቆመውና የከተማዋ እስትንፋስም ቀጥ ብሎ ነበር።

ይህ የተከሰተው ከ42 ዓመታት በፊት፡ እ..1977 .ም በኒው ዮርክ ተመሳሳይ ችግር ከሰፈነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው።

ልክ በዚህ ጊዜ፡ በዚህ ዓመተ ምህረት ነበር በሃገራችን አረመኔው መንግስቱ ኃይለ ማርያም በሚሊየን የሚቆጠሩ ዘመዶቻችንን በቀይ ሽብር መግደል የጀመረው።

ምናልባት የትናንትናው የኒው ዮርክ ማንሃተን መብራት መጥፋት በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን ከተጀመረው የገዳይ አልአብይ ዳግማዊ ቀይ ሽብር ዘመቻ ጋር የሚያገናኘው ነገር ይኖር ይሆናል። ምናልባት የሚጠቁመን ነገር ሊኖር ይችላል፤ ዓለም እኮ ትንሽ ናት።

በጣም ይገርማል፡ በሉሲፈራውያኑ ቀስቃሽነት በመንግስቱ ኃይለ ማርያም ኮሙኒስታዊ አብዮት ከ42 ዓመታት በፊት ታይቶ የነበረው ጭካኔ ዛሬም በ42 ዓመት እድሜው አብዮት አህመድ በመደገም ላይ መሆኑ በጣም ያሳዝናል።

ኒው ዮርክ እና ለንደን የክርስቶስ ተቃዋሚው የገንዘብና ምጣኔ ኃብት ዋና ከተሞች ሲሆኑ ፥ በርሊን የፖለቲካው፣ ቱርክ እና አረቢያ ደግሞ የመንፈሳዊው መናኽሪያዎች ናቸው።

___________________

Posted in Curiosity, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ለሺህ ዓመታት በጨረቃ አምላኪዎቹ እና አጋሮቻቸው የታረዱት ክርስቲያኖች ደም ጨረቃዋ ላይ ታይቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 29, 2018

ያለፈው ሐምሌ ፳ ፪ሺ፲ (July 27, 2018) ኃይለኛ መልዕክቶችን የያዙ ክስተቶች የታዩበት ዕለት ነበር። አንዱ የጨረቃ ግርዶሽ በመባል ይታወቃል። ይህም የምድር ጥላ ጨረቃዋ ላይ ሲያርፍ ደማማ የሆነውን ቀለም በአስደናቂ መልክ አስይቶናል (ደም እየፈሰሰ)። ይህን ለ፩ ሰዓት ከ፵፫ ደቂቃ የወሰደ ተፈጥሯዊ ክስተት ስመለከት ወዲያው የታየኝ፦

ፍፃሜ ዘመን ላይ ደርሰናል፤ እዚህች ምድራችን ላይ በሳጥናኤል አርበኞች የፈሰሰውን የንጹሐን ደም ያው እግዚአብሔር በቪዲዮ ቀርጾ እያሳየን እኮ ነው

የሚለው ስዕል ነበር።

አዎ! በሊቢያና አረብ አገራት የተሰዉትን ክርስቲያን ወገኖቻችንን እንዲሁም በመስቀል አደባባይ በግብጻውያን እጅ ደሙ የፈሰሰበትን ወንድም ስመኘውን፡ እኛ ደካሞቹ ቆየት ብለን እንረሳቸው ይሆናል፤ እግዚአብሔር ግን አይረሳቸውም።

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: