Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጤንነት’

በዶክተሮች ሊፈታ የማይችለው ወረርሽኝ በጻድቁ ማእጠንት ይታጠናል | የማእጠንት ፀሎት በአሜሪካ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020

የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሃብተማርያም የማእጠንት ፀሎት በተወሰኑ የቨርጂንያ መንደሮችና ጎዳናዎች

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፰፤]

ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ

በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው

ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው

የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ

ሌላ የሚገርመው ነገር፤ ልክ እዚህ አካባቢ ነበር ባለፈው ጊዜ የሚከተለው የተከሰተው፦

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይኸው ሰዓቱ ደርሶ አሜሪካ በአቡነ ሃብተማርያም ማዕጠንት እየታጠነች ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፥፲፮]

እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

ይህን ሳይ የሚሰማኝ፤ “እግዚአብሔር እኛ ኢትዮጵያውያንን በመላው ዓለም በስደትም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ከአገራችን አውጥቶ የሚልከን በርገር እየበላን በከንቱ እንድናውደለድል ሳይሆን እንደዚህ እጣኑን እያጨስን መንፈሳዊ ውጊያውን እንድንመራለት፣ ከጠፉት ጋር አብረን እንድንጠፋ ሳይሆን፣ ሁሉም እንዲድን መድኃኒቱን እንድናሳይ ነው።” የሚለው ነው። በእውነት ነው የምለው፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በከንቱ ሌላውን ለመምሰል ብንታገልም ምናልባት 90% መንፈሳውያን ሰዎች ነን።

እንግዲህ ያውልሽ አሜሪካ፤ ግብጻውያን አውሮፕላን አብርረው ከሰማይጠቀስ ፎቆችሽ ጋር በማላተም ሦስት ሺህ ዜጎችሽን ገደሉብሽ፣ ፕሬዝደንትሽ ለጉብኝት ወደ ግብጽ ሲመጡ በንቀት ጫማቸውን ወረወሩባቸውዛሬ የከዳሻቸው ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ግን መቅሰፍቱ ሁሉ ከምድርሽ እንዲርቅ ክቡር እጣኑን ከደመናው ጋር አዋሐዱልሽ። ይህን ውለታ አትርሺ፤ አሜሪካ!

የፃድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን የመጣውን መቅሰፍት ከአገራቸን ኢትዬጵያና ከመላው ዓለም ይሰውርልን!

መምህር ዘመድኩን እንዳካፈለን፦

መፍትሄው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ጭንቅ ውስጥ በገባችው አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየአደባባዩ፣ በየመንደሩ፣ እየዞረች የጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያምን ዕጣን እንድታጥን ተጠይቃ ይኸው ቃሏን አክብራ በጻድቁ አቡነ ኃብተ ማርያም ጸሎት ምድሪቱን እያጠነች ነው።

ዛሬ መጋቢት ፲፫ / ፲፪ /13/2012 .(Mar.22/2020)

በአሜሪካን ሀገር በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 5:00 PM ላይ በኸረንደን ቨርጂንያ 2472 Centreville Rd.Herndon, VA 20171 የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሀብተማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናቱ የጻድቁ የአቡነ ሀብተ ማርያም ሥዕላቸው ተይዞ

በኸረንደን፣

በረስተን፣

በቻንትሊን፣

በእስትርሊንግና በሌሎችም ከተሞች የሚገኙ አደባባዮችና አውራ ጎዳናዎች በማጠን ላይ ይገኛሉ።

ለዚሁ የአሜሪካን ከተሞችና መንደሮች የማዕጠንት አገልግሎት

መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰሎሞን

መጋቤ ካህናት መ/ር ቀሲስ ዮናስ ፍቅረ

ሊቀ ስዩማን መ/ር ቀሲስ ኢዮብ ደመቀ

ሊቀ ልሳናት መ/ር ቀሲስ ጌቱ ተገኑ

ሊቀ ማዕምራን መ/ር ዮሐንስ ለማ

ሊቀ ትጉሀን ዲ/ን አብርሐም ቶማስ

ሊቀ ዲያቆን ገረመው ተዘጋጅተው አገልግሎቱን ጀምረዋል።

አሜሪካ ደንግጣለች። ቤተ ጸሎቶች በሙሉ ተዘግተዋል። የመኪና መንገድ አውራ ጎዳናዎች ሁሉ ጭር ብለዋል። ነገር ግን በእኒህ ሞት ባጠላባቸው የአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶቻችን ጸሎት እንዲያደርጉ የአሜሪካ መንግሥት ፈቅዶላቸዋል። በእውነት ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። ይሄ ምልክት ነው። ወደድንም ጠላንም መጪው ዘመን የኦርቶዶክስ ነው። ኦርቶዶክሳዊነት የዓለሙ ሁሉ ሃይማኖት ይሆናል። ሰዎች ሁሉ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ይተምማሉ። የኢትዮጵያ ሃይማኖት የዓለም ሃይማኖት ይሆናል የሚባለው የአበው የትንቢት ቃል በቅርቡ ፍጻሜውን ያገኛል።

ከኢትዮጵያ ውጪ ብቸኛው የጻድቁ አቡነ ሃብተ ማርያም ታቦት የሚገኘውም እዚሁ ቦታ ነው። በቦታውም ብዙ ህሙማን እየተፈወሱ መካኖች መወልዳቸው ብዙዎችን ሲያስደንቅ መኖሩም ተነግሯል። በእውነት መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁእግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል “(መዝሙረ ዳዊት 68:35)

በጻድቁ ዜና ገድል (ገድለ አቡነ ሀብተማርያም ገጽ.117) ላይ ተጽፎና ተመዝግቦ እንደምናገኘው ልዑል እግዚአብሔር ለጻድቁ በሰጣቸው ቃል ኪዳን መሰረት ስማቸው፣ በተጠራበት፣ ማዕጠንታቸው በታጠነበት፣ ዜና ገድላቸው በተነበበትና ባለበት፣ ጠበላቸው በተረጨበት ሥፍራ ፭ቱ መቅሰፍታት ማለትም :-

፩ኛ.መብረቅ

፪ኛ.ቸነፈር

፫ኛ.የረኀብ ጦር

፬ኛ.ወረርሽኝና

፭ኛ.ሰደድ እሳትና የመሳሰሉት ቦታ የላቸውም። ዜና ገድላቸው እንደሚነግረን በአንድ ወቅት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ልጆቻቸው በእነዚህ ፭ቱ መቅሰፍታት እንዳይጠቁና እንዳይጎዱ ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያምን በቃል ኪዳናቸው ልጆቻቸውን እንዲጠብቁላቸው ሲማጸኑዋቸው የጻድቁ የአቡነ ሀብተማርያም መልስ የነበረው “ወዳጄ ተክለሃይማኖት ሆይ፤ በእኔ ስም ልጆችህና ወዳጆችህ በቃል ኪዳኔ የሚድኑ ከሆነ ይሁን ብለው ቃል እንደገቡላቸው ተመዝግቧል። ይህ ቃል ኪዳን ደግሞ ዘመን ተሻጋሪና ጊዜ የማይሽረው ነው። በእውነት ያለ ሀሰት። እንጠቀምበት።

በኢትዮጵያም በትናንትናው ዕለት የቃሌ አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ካህናት አዲስ አበባ ቃሌ አከባቢ ሲያጥኑ መዋላቸው ተዘግቧል። ትናንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የዐድዋውን ዘማች ታቦተ ጊዮርጊስን ይዛ ማዕጠንቱን ብታካሂድ ወረርሽኙ ድራሹ ይጠፋል በማለት ያሳሰብኩትም ማሳሰቢያዬም መልስ አግኝቷል። የአራዳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መጋቢት 20 ታቦቱን ይዘው ሊወጡ ነው። የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከትም መጋቢት 13 በአዲስ አበባም የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራትም በጋራ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ አዲስ አበባን እንዲያጥኑ መመሪያ ተላልፏል።

በጣልያን ሊቀጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን አናግሬያለሁ። የጣልያን መንግሥት ፈቃድ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ እኛ ዝግጁ ነን ብለዋል። የጀርመኑን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ዲዮናስዮስንም እንዲሁ አግኝቼ አውርተናል። ፈቃዱ ከመንግሥት ካለ እኛ ዝግጁ ነን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እጹብ ድንቅ ነው | የአቡነ ሃብተማርያም ገዳም ካህናት አዲስ አበባ ቃሌ አከባቢ ሲያጥኑ ዋሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020

በዚህ በጣም ተደስቼ ነው የዋልኩት፤ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

ትንሽ ቅር ያለኝ ነገር ግን እዚህ ድንቅ ገዳም ተራራ ጫፍ ላይ አንጋፋውን መስቀል ለማስተከል መስነፋችን ነው።

የፃድቁ አባታችን አቡነ አብተማርያም ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን የመጣውን መቅሰፍት ከአገራቸን ኢትዬጵያና ከመላው ዓለም ይሰውርልን!

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አይሁዱ ተመራማሪ | ለኮሮና መድኃኒቱ እጣን መሆኑን ብሉይ ኪዳን ጠቁሞናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 21, 2020

ቫይረሱ ጋኔን መሆኑን አረጋገጠልን!

ምን እንደሆነ አላውቅም እስከ አለፈው ነሃሴ ወር ድረስ ምናልባት በወር አንዴ ብቻ ነበር እጣን የማጤሰው፤ ካለፈው ጥቅምት ወር አንስቶ ግን በቤትም በመሥሪያ ቤትም በጣም አዘውትሬ አጤሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው፤ ቅዱስ መንፈስ ማድረግ የሚገባንንና የሚጠቅመንን ነገር ሳናስበውና ሳንዘጋጅበት እንድናደርገው ወደ በጎው ነገር ይመራናል።

ዛሬ ወደዚህ አይሁድ ቪዲዮ እንዴት እንደገባሁ ሁሉ አላውቅም፣ ያውም እጣንን በሚመለከት የገባሁበት ገጽ አልነበረም ፤ ግን ያው! ለኮሮና ጋኔን መፍትሄ ይሆናሉ ብዬ ሳስባቸው ከነበሩት ከጸበል፣ ከጸሎት ጎን እጣን እና ከርቤ እንደሚኖሩበት አረጋገጠለን። አሁን በዚህ በጣም እርግጠኛና ደስተኛ ነኝ።

ደካሞችና ምስጋና ቢሶች ሆነን ነው እንጂ አምላካችን እኮ የሚጠቅሙንን ነገሮች ሁሉ ሰጥቶናል፤ ጸበሉንም፣ ጸሎቱንም፣ እጣኑና ከርቤውንም በነጻ ሰጥቶናል። እጣንና ከርቤ ከወርቅ በላይ የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ለብዙ በሽታዎች ፈውስ እንደሆኑ ሳይንሱ ሳይቀር እያረጋገጠልን ነው። Seeing the Unseen of the Combination of Two Natural Resins, Frankincense and Myrrh

እጣኑን በአግባቡ እናጢስ፤ ወገኖቼ፤ ነገር ግን ከተለመደው የቡና ስነ ሥርዓት ወቅት፣ በተለይ ከኦጋዴን እና አረብ ዕጣኖች ጋር አብሮ ማጤሱን ዛሬውኑ ማቆም አለባችሁ! አባቶች ይህን አስመልክቶ አንድ ይበሉን!

አየን አይደለም?! ጠላት ዲያብሎስ ለብዙ ሳምንታት በቂ የኮሮና ቫይረስ በአውሮፕላን እንዲረጭ ካደረገ በኋላ ወሮበላው መንግስት “በረራዎችን አቁሜአለሁ ፣ ይቅርታ ቅብጥርሴአለን። ቫይረሱ ልክ እንደ አንበጣ እስኪፈለፈል የሁለት ሳምንታት ጊዜ ይወስድበታል ተብሏል። ስለዚህ አባቶች ልክ እንደ ጆርጂያ ኦርቶዶክስ አባቶች በተለይ አዲስ አበባን በመኪና እና በሄሊኮፕቶር እየዞሩ ዛሬውኑ ደጋግመው ጸበል ቢረጩና እጣን ቢያጤሱ ትልቅ ሥራ ይሆን ነበር። በተለይ ምዕመናን ለቅዳሴ የማይመጡ ከሆነ ይህ መደረግ አለበት። ቀዝቃዛዎቹ የጉንፋን ወራት ከመጀመራቸው በፊት አስቀድሞ መደረግ ያለበት አንዱ ተግባር ይህ ሊሆን ይገባል።

UPDATE

የመንፈስ ቅዱስን ሥራ እያየን ነው፡ ወገኖቼ? ዋው! የሚገርም ነው፦ ያው መምህር ጳውሎስም እንዲህ ይለናል፦

የማዕጠንት ጊዜ ነው፤ ማዕጠንት ጥሩ ነው፤ በሽታ የሚያርቅ ነው፤ እጣኑንን እያሸተታችሁካህናት በየቤቱ በመዞር ጸሎተ ማርያም እየደገሙና ማዕጠንት እያደረጉ ቢያልፉ በሽታው ያልፋል ከተማው ይታጠላንል አስፈላጊ ከሆነ”።

ወደ እዚህ እንግባና ሙሉውን እናዳምጥ፦

አስደናቂ ስብከት በሽታው የሚርቀው በማዕጠንት ነው መምህር ጳውሎስ መልካሥላሴ ክፍል፪

ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሻሪያ በጓዳ በር | ሙስሊሙ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚንስትር የአልኮል ማስታወቂያዎችን ከለከለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 12, 2019

መቼም ሕዝባችን ይህን ዜና መጀመሪያ ሲሰማ፡ “ዋው! ይሄማ ለበጎ ነው፤ አልኮል እኮ መጥፎ ነው፤ ማንም ይከልክለው ማን፤ ዋናው ጤናችን ነው”ይለናል፤ በጉዳዩ ላይ ሳያንፀባርቅበት።

ግን ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ይህን ሕግ እንዲጸድቅ የገፋፋው የግራኝ አህመድ ቲም አባል የጤና ጥብቃ ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ነው።(በአገራችን የማያክመው ዶ/ር በዛ)

ስለ እስልምና ጠለቅ ያለ እውቀት ያለው ወገን ሥልጣን ቦታ ላይ የተቀመጡትን ሙስሊሞችን በጭራሽ ማመን የለብንም፤ በተለይ የወይን ጠጅ እና ሰባ ሁለት ልጃገረዶች በጀነት ተስፋ የሚያደርጉትን የመሀመድ ተከታዮችን።

ለሕዝባችን ጤና አስቤ ነው” አለን ዶ/ር አሚር፤ መቼም ይህን ከአለቃው ከ ዶ/ር አህመድ የተማረው መሆን አለበት። እነዚህ ሰዎች ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ምንም ዓይነት በጎ ነገር እንደማያመጡ እርግጠኛ ሆኜ ነው የምናገረው። “ለሕዝቡ መስማት የሚፈልገውን እየነገርከው አንት ሥራህን ሥራ” ብሎ የለም በግልጽ በመጸሐፉ፤ አዎ! የምዕራብ ኒዎሊበራሎች /ለዘብተኞች የሚባሉት ሞግዚቶቹ ሹክ ብለውት እንዲጽፍ ባዘዙት መጽሐፉ ላይ። ኢትዮጵያውያን ይህን ትርኪ ምርኪ የተሰበሰበበትን መጽሐፉን አንብቡትማ፤ በኢትዮጵያውያን ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያለውን ንቀት ያሳየብት መጽሐፍ ነው። እነ አፄ ቴዎድሮስ፣ አፄ ዮሐንስን እና ሌሎች የተዋሕዶ አባቶችን ከግራኝ አህመድ ጋር በአንድ ረድፍ ያቆመበት ጽንፈኛ መጽሐፍ ነው።

ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” ብሎታል፡ ተንኮለኛው ፈላስፋ ሄገል።

እንጀራ በሚበላባት ሃገራችን ጠላ ወይንም ጠጅ እና የወይንጠጅ እንጅ፡ ውስኪ፣ ቮድካና ቢራ ከጨጓራ እና ስኳር በሽታ ሌላ ለአገራችን ሰው የሚያስገኝለት ሌላ ምንም ነገር የለም። ታዲያ ይህ እየታየና እየታወቀ ባለፉት ዓመታት በአገራችን የቢራ፣ የአልኮል እና መርዛማ ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካዎች እንደ አሸን ነበር የፈሉት፤ ከውጭ ድጎማ እየተደረጉ።

ታዲያ እነዚህ መጠጦች ትውልድን እያበላሹ መሆናቸው ግልጽ እየሆነ ሲመጣ እንደ መፍትሔ ነው በማለት ማስታወቂያዎችን አሁን ለመከልከል ወሰኑ። ግብዞች! እስከ መቼ ይህን ሞኝ ሕዝብ ያታልሉታል?

/ር አህመድን ሉሲፈራውያኑ ሥልጣን ላይ ሲያወጡት የመጀመሪያው ተግባሩ እንዲሆን ያደረጉት ወደ ትግራይ አምርቶ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ልብ በትግርኛ ቋንቋ ለመሳብ መሞከር ነበር። ያ ሳይሳካ ሲቀር ወደ አሜሪካ በማምራትና ተዋሕዶ አባቶችን “አስታርቂያቸዋለሁ” በማልት አቡነ መርቆርዮስን ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መጣ። አቡነ መቆርዮስ በእነ ሲ አይ ኤ እና ዲያስፐራ ፖለቲካ ፓርቲዎች ግፊት ነው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት፤ እነርሱ ፈቅደውላቸው ነው እንጅ የዶ/ር አህመድ ፍልጎት ወይም ጥረት ስለነበረበት አይደለም። መቼ ነው የዋቄዮ አላህ ልጅ ለተዋሕዶ አስቦ የምያውቀው? በፍጹም!

ሁሉም ነገር ቀስበቀስ ነው፤ የእነዚህ እባቦች የሚቀጥለው እርምጃቸው አልኮል በአደባባይ እንዳይሸጥ ማድረግ ነው፤ ልክ እንደ ሳውዲ አረቢያ። አልኮል እና አደንዛዥ እጽ በሰፊው በመጠቀም በዓለማችን የሚታወቁት ሃገራት የሻሪያ ህግ የሰፈነባቸው ሙስሊም ሃገራት ናቸው። በአደባባይ ባይፈቀድም በድብቅ ግን አደገኛ በሆነ መልክ/ በጓዳ ብዙ አልኮሆል እና አደንዛዥ እፅ ይመረታል። ሻሪያ ኢራን ለምሳሌ በአደንዛዥ እፅ ፍጆት በዓለም የመጀመሪያውን ቦታ ይዛለች።

አንታለለ፤ ወገኖች! የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ዒላማቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ ነው፤ ጦርነቱም በጌታችን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም ላይ ነው፤ በቤተክርስቲያን በህብስት አምሳል የምንቀበለው የክርስቶስ ስጋ በወይን አምሳል የምንቀበለው የክርስቶስ እውነተኛ ደም እንደሆነ አምነን እና ተቀብለን የመዳናችን ሚስጢር የሚፈፀምበትን አምላካዊ ጸጋ ስለምናገኝበት፡ በጣም ስለሚቀኑ መድኃኒታንን ሊነጥቁን ይሻሉ። ሙስሊሙ የጤና ጥበቃ ሚንስትር“የሕዝባችን ጤና ያሳስበኛል” ሲል በተቃራኒው “ሕዝቡን ማኮላሸት አለብኝ” እንደሚል አድርገን መውሰድ አለብን።

ለህፃናቱ ሲባል ብቻ እነዚህ ሰዎች ብዙ ጥፋት ሳያመጡ ከያዙት ቦታ ቶሎ መነሳት ይኖርባቸዋል።

_____________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ የሚያዘወትሩ ሰዎች ደስተኞች፣ ጤናማዎች እና ታማኞች ናቸው | አዲስ የ’PEW’ ጥናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 6, 2019

አሜሪካዊው የ ‘PEW’ ሉላዊ ጥናት አዲስ ባወጣው መረጃ መሠረት፤ እምነት ያላቸው ሰዎች ወይም ክርስቲያኖች ኢአማናያን እና አህዛብ ከሆኑ ሕዝቦች ጋር ሲነፃጸሩ፤

  • + በጣም ደስተኞች ናቸው፣

  • + ረዘም ላለ ጊዜ ነው የሚኖሩት፣

  • + ለመንፈሳዊ ጭንቀት እና ራስን ማጥፋትን አደጋ አይጋለጡም፣

  • + በግኑኝነቶች ያላቸው ታማኝነት ከፍ ያለ ነው፣

  • + በቤተሰባዊ ህይወታቸው የበለጠ እርካታ አላቸው፣

  • + በይበልጥ ደስተኛ የሆኑ ልጆች አሏቸው።

ጥናቱን ያካሄዱት አለማውያኑ እራሳቸው ይህን ሲመሰክሩ ማየቱ ደስ ይላል!

ምንም የሚያጠራጥር ነገር አይደለም፤ በመካከላችን በየቀኑ የምናየው ነው። ኢትዮጵያ በጥናቱ ባትካተትም፤ በኢትዮጵያውያን መካከል እንኳ አማኝ የሆኑት ካልሆኑት በደንብ ይለያሉ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ!

አማኝ ያልሆኑት ወገኖች፣ መሀመዳውያኑንም ጨምሮ፤ ሙሉ ሕይወታቸውን ከመንፈሳዊው ሕይወት በመራቅ፡ እራሳቸውን እያታለሉ ሥጋዊ እና ዓለማዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ ደስታቸውን ለመግዛት ሲታገሉ እናያለን። እነዚህ ወገኖቻችን ደስተኞች፣ ጤናማዎችና ታማኞች አይደሉም። ክርስቲያኑ ግን፡ ምንም እንኳን እነዚህ ደስተኛ ያልሆኑ ወገኖቹ ሊበክሉት፣ ሊያሥሩት፣ ሊጎትቱት እና እያታለሉ ደስታውን ሊነጥቁት ቢሞክሩም ክርስቲያኑ ግን በእግዚብሔር ኃይል፣ በቅዱሳን እርዳታና በ ቤተክርስቲያን ሞግዚትነት ከእነዚህ ነጣቂዎች ይድናል። ክርስቲያኑ ከቡና፣ ጥምባሆና ጫት ከመሳሰሉት አታላይ ጉርብትናዎች ከራቀ ሁሌ ደስተኛና ጤናማ የሆነ እንዲሁም ታማኝነት የተሞላበትን ስኬታማ ኑሮ መኖር ይችላል።

አንድ የሚገረም ገጠመኝ፤ በመስቀል ዕለት፤ ከአክስቴ ልጆች ጋር ሆነን ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ሄድን፤ በጣም ደስ ይል ከነበረው ዓመታዊ ክብረ በዓል በኋላ፡ አምቦ ውሃ ነገር እንጠጣ ብለን ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት በምትገኘው “ቡና” / ምግብ ቤት በረንዳ ላይ ወንበሮች ያዝን (ቢዲዮው ላይ በከፊል ይታያል)። ከጎናችን አንዲት የተሸፋፈንች ሙስሊም ወገናችን ብቻዋን ቁጭ ብላለች፤ ቁና ቋና እየተነፈሰች እግሮቿንና እጆቿን እያንቀሳቀሰች ትቁነጠነጣለች፤ ደስተኛ አትመስልም። ለማንም ሳልናነገር፡ ምን ይሆን ብዬ፡ በጥሞና እከታተላት ጀመር፤ በጣም ያዘኑ የሚመስሉት አይኖቿ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ ነው ያተኮሩት፦ ምን ታስብ እንደሆነ ለማወቅ ያዳግታል፤ ነገር ግን የተዋሕዶ ልጆች በደስታና በፍቅር የቤተክርስቲያኑን ደረጃ ሲወጡና ሲወርዱ ማየቷ አስከፍቷታልአንዴ ወደ ቤተክርስቲያኑ ላለማየት ወደ ጎን ዘወር ትላለችአላስችል ሲላት መሀል ግንባሮቿን ሰብሰብ ታደርጋለችሁኔታውን በቃላት ለመሳል አይቻልም፤ ግን እኔ እርግጠኛ ነበርኩ፤ ለዘመዶቼም ቀስ ብዬ ይህን እንዲያረጋግጡ ሹክ አልኳቸውበአምስት ደቂቅ ውስጥ እነርሱም የተገነዘቡት ነገር ይህን ነበር።

— Pew: Actively Religious People More Likely to Be ‘Very Happy

_________

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

“ሃጂ” የተባለው የዓለማችን በጣም ቆሻሻው ሰው ለ60 ዓመታት ያህል ፈጽሞ ታጥቦ አያውቅም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 28, 2019

ሃጂ” የተባለው የዓለማችን በጣም ቆሻሻው ሰው ለ60 ዓመታት ያህል አልታጠበም

80 ዓመ አረጋዊ ኢራናዊ ቆሻሻነቱ በጣም ያስደስተዋል። ለዚያም ነው ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ፈጽሞ ታጥቦ የማያውቀው። በደቡባዊ የኢራናውያን አንድ መንደር ውስጥ ብቻውን መቀመጥ ይወዳል።

ሃጂ ከውኃ ጋር ያለውን ግንኙነት ይጠላል የመታጠብ ሀሳቡ ብቻ ሲነሳ በጣም ያናድደዋል።

የሃቆዳ የምድር ቀለም ይመስላል። ከአካባቢው ጋር ሙሉ በሙሉ ተደምሮ መኖር ችሏል እንዲያውም ብዙ ከተቀመጠ ስለማይነቀናቅ ድንጋይን ወይም የዓለት ቅርፅ ይመስላል።

ሃጂ እምብዛም የማይታየው ገላ መታጠብ ብቻ አይደለም። ንጹሕ ምግብን እና ንጹሕ መጠጥን በጣም ይጸየፋቸዋል። በምትኩ ግን የሚወደው የበሰበሰና የገማ ስጋ ነው። ለጤንነት ሲል በቀን 5 ሊትር ያህል ውሃ ይጠጣል፥ ነገር ግን የነዳጅ ዘይት በነካው ጣሳ። በጥንባሆ ይልቅ የማጨሻ ቱቦውን እንስሳት ፋንድያዎች በመሙላት ማጨስ ይወዳል። ፀጉሩን ለመቆርጥ መቀስን አይጠቀምም፤ በእሳት ነበልባል ላይ ያቃጥለዋል በክረምት ወቅት በአሮጌ የጦርነት ቆብ ጭንቅላቱን ያሞቃል።

ሃጂ በእውነቱ ቤት የለውም ምድር የእርሱ መኖሪያ ናት በመቃብር እንዳለ ሆን በዋሻ ውስጥ ይኖራል አንዳንድ ጊዜ የመንደሩ ነዋሪዎች በሚሠሩት ክፍት የጡብ ጉድጓድ ውስጥ ይተኛል በአካባቢው ነዋሪዎች ሃጂይባላል «አሙ» በፋርስኛ ቋንቋ፡ አረጋዊ ደግ ሰው ማለት ነው።

የሃጂ የአኗኗር ዘይቤ በጣም ልዩ ነው የመንደሩ ነዋሪዎች በወጣትነት ዕድሜው ከባድ የስሜት መጎሳቆል ደርሶበት እንደነበር ይናገራሉ ይህም እነዚህን የከፉ ምርጫዎች እንዲፈጽም አድርጎታል። እንደዚያም ሆኖ በትላልቅ ቤቶች ውስጥ ምቾትና በመንደላቀቅ ከሚኖሩ ሰዎች ይልቅ ደስተኛ ይመስላል ሃጂ ለዚህም አለም ግድ የለውም። ምንም የሚጎድልበት ነገር የለም ምንም ፍርሃት የለውም

_________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infotainment | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: