Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 22, 2018
ባለፈው ኃሙስ ምድርን ከሚዞረው የዓለም አቀፋዊ የጠፈር ጣቢያ፣ ቤተ ሙከራ፡ ከአይ ኤስ ኤስ ሦስት ጠፈርተኞችን ይዛ ወደ ምድር ትመለስ የነበረችውን የሩስያዋን ሳዩዝ መንኮራኩርን በመቶ ኪሎሜትር እርቀት ላይ ሆኖ የሚከታተለው ካሜራ በመካከለኛው አፍሪቃ አስገራሚ የመብረቅ ብልጭታ ለማንሳት በቅቶ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም፡ ወደ ካዛክስታን ታመራ የነበረችውን መንኮራኩር አጅበው የነበሩት ሦስት የመንኮራኩሯ ክፍሎች የተለያዩት ልክ በሰተሰሜኑ የኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ነበር።
የሚገርም ነው አቡነ ማትያስ የሩስያ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት በዚሁ ዕለት በዚሁ የአውሮፓላን አየር መንገድ አቅጣጫ ነበር። በመካከለኛው አፍሪቃ በተለይ በኮንጎ የኤቦላ ቫይርስ ብዙ ሰዎችን እየገደለ ነው። ይህ ብልጭታ ምናልባት በአፍሪቃውያን ላይ በሽታዎችን እያሰራጩ፣ ህፃናቶቻቸውን እያደነዘዙ እና ሴቶቻቸውን መኻን እያደረጉ ያሉት የዓለማችንን ፈላጭ ቆራጮች እያስጠነቀቀ ይሆናል።
ለመሆኑ እዚያ ጠፍር ላይ ምንድን ነው እየሠሩ ያሉት? ሩሲያና ምዕራባውያኑ እዚህ ምድር ላይ ጠላታሞች እንደሆኑ አድርገው እርስበርስ ሲፎካከሩና ሲወቃቀሱ ይሰማሉ፤ ጠፈር ላይ ግን አብረው ይሠራሉ። ለምንድንስ ነው አንድም አፍሪቃዊ ወደ ጠፈር ተልኮ የማያውቀው?
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: Africa, መብረቅ, ሳዩዝ, ቤተ ሙከራ, ብልጭታ, አፍሪቃ, ኢትዮጵያ, የፈፈር ጣቢያ, ደመና, ጠፈር, ጠፈርተኞች, ISS, Lightning, Soyuz Capsule, Space Station | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 6, 2018
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ዛሬ ወደ ጠፈር ባመጠቀችው ሶዩዝ ሮኬት ላይ ጠበል ከረጩ በኋላ፡ ሦስቱን ጠፈርተኞችንም በጠበል እና በመስቀል ባርከዋቸዋል። ጨረቃዋም በመስቀሉ ኃይል ተገምሳለች!
የሕክምና ዶክተር የሆነችው አሜሪካዊቷ ጠፈርተኛ ፊቷን ሦስት ጊዜ ስታማትብ ይታያል።
ኃይለኛ ምልክት፤ ትልቅ መልዕክት!!!
ፊተኞቹ ኋለኞች እንዳንሆን መጠንቀቅ ይኖርብናል!
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: መባረክ, ሩሲያ, ሶዩዝ የጠፈር ሮኬት, ክርስትና, የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን, ጠፈርተኞች, ፕሬዚደንት ፑቲን, Blessing, Russian Orthodox Church, Soyuz Rocke, Space | Leave a Comment »