Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጥቅምት ፪ሺ፲’

ምዕመናኑን ፀጥ ያሰኘ ስብከት | ቋንቋን ለምን እንደ ሃይማኖት እንጠቀማለን? ከሆነማ ሁላችንም በግእዝ መነጋገር አለብን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 15, 2018

ቋንቋን እግዚአብሔር አልፈጠረም፤ በቋንቋ መንግስተ ሰማያት አይገባም፡ ነገር ግን የመጀመሪያው አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው የመጀመሪያው ቋንቋ ግእዝ ስለሆነ እርስበርስ ለመግባባት እንችል ዘንድ ሁላችንም አሁን ግእዝ ቋንቋን ማወቅ ሊኖርብን ነው።”

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡ አባታችን! (የካሜራዬን ባትሪ መለወጥ ነበረብኝና ሁሉም ስብከታቸው አልተካተተም፡ ይቅርታ!)

አዎ! ዲያብሎስ በቋንቋ እርስበርሳችን እንድንጨፋጨፍና በእንግሊዝኛ ወይም በአረብኛ እንድንነጋገር ከማስገደዱ በፊት ፈጥነን ግእዝ ቋንቋን መማር አለብን።

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል

ትውፊታዊ ታሪኩ

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ፍጥረታት በሐሌዎበነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ። ግእዝ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ስንል አዳም ማለት ያማረ የተዋበ ማለት ሲሆን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው፤ አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው ቋንቋ በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል።

ግእዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ ለማረጋገጥ ከሚያቀርቧቸው ፲ ምክኒያቶች መካከል

፩ኛ. ”ግእዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ

፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ

፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ

፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምሥጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ

፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ትግርኛ በትግሬዎች፣ ኦሮምኛ በኦሮሞዎች፣ ሶማልኛ በሶማሌዎች፣ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች፣ እንግሊዝኛ በእንግሊዞች፣ ቻይንኛ በቻይኖች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ

፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግእዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ

፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።

፰ኛ. «ግእዝ» የሚለው ቃል እራሱ አንደኛ፣ የመጀመሪያ ማለት ነው። የሰው ልጅ የመጀመሪያ የሆነው ቋንቋ አንደኛቢባል ይስማማዋል።

፱ኛ. የዚህ ቋንቋ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሰው አዳም ነው። የዚህ ሰው ስም በቋንቋው ትርጉም ሊኖረው ይገባል። በግእዝ «አዳም» ማለት ያማረ ማለት ነው።

፲ኛ. ሌላው ነገር የግእዝ ፊደላት ከአምላክ የተገኙ ናቸው ለዚህም የአዳም ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖስ በሰማይ ገበታ እንዳያቸው አባቶች ይናገራሉአማርኛ ቋንቋ ከግእዝ ያገኛቸውን በሙሉ ይዞ ሌሎች ፯ ፊደላትን በመጨመር ግእዝ ፳፮ ሲሆን አማርኛ ደግሞ ፴፫ ነው “ቨ”ን ሳይጨምር ማለት ነው፡፡

የግእዝን ፊደሎች ትርጉም ስንመለከት

ሀ፦ ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ፥ የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው

ለ ፦ ብሂል ለብሰ ሥጋ እምድንግል ፥ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን ለበሰ

ሐ ፦ ብሂል ሐመ ወሞተ ፥ ስለኛ ታመመና ሞተ

መ፦ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ፥ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው

ሠ ፦ ብሂል ሠረቀ በሥጋ ፥ በሥጋ ተገለጠ

ረ ፦ ብሂል ረግዓት ምድር በቃሉ ፥ ምድር በቃሉ ረጋች

ሰ ፦ ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ቀ ፦ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ፥ ቃል መጀመሪያ ነበር

በ ፦ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ፥ ጌታችን በትሕትናው ወደኛ ወረደ

ተ ፦ ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ኀ ፦ ብሂል ኀያል እግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔር ኀያል ነው

ነ ፦ ብሂል ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ፥ መከራችንን ያዘልን ሕመማችንን ተሸከመልን

አ ፦ ብሂል አእኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔርን ፈፅሜ አመሰግነዋለሁ

ከ ፦ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር ፥ ጌታችን ቻይ ነው

ወ ፦ ብሂል ወረደ እምሰማይ ፥ ጌታ ከሰማይ ወረደ

ዐ ፦ ብሂል ዐርገ ሰማያተ ፥ ወደ ሰማይ ዐረገ

ዘ ፦ ብሂል ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ፥ ጌታ ሁሉን የሚይዝ

የ ፦ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይልን ታደርጋለች

ገ ፦ ብሂል ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ፥ ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሠራ

ጠ ፦ ብሂል ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ፥ ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱና ዕወቁ

ጰ ፦ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፥ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው

ጸ ፦ ብሂል ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ ፥ ጸጋ እና በረከት ተሰጠን

ፀ ፦ ብሂል ፀሐይ ጸልመት በጊዜ ስቅለቱ ለእግዚእነ ፥ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመች

ፈ ፦ ብሂል ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ፥ ጌታ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ

ፐ ፦ ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ፥ ፓፓኤል የአምላክ ህቡዕ ስም

ትርጉማቸዉ ይሄን ይመስላል።

ስለዚህ ግእዝ የአዳም ቋንቋ ነው የሚለው መላምት የበለጠ ጥንካሬ አለው

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ከ ፪ ዓመት በፊት በመካ ፭ሺ “ሀጂዎችን” የገደለው ፡ ከቁልቢ በቱርኮች ተሠርቆ ወደ መካ የተወሰደው የ ‘ቅ/ ገብርኤል ጽላት’ ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 11, 2018

ግራኝ አህመድ በቱርኮች እየተደገፈ በክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ ዲያብሎሳዊ ዘመቻውን ልክ ባካሄደበት የ16ኛ መቶ አጋማሽ ላይ ኦቶማን ቱርክ መላው አረቢያን ብሎም መካና መዲናን ትገዛ ነበር።

የግራኝ ዘመቻ ክርስትናን መዋጋትና ክርስቲያኖችንም ጨፍጨፍ ብቻ ሳይሆን፣ በተለይ የተደበቁ ቅርሶችንና መረጃዎችን ለማጥፋት፣ ጽላቶችን ለመስረቅ፡ በዚህም የእስልምናን ቅጥፈት እንዲሁም መሀመድን ጎበኘ የሚባለው የጂብሪልን ጋኔናዊነት ለመደበቅ መሆኑ እንደነበር አሁን የሚያጠራጥር ነገር አይደለም።

ነሐሴ ፪ሺ፯ ዓ.ም ላይ ከህንድ ወደ አዲስ አበባ ስበር በዱባይ ቀጥሎም በሳዑዲ አረቢያ በኩል ነበር ያለፍኩት፤ የሆነ ነገር ይሰማኝ ነበር። ከዓመት በፊት መስከረም ፪ሺ፮ ላይ መካኒሳ ቅ/ ሚካኤል ቤ/ ክርስቲያን በነበረኝ ቆይታዬ፤ ደመናው ላይ አፉን የከፈተ አንበሳ ወደ ሳዑዲ አቅጣጫ ነፋሱን የሚነፋ መስሎ ታየኝ (እታች በቪዲዮ አቅርቤዋለሁ በጊዜው)

ወደ ቤት እንደተመለስኩ፤ ቤተሰቦችና ጎረቤቶች በተሰባሰቡበት፤ “ሰሞኑን በመካ ከፍተኛ አደጋ ይኖራል”

አልኩ፡ እንዲያው በዝግታ። መቼም በእኛ ዘንድ ነገሮች እስኪከሰቱ ድረስ ይህን መሰል ነገር በደፈና መቀበል ስለሚቸግረን በጊዜው በቂ አትኩሮ አላገኝም ነበር።

ከጥቂት ቀናት በኋላ፡ በቅዱስ ዮሐንስ ዕለት በመካ ክሬኑ በኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተሰባብሮ 107 ሰዎች ሲሞቱ ከሁለት ሳምንታት በኋላም 5ሺህ የሚሆኑ ሀጂዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ዘመድ አዝማድ በሙሉ እየተገረመ ስልክ ይደውልልኝ ጀመር። እኔም ሁሉም በእጃችሁ ነው“ሂዱና ቅዱስ ሚካኤልን ወይም ቅዱስ ገብርኤልን ጠይቁ” ነበር ያልኩት።

ቁልቢ ገብርኤል ከዚህ ታሪክ ጋር ምናልባት ሊዛመድ እንደሚችል የተረዳሁት ይህ ሰውየ ያቀረበውን ቪዲዮ ከተመለከትኩ በኋላ ነበር። በጣም የሚገርም ነገር ነው፤ ብዙ ወደ ቁልቢ ገብርኤል የሚሄዱ ሰዎች እንደነገሩኝ ከሆነ በጣም ብዙ አረብ ሙስሊሞች በተለይ ለታህሣሥ ገብርኤል ወደ ቁልቢ ይሄዳሉ። ምን/ ማን ይሆን ወደዚህ ቅዱስ ቦታ እንዲጓዙ የሚገፋፋቸው? ይህ የሁላችንም የቤት ስራ ሊሆን ይገባል።

እነዚህ ትዕቢተኞች እጃቸውን ሰጥተው እስኪንበረከኩ ድረስ ገና ይንቀጠቀጣሉ!

+ የቪዲዮው ጽሑፍ በቴሌግራፍ፦

በዚህ ጉዳይ ላይ የጠለቀ ምርምር እስካሁን አልተካሄደበትም

በመጨረሻዎቹ የ 2016 .ም ወራት አንታርክቲካን በሚምለከት ብዙ ምስጢራዊነት የተሞላባቸው ወሬዎች ሲናፈሱ ይሰሙ ነበር።

ኖቬምበር 42016 .ም የወቅቱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር፡ ጆን ኬሪ ወደ አንታርክቲካ አመሩ።

ጆን ኬሪ የመጀመሪያው ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣን ነበሩ የአንታርክቲካን ክፍለ ዓለም ሲጎበኙ። ጆን ኬሪ ለምን ወድዚያ እንዳመሩ ሲጠየቁ የዓየር ጥበቃ ጉዳይ አሳስቧቸው ነው በማለት መልስ ሰጥተው ነበር

ኖቬምበር 23 እና 26 ላይ በአንታርክቲካ 3ፒራሚዶች ተግኝተዋል የሚል ዜናም በየቦታው ይናፈስ ጀመር

ለዚህም ምናልባት ከምድር ክልል ውጭ የመጡ ባዕዳን ፍጥረታት በአንታርክቲካ ሳይገኙ አይቀሩም ይባል ነበር

እንዲያውም አንዳንዶቹ የጠፋችው የአትላንቲስ ከተማ ምናልባት በአንታርክቲካ ሳትገኝ አትቀርም ብለው ይናገራሉ።

የጆን ኬሪ ጉብኝት በእነዚህ ፒራሚዶች ላይ አተኩሮ ይሆን? እዚያስ ከረዓይት ወላጆች “ከወረዱት የሰማይ ልጆች መላእክት” ጋር ለመገናኘት አቅዶ ይሆን?

ኖቬምበር 28 በኑውዚላንዷ ክራይስት ቸርች (የክርስቶስ ብ/ክርስቲያን) 7.8 ዲግሪ ኃይለኛ በነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች።

በዚህ ወቅት ጆን ኬሪ እዚያ ነበር። ምናልባት እነዚህ ከምድር ውጭ የመጡ ፍጥረታት ጆን ኬሪን ምንም ነገር እንዳይነካ መሬቱን በማንቀጥቀጥ አስጠንቅቀውት ይሆን?

ዲሴምበር 12016 ጠፈርተኛው ኦልድሪን በሳንባ በሽታ ምክኒያት አንታርክቲካን ለቅቆ መውጣቱ ተነገረ። የ86 ዓመቱን አዛውንት ኦልድሪንን በመጀመሪያ ማን ነው ወደ እዚያ ቀዝቅዛ ክፍለ ዓለም የላከው?

ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ ዲሰምበር 6 ላይ አንድ እጅግ በጣም አስገራሚ ዜና ተሠራጨ፤ ይህም፦ በጣም አውዳሚ የሆነ ኃይል አለው ስለሚባለው ጥንታዊ የሃይማኖት ቅርስ፡ ስለ ጽላተ ገብርኤል አንድ ትልቅ ወሬ ይወራ ጀመር።

ይህ ጽላተ ገብርኤል በሳዑዲዋ መካ ለሙስሊሞች ቅዱስ ነው ተብሎ በሚነገርለት አካባቢ በመሠራት ላይ ባሉ ህንፃዎች ሥር ነው የተገኘው ይባላል።

የገብርኤልን ጽላትን ልክ እንዳገኙት ብርቱ ኃይል ያለው ነገር ነዝሮ ጽላቱን ያገኙትን 15 ሰዎች በቦታው ገደላቸው።

ከዚያም ኃይለኛ የሆነ ነፋስ የህንፃ መሥሪያ ክሬኖቹን ሰባብሮ ዋናውን የእላሞች መስጊድ ደረማመሰው፤ እዚያ የነበሩትም107ሰዎች ሞቱ።

12 ቀናት በኋላ ይህን የገብርኤልን ጽላት እንደገና ለማውጣት ሲሞክሩ በተጨማሪ የ4ሺህ ሰዎች ህይወት አለፈ።

ነገሩ ያስደነገጣቸው የመካ ታላቁ መስጊድ አስተዳዳሪዎች የሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትሪርክ ኪሪልን ለመገናኘት ወሰኑ።

ለዘመናት በሩሲያውያን እጅ የሚገኘውን አንድ ጥንታዊ የእስልምና ጽሑፍ በሚመለከት ነበር ሳዑዲዎቹ ወደ ሩሲያ የዞሩት።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ የሩሲያው ፕሬዚደንት ፑቲን ወደ አንታርክቲካ የላኩትን መርከብ በ ሳዑዲዋ የቀይ ባህር ወደብ በጂዳ በኩል እንዲያርፍና የገብርኤልን ጽላት እንዲጭን አዘዙ።

በዚህም መልክ ሩሲያውያኑ ጽላተ ገብርኤልን ወደ ቀዝቃዛዋ አንታርክቲካ ወሰዱት።

በፌብርዋሪ 72016 .ም፡ የሮማው ጳጳስና የሩሲያ ፓትርያርክ በ አንድ ሺህ ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስብስባ በኩባዋ ዋና ከተማ በሃቫና ተገናኙ።

6ቀናት በኋላ የሩሲያው ፓትርያርክ ኪሪል ወደ አንታርክቲካ በማምራት በሳዑዲ በኩል ያለፈውን የሩሲያ መርከብ ተቀበሉ።

እንደሚወራው ከሆነ የገብርኤል ጽላት ግኝት ያስከተለው አደጋ ያሳሰባቸው ጳጳስ ፍራንሲስኮ ነበሩ ከፓርትያርክ ኪሪል ጋር ለመሰባሰብ ጥሪ ያቀረቡት።

በዚህ ስብሰባ ጳጳስ ፍራንሲስኮ ለ ፓትርያርክ ኪሪል ስለ ጽላተ ገብርኤል የሚናገር አንድ ጥንታዊ የሆነ ሰንድ አበርክተውላቸው ነበር ተብሏል።

ይህ ሰነድ፡ መጽሐፈ ሄኖክ ላይ በተጠቀሱት “የወረዱት የሰማይ ልጆች መላአክት” (ተመልካቾች) የተጻፈ ነው የሚል ግምት አለ።

ፓትርያርክ ኪሪል አንታርክቲካ በሚገኝ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቅ/ ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን ከጽላተ ገብርኤል ጋር ጥንታዊ የሆነ የጸሎት ሥነስርዓት አካሂደው ነበር ይባላል።

በአንታርክቲካ እንደሚነገረው አንድ ብቻ ሳይሆን 4 የካቶሊኮች እንዲሁም3 የኦርቶዶክስ ዓብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ።

እንደሚነገረው ከሆነ ጽላተ ገብርኤል በአንታርክቲካ ባልታወቀ ጥልቅ ጉድጉድ ውስጥ በሩሲያውያኑ ተቀብሯል።

ስለዚህ ስለ ጽላተ ገብርኤል የሚናገሩ መረጃዎችን ለማግኘት ከባድ ነው።

ይህ ጽላተ ገብርኤል ታሪክ ሦስቱን የ “አብርሃም” ሃይማኖት ቅርንጫፍ ናቸው የሚባሉትን፤

(ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና እስላም) የሚመለከት ቢሆንም፤ አንድ አገር ብቻ ናት የአይሁድ፣ የክርስትና እና የእስልምና እምነቶች ጎን ለጎን የኖሩባት፤ ይህችም ኢትዮጵያ ብቻ መሆኗን ስረዳ፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ላይ ለማተኮር ወሰንኩ።

ኢትዮጵያ በከዳዊነት ከንጉስ ሰለሞን ሥርወመንግሥት ጋር የተሣሰረች ነች፤ አይህዳውያንም ከመጀመሪያ ቤተ መቀደስ ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ኖረዋል።

ኢትዮጵያ ቀዳሚ የሆኑት ክርስቲያኖች ከመጀመሪያ ምዕተ ዓመት አንስቶ ኖረውባታል። ቅዱስ ማቴዎስ በኢትዮጵያ ይሰብክ እንደነበር ይታወቃል። እስላሞቹ የመሀመድ ተከታዮችም ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ነበር።

ታዲያ ከሌላ ቦታ ይልቅ ይህን መሰል ኃብታም ድብልቅ ልምድ ባለባት ኢትዮጵያ ብቻ ነው የጽላተ ገብርኤልን ምስጢር ለመግለጥ የሚቻለው።

በስተምስራቅ ኢትዮጵያ ቁልቢ ገብርኤል የሚባል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መኖሩን ተረዳሁ

ይህ ቤተክርስቲያን እ..አ በ1887 .ም ነበር የተመሠረተው።

የቁልቢ ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን ህንፃ የተሠራው ከ 9ኛው መቶ ጀምሮ ቅዱስ እንደሆነ በሚታወቀው ቦታ ላይ ነው።

9ኛው መቶ ዮዲት ጉዲት በመባል የምትታወቀው አይሁድ ሴት በሰሜን ኢትዮጵያና በአክሱም የነበሩትን ብዙ ዓብያተክርስቲያናትን ለማጥፋት በቅታ ነበር። ጉዲት ማለትም እሳት ማለት ነው።

በዚህ ጊዜ ነበር ጽላተ ገብርኤል ከአክሱም የጉዲት ቃጠሎ ተርፎ በዝዋይ ሐይቅ ወደምትገኝ አንዲት ደሴት የመጣው ይህ ራሱ ሌላ አስደናቂ ታሪክ ነው።

ከዝዋይ ደሴቶች ነበር ጽላተ ገብርኤል በአንድ አባ ሉዊስ በሚባሉ መነኩሴ/ሄዳ ወደ ቁልቢ የተወሰደው

መነኩሴውን ቅ/ገብሬል ነበር ተገልጦላቸው ጽላቱን ወደ ቁልቢ እንዲወስዱ ያዘዛቸው።

16ኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ አህመድ ጸረክርስቶሳዊ የጥፋት ዘመቻ ወቅት ጽላቱ ከ ቁልቢ ጠፍቶ እንደነበር የሚታወቅ ነው።

ታዲያ ጽላተ ገብርኤል በ16ኛው ክፍለ ዘመን በግራኝ ተሠርቆና3ሺ ኪሎሜተር ተጕዞ ወደ መካ ተወስዶ ይሆን?

የጽላተ ገብርኤል ታሪክ ከዚህ ጋር የተያያዘ ይሆን?

መካስ ነበርን? አሁንስ አንታርክቲካ ተቀበሯል የተባለለት

እውነተኛው ጽላተ ገብርኤል ነውን? ወይስ ሌላ ነገር?

ሆነም አልሆነም፡ጽላተ ገብርኤል ወይ አንታርክቲካ ነው የሚገኘው፡ ወይም ደግሞ ከ9ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ የጽላተ ገብርኤል ባለቤት በሆነችው በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን እጅ ነው የሚሆነው።

9ኛው እስከ 16ኛው ምዕተ ዓመት የተከሰቱት ታሪካዊ ክስተቶች እውነቱን እንድናውቅ ረድቶናል

እውነቱ ይህ ነው፤ በይበልጥ ለማወቅና ለመረዳት የሁላችንንም ተሳትፎና ጥረት እጠይቃለሁ።

ይህን የመሰለ ነገር በሚመለከት ቴሌቪዝን እና ሚዲያዎች ሁሉ መረጃዎችን በሚያዳላ መልክ ሲያቀርቡና የምርምር መንገዳችንንም ሲያበላሹብን ቆይተዋል።

ለማንኛውም አገራችን ኢትዮጵያ ገና ያልታወቁ የብዙ ተዓምራት ምድር ናት!

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: